ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ናፍቆት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እንዲህ እንደዛሬ...
በመሀከላችን
ንፋስ ሳይግባብን ፣ ፍጥረት ሳይፈጠር
በኔና አንቺ መሀል...
የነበረው ክፍተት ፣ አንድ ስንዝር ነበር።
አንቺ ሰማይ ሆነሽ እኔ ደግሞ ምድር!!!
............................................
በዚህ ስንዝር መሀል....
እስትንፋስ ያላቸው ሰዎች ተፈጠሩ
እነዚህ ሰዎችም....
ቅርብ ላለች ሰማይ
የምድርን ሀጥያት ይነግሯት ጀመሩ።
"ምድር ዘማዊ ነው
ምድር ሀጣዊ ነው
ብትሸሺው ይሻላል ይህ ዓለም ጠፊ ነው"
እያሉ ሲነግሯት የሰው ወሬ ሰምታ
ሰማይ ፊኛ ሆና...
ትለጠጥ ጀመረ ከኔ ተለይትል
በሰዎች እስትንፋስ...
ወደ ላይ ተነፍታ
ወደጎንም ሰፍታ።
.......................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
................................................
እንደውም እንደውም...
በዛ ስንዝር መሀል ያኔ የተፈጠሩ
እዛሬ ላይ ሆነው..
"ሰማይ ቅርብ ነበር" እያሉ ሚያወሩ
እድሜ የሰጣቸው
ጥቂት ሰዎች አሉ
የኔና ያንቺ ፍቅር የሚመሰክሩ።
.............................................
እንደውም እንደውም....
ሌላ አይነት ማስረጃ ሌላ አይነት ምስክር
ሰማይ ቅርብ ሳለሽ ምጣድ ሆኜ ምድር
እንዲህ እንደዛሬው...
ነፋስ አቀጣጥሎት
ነፋስ የሚያጠፋው እሳት ሳይፈጠር
የሰው ልጆች ሁሉ
በፀሐይ በርሀን ምግብ ያበስሉ ነበር።
.............................................
ፀሐይ ውበትሽ ነው ጠዋት የምሞቀው
ቀን ተቃጥዬበት ሌት የምናፍቀው።
ለሊት ላይ ያመኛል ህመሜም አንቺው ነሽ
ቀኑ ጨለማ ነው...
ነግቶ እስካይሽ ድረስ ትናፍቂኛለሽ።
...........................................
መቼ ነው ሚነጋው?
ፀሐዩ ውበትሽ ምድርን የሚከድነው
መርዙ መድሀኒትሽ...
በሽታዬን ገድሎ ህመሜን ሚያድነው
ካፈቀሩት ጋራ....
እንኳን ላንድ ለሊት
ላፍታ ያህል እንኳን መለያየት ሞት ነው።
.............................................
መቼ ነው ሚነጋው ልቤን ይበርደኛል
ንጋት ላይ የሚሸሽ..
ወረተኛ ፍቅር ጤዛው በዝቶብኛል
አንቺ የሌለሽበት...
ራሴን ሳስበው ራሴን ያዞረኛል።
ለራስ ምታት ህመም..
መድሀኒት እንዲሆን
በሽታን የሚገድል መርዝ ነው ሚቀመም።
...................................
እንጂማ አውቃለሁ እንጂማ ታውቂያለሽ
የሰው ወሬ ሰምቶ ልብሽ ባይረበሽ
እንዲህ እንደዛሬ.
ሳትርቂኝ በፊት ሰማይ ቅርብ ነበርሽ።
........................
እየሔዱ መጠበቅ

