ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ግድብ እና ገደብ

....ፀጉር ቤት
ተመላጭ እያለ መብራት ከነ የለም አትገረም ወንድም ይሄ ብዙ አይደንቅም

ለምን.....ብትል
መብራት ሀይል.. ኤልፓችን እራሱ
በቂ ግድብ የለም እጄ አጠረ ሆኖአል ተዘውታሪ ክሱ.

ግድብማ ሞልቶአል ገደብ እንጂ የጠፋው
ከእለታት ባንዱ ቀን.. ባንዱ ቀን ተነስተው
ግድብ ልንሰራ ነው ጨለማን ሚያጠፋ
ብለው ሰጥተው ተስፋ
እኛም ተስፈኞቹ ከልብ አምነናቸው
እነሱም ሆ ብለው ተሰፋችንን በልተው
ቦጥቡጠው ቦጥቡጠው በ ማን አለብኝነት የ ተስፈኛን ተሰፋ አረጉት እንክትክት

.....አባይ እንኩዋን በ አቅሙ
ማደሪያ የሌለው ግንድ ይዞ ሚዞረው
ግንዱን አስቀምጦ ጭንቅላቱን ይዞ አጃኢብ ነዉ ያለው

...እናም የኔ መልክት
ከሁሉ አስቀድሞ ከ ግድቡ ሁሉ በፊት
ገደብን እንወቅ እንኑር በ ለከት
ጋጠወጥ አንሁን ይኑረን ሰርአት.🙏

በ...ቢንያም ኤሊያስ
@ben_am

@getem
@getem
@gebriel_19
" #የሞራል_ብቃት ?"
-
መቼም ሰው ይስታል ፣ ዋናው መታረሙ
ህመም ሁሉ አይገልም፣ ዋናው መታከሙ፣
በሚል የሞራል ሕግ፣ የወል አስተሳሰብ
ያለማቆላለፍ ፣ ያለማወሳሰብ፣
ስለ አቋሙ ዝንፈት
ስለ ርምጃው ሽፈት
በተረዳኝ አቅም ባሽሙር ሳላነውር
ኮሶ ሁኖ ሚያሽር ሃሳብ ብወረውር፣
አለኝ ትንፍሽ አትበል ጩሆ በድንፋታ
ጫማዬን ሳታጠልቅ ሳትቆም በኔ ቦታ!
ወፈፍ አደረገው ...
ሊሰፍርብኝ ቃጣው ነቅንቆ ሊጥለኝ
ምናል ብረሳበት እግር እንደሌለኝ ፨
------------------///--------------
[በርናባስ ከበደ]

@getem
@getem
@gebrielAQL
"over dose"

ለሰው መድሀኒቱ
የሰው ልጅ ነው ብሎ
ሢያወራ ወዳጄ
አምኜው ያለውን
ሞቴ ቀርቦ ነበር
"over dose" ወስጄ

(amdemariam)

@getem
@getem
@getem
👍2
ግብረ ቴስቲ ሶያ
(ቡሩክ ካሳሁን)

ከአዳም ምቹ ህይወት ከገነት ቆይታ
መጾም መስገድ እንጂ መች ተረፈን ደስታ
ከህጉ ሳይወጡ ተድላን ሚፈልጉ
አኩሪ አተርን ፈጭተው ስጋ አደረጉ
ቴስቲ ሶያ ቢባል ቢበላ እንደ ስጋ
ግብሩ ጎዶሎ ነው ከጠረጴዛ አልፎ መች ይሆናል ለአልጋ?
ህግ መጣስ አንሽም አንት የፈጠራ አባት የጥበብ ማሳያ
እባክህ አምጣልን ግብረ ቴስቲ ሶያ፡፡

