ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ነግቷል አትበሉ
የታል የኛ ጀምበር
ብሩሆች ቢያበሩት
አይጨልምም ነበር!

ሀና ሀይሉ
🌓 @hanahailu


🌜🌛
@getem
@getem
ትላንት ስጠይቅሽ
ልጅ ነህ ብለሺኛል !!
ዛሬ በተራዬ
አርጅተሽብኛል ።

@getem
@getem
@lula_al_greeko
Ethiopia ETHIO UNIQUE SOUND Poetic Jazz|ግጥምን በጃዝ ክፍል 1ገጣሚ ህሊና|……
ETHIO UNIQUE SOUND
ግጥምን በጃዝ ክፍል 1
ገጣሚ :-ህሊና ደሳለኝ
1.2 MB

ግጥም ብቻ

@getem
@getem
ከፃፍሽልኝ መሀል፣ ተዝታ ነው መሰል
የኔ ልብ የሚመኝ፣
ከሚታየው ይልቅ፣ የሰረዝሽው ጣመኝ።

@getem
@getem
@paappii

ኢዛና
እንቆቅልሹ ቅኔ የሆነው ልብህ ፤
ከተፃፈው ይልቅ ስርዝ የሚያስጥምህ ።
ትዝታ ነው መሰል ብለክ የሸወድከው ፤
ስህተትን ማጉላት ማየቱን ወዶ ነው ።

@getem
@getem
@paappii

yami ለኢዛና መልስ
።።በቅርብ ቀን።።

የፌዝ ዶክተር
አዲስ ምርጥ ቲያትር

ደራሲ:- ሞልሼር
ትርጉም:- ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን

በሰው መሆን የፊልምና ቲያትር ብሮዳክሽን የተዘጋጀ

@getem
@getem
አንቺስ አልገባሽም የፍቅር ትርጉሙ
የግልፁን አስትቶ የድብቅ ማስጣሙ
እርሷን የወደድኳት የላይ ውበት ትቼ
ቢሆን ነው ጉዳዬ ከድብቅ አካሏ
ከስርዝ ሽፍኑ ከልቧ ባህር ዉስጥ
ሰምጬ መቅረቴ

@getem
@getem
@paappii

Jada for yami mels
1
ፈራ ተባ የሚል ፣ ልብሽ ልብ ባያገኝ፤
እውነት ከመጋፈጥ ፣ ሠርዞ ቢያመካኝ፤
ስህተት የተባለው ፣ ያንቺን ስርዝ ድልዝ፤
የልብሽን እውነት ፣ የሻተ ዓይኔ ሳይፈዝ፤
ተሻርኮ ከልቤ ፣ የጠፋውን ሊያርም፤
ይተጋል ይፈጋል ፤ እውነታን ሊቃርም!!!

@getem
@getem
@paappii

ፀጋ_ሥላሴ ለyami መልስ
ውዴ አይምሰልሽ
ከጎላው ፅሁፍ ይልቅ መምረጤ ስርዙን
ወድጄ አይደለም ላጎላው ስህተቱን
ግና......
ከፃፍሽልኝ መሀል ስርዙን ስመርጠው
እውነተኛው ስሜት ውስጡ ስላለ ነው።


@getem
@getem
@paappii

Jo ለያሚ መልስ
ሰማኸኝ የኔ ውድ የኔን ስርዝ ወዳጅ
ድብቁን ስትፈልግ ገሃዱ የተፋህ ልጅ
ፍቅሬን ማየት አቅቶህ የተወዛገብከው
የምሠጥህ ፍቅር አልበቃ አለኝ ብለህ
ሚስጥር ስትፈልግ ነው

@getem
@getem
@paappii

Beti ለ jada mels
👍1
አራተኛ ዙር መሠናዶ ሲሆን ወግ ፣መነባነብ፣ግጥም፣ተውኔት እና ሌሎችም በዋሽንት፣ ክራር ፣መሠንቆ እና ኪቦርድ ጋር ተዋዝቶ የፊታችን እሁድ ምሽት12:00 በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ

@getem
@wegoch
@tebeb_mereja
"ጠብቄሽ ነበረ"
ብር ተበድሬ
ሙታንቲ ቀይሬ
ፀጉሬን አጎፍሬ
ፂሜን አበጥሬ
ገላዬን ታጥቤ ፣ ነውሬን ተላጭቼ
ጫማዬን ወልውዬ ፣ ገበሬን አፅድቼ
አዲስ ካልሲ አጥልቄ ፣ ሽቱ ተቀብቼ
ጠብቄሽ ነበረ
በቅዳሜ ዋጋ
ተከራይቼ አልጋ ።
ስትቀሪ ጊዜ
ሰክሬ ልረሳሸ ፣ በብስጭት ወጣሁ
ራሴን እስክስት ፣እስክሰክር ጠጣሁ ፣
ጠጣሁ
ጠጣሁ
ጠጣሁ
አላስታውሰውም
አልጋ ቤቱ ድረስ ፣ ከማን ጋ እንደመጣሁ፡፡
አልኮል አልኮል ምትል ፣ እቺ ደሞ ማናች
አትጠራጠሪ...
ስትቀሪ ጊዜ ፣ ምትመጣ ሴት አለች፡፡

