ለምርቃት ስጦታ ፎቶ ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህ እድል እንዳያመልጦ።
@seiloch
@seiloch
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህ እድል እንዳያመልጦ።
@seiloch
@seiloch
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7.pdf
3.5 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰
💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰
ባትመጪም ቅጠሪኝ
(ቴዎድሮስ ፀጋዬ)
የመውደድን ቅኔ ማህሌት
የፍቅርን ጥዑም ዜማ፡
አብረን ሆነን ልንቀኘው
ተጣምረን ልናንጎራጉር
ቀልባችን እንደተስማማ፡
ለብዙ ቀን ብዙ ዘመን
እየቀጠርሽኝ ባትመጪ
ሲያዝንብሽ ቢኖርም ሆዴ፡
ዛሬ ግን በመሪር ኃዘን
"ለምን አልመጣሽም ?" ብዬ
አልነተርክሽም ውዴ፡
ባይመችሽም ቅጠሪኝ
መንገድ ቆሞ መጠበቁ
አይቅርብኝ ይህ ልማዴ፡
ከሰርክ መቃጠሪያችን
" እንገናኝ" ብለሽ በዪኝ
ሰዓትና ቀን ቁረጪ
ደቂቃ ሰከንዱን ቆጥረሽ
እለት ቀኑን አስልተሽ
ግን ከዚያ ስፍራ እንዳትመጪ፡
ብትፈልጊ በኃያል ወበቅ
ካሰኘሽም በዶፍ ዝናብ፡
ዝም ብለሽ ቀጠሮ ስጭኝ
"ለማልመጣው ነገር" ብለሽ
እንዳይገባሽ ስጋት ሃሳብ፡
ጎህ ሲቀድ ጠዋት ማለዳ
ወይ ማታ ቅጠሪኝና
እንደምትመጪ ቃል ግቢ፡
"ቀጠሮ ላክብር" ብለሽ ግን
ከዘወትር መቃጠሪያችን
መገኘትን አታስቢ፡
እባክሽን ልለምንሽ
ልማፀንሽ ጆሮ አውሺኝ፡
ውለታ ዋይልኝና
እንዳትመጪ! ግን ቅጠሪኝ፡
ስጠብቅሽ ስትቀሪብኝ
ተደግፌው ስንሰቀሰቅ
በዝምታው ከሚያፅናናኝ፡
ወረትን ጨርሶ ባያውቅ
ጧት ማታ ስሄድ ባላጣው
ከአንቺ በእጅጉ ቢሻለኝ፡
ከሰርክ መቃጠሪያችን
ከአጥሩ ፍቅር ስለያዘኝ፡
"ግዑዝ ወደደ" ተብዬ
በለበጣ እንዳልቀጣ፡
በአንቺ እግር የተካሁትን
ግዑዙን ፍቅሬን እየሳምኩ
ጥልቅ ናፍቆቴን እንድወጣ፡
ባትመጪም ቅጠሪኝና
በሰበብሽ ከግንቡ ስር
ሃያ አራት ሰዓት ልሰጣ፡፡
@getem
@getem
@getem
(ቴዎድሮስ ፀጋዬ)
የመውደድን ቅኔ ማህሌት
የፍቅርን ጥዑም ዜማ፡
አብረን ሆነን ልንቀኘው
ተጣምረን ልናንጎራጉር
ቀልባችን እንደተስማማ፡
ለብዙ ቀን ብዙ ዘመን
እየቀጠርሽኝ ባትመጪ
ሲያዝንብሽ ቢኖርም ሆዴ፡
ዛሬ ግን በመሪር ኃዘን
"ለምን አልመጣሽም ?" ብዬ
አልነተርክሽም ውዴ፡
ባይመችሽም ቅጠሪኝ
መንገድ ቆሞ መጠበቁ
አይቅርብኝ ይህ ልማዴ፡
ከሰርክ መቃጠሪያችን
" እንገናኝ" ብለሽ በዪኝ
ሰዓትና ቀን ቁረጪ
ደቂቃ ሰከንዱን ቆጥረሽ
እለት ቀኑን አስልተሽ
ግን ከዚያ ስፍራ እንዳትመጪ፡
ብትፈልጊ በኃያል ወበቅ
ካሰኘሽም በዶፍ ዝናብ፡
ዝም ብለሽ ቀጠሮ ስጭኝ
"ለማልመጣው ነገር" ብለሽ
እንዳይገባሽ ስጋት ሃሳብ፡
ጎህ ሲቀድ ጠዋት ማለዳ
ወይ ማታ ቅጠሪኝና
