ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ረድኤት_አሰፋ

ከዛኛው መደዳ ፥
"ፍሬ ነሳኝ" ብላ፥ ባምላኳ ያቄመች፤
ሰልፏን አመናቅራ፥
ከዚኛው መደዳ ፥መጥታ ተሰለፈች፤
ልጁን የሰጣትን፥
የሰልፏን ፈጣሪ፥ በልጇ ቀየረች።
ከዚኛው መደዳ፥
ፍሬው የከበበው ፥ምንዱብ መፃተኛ፤
የጨቅላ ጉሮሮ፥
ለመድፈን ሲዳክር ፥ይነጋል ሳይተኛ።
ምሬት አስረግዞ፥
ልጅና ማጣቱን፤ ማዘል ያደከመው
ከዚህ ሰልፉን ትቶ፥
ከዛ ለመሰለፍ፥ የለም የቀደመው።
ፍላጎት ሲነግስ፥
ጥማት ልክ ሲያጣ፥ መሻት መርን ሲለቅ፤
በራስ እየለኩ፥
ፈጣሪን መቅረጽ ነው፥ የዘመኑ ማወቅ።

@getem
@getem
@gebriel_19
#ረድኤት_አሰፋ



የጁምዐን ኩታ ፣ ንፋስ ዘረጋጋው
የሚራወጠውን፣ ቀኑን አረጋጋው
ከሰብት እስከ ኸሚስ፣
የየ'ለቱን ቀለም፣ አንድ አረገው መልኩን
ኩታው እስኪታጠፍ፣
አናውቅውምና ፣ የየቀኑን ልኩን
ማወቅ የተመኘ፣
ቤቱ ተሰትሮ፣ይለምን አምላኩን።



٭ ሰንበት የተጣደው፣ ቢገነፍል ድስቱ
٭ እረፍት ታጠኑ ፣ 'ወጥ' ኾኑ ስድስቱ።
٭ ሁሉን ቻዩ አምላክ ሰባት ያረጋቸው
٭ ይሰተሩ ብሎ፣ ባንድ ሾረባቸው።
٭ ተደባልቋልና፣ የሰንበት ቅጥሩ
٭ ወድቆበታልና፣ የእሁድ አጥሩ
٭ ሰኞ ሀሙስ የለም፣ ቀን ፈርሷል ድንበሩ
٭ እስኪለይ አርፋችሁ
٭ ሳምንቱን በሙሉ፣ ሰንበትን አክብሩ
.
.
@getem
@getem
@getem
#ረድኤት_አሰፋ
.
¹አብ ልጁን ለዳረው፣ ምን አስቀናት ፀሐይ?
ፊቷን ያጠቆረች፣ ዓለሙን እንዳያይ።

²ሊጠቅመው አስቦ፣ አባቱ በመላ
ላጀበው ሰው ሁሉ፣ ፅዋውን ሳይሞላ
ልጁን ብቻ አጠጣው፣ የድግሱን ጠላ።

³ደሃ አባት ደግሶ፣ ታዳሚውን ሁሉ
በሬ ሳያዘጋጅ፣ ነው የጠራው አሉ፤
ካጀቡት በኋላ፣ ተጠምተው ተርበው
ከልጁ በስተቀር፣ የለም የሚያቀርበው።

⁴ስንት ቢታረድ ነው፣ ምን ያክል ቢደገስ
ስጋው የሚበላው፣ እስከዛሬ ድረስ?
⁵ የተሰቀለውን፣ ስጋውን ሳይቀምሱ
አጃቢዎች ምነው፣ ተሻሙ ለልብሱ?
⁶ ለሙሽራው ሀሞት ፣ ምን ያኽል ቢጥም ነው?
ለሚዜዉቹ እንኳ፣ አላጠጣም ያለው?

@getem
@getem
@getem
1
አርምሞ
.
.
ፍቅርና
ህብረት፥
አጥሩን ካልጣሰ
.
ንስሃና
ይቅርታ፥
ተበዳይ ካልካሰ
.
ፍርጠማና
ጡንቻ፥
ማዕበል ካልገታ
.
ጥበብና
ብስለት፥
ቋጠሮ ካልፈታ
.
ብትነቃም
ብታውቅም
አቅምህን
ሰብቀህ፥
እንደ ናዝሬት ጌታ
.
ሀቅህን
ባደራ
የምታኖርበት፥
የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ
.
ሽንፈት
እንዳይመስልህ
ቀን
ቆጥሮ
እሚያደባይ
አቅም ነው
ሃይል ነው
ጉልበት ነው ዝምታ።


#ረድኤት_አሰፋ
@getem
@getem
👍1