ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#Rediet_Aseffa

'ዝም'ህ ለቀጠፋት•
አበባዬ ቀብር• አበቦች አርግፌ
የወደቀ በድኗን•
በየበድኖቻቸው• ርብራብ ደግፌ
ባላደመጥካት ልክ• ምናልባት ብትሰማኝ
ቀና ወደ ሰማይ...



በደጅ-አፌ ዘልቀህ•
በሩን ሳታንኳኳ• የነፍሴን ወገግታ
የፅጌሬዳዬን•
የፍካት የውበት• እርምጃ ስትገታ
የንጥቂያን አለንጋ•
የማጣትን ሰንበር•
ምንህ ላይ ገርፌ• ባሳየኹህ ጌታ?!





አበባ እንዳረገፍክ•
አበቦች አርግፌ•
ሰማይ መንበርኽን• በእንባቸው ላናውጠው?
በነፍሳቸው ጩኸት•
በደማቸው 'እሪ'• መቅደሱን ላቅልጠው?


ንገረኝ ምን ጋር ነው• እንባህ የሚፈልቀው
መነጠቅ መቀማት• ማጣት የሚጨንቀው
የቱ ነው ስስ ጎንህ• ድካምህን ልወቀው...
ልወቅና ልውጋህ
ልውጋህ በፀፀት ጦር• ያረግኸውን ላውጋህ





`አድነኝ´ አላለች• ካሠለላት ሕመም...
ቆዳ የለበሰ• አጥንቷን እንዲያጥም
አልጫ ኑሮ ላይ•
የምትነሰንሳት•
ርጋፊ ብትኖራት•የፈገግታ ቅመም•••
ደግሞ እሷንም ማክሰም?



ፈውሰኝ አላለች•
ካደረቃት ደዌ• ካከሳት በሽታ
አላማረረችህ•
አዳኝ ነው ያሏትን• መዳፍህን ሽታ
ተጠየቅ እንግዲህ•
ደዌዋን ልትጋርድ•
በድካም ሸልቅቃ• የከንፈሯን ሽፋል
የምትረጫትን•
ለስላሳ ፈገግታ• መመንተፍ ያተርፋል?



ያረግኸውን ስማ•
ከማህፀን በራፍ•ጣር እያጋፈረ
ከእትብቷ አቀናብሮ•
ለበድኗ መቃብር• ማልዶ እያስቆፈረ
የሳቋ መንፏቀቅ•
በሞት መላክ አክናፍ• በጉቦ ሊቀደም
የደሟ ነቀርሳ•
ውልደትና ሞቷን• ጎዝጉዞ ሲጋደም
በአርምሞ ልታይ•በዝምህ ልትካድም?
ኧረ እንደዝምታህ•
ገሃነም አይፈጅም•ሲኦል አያነድም
አንዲት ጽጌ-ረዳ••
በእሾህ ስትከዳ••
ባትደርስ ባትራዳ••
ከፈሰሰ ደሟ
"ዝምህ" እጁን ታጥቦ
ሊነፃ ሊፀዳ?
በፍፁም•
ይቅር ትበልህ... ፁም•
ስገድ ወይም አልቅስ•
ድፍረቱ አትበለኝ
አድምጠኝ ይልቅስ•
እንዳረጋገፏ
አበባህን ሁሉ
እያጨፈጨፍኩኝ
እልክልሀለው•
ቁጥር ይገድሃል
ይህንን አውቃለሁ•
ከሺህ እንቡጥ ለቅሶ
ከእልፍ ቀንበጥ ሲቃ•
ያንዲት ጽጌ መርገፍ
ማነሱ እስኪያበቃ•
«ሬሳዋን ይንሳኝ!»
አልምርህም በቃ!