እንደምትመጪ ቃል ግቢ፡
"ቀጠሮ ላክብር" ብለሽ ግን
ከዘወትር መቃጠሪያችን
መገኘትን አታስቢ፡
እባክሽን ልለምንሽ
ልማፀንሽ ጆሮ አውሺኝ፡
ውለታ ዋይልኝና
እንዳትመጪ! ግን ቅጠሪኝ፡
ስጠብቅሽ ስትቀሪብኝ
ተደግፌው ስንሰቀሰቅ
በዝምታው ከሚያፅናናኝ፡
ወረትን ጨርሶ ባያውቅ
ጧት ማታ ስሄድ ባላጣው
ከአንቺ በእጅጉ ቢሻለኝ፡
ከሰርክ መቃጠሪያችን
ከአጥሩ ፍቅር ስለያዘኝ፡
"ግዑዝ ወደደ" ተብዬ
በለበጣ እንዳልቀጣ፡
በአንቺ እግር የተካሁትን
ግዑዙን ፍቅሬን እየሳምኩ
ጥልቅ ናፍቆቴን እንድወጣ፡
ባትመጪም ቅጠሪኝና
በሰበብሽ ከግንቡ ስር
ሃያ አራት ሰዓት ልሰጣ፡፡
@getem
@getem
@getem
👍1
የዳር ቋሚ ምኞት! !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
መቼም ግፈኛ ነው ፥ የወላድ ማህፀን
አንቺን መሳይ ጥሎ ፥ ኸምድር ላይ ማምከን
ኸረ እንደው በሞቴ !
በኗሪዋ እናቴ!
እንዴት ቢችሉ ነው ፥ ዘመድ አዝማዶችሽ
ከቤትሽ ስትወጪ...
ለብቻሽ መሆኑን ፥ አይተው ዝም የሚሉሽ?
ኸረ እግዚኦ በጌታ !
በሰማዩ ንጉስ.. .በሀያሉ አምላክ
ምን ያለው እብደት ነው ?
አንቺን መሳይ ወልዶ አምኖ መንገድ መላክ ?
ሲሆን ሲሆንማ..
ለወጉ ለደንቡ
ከወለዱ አይቀር
እንዳንቺ ያለውን ፥ ሸጋ መልከ ግቡ
ሺህ ጠባቂ በቀኝ ፥ ሚልየን በግራ
በጦር የታጀቡ ፥ የጀግናዎች አውራ
የሰማይ ከናፊ ፥ በራሪ ጥያራ
ሰማይ ላይ ዘርግተው
እንደ ንጉስ አርገው
እልፎች አሸርግደው
ጠብቀው ባቆዩሽ ...
ከክፉ አዳም አይን ወጥመድ ባተረፉሽ !
አጃኢብ አንዳንዱ !
የባል ወለፈንዱ
የልቡ መታገስ ፥ የአንጀቱ ማስቻል
ጠቦት መልቀቅ መፍቀድ በአንበሳዎች መሃል !
ምን ያለው ቀልድ ነው ?
ምን ያለው ቸልታ ?
አንቺን መሳይ ወዶ
መስደድ ያለ ቦታ !
ኸረ ሰሚ ልጥራ
ለልባም ልናገር ፥ ለአዳማጭ ልለፍልፍ
ሲሆን ሲሆንማ ...
አንቺን መሳይ ልዕልት
ማንም እንዳያይሽ ከግቢ ውስጥ ቁልፍ !
ክንዶችሽ ስር መስመጥ ያለከልካይ እቅፍ !
አጮልቀው ካዩም
እንቧ ዘራፍ ብሎ ፥ መማዘዝ ነው ሰይፍ !
እንጂ እንደዋዛ
እንደው እንደ ቀላል
የዓመት ቀለብ ስንዴን.. .
ለአሞራ መበተን ፥ የሰው ዥል ያስብላል ።
እውነት!
እውነት!
እውነት!
የኔን መሻት አይቶ ...
የዝምታው ዳኛ ፥ የፍጥረት ባለቤት
ባልሽን ባረገኝ ፥ ይህን ለማሳዬት።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
መቼም ግፈኛ ነው ፥ የወላድ ማህፀን
አንቺን መሳይ ጥሎ ፥ ኸምድር ላይ ማምከን
ኸረ እንደው በሞቴ !
በኗሪዋ እናቴ!
እንዴት ቢችሉ ነው ፥ ዘመድ አዝማዶችሽ
ከቤትሽ ስትወጪ...
ለብቻሽ መሆኑን ፥ አይተው ዝም የሚሉሽ?
ኸረ እግዚኦ በጌታ !
በሰማዩ ንጉስ.. .በሀያሉ አምላክ
ምን ያለው እብደት ነው ?
አንቺን መሳይ ወልዶ አምኖ መንገድ መላክ ?
ሲሆን ሲሆንማ..