@getem
@getem
@gebriel_19
🚭ክብሪትን ለሻማ🚭
ያኔ
እሳት ምግባችን እንዳልነበር
በጭስ በአልኮል እንዳልተጨፈረ
አሁን
ያ ጊዜ ሕልም ሆኖ ከመቃብር ቀረ
አንዳንዴ ሳስበው
በጣም ይገርመኛል
ያጊዜ ያ ሰዓት የሞኝነት አለም
የጅልነት መንደር መስሎ ይሰማኛል
እስቲ ምን ይሉታል
ጭስን እየሳቡ
በሀሳብ መብሰልሰል
ደሞ ቅጠል መብላት
ሚገርም አለመብሰል
በኛ ቤት አራዳ አርደን ሞተናል
ጭስ ነው ሰላማችን
ቅጠል ነው ምግባችን
እንላለን ደሞ አለማፈራችን
የሚገርም ቂልነት
የሚገርም ሞኝነት
አፍን ዋሻ አድርጎ
እድሜን ቀነጣጥቦ
እያወቁ መሞት
አሁን
ጊዜ ተቀይሮ ያ ሁሉ አለፈና
ለመጠቀም በቃን
ክብሪትን ለሻማ😂😂😁
=====//====

💍Ati Ta Adi💍
3:55 Pm

@AtiTaAdi


@getem
@getem
@getem
"ኑ ሀገር እንስፋ!"
።።።።።።።።።።።

ክፍፍል መችነበር፥
በአምላክ አሰራር ፥በቅድመ አፈጣጠር
ሰው ሰው ብቻ ነበር ፥ዘሩ ሳይቆጠር።
ሰውነት ተንዶ፥
እንዲህ እንደዛሬ ፥ ሳይኖር መበታተን
የመቆጣጠር ዛር ፥ መቃብር ሳይከተን
አንድ እናት ነበረን ፥
ቀሚሷ እንደኪዳን ፥ ሁላችን ምንለብሰው
ዛሬ ተለያይተን፥
ክብሯን እንደ እቃቃ ፥ ዳቦ ሳንቆርሰው።
ሻህላ ወረሰን፥
ውስጣችን ተበላ ፥
ፍቅር የጠመቅንበት ፥ ተሰበረ ጋኑ
ለናታችን ቀሚስ፥
ጥጥ የነደፍንበት ፥ ተጣለ ደጋኑ።
ሰው ተተነተነ፥ ሰው ተቆራረሰ
ዘር ስንቆጣጠር ፥ ሀገር ፈራረሰ።
ፍቅር እንደቁና ፥ አርጅቶ ተጣለ
ጥላቻ ድንኳኑን ፥ በላያችን ጣለ።
የናታችን ቀሚስ፥
ባለሶስ ቀለሙ ፥
በሰማይ ዳስ ሲጥል ፥ ለምድር የሚያጠላው
ትውልድ ሲናጠቅ፥
በ"የኔ ነው !" "የኔ " ፥ የጥል እሳት በላው።
ይኼው እና ዛሬ…!
ያች ሙሉ እመቤት
ያቺ ሸዋ ግርድሽ፥
በክፍፍል ክናድ ፥
ከፍቅር ሰገነት ፥ከርማ ስትገፋ
እርቃኗን ቆማለች፥
የቃልኪዳን ልብሷን ፥ ቀሚሷን ተገፋ።
ያ ብልህ አያቴ
ትውልድ በሽሚያ ፥ የቀደደው ልብሷን
ሊሰፋ ይጥራል ፥ የክብር ቀሚሷን።
ስሩ ተቀምጬ፥
በልጅ አእምሮዬ ፥ ጥያቄ ይዘንባል
በቦዘዙ ዐይኖቹ፥
ክሩ ከመርፌው ጫፍ ፥ ላይገባ ይዛባል።
(እንዲህ ጠይቃለሁ?
ምን ነካህ አባባ ፥
ይኼ ቅዳች ቀሚስ ፥ ዳግም ተጠግኖ
እንደቀድሞው አይጥል ፥ ውበቱ ጀግኖ?"
ለምን ትለፋለህ ፥? ብዬ ስጠይቀው
አያቴ እንዲህ አለኝ፥ እንባው እያነቀው።
ልጄ ሆይ አድምጪ፥
መስፋቴ ቅኔ ነው ፥ እንደወርቅ እንደሰም
አላዳውር አይል ፥ ስንጥቅ ኖሮት ቀሰም።
አስተውይ ልጄ፥
መርፌ ማለት ፍቅር ፥ ሰርስሮ ሚገባ
ክር ማለት ሰላም፥
ቀዳዳን ጠግኖ ፥ ዳግም ሚገነባ።
ይለኛል አያቴ፥
ፍቅር ባለው መርፌ፥ ነፍሱ እየተወጋች
ክር ላለው ሰላም፥ ደጀን እየተጋች
የእናቴን ቀሚስ
ሲጠግን ስላየሁ…፥
እንሆኝ አንድ ቃል…!
የናት ክበር ወድቆ፥
የለምና ለክብር ፥ የሚሰነቅ ተስፋ
ኑ እርቃን እንሸፍን፥ ኑ ሀገር እንስፋ።
።።።