Belay Bekele Weya
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ደግሞ ማለም ምን ያደርግና?
------------------------
ያልተወለደ ሕልም መቼ ይወደድና
በተረገዘ ሕልም ይሄው ታመምኩና
ከምን መጣው ብሎ አባቱን አማና
ዕህ ብሎ ዋለ አላድርም ይቅርና

ብረሳው እሣት ነው ባስበው በቆመጥ
አባት አረፍ ሲሌ እናትን በረመጥ
ያልተወለደ ሕልም መቼ ይወደድና
የተወለደ ሕልም እንዴት ይረሳና

እንኳን አባት ቀርቶ እናትም ሆንኩና
በኔ ስም ይጠራል አባት ተረሳና!


@getem
@getem
@paappii

@Johny_Debx
" የሱ ሚስጢር ማወቅ"
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ያንቺ ሚስጢር እና የሱ ሚስጥር ማወቅ ...
ምናልባት ምናልባት ..
እውነት የሚመስል ግን እውነት ያልሆነ
ፍቅር አንደምሰጪው ልቡ ስላሰበ ..
በምን ይሆን ምኞት ስርዙን ለማወቅ እጅጉን ተመኘ

ያንቺ ሚስጢር ማድረግ
ያንቺ ስርዝ ድልዝ እና ሚስጥር ማድረግ
ምናልባት ምናልባት
ላንቺ ብቻ የታየሸ - ለሱ ግን ያልገባው
ደጋግሞ ደጋግሞ - ልብሽን ያደማው
ይን ነገር ልነግሪው ወረቀት ላይ ፅፈሽ
እሱን ላለማጣት ሊሆንም ይችላል ስርዝ ድልዝ ያረክሽ

@getem
@getem
@paappii

Ermamaw
👍1
#ፀጋ_ሥላሴ :

#ለእናቴ_ልጅ...

አንቺ እምዬ ያልሻት፤
እርሷ የሁሉ እናት፤
በሴት ብትጠራ ፣ አንቀጽ ቢወጣላት፤
ለገባው ላሰበ ፣ ወንድም አባትም ናት።

ጎጆ ቀልሳልን ፣ አውሬ እንዳይበላን ፣ ሆኖ ፍላጎቷ፤
አንድም ሳይጎልብን ፣ ሳይነጣ ማጀቷ፤
በከፋ አመላችን ፣ አንድም ሳትከፋ፤
እሱን እኔና አንቺን ፣ ችላ አሳልፋ፤
...........
ቀለብ የምንሰፍረው ፣ ፍቅራችን ተሟጦ፤
እርስ በእርስ መባላት ፣ ሲሆን ተለውጦ፤
አብሮነት ተስኖን ፣ ሁሉ አዋቂ ሆኖ፤
ሺህ ሀሳብ ሺህ ምኞት ፣ አንድነት ተቃርኖ፤
ሁሉ በአንድ ጎጆ ፣ ማደሩ ሲሳነው፤
ጦሱ ለእናት ሆኖ ፣ መፍትሄ ሲጠፋው፤
በእኛ ድካም እናት....
ዛሬ አቅም ስታጣ ፣ ጉልበቷ ሲከዳት፤
ሀገር ወንድ ትሁን ፣ ቀርቶ መባሏ ሴት፤
ስል ተመኘሁላት።
ብልሃት ብልጠቷ ፣ ካልዘየደ መላ፤
ወንድ ትሁንና ፣ ጉድለቶቿን ትሙላ፤
በጉልበት እንደ እሳት ፣ የጠሏትን ትብላ!!!

#ፀጋ_ሥላሴ
18/07/2011 ዓ.ም
ቀትር 06:04

@getem
@getem
@paappii
የሰውን ልጅ ሰው መሆን
ሁሉም ስለሚያውቀው ፣
እስኪ ስናወራ
'የሠው ልጅ ' አንበል
"ሰው" ማለት በቂ ነው ።


ጊዜ ለመቆጠብ !!

መሠረት መኩሪያው
@messimeku

@getem
@getem
@getem
የጥበብ ምሽት ከአንጋፋ አርቲስቶች ጋር
🔰ዕንቁላል ፋብሪካ
ከእምቢልታ ሆቴል ከፍ ብሎ በሚገኘው ገነት መናፈሻ እንድቅትዮን
(የብርሃን ዕለት) በወሩ የመጨረሻ ማክሰኞ መጋቢት ፳፬-፳፻፲፩
ዓ.ም. የጥበብ ድግሱን አሰናድቶ ይጠብቆታል.

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
@getem
በደጄ ሲያንዣብብ ሞት ሲመታ ድቤ
"ገነት ኢትዮጵያ ናት!" ያሉትን አስቤ፣
ከማነበው መጽሃፍ አረግሁኝ እልባት
እጨርሰው ብዬ ስመለስ ምናልባት።
-------------------//----------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1