ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
:
"ተያይዞ ቢቆም ፥ ሁሉም ለአመሉ
አጥር አይምሰልሽ ፥ የከበበሽ ሁሉ!"
。。。
በረከት በላይነህ©

@getem
@getem
@gebriel_19
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6 እነሆ ወቅታዊ ጉዳዮችን እና መዝናኛን አካቶ ለንባብ በቅቷል።
Forwarded from Melkam74 Digital Magazine
Melkam74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6.pdf
4.3 MB
📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6

💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰
ያ ምቹ ልማድሽ
———————
አንጥረሽ ያላሽኝ ፥ ደርሶ ትዝ ቢለኝ
እ'ከንፈሬ ዳር ዳር ፥ ጀመር ያሳክከኝ
ሱስ ገዳይ የነበር ፥ ተንሳፎ ባ'ቦል ላይ
ቅቤሽን ለምጄ ፥ ...መላስ ከላይ ከላይ
ጥላሽ የጠፋ ቀን...
ያ ''ምቹ'' ልማድሽ ፥ አማታኝ ከፀሐይ
.
« ሚኪ እንዳለ »


@getem
@getem
@MMiku
የሄን ጉዳይ ጥቂት ሰዎች ሆነን ነው የጀመርነው
የእርዳታ ጥሪ አልጠላችሁም?

እከሌ ታመመ ገንዘብ እናሰባስብለት/ላት፣እነ እገሌ ተፈናቀሉ፣ ለተፈናቃዮች ፣ ለህጻናት ፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለተጎጂዎ(በልዩ ልዩ ምክንያት)፣ለወንዞች፣,,,,ብዙ ብዙ የእርዳታ ጥሪ ,

አሀ እና ምናለበት ካላችሁ ብትረዱ? ያለው ይረዳል የሌለው ከንፈሩን ይመጣል ወይ ካለው ለምኖ ይሰጣል።እንዲህ ባንረዳዳ ኖሮ እንደህዝብ እንዴት ተደጋግፈን ቆመን ሀገር እንሆን ነበር?

ነጥቤ የእርዳታ ጥሪ ባይሆን ትብብር ስለመጠየቅ ነው። አንዲት አህታችን ሊባኖስ #ቤይሩት የሚገኙ በእስር ላይ የሚገኙ #እስረኞች እና በኤንባሲ ወደሀገራቸው ለመምጣት ጉዳያቸው እስኪያልቅ የሚቆዩ ሰዎችን በምግብ እና በተለያየ መንገድ ትረዳለች።

ከእኛ ይሄን ፈለገች - #መጽሀፍ ብቻ። ሴቶቹ በቆይታቸው ቢያነቡ በጣም በመንፈስ የሚታነፁ አይመስላችሁም? እስኪ እባካችሁ የምትችሉ መጽሀፍ በማሰባሰብ እናግዛቸው። ምን ትላላችሁ?
ያለንን እናካፍል

+251913836124 አብይ @abiywas3
+251919266760 ልዑል

በእነዚህ ስልኮች በመደወል ያነጋግሩን።

@getem
@getem
•••||||••• maddbn ➋➌

*° እውነቱ ይሄ ነው° *

አዝኜ ስከፋ ፤
መሬት ስቆረቁር
አንገቴን ስደፋ፤
ሠማይ የነበረው
በምድር ስር ሾልኮ፤
በቃ ተው አትዘን
እሷ የአንተ ናት እኮ፤
ብሎኛል አምላኬ
ነግሮኛል ፈጣሪ፤
ከእጄ ላታመልጪ
አትወጣጠሪ።
°°°°°°° *** °°°°°°°

@maddbn

@getem
@getem
#⃣ የለም

ፀጉር ቤት መብራት የለም
ባንክ ቤት ሲስተም የለም
ምግብ ቤት ውሃ የለም
ድሀ ኪስ ምንም የለም
ሀብታም ቤት የሌለ የለም
አልጋ እያለ እንቅልፍ የለም
ተምሮ ስራ የለም
ለቅሶ ቤት ሳቅ የለም
ንብ ይዞ ማር የለም
አለ እያለ በዓለም
ለኛ አለ የለም
በዚህ አይነት ተስፋ የለም።

by👉@maddbn

@getem
@getem
@getem
#የአዳም ተቃርኖ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።።
የአዕዋፍ ፣ የአዝርዕርቱ
ያውሬ ፣ የእንስሳቱ ፥ ንጉስ አ'ርጎ ሾሞኝ
ከመልኩ ደም ግባት.. .
ወዘናውን ጨልፎ ፥ ሰው አድርጎ ፈጥሮኝ
"አከበርሁህ" የሚል ፥ ቃሉን ቢሰጠኝም
የዱር አውሬን ያህል ..
የሚያስፈራ ግርማ ስለምን የለኝም?
እኔንጃ አላውቅም !
እውነት ንጉስ የሆንሁ ነኝ ወይ እንደ ቃሉ ?
እውነት እውነት ነው ወይ የርሱስ አባባሉ?
እንኪያስ ስለምን ነው?!
ሆዱን ጦም ሳያድር ፥ የምገዛው አዕዋፍ ፥ እውሩ አሞራ
በለምለም ተውበው ፥ አዝዕርት ተክሉ ፥ ከቆሙበት ስፍራ
እኔን እህል ናፍቆኝ ፥ ከጠኔ መጣፍ ላይ ፥ ብሶት የምቀራ?
በሉዋ መልሱ!