@getem
@getem
እህህ...
እህህ
አንቺ አለሽ በጤና
አውቃለሁ... አውቃለሁ
የኔ ነው የጠፋኝ
ኧረ እንደምን አለሁ?
ንገሪኝ ስለኔ
እንዴት ያልፋል ቀኔ?
አውቃለሁ ያንቺንስ
አውቃለሁ ናፍቀሻል
እኔስ ናፍቆት ራቀኝ?
በምን በኩል ናፈቅኹ?
ፀፀቱስ ለቀቀኝ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
የቅድማያትሽ ቤት
አርሲ ያለው dheራ
ዘመም ጎበጥ ያለው
የኋለኛው አጥር
እንዳዲስ ተሰራ።
የተሰራ ለታ
አጥር ሊመርቁ
የመጡት ጎረቤት
ሰክረው ደጅ ወደቁ።
ሰምቻለሁ እሱን
ንገሪኝ ይልቁን
መርጬ እንዳልበላ
ብስልና ጥሬ
የሚከከክለኝ
የሚጠዘጥዘኝ
ተሻለኝ አልሰሬ?
ወለም ብሎኝ ስወድቅ
ተጣሞ አልነበር?
አሁን እንዴት ሆነ?
ይራመዳል እግሬ?
ሳውቅሽ ደህና ነበርኩ
ስትሄጅ ያመኝ ነበር
ተሻለኝ ወይ ዛሬ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
አያትሽ ካዛንችሽ
ካንድ ቱጃር ጋራ
የመሬት ክርክር
የነበረባቸው
በየመንግስት ቢሮ
በጠራራ ፀሐይ
በእግር ሲኳትኑ
ቱጃሩ ሌ'ት መጥቶ
በእጁ ቀደማቸው።
ሰምቻለሁ እሱን
ንገሪኝ ይልቁን
ትምሕርት ብጤ
ጀምሬ አልነበር?
ተመረቅኩ ወይ ተውኩት?
ስራዬስ እንዴት ነው?
ያኔ የተቀጠርኩት?
አዲስ ሰፈሬንስ
ጠላሁት ወደድኩት?
ልክ እንደቀድሞዬ
እስቃለሁ እቱ?
የሳቄ ታቦትስ
ደስታ ነው ጽላቱ?
ወይስ እንደ ሄድሽው
ከንቱ ነው ውእቱ?
ኧረ እንደምን አለሁ?
አባትሽ ለቮልሱ
አዲስ ጎማ ገዝቷል
ወንድምሽም ጠብሶ
ጫት መቃሙን ትቷል
እናትሽ ቀኝ እግሯን
ይጠዘጥዛታል
አጎትሽ ቀን በቀን
የታክሲ ረዳት ላይ
ሹፌር ላይ ይዝታል
ያ ቦቢ ውሻችሁ
አንገቱ ስር ቆስሏል
ምናለ ትያለሽ!
ሰሞኑን ይሞታል።
አየሁ ያንቺንማ
የኔን ልወቅማ
ንገሪኝ እስኪ የኔን
ይዣለሁ ፍቅረኛ?
አጨሁ ወይ እጮኛ?
ወለድኩ ወይ አግብቼ ?
አደጉ ልጆቼ?
ኑሮ
እሚሉት
ቁልቋል፡
ፀድቋል
ወይስ ደርቋል?
እልህ አሜኬላ
ያቆጠቆጠብኝ
ቆንጥር ነኝ ከድሮም
አልቆረጠልኝም?
እሾህ ነኝ ዘንድሮም?
ኧረ እንደምን አለሁ?
ውበት ፈሶብሻል
አምረሽ ሞት መስለሻል
አየሁሽ በቀደም
ጉንጭሽ የእንጆሪ ደም
ያለፍሽባት ምድር
በጣዝማ ተነክራ
የተራመድሽበት
እንደፃ'ይ ሲያበራ
ግርማሽ አኮስሶኝ
የማማትብበት
ቢጠፋብኝ ቀኜ
«በስመ አብ!» በግራ።
እንኳን ሄደች አልኩኝ
በምልክት ልሳን
አፌን ትንፋሽ ርቆት
ኪሩብ እንኳ አይደለሁ
ስጋዬ እንዴት ችሎ
ሊታቀፍ መለኮት?
ካንቺ እሚተሳሰር
ግሱን ግሳንግሱን
ከደጃፍ ከጓሮሽ
ማን ሳር መበጠሱን
ምን ንፋስ መንፈሱን
የማን ቤት መፍረሱን
የማን መታደሱን
ተይው ሰምቻለሁ
ይልቅ እኔ ጠፋኝ
ንገሪኝ በሞቴ
እኔ እንደምን አለሁ?
ህያው ነኝ ሞቻለሁ?