በገጣሚት ዳግም ህይወት
ሰዕል በ Yohannese T Degu

@getem
@getem
@gebriel_19
፣፣፣፣፣ ደደብ ፣፣፣፣

ደደብ ባይባልም
አንዳንድ ደደብ አለ
ከፍ ያለ ሚመስለው
ሌላው ዝቅ ካለ


@getem
@getem
@paappii

(amdemariam)
ብሣና ላክልኝ
-------------
ገላዋ ካደረ ፣ እርቆ ከደጇ
አንተን ከከጀለች ፣ ከኔ ከወዳጇ
ከጉያህ የጣላት
ከገላህ ያዋላት
ልቧ ነው እመነኝ
ለኔና አንተ ኪዳን ፣ ..ብሣና ላክልኝ
.
« ሚኪ እንዳለ »
@MMiku

@getem
@getem
**** ቅደሚኝ ****
።።። @Johny_Debx ።።።
ሰው ቢኖርሽ ... የታል?
ከኔ ፊት እረፊ ~
ብንኖር ... ተፋቅረን!
ሁሉም ሰው አላፊ!
*
ማን ያለቅስ ... እንደ'ኔ?
ቆሜ ቅደሚ ና
ከ'ኔ ፊት ሙቺ ና !

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

@getem
@getem
@getem
👍1
​አንዳንዴ
ተፈጥሮ
የነፍሴን ስስ ጭራ
በስሜት ወጥራ
ባር ባር በሚል ጣቷ፣ ገርፋ ስትሞዝቀኝ
እኔም የማላውቀው፣ እሱም የማያውቀኝ
የሆነ ሩቅ ሀገር፣ አለ ሚናፍቀኝ ።

@getem
@getem
@paappii


#nuradin isa
Forwarded from SPACE COMPUTER
ፍቅር ፍልስፍና :ትዝብት ፖለቲካ
እዉነት እና ሀሰት :እምነት ፅናት ተስፋ
ባደሩበት ግርግም
በነሱ ምርኮኛ የተፃፈ ግጥም!!

#በጂማ ዶሎሎ international hotel
#በሀዋሳ rori internatinal hotel

ይመረቃል!

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
👍1
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (👋ገብርዬ)
🎨አርቲስት #ሩት_አረጋ ትባላለች የ 17 አመት ታዳጊ ስትሆን በሀዋሳ ከተማ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ናት፣ለየት ያሉ የሦዕል ሰራዎች አሏት ቻነሉዋን join በማድረግ ስራዎቿን ይጎብኙ።
@abiruta
@abiruta


@seiloch @seiloch
👉የ ማስቲካ ቅሬታ...
.
በክብር ተቀምጬ..
ካለሁበት ልጣጭ
አዉጥተዉ ሲያኝኩኝ..
እንዳልሰጠሁ ጣፋጭ
ጥፍጥናዬ ሲያልቅ...
እ ን ት ፍ...ብለዉ ተፉኝ😔
ለ ኣፋቸዉ ጠረን...
ደስ የሚል መኣዛ...
ቃና እንዳልሰጠሁኝ።😏
____/____
/
F.D.N
07/09/2011

