ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እንደው ለትውስታ ያህል 376 ከተሰኘው የ ልዑል ሀይሌ መፅሀፍ ውስጥ ''የትዝታ አልዛይመር'' የተሰኘውን እንሆ
አንባቢ :- ሚኪያስ ልየው @Mykey21

@getem
@getem
@getem
"ወርቅ ሲመሰጠር"

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።።

ጭንቁ አልባስ ሆኖት ፥ ሜዳ ለወደቀ

ሆዱን እህል ናፍቆት ፥ አካሉ ላለቀ

ተስፋው ለደቀቀ!

እሳት ላደባየው ፥ ህላዌው ተማግዶ

አመዱ ለሚታይ ፥ ምጥን ስጋው ነዶ

ለዛ ምስኪን ነዳይ !

"ጌታን ካልተቀበልህ ፥ እሳት ይበላሀል"

ብለህ ስትሰብከው ፥ ቆመህ ካደባባይ
የቃል ዛቻ ቆጥሮ

ለነፍሱ ደንብሮ

ጌታውን ባይቀበል

ለምን ሳተ ? አትበል

ከሚዛን አትቅለል።

.

አንተ ባለ ስንጥር!

ቁስል ባየህ ቁጥር ፥ የ'ጅህን አትወርውር።

ይልቅ መጣፍ ግለጥ...

ድፍኑ ተስፋውን ፥ በቃል ምሳር ፍለጥ ።

ይሄ ያልኩህ ንጉስ!

የሰበክሁህ ጌታ !

እንኳን ክቡሩን ሰው ፥ መልኩን ለወረሰው

በአርያው በአምሳሉ ፥ ፈጥሮ ላበጃጀው

ተከፍቶ የቆየ ፥ ጉሮሮውን አይቶ

አሞራ ይመግባል ፥ ህብስቱን አብዝቶ።

ብለህ ተናገረው...

ተስፋውን ቀጥለው

አስፈራርተህ ሳይሆን ፥ ፍቅርን ችረህ ሳበው።

ደግሞም ይሄ ምስኪን!

ያልከው ውሉ ጠፍቶት ፥ ዳግም ከጠየቀ

ከሠሙ አንደበትህ...

ወርቁን ማወቅ ሽቶ ፥ ምናቡን ካራቀ

አሞራ የምልህ ...

አይደለም በራሪው !

አይደለም አዕዋፉ !

አሞራው እኛ ነን ፥ አዳም ባለ ክንፉ

ሁሉ ምሉዕ ሆኖ ፥ አንዳች ሳይጎልበት

በሄዱበት መክሰም ፥ 'መልመድ ልምድ ' ሆኖበት

ለመልዕክት ሲሰዱት ...

እሺ ብሎ በሮ ፥ መምጣት ያልቻለበት

ብለህ መልስለት! !


@getem
@getem
@getem
:
ስጁድህን ወርደህ ገና በጅማሮ ሳትጨርስ ረ' ካ፤
እንኳንስ ጀሊሉ ፤
መለይካው ልጅ ሁኖ ያረበና እያለ ይስምሃል ለካ ።

መልካም ጁምኣ!!!💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
" ልጄ "
( በአምባዬ ጌታነህ )
አንደበቱ ጣፋጭ ንግግሩ እውነት፣
ያስደስታል በጣም ልጅ ሲቦርቅ ከቤት።
ሲኮላተፍ ሲስቅ ሲራመድ ሲያወራ፣
ሲጫወት ሲያለቅስ ሲተኛ ሲፈራ፣
አለም አይደል እንዴ መኖር ከልጅ ጋራ።

መረበሽ ነው እንጅ ተው ብትል አይሰማ፣
ተው ማለት አርግ ነው በልጅ ቋንቋ ዜማ።
ልጅ ቤት ሲኖር አይደል፣
ጎጆ የሚመስል፣ ከሩቅ ሆኖ ሲታይ፣
ያትረፈርፈዋል ልጅ ነው ትልቅ ሲሳይ።

ሙሉ ነው ጎጆየ የለም የጎደለኝ፣
ስገባ ልጄ አለ አባየ የሚለኝ።


@amba8


@getem
@getem
@amba88
ማፍቀር መታደል ነው!!!
(ቡሩክ ካሳሁን)

