ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ

ወጣት ማሙሽ ቀጀላ ተክሌ
ይድረስ ልጅህ ማሙሽ ቀጀላ ነኝ ማለትም 1982 ዓ.ም ማጂ ከተማ ሻልት የሚባል ቦታ ስታስተምር ነበርበመቀጠል አሮ ተቀይረህ እኔም እዛው ተወልጄ እያለሁ ወደ አዲስ አበባ ከሄድክ በኃላ አልተመለስክም እናቴም ሰንበቴና እኔ ማሙሽ ቀጀላ ፈልገን የአንተን አድራሻ ለማግኘት አልቻልንም
ውድ ጋደኞቼ የአባት ቀጀላ ተክሌን አድራሻ የምታውቁት ካለችሁ ከታች በተገለፀው ስልክ ቁጥር እድትጠቁሙን በትህትና እንጠይቃለን።

Tel:-0910540871

@getem
@gebriel_19
Ethiopia || hayleyesus getahun "መንታ መንደር" 2019 16k
Lomi ሎሚ Tube
hayleyesus getahun "መንታ መንደር" 2019
👤 ግጥም ብቻ
🕣 03:14
💾 397.6 kb

@getem
@getem
@gebriel_19
#መሄዴ ነው

ባር ባር አለ ሆዴ ፥ ልቤ መሬት ለቆ
ሊያከንፈኝ እንዳይሆን ፥ አለግብሩ መጥቆ
አለአስተዳደጉ ፥ አለባህሉ ወድቆ፡፡
ሽው እልም ሽው እልም ፥ ልቤ ወፌ-ይላላ
በመስተፋቅር ቀስት ፥ በሮሮ ምህላ
እንደደመና አክናፍ ፥እንደጮራው ጥላ
ሸው እልም ሽው እልም ፥ ሽው እልም ይላላ፡፡
ነሸጠው ፥ ሸፈጠ ፥ ሄደ ሸመጠጠ
በመስተፋቅር ጦር ፥ በሮሮ አመለጠ ፡፡

ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

@yeaseratfere

@getem
@getem
@getem
ስምሽ ከመዳቡ በጉልህ የተፃፈ
ሀገሬ ገንዘብ ነሽ ለአለም የተረፈ
ዘር ሀረግ ቆጥሬ
ከሰውነት ይልቅ ብሄር ካስመረጠኝ
በአፈርሽ ምላለሁ
ያ ግርማ ሞገስሽ አንበሳው ይንከሰኝ፡፡
- ኢትዮጲያዊነት ይለምልም
- ክብር ለሰው ልጆች
መባ(ጥቁር ሰው)

@getem
@getem
@Bookfor
#የታለ_ሰንደቅሽ?

የብዙ ሺ አመታት... የታሪክ አዝመራ
የጥበብ የፍቅር ...የሰላም ጎተራ
የሃይማኖት ትጋት ፀሎት ከበዛበት
በምግባር ትሩፋት ስብዕና ካ'በበት
ሳባ ወእስራኤል ከሆነ ነገድሽ
የጦቢያ ደምግባት ካለ በፊት ገፅሽ.....

ጥማትሽን ማርኪያ ውሀ 'ምትቀጂው
ፈለገ ጊዮን ከሆነ 'ምትጎነጪው
ገዳማት ሀሰሳ ጣና ኃይቅን ቀዝፈሽ
ማዕበሉን ካልፈሽ በረከትን ሽተሽ
ጥበብን ለማድነቅ በአንድም በሌላ
እግሮችሽ ካቀኑ ወደ ላሊበላ......

ጠዋት በማለዳ እርሱን ለማመስገን
ከገሰገሽ ፈጥነሽ ወደ አክሱም ጽዮን
ወደ ታላቁ ረመዳን
የአበው ደመቻው ዛሬ አንቺን ከሠራ
ኣንግሶ ካኖረሽ በዙፋኑ ስፍራ
የማንነት ኪዳን የጦቢያዊነትሽ
ከዙፋኑ በላይ የታለ ሰንደቅሽ ???
መኳስ