@getem
@getem
@getem
< ሲገባኝ.....>

ቀን ይታገሳታል
ፍቅሬ ያሳሳታል
በዚም ጋር ከፍቷታል
ፍቅሬ ተጨንቃለች
የሀሳብ ዳር አታለች
እኔም አስባለው
መኖር አብሮ መሆን
መኖር መለያየት
እዳልሆነ አውቃለው

መሳሳብ ነው እንጂ በደም መወዳጀት
መጣጣም ነው እንጂ በፍቅር መጃጀት
መራራብ ነው እንጂ በሰሀት ልዮነት
እንጂ መኖር ማለት
አይደል አብሮ መሆን
አይደል መለያየት፡፡


ፀሀፈ..ልጅ ኤቢ(አብርሀም)
@artbekiyechalal


@getem
@getem
ህግህን ገርበው!!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።

እግዜር ሆይ...

ላማክርህማ ቆይ !

ዳሽንን የሚያህል ፥ ትልቁን ተራራ

ዳሌ አበጃጅተህ ፥ አርቅቀህ ስትሰራ

አዳም በርሱ ስቶ ፥ በዝሙት ለመውደቅ

አቅል ቀልቡን ስቶ ፥ ባይኖቹ ለመስረቅ

ወደ ኋላው ማትሮ ፥ እንደማይዞር ስታውቅ

አታመንዝር ብለህ ፥ ህግን ስትቸረው

አይሆንም ወይ ስላቅ? ? :)

ኸረ ተው !

የሄዋኗን ውበት እንደማይሆን አርገው ።

እግሯ ሎሚ አይምሰል 

አድርግባት ጠብደል 

ከንፈሯ ጠቋቁሮ

ይምሰለን አሻሮ 😃

ጡቷም እይቀሰር.. . እንደ ጦር አይዋጋ 

እንደ ጆሮ አድርገህ ...

ጠፍጥፍባትና ፥ ከደረቷ ይርጋ ።

ደግሞም ...

ጠጉሯን አይተን ፥ እንዳንገባ ጣጣ 

ከራሷ ላይ ላጭተህ ፥ አድርጋት መላጣ።😂😂

ኸረ ተው !

ድመት አርገህ ፈጥረህ 

ቋንጣ ማንጠልጠሉን 

ፍየል አበጃጅተህ

ነብር መኮነኑን 

ልክ አይደለምና ...

ስራህን ከልሰህ ፥ ፍጠር እንደገና ።

ምነው እቴ ተቃፀልን እኮ :)

@getem
@getem
@getem
ያንቺ ፍቅር ሰይጣን!

፨ ሚካኤል አስጨናቂ ፨

ያንቺ ፍቅር ሰይጣን!
ካህን የማይፈራ
ፅናፅል ስዕሉን
ቀርቦ ያናናቀ
ያደረገ ተራ!
.

ቁርባን አስደንግጦት
ታቦት ያላራደው
የመንፈስ ነበልባል
የመንፈስ እሳቱ…
ስሜት የማይሰጠው!
.
በክፋት ተስሎ ፥ በስሎ የመጠቀ፤
በፀበል ፣ በፀሎት ፥ ቦታ ያለቀቀ።
.
ዓይን የሚሰውር ፥ እንስት የሚጋርድ፤
ካንቺ ገላ ውጪ ፥ ሌላ ‘ማያስወድድ።
.
ሀሳብ የሚሰልብ ፥ የመንፈስ ጠበኛ፤
በቅናት ጠፍሮ ፥ ሌት ‘ማያስተኛ።
.
ያንቺ ፍቅር ሰይጣን!
ደቁኖ የቀሰሰ!
ከሰዋራ ገዳም…
ዓለም በቃኝ ብሎ
ሙቶ የመነኮሰ።
.
ያንቺ ፍቅር ሰይጣን!
ይለቅ እንደሁ ብለው….
እምነት እየቀቡ ፥ በላይ ቢለውሱት፤
ሰይፈ ሚካኤል ፥ ተዓምረ ማርያም፤
እያነባነቡ ፥ በሽብር ቢያምሱት፤
እጣን አጫጭሰው ፥ ዜማ እያወረዱ፤
ቅዳሴ ቀድሰው!
ከበሮ ደልቀው !
ልቡንም ቢያርዱ ...............
“እንቢኝ ፥ አሻፈረኝ”! አለቅም እያለ፤
እንዲያ እንዳልተኩራራ……
እንዲያ እንዳልፎከረ ……….
.
አንቺን ከሌላ ሰው ፥ ያየሽ ‘ለት ደንብሮ፤
እኔን ለቆ ጠፋ ፥ ቀድሞ ከቀጠሮ ።