እኔን ከማይጥሙኝ ከማልስማማበት
አባባሎች መሃል ሊይውም በዋናነት
ስህተታዊ ሃሳብ በውስጡ የያዘው
ምንድን ነው? ብትሉኝ ‹ማፍቀር መታደል ነው›
ማፍቀር መታደል ነው አዘውትረው ሚሉ
ፍቅር ያልገባቸው አወቅን ባይ ሁሉ
ቢገባቸውማ መቼ እንዲህ ይላሉ!
የእውነት ላፈቀረ ማፍቀር ስህተት ነው
የፍቅሩን ጥልቅነት ዝምብሎ ሲያጤነው
ከራሱ አብልጦ ለሌላው ማሰቡ
መጨነቁ ሁሉ አብዝቶ ከልቡ
ስህተት ሆነበት ሲያስበው ሲያስበው
ምክንያቱ ምንድን ነው?
ፍቅሩ የእውነት ነው!!!
ማፍቀር መታደል ነው እነማነው ሚሉት?
የናንተን እኔንጃ እስኪ የኔን ስሙት
እኔን የሚመስለኝ ወይ የተፈቀሩ
አለበለዚያ ግን የውሸት ያፈቀሩ።
ስለምን ይላሉ እነዚ ሁለቱ
የተመረጡበት ምንድን ነው ምክንያቱ?
ፍቅር በዚህ አለም ባይኖረውም ፍቺ
ተመጣጣኝ ሚሆን ለመግለጽ አመቺ
ላስተዋለው ሰው ግን ሳይሆን ከላይ ከላይ
ፍ.ቅርን ይለዋል ደስ የሚል ስቃይ
ከዚህ ተነስታቹ የፍቅርን ፍቺ ትርጉም ስትባሉ
ምንም ሳታቅማሙ ስቃይ ለምትሉ
‹ይህን ስቃይ በዝች አለም
የሚገልጸው ቃላት የለም›
እንዳለው ዘፋኙ
እውነቱን ነውና በሉ አተሞኙ
ስቃይ ፍቺው ባይሆን ባይተጉመውም
ግን ተጠቀሙበት እንደ ተውላጠ ስም
ታዲያ ለምንድን ነው አዘውትረው ሚሉት
የተፈቀሩና የውሸት ያፈቀሩት
ምንስ አገዳቸው እንዲህ እንዳይሉ?
የእውነት አፍቅረው ፍቅርን ስላላዩ
የእውነት አፍቅረው ስቃይ ስላላዩ
ለዚህ ነው ማይጥመኝ ስሰማው ሚቀፈኝ
ለሽንገላ ቃላት ቦታ ስለሌለኝ
ማፍቀርን በራሱ ካሉ መታደል ነው
መፈቀርስ ደሞ ኸረ እስኪ ምንድን ነው?
ይልቁንስ ማፍቀር መታደል ሚሆነው
ያፈቀሩትን ሰው ከእጆ ካስገቡ ነው
ከእጃቸው ያስገቡ አባባሉን ቢሉ
ለትንሽ ትልቁ ለጠየቁ ሁሉ
ብላቹ አታስቡ የውነት ከልባቸው ስላላፈቀሩ
መሆኑ ነው እንጂ በተዘዋዋሪ ስለተፈቀሩ፡፡
24/10/2006

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc


@getem
@getem
@getem
#የናቴ~ልጅ~እኔ

ከፊትሽ ገፅ ላይ
ቁጭት አነባለሁ
ማየትን የጠላ ማንነት እረክሶ
ጥርስሽ ይናገራል
የልብሽን ሚስጥር ከንፈርሽን ነክሶ

ጠይም ወዘናሽም
ሀበሻዊነቱን ማርጀትሽ ሳይነጥቀው
የግንባርሽ ሽብሽብ
ያ'ይኖችሽን ብሌን እይታ ሳይሰርቀው

ባገር ተመስሎ
እልፍ አንቺነትሽን በግልፅ እያወጋኝ
የዛሬው እኛነት
ካንቺ ሲነፃፀር ብርታቴ አሰጋኝ፡፡

ግና ተስፋ አልቆርጥም
የደምሽ ውጤት ነኝ ካንቺው የተቀዳው
ለዚህ ነው እምዬ
ሺ ዘመን ቢቀየር
በ'ናትና ባ'ገር የማላወላዳው፡፡

ልብ አልባው ገጣሚ

@getem
@getem
@getem
ብላችሁን እንጅ፤
ነግራችሁን እንጅ፤
ጎጆአችን ፈራርሶ በትልቅ አዳራሽ እንተካው ብላችሁ ፤
ምነው በስተማታ ፤
ተሰርቶ ሲያበቃ አናስገባም የሚል ነገር አመጣችሁ ፤
አደራ እንዳትረሱ ፤ ፤
የክብሪት ዘመዶች፤
ዛሬም ማንደጃውን በገል ተሸክመን አለን በቤታችሁ ።