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል
@burukassahunC


@getem
@getem
@gebriel_19
ረድኤት አሰፋ

ቅዱሳን ቢደርሱት፥ ጻድቃን ቢጸልዩት
ሾላ በድፍን ነው፥
ጸሎትን ፈልፍለው፥ እንደራስ ካልበሉት፤
እጸድቃለሁ ብለሽ፥
ከገዛ ራስሽ ጋር፥ እንዳትካካጂ
ለጸሎት ስትቆሚ፥
'እክህደከ ሰይጣን'፥ ብለሽ አታውጂ።

@getem
@getem
@gebriel_19
ለምን ይመስልሻል
ጥላኝ ሔደች ብዬ ፣ የማልጨነቀው?
መንገድ ስለሆንኩኝ
መሔድሽን አይታ
የምትመጣ እንዳለች ፣ ቀድሜ ነው ማውቀው። (ርእሱ ነው )
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
።።።
ስንት አመታት ሙሉ...
በመጋባት ናፍቆት ፣ ልቤን አንጠልጥለሽ
የኔፍሴን ህያው መልስ ፣ ጥያቄ ላይ ጥለሽ
ቅድሚያ ለእግረኛ
ትሰጫለሽ እያልኩ
መኪና ሲመጣ ፣ ሔድሽ ተንጠልጥለሽ
፡፡፡፡፡፡፡
ስለ ቬሎሽ አይነት...
ስላዳራሽ ኪራይ ፣
ሳወራሽ ከርሜ ፣ ስታወሪኝ ኖረሽ
ተንጠልጥሎ መሔድ ፣ ስለምን አማረሽ?
።።።።
ምንም ጋልቦ ባይሔድ ፣ ባልሞላበት ነዳጅ
እኔም መኪና አለኝ ፣ ምሰፋበት ቅዳጅ
ነይ ልብ እሰፋለሁ ፣ የሚሸሽ ከወዳጅ!!"
።።።


@getem
@getem
@getem
።።ጠያቂ ፀረ ሰላም ነው።።

በኔ ሀገር ስኖር
ህዝብ ቸግሮት ሲያድር
እሚቀምሰው አጥቶ
ጥም እራብ በርትቶ
ሰቆቃው በርክቶ መኖር ተሰልችቶ
ሰላም አለ ሲባል ውስጥህ ሰላም አጥቶ
ትርጉሙ ጠፍቶብህ
ሰላም የታል ብለህ
ሲታወክ ሰላምህ
ሰሚ ሰው ፈልገህ
በሰላም ብትጠይቅ ሲፀናብህ ጥምህ
በጠኔ ተንጣነህ
ወሃ ብለህ ብጮህ
በነሱ አሰማም ያኔ ነው ስህተትህ
ያኔ ሰላም የለም
ሀገርም ታምሷል
ጥላቻ ታውጇል
....
.....
ምክንያቱም ወዳጀ ጠምቶህ ዝም አላልክም
ልተንፍስ ብለሀል ከፍቶህ አልታፈንክም
ያንተ የውሀ ጥያቄም ሆኗል ፀረ ሰላም
እናማ አትድከም
የሰላም ትርጉሙም ዝምታ ነውና
ሰላም እነዲሰፍን ዝምታን እናፅና ።
እስጢፋኖስ ተስፋየ
woldia university

@getem
@getem
@gebriel_19
©©ሳይፀልዩ ማደር☜☜

የተራበነብር ከሩቅተመልክታ
ሚዳቋዋፀለየች አውጣኝ አውጣኝ አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ ወደአምላኩቀርቦ
አንጀቱከሆዱ እንደተጣበቀ ሚዳቋዋን አይቶ
ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ

የሁለቱም አምላክ የሁላችን ሰሪ
ፀሎታቸውን ሠማቸው ፈጣሪ

አምላክም በድምፁ ሚዳቆዋንአላት
እሩጠሽ አምልጪ ከበረታጠላት
ነብሩንም አለው እሩጥ ተከተላት ምግብአርገክ ብላት
ሚዳቆዋም ስትሮጥ ከነብሩ ለማምለጥ
ነብሩም ሢከተላት ሆዱን ሊሞላባት