ለወጉ ለደንቡ
ከወለዱ አይቀር
እንዳንቺ ያለውን ፥ ሸጋ መልከ ግቡ
ሺህ ጠባቂ በቀኝ ፥ ሚልየን በግራ
በጦር የታጀቡ ፥ የጀግናዎች አውራ
የሰማይ ከናፊ ፥ በራሪ ጥያራ
ሰማይ ላይ ዘርግተው
እንደ ንጉስ አርገው
እልፎች አሸርግደው
ጠብቀው ባቆዩሽ ...
ከክፉ አዳም አይን ወጥመድ ባተረፉሽ !
አጃኢብ አንዳንዱ !
የባል ወለፈንዱ
የልቡ መታገስ ፥ የአንጀቱ ማስቻል
ጠቦት መልቀቅ መፍቀድ በአንበሳዎች መሃል !
ምን ያለው ቀልድ ነው ?
ምን ያለው ቸልታ ?
አንቺን መሳይ ወዶ
መስደድ ያለ ቦታ !
ኸረ ሰሚ ልጥራ
ለልባም ልናገር ፥ ለአዳማጭ ልለፍልፍ
ሲሆን ሲሆንማ ...
አንቺን መሳይ ልዕልት
ማንም እንዳያይሽ ከግቢ ውስጥ ቁልፍ !
ክንዶችሽ ስር መስመጥ ያለከልካይ እቅፍ !
አጮልቀው ካዩም
እንቧ ዘራፍ ብሎ ፥ መማዘዝ ነው ሰይፍ !
እንጂ እንደዋዛ
እንደው እንደ ቀላል
የዓመት ቀለብ ስንዴን.. .
ለአሞራ መበተን ፥ የሰው ዥል ያስብላል ።
እውነት!
እውነት!
እውነት!
የኔን መሻት አይቶ ...
የዝምታው ዳኛ ፥ የፍጥረት ባለቤት
ባልሽን ባረገኝ ፥ ይህን ለማሳዬት።
@getem
@getem
@getem
ለምርቃት ስጦታ ፎቶ ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ማዘዝ ይቻላል ።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህ እድል እንዳያመልጦ!
@seiloch
@seiloch
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ማዘዝ ይቻላል ።
ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
ይህ እድል እንዳያመልጦ!
@seiloch
@seiloch
#ከሠዓሊው_ደጃፍ
አይቀድምም ሰዕሉ ከምኖር ላይ ባለም
ከዚች ግዙፍ ምድር ያልተቀዳ የለም
በተመስጦ ጋሪ መምሰልን ሰግሮ እውነትን ሚጋልብ
አያውቁም ብሎ ነው የተኖረ ሰዕል ለሰው የሚያስነብብ
አትስጡ ድማሜ ላረንጓዴ ቅጠል እውነትነት ላጣ
ዛፉን ሰብሮ ሰብሮ ብሩሽ ባደረገው በሠዐሊው ተንኮል ሸራ ላይ በወጣ
ምድር ትግስተኛ ምንም አትናገር ውበቷን ሲሰርቁ
ገብቷት ይሆን መሰል ዘመኗን ሲጨርስ ዘመኑ ማለቁ
አትስጡ ድማሜ ሳርሳሩን የሚግጥ በሬውን አየታችሁ
በተሳለ ቢላ ስጋውን በልቶ ነው ቆዳውን ወጥሮ ሳልኩት የሚላችሁ
እንዲ ነው ሰዐሊ በወጠራት እውነት ውሸቱን ይኖራል
ያደነቁት አይኖች በጨመቁት እንባ ቀለሙን ይሰራል
አትስጡ ድማሜ በሰፊው ጎዳና ነፋስ ተንተርሶ
ገላውን ሚመስል ጠባብ ሱሪ ለብሶ
ሆዱን በእግሩ ቀብሮ የተራበ አንድ ሰው
ከመቀመጥ ብዛት መነሳት ያነሰው
ሳንቲም አየሰጠ መውደቁን የገዛው ይህ ሰዓሊ ነበር
ከደጃፉ አንስቶ ሸራ ላይ ጥሎት ነው ሚፎክረው ላገር
ይህ ነው መጨረሻው አይን እየከፈቱ አዕምሮ የዘጉ ለት
ዝም ብሎ መመሰጥ ዝም ብሎ ማጨብጨብ ሲቸረቸር አውነት
ስዕል