@getem
@getem
@getem
//ቀያይ ሰማያት//

ምዕራባዊ አጽናፍ ቀይ ሰማይ ታየኝ፣
መሬት ከዛቢያዋ ልጠልቅ መሰለኝ።
ሰማይ ቢታጠፍም እስከ ሰባተኛ፣
አይንሽን ሳላየው አልችልም ልተኛ።
መንበሩ ቢሰፋ ቆሞ ከመንግስቱ፣
አያግደኝም ጊዜ ነው ምሽቱ።
ጽድቅና ኩነኔ ቢሆን የሱ ምንጣፍ፣
ለምነው ሚላላ አፈቅርሻለሁ ሲፃፍ።
ከጠፈር ጠረፍ ላይ ከሕዋው መጥቆ፣
የሞትኩልሽ ፈሊጥ ቢለፈፍ ለጥቆ።
በአሸን ክዋክብት ይታጀባል እንጂ፣
ደም አይለቀስም ለጨረቃ ፍጂ።

መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)

@getem
@getem
@getem
ይድረስ......
ንጉሱም እንዳይከሰስ
ከሀሳብ እጅጉን ርቆ
ሰማዩም እንዳይታረስ
ከጠፈር ባንድ ሸምቆ።
* * * * * *
ይህ ምስኪን
ሆድ የባሰው ህዝብ
የሚላስ ሚቀመስ ያጣው
ስምክን በየአድባሩ ጥግ
ሰርክ ከሚያሳቅለው
አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ
ንጉሱን ባትችል እንኳ
ሰማዩን ትንሽ ዝቅ አርገው።

ዳኒ.B

@getem
@getem
@getem
ሦዕል ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 order ማድረግ ይቻላል።

@seiloch
@seiloch
ባዶህን ያዝ

1 2 3 4 5 6 7 8 9
በቁጥር አሀዝ ውስጥ
ለጥቆ ሚመጠው ስንት ነው ብላቹ
10 እንድትሉ ግልፅ ነው መልሳቹ
ግና ከ 0 አልጀመርክም ብሎ ሚጠይቀኝ
እርግጥ ነው ከመካከላቹ 1ም ሰው አላገኝ
ጥሪው እንኳን ቀርቶ ከትርጉም ማትገባ
ቀድማ ብትገኝም ቀድማ ማትጠራ
የመጀመሪያ መጀመሪያ
ባዶ ናት ምንም ናት 0 ናት
ብትደመር ብትቀነስ ዋጋም የላት
በጅ ላይ ላትታይ ከኪስ ላትወጣ
ምእናብ ብቻ ሆና ማትያዝ ማትመጣ
የመጀመሪያ መጀመሪያ
ባዶ ናት ምንም ናት 0 ናት

ጅማሬን ከባዶ
ማድረግን ማን ወዶ??

ሰራተኛው ጌታ ከባዶ ጀመረ
1 2 እያለ አለምን ፈጠረ
መፍጠር ብቻ ሳይሆን ማኖር ነው ትረጉሙ
ከእርሱ የወጣው የዘላለም ቃሉ
ሁሉን ቻዪ ጌታ ከባዶ ጀመረ
1 2 እያለ አለምን ፈጠረ

አናም አንተም ዛሬም

በመስረቅ ማምታታት በውሸት ድንጋይ ላይ ቁጢጥ ከምትል
አቋራጬን ሄደህ ጌታን ከምትጥል
ባዶህን ያዝና ካምላክህ ጋር ጀምር

ግጥም:ምህረት ሻውል(ምሬ)

@getem
@getem
@getem
ልብሽን ዝሪበት

አንገቴን ሰውተሽ
ሰማዕት ሁኚበት፥
ደሜን አንቆርቁረሽ
ቅኔ ዝረፊበት፥
አጥንቴንም ወስደሽ
ማኅሌት ቁሚበት፥
ንጠቂና ነፍሴን
ከመቃብር ወርደሽ
ሙታን አስነሺበት፥
ልቤን ግን ስትወስጂው
ዘር የለውምና
ልብሽን ዝሪበት።

💝💝 ሜሎስ 💝💝

@getem
@getem
@getem
አልሞትም
(በላይ በቀለ ወያ) በበእውቄ ስታይል
.
.
ስሚ
ፎቶ ባሳጥብም ፣ ልብሴን አቆሽሼ
ግዙፍ ነኝ በሚል ፊት ፣ ብታይም አንሼ
ሀገር እንደ ሀገር ፣
አንድ ሆና እንድትቀጥል ፣ አቅለ ቢስ መስዬ
እልፍ አእላፍ ጎልያድን ፣ በአንዲት ጠጠር ጥዬ
ልኩን ሳላሳውቅ ፣አቅሜን ሳላሳየው
ያልታወቀ ኋይል
የሚሉትን አካል ፣ ኋይሉን ሳላጋየው
ገንጣይ አስገንጣዩን ፣ ከህዝቡ ሳልለየው
ፍቅርሽ ቢገድለኝም፣ አልሞትም እንቢየው!
።።።