ቋጥኙን ስትዘል እግሯተሥፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛከርከሮ

ከንቅልፉሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየውነብር

አውጣኝያለው ወቶ አበላኝያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው ከርከሮ ተበላ

☞☞☞☞ በረከት በላይነህ☜☜☜☜



@lula_al_greeko
@getem
@getem
ከንፈር ልሶ ማደር
———//————

መለየቱ ሲያምርሽ ፥ ከላዬ'ላይ መብረር
ከኔ ጉያ ርቀሽ ፣ ከዛኛው ለማደር
በለመድኳት ም'ኛት እንዲ ትይኝ ነበር
''በጊዜ ካልገባው፥ይቆጣኛል ፋዘር!!''
ግና ከኔ ርቀሽ
ሳደርሺ ካባትሽ
እንደ መንገድ እሸት፥የወይን ዘለላ
ይቆርጥሽ ነበር...
ከመንገድ ላይ ቆሞ፣የለመድሽው ገላ
እኔም በባዶዬ፥ጾሜን ላለማደር
አንቺን ተከትዬ፥ከደስታቹ መንደር
የሐሴት ግርፋት፥ሲወርድብሽ በትር
ሲቃሽን ላደምጥው፥እቆማለው ከበር
ልማዴ ነውና…
ጩህትሽን ሰምቶ፥ከንፈር ልሶ ማደር

ሚኪ endale
@MMIKU

@getem
@getem
(#ፋሲል_ስዩም)
©
...
ከላይ...
ከወደ ሰማይ...
ለአፍታ ማይጨፈን የፈጣሪ አይን፣
ከውብ ሽፋሽፍቱ የምትምዘገዘግ የስስት እይታ፣
ለፈጠረው ምድር፣እንደ ልብ ትርታ፣
(የዐይኑ ብልጭታ)
.
(ከታች)
ከእኔ ካንቺ መንደር...
ፈጣሪን የሚያሙ ማይዘጉ አፎች፣
እሳት የፀነሱ...እሳት የሚወልዱ...እልፋን አንደበቶች፣
(ክፍት አፎች፣)
.
(ከመሃሉ)
ቀይ ክር ያለበት የታሰረ ስጋ
ነክሶ የሚበርር
ጥምብ አንሳ አሞራ፣
ከነፋስ ጋር ምትዞር አንዲት የርግብ ላባ፣
ከምድር ተነጥቃ ከነፋስ ያበረች
ፅጌ-ሬዳ አበባ፣
(ትንሽ ከፍ ብሎ)
በደመና ስዕላት፣የተቀላለመ፣
የውብ ቆንጆ ስዕል፣
የሆነ መልክም አልባ፣
የሆነ ደምም አልባ፣
የሆነ ገላም አልባ፣
የደመቀ ምስል፣

(እኔ)
ከመንደሬ ካለች ወንዝ ዳር ቁጭ ብዬ፣
ምናቤን፣
ከበላይ...ከመሃል...ከበታች
ደግሞም ካንቺ ጥዬ፣
በትንሽ ዛፍ ጥላ 'ራሴን ጠልዬ፣
(ግጥም እፅፋለሁ)
)ስንኝ እጥፋለሁ(

ከወንዙ ባሻገር፣
ለጋነት ያነቃት፣አንዲት ልጃገረድ፣
ከጋለ አለት ላይ፣ለመብረድ ተቀምጣ፣
እግሮቿን ተከፍተው፣ቀሚሷ ተገልቦ፣
አዳፋ ብጫቂ፣ውራጅ ጨርቅ ታጥባለች፣
.
ቀና ስል ካየሁት፣ዝቅ ስል አጥቼ፣መሃል ላይ ካዋልኩት፣
የውበት ገፅታ፣
እኔን የማረከኝ፣
ብዕሬን ቀጥ አርጎ፣
ግጣም አሳይቶ፣
መግጠምን ያስረሳኝ፣
ከባሻገሬ ላይ፣
ከክፍት ቀሚስ መሃል፣
ተከፍቶ ያየሁት፣የውድዬ ሲሳይ፣!
(ከላይ)
(ፈጣሪ እንዳያይ)