የሚቀበባበት ብሩሽ ላጣ ቆሌው ከጥበብ ለመነነ
እውነት መስረቅ ለሱ ስዕል መሳል ሆነ ፡፡
ተፃፈ 6-09-2010
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@getem
አይቀድምም ሰዕሉ ከምኖር ላይ ባለም
ከዚች ግዙፍ ምድር ያልተቀዳ የለም
በተመስጦ ጋሪ መምሰልን ሰግሮ እውነትን ሚጋልብ
አያውቁም ብሎ ነው የተኖረ ሰዕል ለሰው የሚያስነብብ
አትስጡ ድማሜ ላረንጓዴ ቅጠል እውነትነት ላጣ
ዛፉን ሰብሮ ሰብሮ ብሩሽ ባደረገው በሠዐሊው ተንኮል ሸራ ላይ በወጣ
ምድር ትግስተኛ ምንም አትናገር ውበቷን ሲሰርቁ
ገብቷት ይሆን መሰል ዘመኗን ሲጨርስ ዘመኑ ማለቁ
አትስጡ ድማሜ ሳርሳሩን የሚግጥ በሬውን አየታችሁ
በተሳለ ቢላ ስጋውን በልቶ ነው ቆዳውን ወጥሮ ሳልኩት የሚላችሁ
እንዲ ነው ሰዐሊ በወጠራት እውነት ውሸቱን ይኖራል
ያደነቁት አይኖች በጨመቁት እንባ ቀለሙን ይሰራል
አትስጡ ድማሜ በሰፊው ጎዳና ነፋስ ተንተርሶ
ገላውን ሚመስል ጠባብ ሱሪ ለብሶ
ሆዱን በእግሩ ቀብሮ የተራበ አንድ ሰው
ከመቀመጥ ብዛት መነሳት ያነሰው
ሳንቲም አየሰጠ መውደቁን የገዛው ይህ ሰዓሊ ነበር
ከደጃፉ አንስቶ ሸራ ላይ ጥሎት ነው ሚፎክረው ላገር
ይህ ነው መጨረሻው አይን እየከፈቱ አዕምሮ የዘጉ ለት
ዝም ብሎ መመሰጥ ዝም ብሎ ማጨብጨብ ሲቸረቸር አውነት
ስዕል
የሚቀበባበት ብሩሽ ላጣ ቆሌው ከጥበብ ለመነነ
እውነት መስረቅ ለሱ ስዕል መሳል ሆነ ፡፡
ተፃፈ 6-09-2010
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
@getem
@getem
@getem
ወንድም በወንድሙ ፤
በሚጨክንበት፤
ቢላዋ እየሳለ በሚፎክርበት፤
በውልክፍክፍ ጊዜ በዘመን አሙካ ፤
እንዴት ከረማችሁ ፤
እንደምን አላችሁ አይባልም ለካ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
በሚጨክንበት፤
ቢላዋ እየሳለ በሚፎክርበት፤
በውልክፍክፍ ጊዜ በዘመን አሙካ ፤
እንዴት ከረማችሁ ፤
እንደምን አላችሁ አይባልም ለካ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
የትውልዱ ገድል???!!!
ያ ትውልድ የሰራው ፤
መግደል መገዳደል ፤
ማቸነፍ ማሸነፍ የሚባል ፉከራ የዘመን ደንቀራ ፤
ዳግም ላይደገም ፤
ሁሌ በየወንዙ ቃል ስንፈጣጠም ማህላ ስንሰራ፤
ነበረ ህልማችን ፤
በደም ግብር ጩኸት ዘመን እንዳትከስር ሃገር እንዳትጠፋ ፤
ታዲያ ምን ዋጋ አለው ፤
በእኩያኖች ስብከት ፤
በሞት ደጋሾች እጅ ፤
ዛሬም በዚች ሃገር ፤ ወንድሙን ያመነ በወንድም ተገፋ ።
እኒያ አባቶቻችን ፤
ያኔ በዚያ ወራት፤
ደረቅ ፊደል ይዘው በተውሶ ርእዮት እያንገራገሩ፤
በማኦ በስታሊን ፤
በራሺያ በቻይና በሚባል አረቂ ጢምቢራቸው ዙሮ እየተሳከሩ ፤
በፀጉር ስንጠቃ ፤
በፓርቲ ቀኖና ፤
አጥር ገረገራ ማዶ ለማዶ ላይ በአሻጋሪ ቆመው ድካ እየመተሩ ፤