@getem
@getem
@paappii

#rediet aseffa
እቱ
ኧረ ባዛኝቱ፡
ይብቃሽ ካባነቱ
አንቺን የደረበ የማንም ትከሻ፡
በተጋፋኝ ቁጥር
እንኳን መመከቻ፡ አጣለሁ መድረሻ።
አንቺዋ
እንደው በግሸኗ ፡ በማር ወለላዋ
ነፍስያሽ ጳዚዮን፡ ገላሽ የሉል ፅዋ
ምነው ባትግቺኝ፡
የጨመቁብሽን፡ ሬትና ግራዋ?
ናተይ
በማርያም አደይ
እግር ላለው ሁሉ፥ ጫማነትሽን ተይ
ትቁምብህ ተብሎ፡ ገላ- አፈር ቢሰ'ጠኝ
ባንቺ እየመጣ ነው፡
ስንቱ ተረከዛም፡ ጥፍራም የረገጠኝ።
የደረቡሽ ሁሉ፡ የተጫሙሽ ሁሉ
በካባሽ በጫማሽ- ፅዋሽን ታቅፈው
ጣዕሟ ነን እያሉ-"ታደልን" እያሉ
በደጄ ያልፋሉ።
እውነትም ታደሉ!
ላንድ አንቺ ቆፍረው
እኔንም ለመቀብር -ከተደላደሉ
አንቺ ላይ ተኩሰው እኔን ከገደሉ
ትርፍ ነፍስ አገኙ፡ እውነትም ታደሉ።
ምርቃት ፈቃዴ የፍቃድሽ ቅጣይ
ይች ጭማሪ ነፍሴ የነፍስሽ ተከታይ
ስንቱ ሬት አጠጣት
ስንቱስ ደፈጠጣት፡
ፅዋና ካባሽን ፡ውብ ጫማሽን ስታይ።
ከእንግዲህስ ይብቃኝ
አይግፉኝ
አይድፉኝ
የሷ ነው እያሉ- ግራዋ አያል´ፉኝ
አያታልለኝም
ካባሽም ፅዋሽም- ጫማም ካሁን ወዲህ
ራቁትሽን ነይ- እንዳምንሽ ከእንግዲህ።
# እንቅልፍ_አያ_ጥጋብ_አትመጣም ?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa
👍1
<ትናንት>
ውብ ናት...
ውብ ልጃገረድ
ፈላጊዋ
ደጅጠኚዋ
መዓት
የኛ ቢጤ ቢለምናት
የኛ ቢጤ ቢከተላት
ግድ አይሰጣት።
ስናስጠላት!
<ነገ>
መልከጥፉ ግርጣት ፉንጋ
የለም ደጇን የሚጠጋ
ሽቅርቅሩን
ልጅ እግሩን
ታጠምዳለች በምን አቅሟ?
የኛ ቢጤ የሌት ሕልሟ።
ዛሬ ሆና እስክታጠምደን
ስትወደን!
ዛዲያ ጠምሞ እድላችን
የኛ ቢጤ ችግራችን
የሰው ልጆች መሆናችን
የጠላንን መውደዳችን።
-የትናንት ምርኮኛ-