(( ጃ ኖ ))💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ከሙፍቲ ኡመር ቤት እሁድ ሆጤ ዝለቅ!!!"
በሸጋ ሙሃባ በኢልምና ኢማን የተሽሞነሞኑ ፤
በዚህ በኛ ሪጋ በላይኛው ገታ በታችኛው ቃሉ፤
ደባትይ ዛውያው፤
ዳና ከጎራው ዘንድ አደብና ኪታብ አንድ ላይ የቀሩ ፤
በዱኣ በቱፍታው በኑር በከራማ የተሽቀረቀሩ ፤
ጥላ ሚሆኑልን ፤
የሰው ዛፍ ዋርካዎች ዛሬም በዚህ አሉ ።


ትከጅል እንደሆን ፤
የበረካ ትንፋሽ ካሰኘህ እንደኔ ፤
እሁድ ሆጤ ዝለቅ ፤
ወሎን ያሽሩታል በሰውኛ ለዛ ሸህ ኡመር ቦረኔ ።
ሰውነት ምሰሶ ሰውነት ማገሩ ፤
ሰው መሆን መነሻው ሰው መሆን ድንበሩ ፤
ሆጤ ከሜዳው ላይ ፤
አርሂቡ ብሎሃል የሙፍቲ ኡመር ቤት ወሎ ገራገሩ ።

ሸጋው ቅዳሜ!!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ገላ መንገደኛ
(በዕውቀቱ ስዩም)

ገላ መንገደኛ : በመሸበት ያድራል
ሲመቸው ተሻግሮ: አዲስ ቤት ይሰራል
ልብ ነው ቁሞ-ቀር
እንደ ጥንቱ አይሰላም : የለመደው ሲቀር::

@getem
@getem
@getem
ክብርሽ ተዘንግተው
ስለ እ*ስ ስለ ቂ* ሲወራ ሚረኩ
እነሱ ደድበው
የደደበ ሀሳብ ደርሰው ለሚያመልኩ
የመዘመን ጥጋት
ሆነሽ የተሳልሽው የመክሰም ጅማሬ
ነቅተሽ ያሸለብሽው
የከንቱዎች ቀዬ እንዴት ነሽ ሀገሬ?

እኔማስ ደህና ነኝ
ምን ይሆናል ብለሽ ከቶ አትጨነቂ
ብቻ ግን እምዬ
መተኛቱ ይብቃሽ እባክሽን ንቂ፡፡

እኔን የጨነቀኝ
ተኝተሻል ብለው በጎጥ ሊደልሉኝ
መልስ እንዳላጣ ነው
መምጫቸው ጠፍቷቸው ከየት መጣህ ሲሉኝ፡፡


(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@getem
።።።። መአ....ት አባወራ ።።።

እንዳየነው በተለምዶ
ልጇን ወዳ ልጇን ወዶ
ተጋግዘው በአንድነት
ሁለቱ እያበሩ
በመታገዝ ፋንታ
ልጆችን ከጦሩ
ባንድ ቤት ባንድ ጣራ
ሲፈጠር ይኖራል መአ......ት አባወራ።

@getem
@getem
@paappii

#biniyam fikadu
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጭንቄን ተን-ፈስ
""""""""""""""""""""
አሰይ ፈሳሁ
ኡፈይ ፈሳሁ
እንኳን ፈሳሁ

ነገር መውጫ ሲያጣ መዳኒት ነው ለካ ፈስ
የሀሳብ ምጥን ላረገዘ
ያደርገዋል ለካ ተንፈስ
ምስጢር ሰው እንዳይሰማ በትንሹ በቀስ በቀስ
-ፕስስስስስ-

(አልያም)
ከፈለገም ሰው ይስማው
በፈለገው ይተርጉመው
ከድምፁ ቢጎድል ከጠረኑ ላያመልጥ
እና እኔ ምንተዳዬ ቢጋለጥ- ባይጋለጥ
-ዘረጥጥጥጥ-