@getem
@getem
@getem
ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እንኳን ለ ኢዳልፈጥር በአል በሰላም አደረሳቹ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
🕌 ኢድሙ ባረክ 🕌
🕌 @DEREAMANDESE 🕌
🕌 @getem 🕌
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብርዬ)
ሰላም ጤና ይስጥልኝ. አርቲስት #በረከት_ግርማ (አቢቹ) እባላለው የአዲስ አበባ ነዋሪ ስሆን የተለያዩ የኪነ #ቅርፅ እና ኪነ #ቅብ ስራዎችን እሰራለው። ስራዎቼን @artbekiyechalal ገፅ ውስጥ በመቀላቀል እንድትጎበኙልኝ በ አክብሮት ጠይቃለው።.................

@artbekiyechalal @artbekiyechalal

አመሰግናለው!!

@seiloch @seiloch
በዓለም ላይ ምን ያህል ታራሚ እንዳለ ያውቃሉ?
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
የምን ታራሚ የሚለው ጥያቄ ይቅደም
(የህሊና፤የማረሚያ ቤት(በእርግጥ የህሊና እስር ቢኖረውም)፤ የሌላም ሌላም..)
.
ለማንኛውም አልቆጠርኳቸውም ለማለት ነው የቆጠራችሁ ወዲህ በ ካላፊ ካግዳሚ ከሚመላለሰው
ማነው የሚፈታው የታሠረውን ሠው? በርግጥ የሚፈታው ህግ ቢሆንም ታራሚዎችን መፅሐፍት እንዲያነቡ
መርዳት ማለት የአስተሳሰብአድማሳቸውን አስፍተው ለሕብረተሰባችን ካጠፉት ጥፋት በላይ እንዲክሱ ማድረግ መቻል ይመስለኛል። እስቲ ግድ የሎትም ነገ ብሔራዊ ቴአትር 11 ሰዓት ላይ ታራሚዎች ቢያነቡት ይጠቅማቸዋል ብለው የሚያስቧቸውን ሁለት እና ከዚያ በላይ መፅሐፍት ይዘው ይምጡና የጥበብ ድግሱን እየኮመኮሙ ታራሚዎች እንዲታረሙ ያድርጉ!!...አደራ ተብላችኋል ለማለት ነው አመሠግናለሁ

@getem
@wegoch
# እኔ~ማለት~እንዲህ

እግዜር በጥበቡ
ለምለሙን አፈሯን በጊዮን አቡክቶ
ለእምነቴ ክታብ
አክሱም አልነጃሽን በዙሪያዬ ሰርቶ፡፡

የሀበሻን ምድር
እንዳሻህ ኑርበት ብሎ ያወረሰኝ
አስፋሪ ሰፋሪ
ሚሉት ጠባብነት የሚኮሰኩሰኝ፡፡

የቃሉ ተስፈኛ
የምፅኣት ዘመን ክብሬ ሰማያዊ
ታሮስ ማለት እኔ
ሀገሬን የምወድ ኩሩ ኢትዮጲያዊ፡፡

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem
እንኳን ለ 1440 ኛው የ #ኢድ_አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን!

መልካም በዓል

@seiloch
@getem
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
Eid-Mubarak
@Mykeyliyew
የቀረንን እንጫወት
ተኩሰን ብንስትም ሞት ፈርተን ግን ነፍስ አንሰስትም!
ህልም ባንከስትም ራዕይ አለንና አንወሰልትም!
ቢያንስ ሰው ነንና ሰው እንወዳለን!
እንዳመጣጡ እናስተናግዳለን!
ምድር ከተፈጠረ ምስጢር ከተቋረጠ
እስካሁን እስካለንበት
ከድህነታችን በቀር እኛነታችን
ሰው ፊት የማያስቀርብ ምንም እንከን የለበት!!
ደማችን ውስጥ ኢትዮጵያዊነት አለበት።

(( ሙልጌታ ተስፋዬ -የባለቅኔው ምህላ ))💚💛

ሸጋ ቀን !!💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ቅድስቷን ሀገሬን
አቆሽሻት ብዬ እድል ከምሰጥህ
እርዳታህ ይቅርብኝ
ደሀ ሆኜ ልኑር በማጣት ልብለጥህ፡፡

ዝም አልልም እኔ
ግብረ ሰዶም ሆነው ከቤቴ ሲመጡ
እዛው በቀያቸው
ከበክትነት ጋራ አርፈው ይቀመጡ፡፡

ሼር ጓዶች ጉዳዩ ቸል የሚባል አይደለም፡፡ የመንግስት
ቸልተኝነትም አልጣመኝም ለክብራችን

((ልብ አልባው ገጣሚ))

@getem
@getem
@getem