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa
ጥርሷ ሲስቅ ትንሳዔ ነው
ዐይኗ ሲያለቅስ ጎልጎታ
ከእንባዋ ታግዬ ረታሁ
ሳቋን አግዘኝ ጌታ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa
"ሐሙስ እንጋባ"

በዚህ በ'ኛ ዘመን ፥
ሰዉ ለሰው ላያስብ ፥ተጨካክኗልና
የዘመድ አዝማድ ሆድ፥
ል'ናዝል ፈረዱ ፥ፍቅራችን ሳይጠና።
የጠጪው እስክስታ፥
የበዪው ዳንኪራ ፥ ከሰርጋችን ቢቀር፤
አይፀና ይመስል ፥የቤታችን ማገር...
የዉርስ እርግማን ፥
የልማድ ሥርዓት፥ ሰቅዞ ይዞናል
ይኸው ባንደግስ፥
ጎጇ'ችን ባንድ ሌት ፥ይፈርስ መስሎናል።
በጠመቅሽው ጠላ፥ ወጋቸውን ሊያዩ፥
በጣልኩት ፍሪዳ ፥ትውስታ ሊያቆዩ፤
"ዓለምህ ዛሬ ነው" "ወግሽ ነው "እያሉ፥
በተስፋችን ሞረድ፥ጥርሳቸውን ሳሉ።
ወዴት እንሸሻለን?
እንታረድና፥
ቅሪላቸው ይሙላ፥ ጥማቸው ይረስርስ፥
ብቻ የሰርጉ ቀን፥
ይዘዋወርልን ፥ከእሑድ ወደ ሐሙስ።
እሁድ ሰንበት ሲሆን፥ ሐሙስ ስንብት ነው
በጌታ ትንሳኤ፥
በዓለሙ እረፍት፥
ነፍሳችን የሚዝል፥ የምንደክም ምነው?
ምነው የምንደግስ?
ጎራሽ የምንጠራ፥
ጠጪ የምንቀጥር፥ በእለተ ሰንበት
ሀሙስ ይሁን እንጂ፥
እንደፈረደብን፥ እንደፈረደበት።
ሐሙስ ሲመሰጠር፥
"ሕጽበተ ሐሙስ" ነው ፥የመጨረሻ 'ራት
ጌታችን ኢየሱስ ፥
ከሐዋርያት ጋር ፥የተመገበበት
የተበደርነውን ፥
ጠጅ ሲጨልጡ፥ ፍሪምባ ሲያደቁ፥
ከሰርጉ በኋላ፥
እንደማንበላ ፥በዚያዉም እንዲያውቁ
ለደስታቸው ብለው ፥
ባበጁት ሥርዓት ፥ጉሮሮ እንደዘጉ
ዳግም የማንበላው፥
የመጨረሻ ራት ፥
መሆኑ ይግባቸው ፥ሐሙስ ይሁን ሰርጉ።
ባክሽ እንቀይረው፥
ሐሙስ እንጋባ ፥ይቅርብን የእሁዱ፤
ስጋችንን ቆርሰን ፥
ደማችንን ቀድተን፥
እንደጋበዝናቸው ፥ምናልባት ቢረዱ።
.
.
(ይቺ ግጥም እለተ ቀኗ ነው በሚል...
ድጌ 2007.ዓ.ም)

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa
👍2
ምን አገራረፈን?