እንማከር ብለው መላ እንስራ ብለው ከአድባሩ ከወንዙ ሳይነጋገሩ ፤
እናቸንፋለን እናሸንፋለን በሚል አማርኛ እየተፋከሩ ፤
በቸ እና በሸ ቅርፅ፤
በሆሄ ተጣልተው እየተናናቁ እየተናነቁ ቂም እየጋጋሩ፤
ዘመን ጋር ተጣልተው ፤
ፊደል ቃል ተኳርፈው፤
በፊደል ተጣልፈው በየጥሻው ወድቀው በየሜዳው ቀሩ ።
እነዚያን ትውልዶች ያደናቀፋቸው አሽከላ ድሪቶ ፤
እኔን ብቻ ስሙኝ፤
እኔን ብቻ አምልኩኝ የሚሉት እንቅፋት የዘመን ቡትቶ ፤
ደግሞ እንደ ጅብራ ፤
እኛንም ጠበቀን ከመንገዳችን ላይ አታልፉም እያለ ዛሬም ተጎልቶ
የትውልዴን ፍኖት መረማመጃውን ጎዳናውን ዘግቶ ፤
ይኸው የኔም ትውልድ፤
እኔን ብቻ ስሙኝ፤
የኔ የኔ እያለ በየጥሻው ቀረ በአፍጢሙ ተደፍቶ ።
እኒያ አባቶቻችን በተጠለፉበት፤
በዚያ እንቅፋታቸው ደግመን እንደገና እኛም ከሄድንበት ፤
አይናችን እያየ ፤
ከታሪክ ሳንማር እኛም በተራችን በሞቱበት መንገድ ከተራመድንበት ፤
እንቅፋቱ አይደለም ፤
ጎዳናው አይደለም ፤
ደርሶ ሚወቀሰው እሱ ምን በወጣው እሱ ምን ፈርዶበት ፤
እሱማ መንገድ ነው፤
አትሂዱ አይለን ግር ብለን እንደ በግ እኛ ከሄድንበት ፤
ይልቅ ከሰማሃኝ ፤
እኛ ነን እንቅፋት እኛ ነን ድንጋዮች ፤
ከዘመን እንቅፋት ፤
ከዘመን ጉልጭማ ፤
መቆምን ያልተማርን የዘመን ጥላሸት የዘመን ብካዮች ።
የለም ባለም ታሪክ ፤
ንፁህ ወንድሞቹን ፤
በየሜዳው ገድሎ ነፃነት ሰላሙን በደም ያስከበረ ፤
የአቤል ደም ህያው ነው ፤
ይጮሃል በሰማይ ወንድሙ ቃየልን ሰርክ እያባረረ ።
የአቤል ደም አይበርደም፤ እንዲህ እንደዋዛ በመፈክር ብዛት ፤
ደግሞ ባለተራው ቃየል ሳይገደል አፈሯን ሳይቀምሳት ፤
እንዲህ ነው በሽታው በነጋ በነጋ የደም አዙሪቱ ፤
አትድከም ወንድሜ ፤
ደም ነፃ አያወጣም ለገዳይም ገዳይ ሞልቷል በየቤቱ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ያ ትውልድ የሰራው ፤
መግደል መገዳደል ፤
ማቸነፍ ማሸነፍ የሚባል ፉከራ የዘመን ደንቀራ ፤
ዳግም ላይደገም ፤
ሁሌ በየወንዙ ቃል ስንፈጣጠም ማህላ ስንሰራ፤
ነበረ ህልማችን ፤
በደም ግብር ጩኸት ዘመን እንዳትከስር ሃገር እንዳትጠፋ ፤
ታዲያ ምን ዋጋ አለው ፤
በእኩያኖች ስብከት ፤
በሞት ደጋሾች እጅ ፤
ዛሬም በዚች ሃገር ፤ ወንድሙን ያመነ በወንድም ተገፋ ።
እኒያ አባቶቻችን ፤
ያኔ በዚያ ወራት፤
ደረቅ ፊደል ይዘው በተውሶ ርእዮት እያንገራገሩ፤
በማኦ በስታሊን ፤
በራሺያ በቻይና በሚባል አረቂ ጢምቢራቸው ዙሮ እየተሳከሩ ፤
በፀጉር ስንጠቃ ፤
በፓርቲ ቀኖና ፤
አጥር ገረገራ ማዶ ለማዶ ላይ በአሻጋሪ ቆመው ድካ እየመተሩ ፤
እንማከር ብለው መላ እንስራ ብለው ከአድባሩ ከወንዙ ሳይነጋገሩ ፤
እናቸንፋለን እናሸንፋለን በሚል አማርኛ እየተፋከሩ ፤
በቸ እና በሸ ቅርፅ፤
በሆሄ ተጣልተው እየተናናቁ እየተናነቁ ቂም እየጋጋሩ፤
