ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ምህረት
:
:
:
ፍቅሬ ...
ይህቺን ስሚኝ ዛሬ
በገረፍሺኝ ብዛት ላቤንና ደሜን ...
...ቀላቅዬ አኖሬ
ብሶት ሚባል ቀለም ለራሴው ፈጥሬ
እኔ አንቺን ስስልሽ ያሳብ ሸራ ወጥሬ

ፍቅርሽ:–ጫካ ኖሮ ኖሮ
ፀጉሩን አጎፍሮ
ወደ ስልጣን ሰማይ በደም እንዳረገው
ህዝብን አመካኝቶ ለራሱ ጥቅም ሲል... ...እንደደነገገው
ደሀን መርጦ ብቻ ሚተገበረውን ያን «ህግ» ...ይመስለኛል
ትዝታሽም ደግሞ ሀገሬን የሚል ሰው... የሚማቅቅበት «ወህኒ ቤት» ሆኖ በቅርብ... ...ይታየኛል።
:
:
ይልቅ የኔ ፍቅር ...
ላም ባልዋለበት ኩበትን ለቀማ
የሚል ቃል ሳልሰማ
ፍቅርና ያን ህግ ትዝታና ወህኒን ምን... ...ያገናኘዋል በሚል ሳልታማ
እንዴት አዋህጄ እንዴት አሳክሬ
ቀለምን ቀምሬ ሸራዬን ወጥሬ
ፍቅርሽን ከዚያ ህግ ወህኒን ከትዝታሽ
እንዳመሳሰልኩት ስሚኝ ቆይ ላስረዳሽ።
:
:
ያኔ ባማን ደና
ፍቅራችን ሳይታመም እያለ በጤና
ባንድ ላይ ተሳስረን
ስንት ሽንቁር ደፍነን ስንት ካብ ሰርስረን
ኖረን ኖረን ኖረን
ሁሌ አንቺን አንቺን ስል ድንገት በቀን መጥፎ ...ባልሰራውት ጉድፍ
ሚዛነ ቢስ «ፍቅርሽ» እጅግ ጨክኖብኝ... ...ህሊናዬ እስኪያድፍ
«በትዝታሽ» ጎጆ በናፍቆት ሰንሰለት እጅ... ...እግሬን አስሮ
ፍርድሽ በኔ ፀንቶ እንደ ዕድሜ ፍታ... ...ያለአመክሮ
ካንዴም ሁለት ሶስቴ ይግባኝ መጠየቄ
«ንጉስ አይከሰስም» የምትለው አንቀፅ... ...አንቺም ቤት እንዳለች ወይ አለማወቄ።
:
:
አውቃለው ...
ፍርድን አገምድሎ በመዶሻ ማለም
ሲያደርጉ አይተሽ እንጂ ያንቺ አሳብ አይደለም።
:
:
ቢሆንም ቢሆንም ባገራችን ሰማይ አሁን... ...ፀሀይ ወጥቷል
ነገን የሚያበራ አዲስ ተስፋም ታይቷል
ማሰር ሚለው ቀርቶ መማር ሚለው ፀንቷል
ይህንም ታውቂያለሽ ጠማማውም ቀንቷል።
:
:
እንዳምና ታችአምና እውነት ከቶ አይቀልም
ዛሬ ባገራችን እንኳን ፍቅር ቀርቶ በርባን ...አይሰቀልም
ሀገሩን ሚያፈቅር ንፁ አፍቃሪ እንጂ አሸባሪ አይባልም።
:
:
እናልሽ የኔ እናት ያኔ አተሺው ቅጡን
እውነቱ ሳይጠፋሽ እያወቅሽ እርግጡን
የናፍቆትን ሾተል የትዝታ ማጡን
አንቺን በማለቴ ምንም ሳላጠፋ በኔ ... ...እንደበየንሺው
አሁን ነግቷል እና ካገርሽ ተምረሽ በይ ... ...በምህረት አንሺው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu


@getem
@getem
@getem
በእሾህ መደገፊያ ከእሾህ መቀመጫ
ወግቶ ለመወጋት ይሄ ሁሉ ሩጫ
ምን ይሆን ነገሩ ምንድነው ሚስጥሩ?
መድሃኒት የሚያሻው ሰዉ ነው ወንበሩ?

