ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ፀጋ_ሥላሴ :

#ለእናቴ_ልጅ...

አንቺ እምዬ ያልሻት፤
እርሷ የሁሉ እናት፤
በሴት ብትጠራ ፣ አንቀጽ ቢወጣላት፤
ለገባው ላሰበ ፣ ወንድም አባትም ናት።

ጎጆ ቀልሳልን ፣ አውሬ እንዳይበላን ፣ ሆኖ ፍላጎቷ፤
አንድም ሳይጎልብን ፣ ሳይነጣ ማጀቷ፤
በከፋ አመላችን ፣ አንድም ሳትከፋ፤
እሱን እኔና አንቺን ፣ ችላ አሳልፋ፤
...........
ቀለብ የምንሰፍረው ፣ ፍቅራችን ተሟጦ፤
እርስ በእርስ መባላት ፣ ሲሆን ተለውጦ፤
አብሮነት ተስኖን ፣ ሁሉ አዋቂ ሆኖ፤
ሺህ ሀሳብ ሺህ ምኞት ፣ አንድነት ተቃርኖ፤
ሁሉ በአንድ ጎጆ ፣ ማደሩ ሲሳነው፤
ጦሱ ለእናት ሆኖ ፣ መፍትሄ ሲጠፋው፤
በእኛ ድካም እናት....
ዛሬ አቅም ስታጣ ፣ ጉልበቷ ሲከዳት፤
ሀገር ወንድ ትሁን ፣ ቀርቶ መባሏ ሴት፤
ስል ተመኘሁላት።
ብልሃት ብልጠቷ ፣ ካልዘየደ መላ፤
ወንድ ትሁንና ፣ ጉድለቶቿን ትሙላ፤
በጉልበት እንደ እሳት ፣ የጠሏትን ትብላ!!!

#ፀጋ_ሥላሴ
18/07/2011 ዓ.ም
ቀትር 06:04

@getem
@getem
@paappii