ዘመን ፈልፍሎብህ፥
ጅራፍ የጨበጠ፥ ክፉ ተጣማሪ
በተቀኘኸው ልክ፥ ገዳይና ማሪ
መቀበል ያስጠቃል፥ አቀብል አዝማሪ።
..........አቀብል...እንካማ...
.....||ዐይን ሰርግ ሊሄድ፡ ሲኳኳል ቆቡ ስር
.....ማን ይየው የታቹን?
.....ደምቶ ማለቁ ነው፡ አፍንጫ በነስር።||
የሚያዘንቡብህን፥
ስንኞች ወጥረህ፥ በማሲንቆህ ቆዳ
የሚቀዱብህን ፥ አዙረህ ብትቀዳ
ጥያቄ እንደፈራ፥ ሰነፍ አስተማሪ
ምላሹ ጅራፍ ነው፥
አትቀበል ተወው፥ አቀብል አዝማሪ።
............አቀብል... እንካማ
.....||እንደአረፋ ሙክት፡ ልክ እንደዒድ በሬ
.....ሰርክ የሚያሳርደኝ፡ አለመሶበሬ||
የመንደሩ ወግ ነው ፥
ግንድ እየደበቁ፥ ንፋስ መማገሩ
አቀባይ እጅ እንጂ፥
ተሸካሚ ጀርባ፥ የለውም ሀገሩ
ብልጥ...ሁን ... እባክህ
ገንዘብ እንደሌለው አራዳ ቆማሪ
ሳትሰጥ ሳትቀበል፥
አየር ባየር ብላ፥ አቀብል አዝማሪ
............አቀብል... እንካማ
....« በሳቅ መፍረስ የሚል ፡ ፈሊጥስ ነበረን
..... ፈርሶ መሳቅ ደሞ፡ ማነው ያስተማረን?»

@getem
@getem
@paappii
#Rediet aseffa
👍1
ዐየኋት!
አማልክት እሳት ጭረው፥ ፈንድሻ እንደቆሉበት
ጥርሷ ከንፈር እየጣሰ፥ ይፈነዳል እንደዘበት
እ.ን.ደ.ዘ.በ.ት.
ያወራታል...ትስቃለች
ተርገፍግፋ
ተንፈራፍራ
በወጉ እቶን ትነፍራለች
ሁለት ዐይኗ እስኪከደን፥ ያለችበት እስኪጠፋት
ፊቷ ሳምባ እስኪመስል፥እንባ ቁልቁል እስኪረግፋት
ባሳሳቋ እንግዴነት፥ ማን መኾኗ እስኪጠፋኝ
"ከኔ ስትስቅ አልነበረም?" እስክል ድረስ እስኪከፋኝ።
ትነፍራለች እ..ን..ደ..ዘ..በ..ት..
ቧጥጦ መውጫው ከቸገረኝ
ከሳቋ አምባ ያለ እጅ'ግር፥ በቀልድ አክናፍ ሲወጣበት
የናፈቅሁት ፈገግታ ላይ፥ ጭንጋፍ ወጋም ሰው ሲያዝበት
እ...ን...ደ...ዘ...በ...ት...
ኾድና ብብቱን
እንደኮረኮሩት፥ ጨቅላ ሳቅ ሲያጠምቃት
እንደዐለት ካይኖቿ
በጨዋታው በትር፥ እንባ ሲያስፈልቃት
ለመታዘብ ማቃት፤
ቢቻል ባንዳች መላ
እውን ላይ ተኝቶ፡ ወደ ቅዠት መንቃት።
የአፍቃሪ የወዳጅ ጸሎት ምርቃቱ
ብትገመስ እንኳ
የልቡ ሴት... ሐሴት
ክብሩ ሞገሱ እንጂ፥ መች ነበር ጥቃቱ?
ማለት ማመዛዘን ... ራስ መግራት ከንቱ!
ተውኝ ላልቅስበት
ጥርሷ ላይ ታውቆኛል፡
ተስፋ እያርከፈከፍኩ
ወራት ያቆየሁት፡ ፍቅራችን መሞቱ።
ወትሮም...
ቢታረድ ቢቀጠፍ ቢጣፍጥ መብሉ
በጥርስ ነውና፥ የሚፈታው ውሉ
በገደል በጋራው፥ ፍቅራችን ቢያልፍ ሁሉን
ሳቅ ነበር መለኪያው፥ መክበዱን መቅለሉን።
እንዳ'ደይ መፍካቷ፥
ልቤንም ቢከፋው፡ ልቤን ደስም ቢለው
ከቶ እንደምን ብዬ፥
በጥርሷ ሚዛን ላይ፥ መቅለሌን ልቻለው?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
👍9
ስንለያይ ፀደቀች፣ ሰማይ ሆነ እልፍኝ ቤቷ
ሲዖል ፍቅር ያሳኋት፣ እኔ ነበርኩ አንድ ሀጢያቷ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
👍9🔥1
ጥለሽኝ ስቴጂ
ጩአት እሪታዬን እንደምን ላምቀው?
አስጩኦ አይደለም ወይ?
ሰይጣን የሚለቀው?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
😁68🔥25👍2017🤩11
በእሺታዋ ንዝረት፣ ከሚረግፍ ክንፌ
በእምቢታዋ ምርረት፣ ከሚለጎም አፌ
ምናልባቷን ሰጥታኝ፣ በተኛው አርፌ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
👍437😁5🔥1
ጥርሷ ሲስቅ ትንሳኤ ነው
አይኗ ሲያለቅስ ጎልጎታ፣
እንባዋን ታግዬ ረታው
ሳቋን አግዘኝ ጌታ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
83👍30😱3👎2
👍27🔥81
ሳቅሽ ብርድ አለበት?
ለምንድነው እንባ
የምትደርቢበት?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
👍9821🔥11😱4
ሰማዩን ወደደች
በመውደዴ ቀናው
ቀንቼ አቀረቀርኩ፣
ዐለሙን ወደደች
በዐለሙ ቀናው፣ ሁሉን ጥዬ መነንኩ።