@getem
@getem
@gebriel_19
ኖር
(በተስፋ ብዙወርቅ)
በፊት በፊት ድሮ ድሮ፣
ድንጋይ ሁሉ ዳቦ ጠጠር ሁሉ ንፍሮ፣
በነበረበቱ
ኖር………… በጃንሆይ
ኖር ………… በእግዜሩ
ነበር ንግግሩ
በፊት በፊት ድሮ ድሮ
ጭልፊት ሳለች ዶሮ
ክንፍ ሳትሰፋ
ኖር ሲባል
ኖር
ኖራ ……… በግዜራ
ኖራ ……….. ሆራ
ሎን ኩመ ሆራ
የሺዎች አባት ሁን
እልፍ መንጋ አፍራ
በሺህ ሰው ተፈራ
ነበር ንግግሩ

ዛሬ ዛሬ
ተተወ ማክበር ሽበት
ኖር ቀረ ሆነ ተረት
ነበር ተብሎ የሚተረት
ያለውም ሆነ ካንገት
ከበደ ብድግ ከተቀመጡበት
ወገብ ስራ በዝቶበት፡፡

@getem
@getem
የሰምና ወርቅ ምድር !
__________________
እናትን እ_ናት ናት ብለን ቃል ካማጥን
ሀገርን ሀ_ገር ናት ብለን ከመሠከርን
ሰሟን(someone) እንፍጨርጨር ወርቋ ስለራቀን።

ብሩኬ(የወይን ፍሬ)

@getem
@getem
እቴን ለኔ ብቻ

እቴ ስትርቂኝ፣

ምሽቱ ጸጥ ይላል፣
ጀምበር ትሸሻለች፣
አጽናኝ ብርሀኗን፣
ትደብቀኛለች

ወፎች መዘመር፣
ማዜም ያቆማሉ፣
አንቺ እስክትመጪ፣
በድን ይሆናሉ

እቴ ስትርቂኝ

አበቦች አይፈኩም፣
ከዋክብት አያምሩም፣
ተራሮች ኮረብቶች፣
ሁሉም ያስጠሉኛል፣
ነፋስ በሌለበት፣
የፈዘዙት ዛፎች፣
አስጠልተውኛል

እኔ ለኔ ብቻ፣
የሆንኩኝ መሰለኝ፣
ይሄ ሰፊ ምድር፣
እጅጉን ጠበበኝ፣
ሽታ አልባው
ውሃ እንኳን
መራር መስሎ ታየኝ

ምድሩ ባዶ ሆነብኝ
ልቤም ተሸበረ፣
ናፍቆት ሽቅብ ስቦት፣
አንቺን ለመፈለግ፣
ሰማይ ሰማይ እያየ፣
ተለጥፎ ቀረ

ምን ሆኗል እያለ፣
ጎረቤት በሙሉ፣
አብሮ ያንሾካሹካል፣
እኔስ ምኑ ጨንቆኝ፣
እንኳን ለሰው ቀርቶ፣
የሚያስብሽ ልቤ፣
እኔን ጥሎ ከንፏል

እቴ ስትርቂኝ

በእረፍት አልባው
ምሽት
አይኔ ይስለመለማል፣
ሰዎች ይሸሹኛል፣
ግልምጫው ትችቱ፣
ሀሳቡ ጭንቀቱ፣
ጸንቶ ልብ ያደማል፣
የሚመረጥ የለም፣
ሁሉም ነገር ያማል

አድማሱ ጠቋቁሮ፣
ጀንበር ተለይታው፣
ወርቃማ ብርሀኗን፣
ከላዩ ላይ ገፋው፣
አእዋፍ በዙሪያው፣
መንዣበብ አቁመው፣
ሌላ አለም መሰለኝ፣
የናፍቆት ማእበል፣
ጸንቶ ሲያናውጠኝ

ዮሐንስ

@getem
@getem
@getem
((በላይ በቀለ ወያ))

