ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Fegegita nw yemekedmegni
<unknown>
📙ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ📙

ገጣሚ ፦በእውቀቱ ስዩም
እንባቢ ፦ መአዛ ድሪባ


@getem
@getem
@getem
ለሷ ብቻ
*
እንቅልፌን ውሰደው ~ሞቴን አቅርብልኝ
ሰላሜን ቀንሰህ ~ ሰላሟን ስጥልኝ
*
*
ለኔ ያሰብከዉን ~ለሷ ብቻ አድርገው
እንቅፋቷን ሁሉ ~በገደል አስርገው
*
እያልኩ ዘወትር ~ ከደጅህ መቆሜ
በሷ ታስሬ ነው~ አይደለም ታምሜ
***** ******
(✍️እሱባለው @esubalewbuze )

@getem
@getem
@getem
ስንቱስ ከሀገር ወጣ ስንቱስ ተሰደደ
ስንቱስ እስር ስቃይ ላንቺ ሲል ፈቀደ
ስንቱስ ከዚህች አለም በህይወት አለፈ
ላንቺ ሲል ላንቺ ሲል .............
በደምና በአጥንት ታሪክ እየፃፈ።

@getem
@getem
@paappii

Adem hussen
ኢትዪጲያ 💚💛❤️

እፎይ ብላ እንድታርፍ ፀሎቷ ተሰምቶ
ምላሽ እንድታገኝ እጇ ተዘርግቶ
ጥላቻ እይብቀል ጥላቻ ተዘርቶ!!!!

(ሀና ሀይሉ)

Join here
@hanahailu
@hanahailu
<ጠልቼሽ አላውቅም>
እሱባለው ኢ.

እኔ ላንቺ ማለት
ከሬሳዎች መሀል~ ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ~ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው~ ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ ~መንፈሱ ተሟጦ፣
ተተጠሪ የሌለው ~ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ~ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ~ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ~ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ ~አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው~ ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ~ህይወትሽ ቢርቅም፣
....ጠልቼሽ አላውቅም።
*** ✍️እሱባለው ኢ

.( @esubalewbuze)

@getem
@getem
@getem
antn ymsel
<unknown>
📙አንተን የመሰለ

ገጣሚ ፦መእዛ ድሪባ
እንባቢ ፦ መአዛ ድሪባ


@getem
@getem
@getem
* ባዶነት*
.
.
አምቄ በውሥጤ
ሺ ሀሜት
ሺ ቅናት
ሆኖብኝ መንገዴ
የ ርኩሠት
የ ዝሙት

ሥጨነቅ እየዋልኩ
ለሥጋ ለሆዴ
ሣልፆም አርብ እና እሮብ
ገና እና ሁዳዴ

ቄሥ ባገኘሁ ቁጥር
ይባርኩኝ እላለሁ
ብሩክ ሣይታሠብ
መባረክ የት አየሁ??


©marry

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ሠፊ ንፁህ ሰማይ
ከላይ ተዘርግቶ
ለምለም አደይ መሬት
እፊቴ ተሰጥቶ።
ማስተዋያ ልቤ
ብሌኔ አንቺ ሆነሽ

"ውብ ነው" ያሉት ግዛት.....
"ውብ ነው" ያሉት መሬት......

አሁን እንዴት ይፍካ አንቺ የሌለሽበት.....?....።

ዳግማዊ 2007 ዓ.ም

@getem
@getem
@lula_al_greeko
አውቃለው አትበይኝ
*እሱባለው
*
*
ያወቀ መች በቅሎ~ ፍሬውን የታየን
ካምፓስ ውስጥ ያለነው~እውቀት መች ገበየን
ያልገባውን ተይው
ሆስፒታል የገባው ~ስንት ሰው ተለየን
*
አውቃለው አትበይኝ
ያወቀ መች ያውቃል~ አውቆስ ምን አመጣ
ምሁራንን ይዘን ~በረሃብ ስንቀጣ
ለምለም መሬት ይዘን ~ልመና ስንወጣ።
*
አውቃለው አትበይኝ
ማወቅሽ~ ምን በጀኝ
አብሬሽ እየኖርኩ ~ፍቅርሽ እየፈጀኝ።
*
*
*
*
እሽ በቃ ታውቂያለሽ
*
(✍️ Esubalew, @esubalewbuze )