...///...
ዲላ

@getem
@getem
@gebriel_19
"ትክክል? /ስህተት? "
( በአምባዬ ጌታነህ )

ልክ ነበርሽ አንቺ
ልክ ነበርኩ ያኔ፣
የእኔ በአንቺ መሄድ
መማገጠሽ በእኔ።
የለገመ ወስፌ
ቅቤ የማይወጋው፣
የኔና አንቺን ናፍቆት፣
የበረሀ ጋመን
በጧት ያቃጠለው፣
ከመውደድ ከመጥላት
የተሰላቸነው፣
ከትላንት ወዲያ ነው።
ምፅአት ቢመጣ እንኳ
ከእንግዲህ ህልም እልም፣
በድጋሚ አንድ ላይ
እኔ እና አንቺ አንሆንም።
ከድሮውም ቢሆን፣
የኔና የአንቺ ፍቅር
የማስመሰል ጥበብ
የላይ ብቻ ነበር።
ከእኔ መለየቱ ስኬትሽ ከሆነ፣
እኔም የስንት ጊዜ ህልሜ እውን ሆነ።
07/09/2011 ጠዋት 12:14

@amba88 የቻናሉ ቤተሰብ ለመሆን

@getem
@getem
@getem
#ሠማይ_የላሰ_መሬት
.
ዘማሪው "ወደ ላይ!" ...
ዘፋኙም "ወደ ላይ!" ...
መጽሐፉም "ወደ ላይ!" ...
''ወደ ላይ!'' .... "ወደ ላይ!' ... ሰማነው ይበቃል
እስኪ ጎንበስ እንበል፣
''ወደ ታች!" ..... "ወደ ታች!" ......
ከ'ኔ ቢጤዎች ጋር ፣ እግዜር መሬት ወድቋል!!
-----------------------//-------------------------------
---------------( በርናባስ ከበደ )----------------