@getem
@getem
@paappii

#ምህረት ደበበ
ምኞቴን በለገጣ ስገልፀው ይህን ይመስላል። ተስፋ ግን አልቆርጥም

#ምህረት
:
:
:
ፍቅሬ ...
ይህቺን ስሚኝ ዛሬ፣
በገረፍሺኝ ብዛት ላቤንና ደሜን ቀላቅዬ አኑሬ፣
ብሶት ሚባል ቀለም ለራሴው ፈጥሬ፣
እኔ አንቺን ስስልሽ ያሳብ ሸራ ወጥሬ ...

«ፍቅርሽ»...
ጫካ ኖሮ ኖሮ፣
ፀጉሩን አጎፍሮ፣
ወደ ስልጣን ሰማይ በደም እንዳረገው፣
ህዝብን አመካኝቶ ለራሱ ጥቅም ሲል እንደደነገገው፣
ዘርን መርጦ ብቻ ሚተገበረውን ያን «ህግ» ይመስለኛል፣
«ትዝታሽም» ደግሞ ሀገሬን የሚል ሰው የሚማቅቅበት «ወህኒ ቤት» ሆኖ በቅርብ ይታየኛል።
:
:
ይልቅ የኔ ፍቅር ...
ላም ባልዋለበት ኩበትን ለቀማ፣
የሚል ቃል ሳልሰማ፣
ፍቅርና ያን ህግ ትዝታና ወህኒን ምን ያገናኘዋል በሚል ሳልታማ፣
እንዴት አዋህጄ እንዴት አሳክሬ፣
ቀለምን ቀምሬ ሸራዬን ወጥሬ፣
ፍቅርሽን ከዚያ ህግ ወህኒን ከትዝታሽ፣
እንዳመሳሰልኩት ስሚኝ ቆይ ላስረዳሽ።
:
:
ያኔ ባማን ደና፣
ፍቅራችን ሳይታመም እያለ በጤና፣
ባንድ ላይ ተሳስረን፣
ስንት ሽንቁር ደፍነን ስንት ካብ ሰርስረን፣
ኖረን ኖረን ኖረን፣
ሁሌ አንቺን አንቺን ስል ድንገት በቀን መጥፎ ባልሰራውት ጉድፍ፣
ሚዛነ ቢስ «ፍቅርሽ» እጅግ ጨክኖብኝ ህሊናዬ እስኪያድፍ፣
«በትዝታሽ» ጎጆ በናፍቆት ሰንሰለት እጅ እግሬን አስሮ፣
ፍርድሽ በኔ ፀንቶ እንደ ዕድሜ ይፍታ ያለ አመክሮ፣
ካንዴም ሁለት ሶስቴ ይግባኝ ጠይቄያለሁ፣
«ሰማይ አይታረስም ንጉስ አይከሰስም» የምትለው አንቀፅ አንቺም ቤት እንዳለች በርግጥ አውቄአለሁ።
:
:
እርግጥ አውቅሻለሁ...
ፍርድን አገምድሎ በመዶሻ ማለም፣
ሲያደርጉ አይተሽ እንጂ ያንቺ አሳብ አይደለም።
:
:
ቢሆንም ቢሆንም ባገራችን ሰማይ አሁን ፀሀይ ወጥቷል፣🤣
ነገን የሚያበራ አዲስ ተስፋም ታይቷል፣🤣
ማሰር ሚለው ቀርቶ መማር ሚለው ፀንቷል፣🤣
ይህንም ታውቂያለሽ ጠማማውም ቀንቷል።
:
:
እንዳምና ታችአምና እውነት ከቶ አይቀልም፣😂🤣
ዛሬ ባገራችን እንኳን ፍቅር ቀርቶ በርባን አይሰቀልም።
ሀገሩን ሚያፈቅር ንፁ አፍቃሪ እንጂ አሸባሪ አይባልም። 🤣🤣🤣🤣🤣
:
:
እናልሽ የኔ እናት ያኔ አተሺው ቅጡን፣
እውነቱ ሳይጠፋሽ እያወቅሽ እርግጡን፣
የናፍቆትን ሾተል የትዝታ ማጡን፣
አንቺን በማለቴ ምንም ሳላጠፋ በኔ እንደበየንሺው፣
አሁን ነግቷል እና ካገርሽ ተምረሽ በይ በምህረት አንሺው።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
👍343🔥1🤩1