@getem
@getem
@getem
*** ከተራራው ግርጌ ***

በረሃብ አለንጋ በጭቆና ጅራፍ የተጎሳቆሉ
የችግራችን ምንጭ ምንድን ነው እንዳይሉ
በቁና መሉ ክክ በድጎማ ስንዴ እየተደለሉ
ከተራራው ግርጌ ተገፍተው ተጣሉ

የአገዛዙን ቀንበር ሰብረው እንዳይወጡ
ባለማወቅ ገመድ ታስረው ተቀመጡ
ወጣቱ እንዳይጠይቅ እንዳይሆን መርማሪ
ቤተመፅሐፍት የለ የህዝብ ላይበራሪ
በየጥጋጥጉ ነፍ ጭፈራ ቤት ነፍ ግሮሰሪ
በየመንገዱ ዳር የዝሙት ማህበር
ታች አንበሳ-መደብ ከላይ ሸራ ሰፈር
ደፍሬ እንዳልልሽ ሰዶም ወገሞራ
ከደጅ ይዘረፋል የወንጌሉ አዝመራ

ፍቅርሽ ተደግሶ ፍቅር ይዘከራል
እምወድህ ስትይ ልቤ ይሸብራል
ወይ ንስሐ አትገቢ ልክ እንደ ነነዌ
ሁልጊዜ ቃጠሎ ጥዋት ማታ ደዌ
አልቮ ልምላሜ ጉም ጥርት ያለ ሰማይ
እንደ እሣት ምትፋጅ አሳቃቂ ፀሐይ
ኤድስ አቫላዘር ወስፋት ወቁርባ
ሲፈራረቁብሽ ልብሽ የማይባባ
በፈርጣማ ክንዱ ችግር ያደባዬሽ
ለብዙ ዘመናት መቅሰፍት ያልተለዬሽ
በማን እና በምን እመስልሻለሁ
አስተዋይ ልቡናን እመኝልሻለሁ
እሳት ነበልባሉን ፍሙን የሚገታ
ዳግማዊ ዮናስ ይላክልሽ ጌታ

© ዶ/ር ጌታነህ ካሴ 12/07/2011 ዓ.ም

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
ፈራጅ ሚዛን ጥሎ?
በጦዘ ዘመን ላይ - አብረው የሚጦዙ፥
የዘመን ዐለቆች - መንበርን ሲይዙ፥
“እኔ ብቻ ልታይ”፥
የሚልን ተከታይ፥
ደርሶ የሚያሰክን - ይጠፋል ካ’ገሩ፥
የሚሰማም አይኖር - እንዳይነጋገሩ።
“እስቲ ያውሩም” ቢባል - በየትኛው ዳኛ፥
ኹሉም ለ’ህል ፈራጅ - እስከዳር ቀማኛ።
ጥያቄውም ከንቱ - ባለመልሱም ከንቱ፥
ያ’ገር እንቆቅልሽ - በዘር የሚፈቱ።
ይነሳል ጥያቄ - መልስ ያልኾነ ምሱ፥
ለሕዝብ ያጮኹታል - የሚያተራምሱ፤
ይቀበላል መንጋ - መጯጯህ የራበው፥
ጠያቂም፥ መላሽም - ይጠቅሳሉ “ካ’በው”።
“ጭቁኖች ነን” ባዮች - ዘውትር የሚከሱን፥
ልዩነቱን እንጂ - አይፈልጉም መልሱን፤
ጥያቄን አይሰማም - ጆሮውን የያዘ - “መላሽ ነኝ” ባይ ደሞ፥
ይባስ የገዘፈ - ጥያቄን ይሸጣል - ትንሿ ላይ ቆሞ።
ተረግሟል ሀገሩ፥
ተጠልቷል መንደሩ፥
የጥያቄ አምላክ - ይቅር አትቆጣ፥
መልስ፥ መልሱ ይቆይ - ጥያቄውን አምጣ፤
መልስ ፈላጊዎች - ከጥያቄ መንደር - ጠፉ እየሸሹ፥
በጩኸት የሚያምኑ - ጥያቄዎች ሲያጡ - መልሶችን የሚሹ!