ታዘብኩሽ ቂጤን ላልላት
በሰው ፊት ብታዋርደኝ
ጭንቅላቴን ነው የታዘብኩት
በአፍ ማውራትን ቢያሳቅቀኝ
በፍራቻ መረብ ሰቅዞ
ሀሳብ ነፃነቴን ቢቀማኝ
እሱን ነው የታዘብኩት
ሌላውማ ምን አረገኝ?
***

ይሳቁ ያልገባቸው
የሆድ ነገር ጭንቀት ምሱ
ተገላብጦ መውጫ ሲያጣ
የሀሳብ መንገድ ግሳንግሱ
አፍ ተለጉሞ ሲያዝ
ባይናገር በምላሱ
ነገር በታች እያላሉ
እፎይ ማለት ግድ ነው ሳይሳቀቁ በፈሱ
የሆድ ባህር ጭቃው መንገድ
እንዲጣራ ድፍርስርሱ።

(በትንሹ በትንሹ)

ወይ ዘረጥ ----ይለይለት
ወይ ቱስስስስ--- በቀስ በቀስ
****

ሳቁ እናንተ ልፈሳ ነው
አይገባችሁም ነገሬ
ግን ሆዳችሁ ነገር አዝሏል
ሳያችሁ በትኩረት አንክሬ
እኔ ግን ልፈሳ ነው
አፍኖኛል ጭንቅ አጅሬ!!!

ከሳቃችሁ ግን-እሰይ ፈሳሁ
ኡፈይ ፈሳሁ
እንኳን ፈ

ሁ።

አብርሃም
@Run_Viva_Run


@getem
@getem
@getem
እኔም ቁስል አለኝ

እኔም ቁስል አለኝ ያንተን የሚመስል
ልክ ያንተ ሲነካ የኔም የሚቆስል
እንደ ፈላ ውሀ፤
እንደ ሰደድ እሳት እጅግ የሚያቃጥል
እኔም ቁስል አለኝ ያንተን የሚመስል
አንተም እንደኔ ሰው ፤እኔም እንዳንተ ሰው
ማወቅ አልፈልግም ዘርህን ወደዛው
ወንድምህን ስታጣ አንጀትህ ሲቆስል
በዱላ ተተልትሎ ጀርባህም ቢቆስል
በእግዜር እምላለው ምንም ሳላስመስል
እኔም ቁስል አለኝ፤ ያንተን የሚመስል

@Leulewnetu

@getem
@getem
@getem
#ህልሜና ~ትርታሽ

በሰመመን ጉዞ
እርቄ ከትሜ ውን አለሜን ትቼ
ከመዳፍሽ እቅፍ
በጡችሽ መሀል ልብሽ ላይ ተኝቼ
ለምን እንደው እንጃ
በትርታሽ ምናብ እቁነጠነጣለሁ
ከሀሳብሽ ሞገድ
ግራ የተጋቡ ቃላት አደምጣለሁ፡፡

መሄድ ነው ውጥንሽ
ከ'ኔነቴ መራቅ መልመድ ከሌላ ሰው
ታዲያ በምን አቅሜ
ከ'ንቅልፌ ነቅቼ ህልምሽን ላፍረሰው?

አልችልም ታውቂያለሽ
የማፍቀሬ ጣራ ነፃነት ነው ጥጉ
መሻትሽ ቢያመኝም
ከጉዞ አይገታሽም አንቺን መፈለጉ

እናም በሃሳብሽ
እርቀሻል ብዬ አልነቃም ከ'ንቅልፌ
ነግቶ እስክትለይኝ
በእጆችሽ ላይ ልደር እቅፍሽ ነው ትርፌ፡፡


(ልብ አልባው ገጣሚ)

@getem
@Getem
@gebriel_19
©©ሳይፀልዩ ማደር☜☜

የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋዋ ፀለየች አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ
አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ሚዳቋዋን አይቶ
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ

የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውን ሠማቸው ፈጣሪ

አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋን አላት
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታ ጠላት
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት ምግብ አርገክ ብላት
ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ
ነብሩም ሢከተላት ሆዱን ሊሞላባት

ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተሥፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛ ከርከሮ

ከንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር

አውጣኝ ያለው ወቶ አበላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው ከርከሮ ተበላ

☞☞☞☞ በረከት በላይነህ☜☜☜☜



@lula_al_greeko
@getem
@getem