አንቺ ሚያበሳጭሽ ፣ የኔ ፎቶ ማብዛት
እኔ ምጨነቀው
ዘር ላመማት ሀገር ፣ መድሐኒት ለመግዛት።
አንቺን ሚያስጨንቅሽ ፣ የወንዶች ጋጋታ
እኔን ሚያስጨንቀኝ ፣ የመንጋ ጫጫታ
።።።
አንቺ የምትዩኝ ፣ ገብተህ ተኛ መሽቷል
እኔ ግን የምልሽ
ሲሮጥ የታጠቀ ፣ ሲሸሽ ትጥቅ ይፈታል
።።።
አንቺ ምታወሪኝ ፣ ዋይፋይ ስለሞላ
እኔ የማወራሽ
ቴሌ ጅብ አስሬ ፣ ካርድ እየተበደርኩ ፣ ካርዴን ከሚበላ
አንቺ ሚያስጨንቅሽ ፣ ዘር ማንዘር ቆጣሪ
እኔ ሚያስጨንቀኝ ፣
"ያልታወቀ ኋይል ፣ ሚሉት አሸባሪ
የኔ ሀሳብ ሀገር ፣ ያንቺ ሀሳብ መንደር
እኔ ያልኩሽ ሰላም ዋይ ፣ አንች ያልሽኝ ደናደር
።።።
አንቺ ሚያምርሽ ዘፈን ፣ የሚያምረኝ ፉከራ
የኔ ርሃብ ፍቅር ፣ ያንቺ አምሮት እንጀራ
ምስለው ነጭ እርግብ ፣ ሚታይሽ ገጀራ
።።
ታዲያ እኔናአንቺ ፣በምን እንግባባ
ያንቺ ናፍቆት ዜማ ፣ የኔ ናፍቆት እንባ
ወሬያችን አንድነት ፣ ኑሯችን ለየቅል
አንቺ ሚያምርሽ ልቤ ፣ እኔ ሚያምረኝ ቅቅል (አስተናጋጅ መረቅ
ጭማሪ)
የኔ ተስፋ አንድነት ፣ያንቺ ተስፋ አንድ ቀን
ቋንቋ እንዴት ያግባባን ፣ ፍቅር እያራራቀን?

@getem
@getem
@getem
👍1
በጭድ ላይ ጭነት
"""""""''''፠""""""""፠"""""""

ተከምሮ ቁልል ጭድ ታይቶ ለእሳት
ተቃጥሎ ከቀረ አለፉት አመታት
*
ያ ሁሉ ተንዶ... ጭድ 'ና ጭነቱ
ሞልቶ አያቅ "ክምር" ቢለኝ ባለቤቱ
*
እኔም አልኩ ታዲያ~
ከስር ከስሩ መዘህ ፣ ከላይ ተመንምኖ
ጭድ እ'የት ያቅና መክበድ ተመዝኖ?
.

@getem
@getem
@Johny_Debx
የእንትን ግጥም(ልዑል ሀይሌ)
እንትን እንትን ላሉሽ እንትን አትበያቸው፤
እንትን ስለሆነ ነው እንትን እንትናቸው፤
.
እንትናም ነው መቼም የእንትን እንትኑ፤
እንትን አይሉትም እንትን ስላልሆኑ፤
እንትንሽን እንትን በይ እንትን እንዲያደርጉ፤
እንትን እንትን ይላል የእንትን እንትን ወጉ፤
.
እናም እንትናዬ...
እንትና እና እንትና እንትን ሲጠይቁ፤
እንትን አይምሰልሽ
እንትን ስላሉ ነው እንትን እያወቁ፤
.
እንትኔን 'ታቂያለሽ...
ጊዜውን ማያምን
እንደኔ ያለሰው ብዙ ይጠነቀቃል፤
መልዕክቴ ሲደርስሽ
በእንትን ተርጉሚው
እንትን ያልኩሽን ቃል፤
፬-፰-፳፻፲፩ ዓ.ም.

@gebriel_19
@getem
@getem
#ለሸገር#

ቅጠልሽ በፀሃይ ብዛት 'ማይጠወልግ
ዘር'ሽ የሰማንያ ብሄር ሃረግ፤
ፍቅርሽ፥እያደር አዲስ የሚያባባ
የማዕ'ዛሽም ጽጌ ፥እንደ ጥቅምት አባባ።

በስስት መወርወሪያ፥ ዉዴ ደጅሽ ከተዘጋ
ቶጵያዊነቴም ይታ'በይ ፥እንዳይቆጥሩኝ በለዉ ዜጋ
እነሆ
ሃገሬም ያለመዲና
ምድረ-በዳ ናትና።


መሪጌታ
@getem
@getem