ዘመን ጋር ተጣልተው ፤
ፊደል ቃል ተኳርፈው፤
በፊደል ተጣልፈው በየጥሻው ወድቀው በየሜዳው ቀሩ ።
እነዚያን ትውልዶች ያደናቀፋቸው አሽከላ ድሪቶ ፤
እኔን ብቻ ስሙኝ፤
እኔን ብቻ አምልኩኝ የሚሉት እንቅፋት የዘመን ቡትቶ ፤
ደግሞ እንደ ጅብራ ፤
እኛንም ጠበቀን ከመንገዳችን ላይ አታልፉም እያለ ዛሬም ተጎልቶ
የትውልዴን ፍኖት መረማመጃውን ጎዳናውን ዘግቶ ፤
ይኸው የኔም ትውልድ፤
እኔን ብቻ ስሙኝ፤
የኔ የኔ እያለ በየጥሻው ቀረ በአፍጢሙ ተደፍቶ ።
እኒያ አባቶቻችን በተጠለፉበት፤
በዚያ እንቅፋታቸው ደግመን እንደገና እኛም ከሄድንበት ፤
አይናችን እያየ ፤
ከታሪክ ሳንማር እኛም በተራችን በሞቱበት መንገድ ከተራመድንበት ፤
እንቅፋቱ አይደለም ፤
ጎዳናው አይደለም ፤
ደርሶ ሚወቀሰው እሱ ምን በወጣው እሱ ምን ፈርዶበት ፤
እሱማ መንገድ ነው፤
አትሂዱ አይለን ግር ብለን እንደ በግ እኛ ከሄድንበት ፤
ይልቅ ከሰማሃኝ ፤
እኛ ነን እንቅፋት እኛ ነን ድንጋዮች ፤
ከዘመን እንቅፋት ፤
ከዘመን ጉልጭማ ፤
መቆምን ያልተማርን የዘመን ጥላሸት የዘመን ብካዮች ።
የለም ባለም ታሪክ ፤
ንፁህ ወንድሞቹን ፤
በየሜዳው ገድሎ ነፃነት ሰላሙን በደም ያስከበረ ፤
የአቤል ደም ህያው ነው ፤
ይጮሃል በሰማይ ወንድሙ ቃየልን ሰርክ እያባረረ ።
የአቤል ደም አይበርደም፤ እንዲህ እንደዋዛ በመፈክር ብዛት ፤
ደግሞ ባለተራው ቃየል ሳይገደል አፈሯን ሳይቀምሳት ፤
እንዲህ ነው በሽታው በነጋ በነጋ የደም አዙሪቱ ፤
አትድከም ወንድሜ ፤
ደም ነፃ አያወጣም ለገዳይም ገዳይ ሞልቷል በየቤቱ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
@getem
@getem
@balmbaras
ፈጣሪና ምኞት
"""""""""""""""""
"ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት"
ብሎ የፀለየው ያአፍላ ወጣት
እግዜር በጥበቡ
ፀሎቱን ሰማና ካንቺ ጋራ አድሮ
ጠዋት ሞት ቢመጣ ሊገለው ከጅሎ
"ና በል ልገልህ ነው" ሞት ሲለው በቁጣ
ከጭንሽ ውስጥ ገብቶ "አልነጋም" አያለ እስካሁን አልወጣ!
ምነው ባልፀለየ
ጭንሽ ጭንቅላቱን ፈፅሞ ባይበልጠው
ይኸው እዳ ገባ
ከጭንሽ ሲወጣ ሞት ነው 'ሚጠብቀው😔
(እንደኔ እምመክረው)
እንዳለ ከጭንሽ
ድጋሚ ይፀልይ ፈጣሪ ከሰማው
ሞትን ቢያርቅለት
ከደጃፍ ከበሩ እንዳላየ እንዲያልፈው
መቼን አንዳንድቀን
ፈጣሪና ምኞት ይገጣጠሙና
ለቀልድ ያወራናት
ገዝፋ ትገኛለች ፈጣሪ ያ.ዝ.ና።
አያድርስ
አብርሃም
@Run_Viva_Run
@getem
@getem
"""""""""""""""""
"ካንቺ ጋር አድሬ ሲነጋ ልሙት"
ብሎ የፀለየው ያአፍላ ወጣት
እግዜር በጥበቡ
ፀሎቱን ሰማና ካንቺ ጋራ አድሮ
ጠዋት ሞት ቢመጣ ሊገለው ከጅሎ
"ና በል ልገልህ ነው" ሞት ሲለው በቁጣ
ከጭንሽ ውስጥ ገብቶ "አልነጋም" አያለ እስካሁን አልወጣ!