አልበቃትም መሰል፣
ማነስ መጎንበሴ፣
ዐለም በቃኝ ብዬ፣
ጤዛ ልጥ መልበሴ።

ወደደኩህ አለችኝ
የት ልሽሽ ከራሴ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet assefa
90👍35😁11👎4🔥3
ልብሽ ልቤ ያልሰደደው
የእልሃችን ድምፅ ጎዳን፣
እስኪ ደግሞ እንሞክረው፣
ያለ ጆሮ እንደ ጉንዳን
ቃላት ቁስል አይቀስቅሱ
በዝምታ ጠበል እንዳን።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
26👍11
ሀዘን መለኮት ነው፣ ፈገግታ ደግሞ ሰው፣
ማን ናት ይቺ መሲህ፣ ግንብ ምታፈርሰው?
እንባን የምታስቅ፣ ሳቅ የምታለቅሰው?
ተዋህዶ ፊቷ፣ የክርስቶስ ፈለግ
ፍፁም ንፁህ እንባ፣ ፍፁም ንፁህ ፈገግ


@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
90👍34🔥6😱6😢2
ሰማዩ መጅ
ምድሩ ወፍጮ
አተር ነፍሴ፣ እማህል ላይ ተንገርጭጮ
ቅጤ ቅርሴ ሲፈራርስ፣
"ኅጢያቴ ነው " ?፣ ልበል ላልቅስ?
"እቅዱ ነው"፣ ልበል ወይስ
እርደኝ ብዬ ፀሎት ላድርስ?
በላይ በታች፣ መንትያ ጥርስ
አተር ነፍሴ፣ ሲፈራርስ
"አሜን" ልበል ወይ "አያድርስ"?

@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
👍4121😱9🔥4😢4
አንድ አንድ ሞት አለ አይደል?
ቢሞቱት ቢሞቱት፣ የማይሉት በቃኝ?
ይኸው ትናንትና
በቃኝ ብዬ ሞቼ
ሙት በድን ስጋዬን
በምታርግ ነፍሴ፣ ዞር ብዬ በቃኝ
የገደለኝን ጅብ
ሊቀድስ አይቼው፣ ሳቅ ከሞት አነቃኝ።

@getem
@getem
@paappii

#Rediet Aseffa
👍63😁3021🔥6😱3👎1