@getem
@getem
@gebriel_19
🏿"በጭስ ተደብቄ"

መሄጃ ቢጠፋኝ ካንቺ ምርቅበት
አንቺን ሳላስጨንቅ እኔም ሳልጨነቅ
ዝም ከምልበት
ጭስን ምርጫዬ አረኩ
መደበቅን ወሰንኩ
ቀንም ሌትም በጭስና ሀሳብ
ስብሰለሰል ዉዬ
ሰውነቴ አልቆ በማሽን የላጉት
ጣዉላ መስዬ
ሰው ሁሉ በዓይኑ እየሳተ ያልፈኛል
ምን ብዬ ልንገርሽ ሰማይና ምድሩ
ገደል ሆኖብኛል
እየሄድኩ ቃዣለዉ እለፈልፋለው
አሁን አሁንማ ድምፄ ተለዉጦ
ጃዟ ያለቀባት ቴፕ መስያለው
በጭስ ዉስጥ ስደበቅ
ሰላም ይሰማኛል
አንቺን አንቺን ያየው
ከቅፌ የገባሽ መስሎ ይሰማኛል
አዎ እራሴን ልጣ ሰዉነቴም ይለቅ
ሱሪዬም ይካደኝ
መቀመጥ አቅቶት ከላዬላይ ወልቆ
እርቃኔን ያስቀረኝ
አንቺን ማጣት ለኔ ከዚህም በላይ ነው
ከገነት ተጥሎ ወደሲኦል ገብቶ
መቃጠል ያክል ነው
አዎ አጨሳለው በደምብ አጨሳለው
በጭስ ተከብቤ ሳልምሽ ኖራለው
አንቺ ማለት ለኔ ከምንም በላይ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ የፍቅር መማርያዬ
ልዩ ብዕሬ ነሽ
አንቺ ማለት ለኔ ፍቅርን ያየሁብሽ
ልዬ ብሌኔ ነሽ
በዓይኖቼ ያላየሁሽ እየሸሸው የወደድኩሽ
አንቺ ለኔ ልዬ ሴት ነሽ

@AtiTaAdi


@getem
@getem
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰካራሙ ሴራ

ሴራ በዚህ አገባብ ተንኮል የሚለውን አቻ ፍቺ ይዞ የሚገኝ ሳይሆን ይልቁንም በልብ-ወለድ፣ በፊልም ድርሰትና በመሳሰሉት አላባ ሆኖ ምናገኘውን ‹ሴራ› ማለትም ምክንያትንና ውጤትን በአንድ ላይ በመያዝ የታሪኩን ቅጥጥል የሚፈጥርልን እንደ ማለት ነው፡፡

ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል👇
@burukassahunc

@getem
@getem
#ረድኤት_አሰፋ

ከዛኛው መደዳ ፥
"ፍሬ ነሳኝ" ብላ፥ ባምላኳ ያቄመች፤
ሰልፏን አመናቅራ፥
ከዚኛው መደዳ ፥መጥታ ተሰለፈች፤
ልጁን የሰጣትን፥
የሰልፏን ፈጣሪ፥ በልጇ ቀየረች።
ከዚኛው መደዳ፥
ፍሬው የከበበው ፥ምንዱብ መፃተኛ፤
የጨቅላ ጉሮሮ፥
ለመድፈን ሲዳክር ፥ይነጋል ሳይተኛ።
ምሬት አስረግዞ፥
ልጅና ማጣቱን፤ ማዘል ያደከመው
ከዚህ ሰልፉን ትቶ፥
ከዛ ለመሰለፍ፥ የለም የቀደመው።
ፍላጎት ሲነግስ፥
ጥማት ልክ ሲያጣ፥ መሻት መርን ሲለቅ፤
በራስ እየለኩ፥
ፈጣሪን መቅረጽ ነው፥ የዘመኑ ማወቅ።