ምነው ባልፀለየ
ጭንሽ ጭንቅላቱን ፈፅሞ ባይበልጠው
ይኸው እዳ ገባ
ከጭንሽ ሲወጣ ሞት ነው 'ሚጠብቀው😔
(እንደኔ እምመክረው)
እንዳለ ከጭንሽ
ድጋሚ ይፀልይ ፈጣሪ ከሰማው
ሞትን ቢያርቅለት
ከደጃፍ ከበሩ እንዳላየ እንዲያልፈው
መቼን አንዳንድቀን
ፈጣሪና ምኞት ይገጣጠሙና
ለቀልድ ያወራናት
ገዝፋ ትገኛለች ፈጣሪ ያ.ዝ.ና።
አያድርስ
አብርሃም
@Run_Viva_Run
@getem
@getem
#እውር_እና_እውር
:
:
:
«ሲመሽም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት
ሲነጋም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት
ግን ዛሬም አልቻልኩም አንቺን መርሳት»
:
:
እንደዚ ሚለውን እርባነ ቢስ ዘፈን ከሰማ በኋላ
አፍቃሪው በሞላ
ፍቅረኛዬ ባላት ገና እንደተከዳ
ባለጌ ወንበር ላይ እግሩን አነባብሮ ጂኑን እያስቀዳ
ጠዋትና ማታ መጠጣት ጀመረ
እንቶ ፈንቶ ሰምቶ ሱሰኛ ሆኖ ቀረ።
:
:
እውር እና እውር ተያይዞ ገደል
ማለት ይሄስ አይደል።
:
:
ሲመሽ እየጠጣ ሲነጋ እየጠጣ እንዲ ብሎ መቃኘት
«ሱሰኛ» ነው እንዳይባል ሴትን ማመካኘት
የራስን ደካማ በሰው ላይ መለጠፍ
በሴት ላይ መለጠፍ
እንኳን ለንጉርጉሮ ለማውራትም ሲቀፍ።
:
:
በርግጥ ሰው ይጎዳል በርግጥ ሰው ያደማል
በጊዜ ሂደት ውስጥ ሁሉም ይታከማል።
ያመኑት ሲከዳ ምንም ቢቆረጥም
ላያስችል አይሰጥም።
:
:
ላንድ ሰሞን ቁስል ቀናቶች ሲያልፉ ለሚሽር ዳግመኛ
ጠዋትና ማታ መጠጥ እየላፉ ከመሆን ሱሰኛ
ብቅልና ብሶት ሆድን ከሚፈጀው
ባለን መደሰቱ እሱ ነው ሚበጀው።
:
:
በዛሬ መገፋት ዛሬን የወደቁ
ነገ ካልተነሱ ሊያውም እየሳቁ
ይቺን ቀን ለመርሳት መጠጥ ቤት ከሮጡ
ቀን በቀን ከጠጡ
የነጋቸው ገዳይ የራሳቸው ዓለም
እራሳቸው እንጂ ትናንት የጣላቸው ገፊው እጅ አይደለም።
:
:
ሰውን አመካኝቶ ቀን በቀን መጠጣት
እራስን ማታለል ማንነትን ማጣት
ወድቆ አለመነሳት
በጣም ትልቅ ጥፋት
ከመሆን ባሻገር፣
ከቶ አያስደፍርም ጥምብዝ ብሎ ሰክሮ
እሷ ናት ምክንያቴ ብሎ ለመናገር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
@getem
:
:
:
«ሲመሽም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት
ሲነጋም ጠጣለው ባንቺ ምክንያት
ግን ዛሬም አልቻልኩም አንቺን መርሳት»
:
:
እንደዚ ሚለውን እርባነ ቢስ ዘፈን ከሰማ በኋላ
አፍቃሪው በሞላ
ፍቅረኛዬ ባላት ገና እንደተከዳ
ባለጌ ወንበር ላይ እግሩን አነባብሮ ጂኑን እያስቀዳ
ጠዋትና ማታ መጠጣት ጀመረ
እንቶ ፈንቶ ሰምቶ ሱሰኛ ሆኖ ቀረ።
:
:
እውር እና እውር ተያይዞ ገደል
ማለት ይሄስ አይደል።
:
:
ሲመሽ እየጠጣ ሲነጋ እየጠጣ እንዲ ብሎ መቃኘት
«ሱሰኛ» ነው እንዳይባል ሴትን ማመካኘት
የራስን ደካማ በሰው ላይ መለጠፍ
በሴት ላይ መለጠፍ
እንኳን ለንጉርጉሮ ለማውራትም ሲቀፍ።
:
:
በርግጥ ሰው ይጎዳል በርግጥ ሰው ያደማል
በጊዜ ሂደት ውስጥ ሁሉም ይታከማል።
ያመኑት ሲከዳ ምንም ቢቆረጥም
ላያስችል አይሰጥም።
:
:
ላንድ ሰሞን ቁስል ቀናቶች ሲያልፉ ለሚሽር ዳግመኛ
ጠዋትና ማታ መጠጥ እየላፉ ከመሆን ሱሰኛ
ብቅልና ብሶት ሆድን ከሚፈጀው
ባለን መደሰቱ እሱ ነው ሚበጀው።
:
:
በዛሬ መገፋት ዛሬን የወደቁ
ነገ ካልተነሱ ሊያውም እየሳቁ
ይቺን ቀን ለመርሳት መጠጥ ቤት ከሮጡ
ቀን በቀን ከጠጡ
የነጋቸው ገዳይ የራሳቸው ዓለም
እራሳቸው እንጂ ትናንት የጣላቸው ገፊው እጅ አይደለም።
:
:
ሰውን አመካኝቶ ቀን በቀን መጠጣት
እራስን ማታለል ማንነትን ማጣት
ወድቆ አለመነሳት
በጣም ትልቅ ጥፋት
ከመሆን ባሻገር፣
ከቶ አያስደፍርም ጥምብዝ ብሎ ሰክሮ
እሷ ናት ምክንያቴ ብሎ ለመናገር።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henokbirhanu