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የሱፍ አበባ ነሽ
( ናትናኤል ጌቱ )
አልተመለከትሽም ?
ሳቅሽ ዘቢብ ሁኖ ፣ ምድሩን ሲያጣፍጠው
የፈገግታሽ ዘሀ ፣ ሁሉን ሲቀይጠው
ሰሌን የነበረው ፣ ለሐፍ ሁኖ ሲያበራ
የበዛ ውበትሽ ፣ ላንቺም እስኪያስፈራ
አይኖችሽ ሲፈኩ፣ ኮኮበ ዝሑራ
መስለው እንደሚያድሩ አልተገነዘብሽም ?
የሱፍ አበባ ነሽ ፣ የበረሀ ኮሽም
...
ንቦቹ ያልቡሻል ፣ አኮሌ ገድበው
ፀሀያቱ ሁሉ ፣ ይሞቁሻል ከበው
የሽቱ አበባዎች ፣ ይምጉሻል ቀርበው
እንዚራሽን ይዘሽ ፣ ለአንባው ሳትዘይሚ
የገረጀ መንፈስ ሳታለመልሚ
ከወዘናሽ በታች ፣ ድንጉል ስትስሚ
ጀንበር ሁነሽ ሳለ ፣ ኩራዝ ተከትለሽ
እንደ ስናር በቅሎ ፣ በዳገቱ ሰግረሽ
እድሜሽን አባክነሽ ፣ እንባ ለብሰሽ ቀረሽ ?
የሱፍ አበባ ነሽ !
...
አየሩን በእጆችሽ ፣ ስትችይ ልትቀዝፊ
አየሁሽ ስትለፊ
ከእርከንሽ ዝቅ ያለ ፣ ለማበጀት አጋር
አጵሎን ሁነሽ ሳለ ፣ ከደርባባዎች ጋር
አኮፋዳ ከፍተሽ ትለማመኛለሽ
ከጠዋት እስከማታ ፀሀይ ተከትለሽ
ማለዳ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ምሽቱን
አንገት መቀልበሱን
ተለማምደሽዋል
ሊቅ ሁኖ ተፈጥሮ ፣ ዘሊብ ሁኖ መዋል
ለፀፀት ያልዳረሽ ፣ የሱፍ አበባ ነሽ
ሐር ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ !
...
ባንቺ አልተፈወሰም ?
ዝማ ያስጨነቀው ፣ ፈዋሽ ዳማከሴ ?
ዘማዊ ሆንሽና ፣ ልብስሽ የመነኩሴ !
ቢጫ እየለበሱ ፣ ከአንድ ፀሀይ ጋራ
ዝም ብሎ ዳንኪራ … ?
ከቡኒ ክብሽ ላይ ፣ ነጭ ሁኖ ተሰቅሎ
ኮኮብ መሆን ሲችል ፣ ዘርሽ ሆነ ቆሎ !!
የሱፍ አበባ ነሽ ! አንሰሽ አትተከይ
ስለራቀሽ ብቻ ፣ ጀንበር አትከተይ
አይንሽን ብታይ ፣ የብርሀን ምንጭ አለው
ፀሀዮች ይዙሩ ፣ አንቺን ተከትለው
አልተመለከትሽም ? የሱፍ አበባ ነሽ
ሰርፍ ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ
ባንገትሽ ሳትዞሪ ፣ የነጋው አይመሽም
አበባ ነሽ የሱፍ ፣ ከረባት የለሽም !
ከስቃይ ተዋደሽ ፣ መንፈስሽ ዋለለ
ዘባተሎ ተባልሽ ፣ ቬሎ ሁነሽ ሳለ
ማር እየከነበልሽ ተጣባሽ ጡት አስጥል
ጨለማ አታፈቅሪም ስለማያቃጥል !
የሱፍ አበባ ነሽ …የሱፍ አበባ ነሽ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
(#ፋሲል_ስዩም)
(!የምስራብ ስባሄ!)
.........
አሜን ተባረኪ፣
እድሜሽን 'ባውድ አመት፣
በጠሃይ ምስረቃ፣
ያፍካው ያለምልመው፣
ዱልዱሙ ገፅሽን፣
የዘመን ሽክር ሞረድ፣
ይሞርድ ይሳለው!...
(አሜን ተማረኪ!)
ያ ስሉ ዘመንሽ፣
አንገትሽን ይቅላው፣
አንጀትሽን ያውልቀው፣
ጣየ ምስራቅሽን፣
ምዕራብሽ ይነቀው!
(አሜን ተባረኪ!)
(አሜን ተማረኪ)


...///...
ዲላ

@getem
@getem
መፍትሄ
(በረከት በላይነህ)

በር መስኮት ዘግተህ ፣
ቀዳዳውን ደፍነህ
የለኮስከው ሻማ "በራ"! ፣"ጠፋ"! ካለ፤

ጠርጥር!
ቤት ያፈራወ ንፋስ ከጎጆው እነዳለ።

@getem
@getem
@gebriel_19
TESFA ., [16.05.19 16:17]
[ Photo ]

TESFA ., [16.05.19 16:17]
[ Photo ]
#ሮሐ_ሙዚቃል
32ተኛ ምሽት
ደግነት
:
#ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን

ግጥሞች
ዲስኩር
ከመፅሀፍ ገፅ
ሙዚቃ

እሁድ ግንቦት 11/2011 ዓ/ም በ10 ሰዓት
#በፈለገ_አረጋዊያን_መርጃ_ማዕከል
(አድራሻ;–አለም ሆቴል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ)