@getem
@getem
@gebriel_19
[#ፋሲል_ስዩም]
.
ጥፎ ለባሽ!
...///...
ደጋን ጨባጭ መዳፍ፣ቀስትን አስፈንጣሪ፣
የንድ አሳብ ዐውድ፣የፊደል ቃራሚ፣
አጁ 'የሻከረ፣
ጣቱ የተቃማ፣
ልባሱ ተቀዶ፣ገላው የደማማ፣
ሱሪው የወለቀ፣ሳያብድ ያበደ፣
የሰው'ነቱን ልኬት፣አስሮ ያነደ፣
በምናብ የሚነጉድ፣
በምናብ የሚነድ፣
ለምናብ የሚሰግድ፣
'ራቁታም ጫሪ፣
ራቁት ሰዐሊ፣
ራቁት ደራሲ፣
ራቁት አንባቢ፣

የሲቃውን ንባል በብዕሩ አርካሽ፣
ቅዳዱ ልባቡን ዳግ ጥፎ ለባሽ!
...///...

@getem
@getem
@gebriel_19
ስም ኣጣሁልሽ..

የ ቋንቋዎች ሚስጥር
የ ፈጣሪ ድንቅ ስራ
የ አምላኬ ልዩ ቀመር
እማ...
ኣንቺ ማለት እናትነት
እናትነት ፈጣሪነት...
ተፈጥረሽ የምትፈጥሪ
የፈጣሪ ድንቅ ስሌት
ኣንቺነትን ዪገልፅ ዪመስል
ስም ሰይመዉ በ ሁለት ፊደል
እማ...ቢሉሽ ምን ሊፈይድ
ስምሽ ከ አንቺ ሳዪዋሃድ
እማ የሚለዉ ጠባቡ ቃል
ተግባርሽን ላያሰላዉ
ላይገልፅልኝ የፍቅሬን ጥግ
ላንቺ የሚሆን ስም ፍለጋ
ከ ስሞች መሃል ስም ስምግ
ስም ባጣ እንኳን ስም አልፈልግ
ላወጣልሽ ኣልኳትንም
ለ አንቺ የሚሆን ስምፍለጋ
ካል ገጥሜ ስም አልሰራም፡፡
===/===
ቀን፡21/03/2011 በ፡ፊራኦል ደሰታ

@getem
@getem
@gebriel_19
ቀጥሮኝ ጠፋ ብለሽ
ስልኩ ዝግ ነው ብለሽ ፣እንዳትናደጂ
ፓወር ባንክ ያላት ጋር
ቻርጅ እያደረኩ ፣ አድሬ ነው እንጂ
በሌላ አትጠርጥሪኝ
ሲነጋ ደውዬ ፣ መጣለሁ ሳትቀጥሪኝ

(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem
@gebriel_19
ለ'ሷ


1ኛ
ይቺ...
አይሉዋት ነገር
ከብረት ጠጥራ ከድር የሀየለች
ከነብር አኩርፋ ከሠደድ የሞቀች
ከአጥቢያ ውበት ነጥቆ ውበት እሱዋን አርጎ
ነጎድጉዋዱ በርዶ
አለማቱ ላይኑዋ ከነአንገቱ ሠግዶ
እንዴት አንቺ ትባል?
ካጥንቴ ተፈጥራ
ከጎኔ እንደወጣች ቀዳማዊት ሄዋን ሥያሜዋ ይቅለል?

2ኛ
አንተም....
እንዳትባል
ከእ'ርግብ ለሥልሣ ከንብ የወዘነች
እንደአሮን ብትር ታጥፋ የተቃናች
እኩይ ፈገግተዋ........
ከሰማይ ክዋክብት ከጨርቃ ደምቆ ከፀሀየ የላቀች
ካናት እንደወጣ አደንዛዥ ቅራሬ ከደም የወፈረች
እንዴት አንተ ትባል?
ቅጠልን በእግዜሄር ቀይሮ በሚያብል

3ኛ
ስያሜ ማጣቴ.....
ለሥርንቅ ደረቷ
ፍቅር ነው መክሊቷ

@getem
@getem