@getem
@getem
@paappii

ንጉሱ አበረ አያሌው
Ethiopia: “መምህር ሆይ ስማን“ በገጣሚ ኤፍሬም 16k
Andafta
“መምህር ሆይ ስማን“

በገጣሚ ኤፍሬም

@getem
@getem
@gebriel_19
" ዛሬም ወድሻለው "

ዘምናትን ኖሬ እንደ ሌለው ሆኜ
ብቻዬን ሥወድሽ በፍቅርሽ ባክኜ
መክሳቴን አይቼ ልተውሽ ወስኜ
መክሳቴ ጀብድ ይሁን ለፍቅር ታምኜ

በነጋ በጠባ በሀሳቤ አንቺ ነሽ
ለኑሮዬ ድርሰት ታሪኬ የምልሽ
ከልቤ ላይ ፅፌሽ ሳነብሽ ሳነብሽ
እንደ ልዩ ድርሰት ስገረም በስምሽ

የደመቀው ምስልሽ ከቀለም የፈካው
ቀለም በምን አቅሙ ካንቺ የሚልካካው
ከውብ ገፅታሽ ላይ ፍቅር
ተጨምሮ
ቢያደማኝ ቢያቆስለኝ ገላዬን አጥቁሮ

ጉልበት እስኪከዳኝ ቢርቀኝ ውበቴ
ዛሬም ወድሻለው ዛሬም ነሽ ህይወቴ
ባጥንቴ እስክቀር እስከለተ ሞቴ


ገጣሚ ኢብራሂም ለጃ

@ebro43

@getem
@getem
👍1🎉1
*ዋይታ*
ስንታየሁ ሙሉጌታ

በወየው ወየው ሀገር
በወይኔ ወይኔ ቀዬ
እሪታ የቀፈፈው ኑሮዬ
በጎ ነገር ይሰማ እንደሁ
ይናፍቃል ጆሮዬ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
ፍርድና እውነታ
########

ልብ ልብ ሳይል
በትዝታ ማዕበል
በሃሳብ ሲጉላላ...በፍቅር ሲዋልል
*
እግር የልብ ሎሌ
ሲሆንለት ታዛዥ
ባለመመበት ሳይሆን
እንዳመራው ተጓዥ
ሂድ እንዳለው ሄዶ
ባላሰበው ደራሽ
*
ዓይንም የልብ አሽከር
ልብ የጆሮ ጌታ
ዓይተው የማያዩ
ሰምተው የማይሰሙ የዓለምን ሁኔታ
ሰው ፊት ላይ የኖሩ እንዲያው ለእይታ
*
እሳትን ከበሪድ
የማይለይ ሆኖ እጅም የማይዳስስ
ጣፋጭ ከመራራ አላጣጥም ብሎ
ምላስም የማይቀምስ
አፍንጫም በቁሙ ምንም የማይሸተው
ሽታ አለይ ቢለው ቢምገው ቢምገው

*
...እንዲ እንዲህ ሆኖ
...በትዝታ ማዕበል
እያስፍወነጨፈ..ልብ እግር ካበጀ
ቀልቤ በሌለበት....
በድኔ በቆመው...
"ለየለት!!!" እያለ...ሰው እኔን ፈረጀ?
አብርሃም

@getem
@geteM
@gebriel_19
👍1😢1
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቀንዲል Digital Magazine(1).pdf
4.9 MB
#ቀንዲል ዲጂታል መፅሔት

ቅፅ 1- ቁጥር2

💰ፓኬጅ ከገዙ 0.60 ሳንቲም ብቻ💰

@kendilM
@kendilM
👍1
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ድርሰቴ
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ

እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ

እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ፡ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም

እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ

ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የመድረስ አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ

Dani yop

@getem
@getem
@gebriel_19
ህይወት ከጠራችኝ ከካቧ ወድቄ
እድል ሲጎትተኝ በሀሳብ ታንቄ
ባለፍንበት መሄድ መመለስ ባይኖርም
ትዝታ ሸጋ ነው ያሻግራል የትም
...የትም ...የትም...
በቃላት ልውውጥ የትም ስልህ ውዴ ..
የትም ካለህበት ይታያል መውደዴ
ከንፋስ በላቀው በከፍታው ሰማይ በጉርዱ ጎዳና
ባዝተው የቆለሉት ጥጥ መሰል ደመና
መሀሉ ሰንጥቄ ስመጣ ባየሁት
በፀጥታው ወደብ ከምድር እርቀት
ጭንቀትና ስጋት የህይወት እድምታ
ነብሴ ከስጋዬ ላትወድቅ ተጠግታ
ደስታዬ ከጭንቀት ተቀላቅለውበት
ህልም እየመሰለኝ የሰማዩ ሂደት
አገሬ ገብቼ ኪንዳን የማስርበት
ያለከልካይ ጉዞ ህግ እማይረቅበት
ያሁን ነፃነቴን እዛ ነው የጀመርኩት
ሸክላ መሰል ወለል የምድሩ ንጣፉ
ከሰማዩ በታች ከደመና በላይ
አልሜ ወስጄህ እዛው ከፍታ ለይ
ደብቄ ባኖርኩህ እያልኩ እመኛለሁ
የምድር ጭንቀቴን እዛ ስለረሳሁ
ባየ በቀመሰ ምስክርህ ሆኜ
በፍቅር ጥላ ስር ላንተ ስል ታምኜ
ባንተ ውስጥ ወልደኸኝ በውስጥህ ሳክትም
የነብሴ መኖሪያው እስትንፋሴም ቢቆም
ባንተ ውስጥ እስካለሁ
ይመቸኛል የትም..የትም
በኔ እና አንተ አለም የማይሆነው የለም
የውልህ የኔ ውብ..!
ከሰማይ ከፍታ ምድሪቱን ስረግጣት
ሲጠቁም ያየሁት አንዱን ያ ሌባ ጣት
እጣውን ሊሸልም እሷን ሲጠቁማት
እሱን አስታውሼ ቀን እዘክራለሁ
ያገሬን ነፃነት ፍቅርህ ውስጥ እያየሁ...!!!!

@getem
@getem
@paappii

ሮዚ የያቡ
ግጥምና ፍቅር
(ደሱ ፍቅርኤል)
የኔ ፍቅር............
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና
የኔ ፍቅር.........
እንደ ኢህአፓ ጓድ አሁንም አሁንም ሰዓቴን አያለሁ
ስንኝ ሲነጥፍብኝ
ጭረት የበዛበት ቆሌ የመሰለ ስዕል እስላለሁ
(የሚገርምሽ ነገር)
ስላንቺ ማሰቤን ለጊዜው አቁሜ
እንደ ባህር ከዘራ ሃሳቤን ቆልምሜ
ስለከዱኝ ሴቶች ብዕሬን ባነሣ
የቅኔ ስካሬ ዓይኑን እያሻሼ ከ'ንቅልፉ ተነሣ
ላንቺ ለምወድሽ ፈልጌ አስፈልጌ ከቆጡ ከባጡ
(ያጣኋቸው ቃላት)
ለነገር ሲሏቸው እየተራኮቱ በምናቤ መጡ
ያፈቀረን ትቶ ለካደ ማሽቃበጥ ስሙ ምን ይባላል?
(ሳምንሽ ጉድ ሰራሽኝ
ስወድሽ ጎዳሽኝ)
ምናምን እያሉ እንደ ሴት ገጣሚ ማላዘን ያስጠላል
(ኤጭ)
የኔ ፍቅር..........
ፍቅርሽ ተዓምር ነው እንደ ባታ ጸበል ድውይ ይፈውሳል
የከንፈርሽ ቃና እንኳንስ ከዱካክ ከሙታን ያስነሳል
ታስታውሽ እንደሆን የሆነ ጊዜ ላይ
ማታውን ስመሽኝ ጧቱን ጀግና ሆንኩኝ
ኢንፎርቲዬን ትቼ
ዝናሬን ፈትቼ
ከንፈርሽን ታጥቄ ጦር ሜዳ ዘመትኩኝ
ታስታውሽ እንደሆን
ጥይት እንዳይመታኝ በፍቅርሽ ተከለልኩ
በጡቶችሽ መሃል ተደብቄ ተረፍኩ
አንችኮ መውደዴ አንቺኮ ናፍቆቴ
የጥይት ማምከኛ ያ'ስማት ክታቤ ነሽ ኩንፈል መድኃኒቴ
ግና ይኸው አሁን
ግጥም ልፅፍልሽ አሰብኩ አሰብኩና አሰብኩ አሰብኩና
ቃላት አጠሩብኝ እንደአፍሪካ ፀጉር እንደ ቦትስዋና

@getem
@getem
@paappii