#መግቢያ
①የንፅህና መጠበቂያ ቁሶች(ሳሙና፣ዲቶል፣ላርጎ…)
ወይም
② የምግብ ውጤች (ስኳር፣ዘይት፣ፓስታ…)
ወይም
③ ፍርኖ ዱቄት

@tebeb_mereja
@teneb_mereja
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከቃል በላይ

ቢሆንልኝ ኖሮ ፀሐይን አውርጄ በእጄ በያዝኳት

ፈካ ያለ ፊቷን ብርሃንዋን እያየው እስከ ለተሞቴ ከጎኔ ባኖርኳት

ብችልማ ጨለማን ደምስሼ እለውጠው ነበር ምሽትን በንጋት

ተፈቅዶልኝ ቢሆን ሙታንን አንስቼ
አፅምን በስጋ ገንብቼ

ተነስተው ሊኤዱ በሙሉ አካላቸው ነፍስንም ዘርቼ
ያዳም የሄዋንን ጥፋትንም ትቼ

በፍቅር ባኖኩዋት ይችን ምድር በጄ (*2)

ውዴ--ዴ---ዴ---(*2)

ብችልማ ኖሮ ከቃል በላይ ሆኜ ሁልጊዜ በኖርኩኝ

ፍቅርዬ አንቺኑ እያልኩኝ
ደግሜ እንዳላጣሽ ከጎኔ ባኖርኩኝ

ከቃል በላይ በሆንኩኝ።


(ሀብታሙ ወርቁ)

@getem
@getem
@gebreil_19
*ምን አለበት**** (ሳሙኤል አዳነ)
     አሁን ምን አለበት ...
 ሰው እንዳሻው ቢኖር
    በራሱ ዳር ድንበር ፣
በልበ ጥፉዎች
       ልብ ባይሰበር ።

እውነት ምን አለበት ...
    ሜዳውን ፈልጎ ዳገቱን ለወጣ፣
ሌላ መሰናክል
      ሌላ እክል ባልመጣ ።
ምን አለበት
      ሰው ከገንዘብ በላይ
ለፍቅር ቢታደል፣
   በምንዝር አለቃ ፍትህ ባይጓደል ።
ቢቻል ለፈጣሪ ባይሆን ለህሊና፣
     ምናል  ይሄ ትውልድ  ለክፋት ባይቀና።

እውነት ምን አለበት ...
        በውዥንብር አለም
ግራ ባይገባ፣
ቁማር ባይጫወት
       ሰው ከግዜሩ ጀርባ ።

ምን አለበት...
       ላዳም የተሰጠው
የማፍቀር  ልቦና ።
        ዛሬም በዚህ ጊዜ ቀጥሎ ቢፀና።

 እውነት ምናለበት ...
   ሰውን በ ሰውነት
              ሁሉ ባከበረ ፣
    ግን በሚል አንድምታ
               ተቃርኖ ባልኖረ  ።
.....
ይገርመኛል ....
    ሰው በትምህርት አለም
              ጎልቶ እየዘመነ ፣
     በጭላንጭል እውቀት
                በራሱ መስተዋል
                  እየተማመነ ፣
     ከጥቁር ሀሳብ ጋር
                አብሮ እየዳመነ ፣
    ትናንትን ተወና
               የባቶችን ፀጋ
                የበረከቷን ቀን ፣
      በጦር አውድማ ላይ
        ተጨንቆ  እየዋለ
         ያድራል በሰቀቀን ..

እና ምን አለበት
      ሰው መነሻውን ቢያቅ
                  ትናንትን በይረሳ ፣
       በአምላክ ፍጡር ላይ
                   እጁን ባያነሳ ፣
    አውነት ምን አለበት
             በአባቶች ልቦና ፤
             በአባቶች እግር ፤
             መራመድ ቢበጀው ፣
ይሄን ጭንቅ ጊዜ
             በጥበብ ቸሻግሮ
              በፍቅር ቢዋጀው።

ምን አለበት ??????????......
 
07/09/2011
 ከምሽቱ 2:45
አ.አ


@getem
@getem
@gebriel_19