@getem
@getem
@getem
# አልገጥሞ!!!!!
ይህች # ጦቢያ ሚሏት ፤
የገደል ጫፍ ጎጆ ፤ አይሞላላት ነገር ታሳዝነኛለች ፤
ማገሯ ሲወፍር ፤ወርዷን ታጠባለች፤
ጣራዋ ሲወፍር ምሰሶ ጠበበኝ ብላ ትሰፋለች ፤
ይኸው ስንት ዘመን ፤
ልጥበብ ልስፋ እያለች፤ ትንዘፋዘፋለች ።
እኛን የቸገረን ለወሬ ነጋሪ ፤
ከሰፊነቷ ላይ ደርቆ የሰለለ # ጭራሮ ቀርቃሪ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት
@getem
@getem
@balmbaras
ይህች # ጦቢያ ሚሏት ፤
የገደል ጫፍ ጎጆ ፤ አይሞላላት ነገር ታሳዝነኛለች ፤
ማገሯ ሲወፍር ፤ወርዷን ታጠባለች፤
ጣራዋ ሲወፍር ምሰሶ ጠበበኝ ብላ ትሰፋለች ፤
ይኸው ስንት ዘመን ፤
ልጥበብ ልስፋ እያለች፤ ትንዘፋዘፋለች ።
እኛን የቸገረን ለወሬ ነጋሪ ፤
ከሰፊነቷ ላይ ደርቆ የሰለለ # ጭራሮ ቀርቃሪ ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤
ሸጋ ምሽት
@getem
@getem
@balmbaras
ከመንገዱ በፊት!!!!!
ረጅም ነው ዙሩ፤ የዱንያ ጎዳና፤
በመሮጥ በመክነፍ፤ መች ይደረስና፤
እባክህ ጀሊሉ፤ ሶብር ይዘህ ናማ።
የመንገዱ ነገር፤ አቀበት ጉብታው፤
ቁልቁለት ሸለቆ፤ ሜዳና ኮረብታው፤
አላስኬድም ካለ፤
ገደላ ገደሉ፤ጭቃና ዝቅታው፤
ከመንገዱ በፊት፤
በርከክ ሲሉ ነው፤ ቁጥሩ የሚፈታው።
እናማ፤
ከመንገዱ በፊት፤
መንገዱን ጀምረው፤ ስጁድ ያለፋቸው፤
ይኸ ሁላ መንገድ፤
በሩጫ ሚደፈር እየመሰላቸው፤
ተቆጥረው አያልቁም፤
መንገድ እየሄዱ፤መንገድ የበላቸው።
እመዋ እመዋ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!!💚
@getem
@getem
@balmbaras
ረጅም ነው ዙሩ፤ የዱንያ ጎዳና፤
በመሮጥ በመክነፍ፤ መች ይደረስና፤
እባክህ ጀሊሉ፤ ሶብር ይዘህ ናማ።
የመንገዱ ነገር፤ አቀበት ጉብታው፤
ቁልቁለት ሸለቆ፤ ሜዳና ኮረብታው፤
አላስኬድም ካለ፤
ገደላ ገደሉ፤ጭቃና ዝቅታው፤
ከመንገዱ በፊት፤
በርከክ ሲሉ ነው፤ ቁጥሩ የሚፈታው።
እናማ፤
ከመንገዱ በፊት፤
መንገዱን ጀምረው፤ ስጁድ ያለፋቸው፤
ይኸ ሁላ መንገድ፤
በሩጫ ሚደፈር እየመሰላቸው፤
ተቆጥረው አያልቁም፤
መንገድ እየሄዱ፤መንገድ የበላቸው።
እመዋ እመዋ!!!!
((( ጃ ኖ )))💚💛❤
ሸጋ ጁምኣ!!!💚
@getem
@getem
@balmbaras