ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
።።።ናትናኤል ጌቱ።።።

የተከታዩ ግጥም የአፃፃፍ ስልት ገና በሙከራ ላይ ያለ የግል ፈጠራዬ ነው ።
ማብራሪያውን ከስር አስፍሬያለሁ
.
.
ሁለቱ ፍጡሮች
.
ሚ.ካ.ኤ.ል … ሳ.ጥ.ና.ኤ.ል
በሆነ ማለዳ ÷ ከሠማያት ወርደው
በአውሎ ነፋስ ወጀብ ÷ መንደሩን አርደው
ረጅም ክንፋቸው ÷ ጎጇችንን ታኳት
የቤታችንን በር ÷ ጀመሩ ማንኳኳት

ማንኳኳት ጀመሩ ÷ በወፍራም ላባቸው
ታኳት ጎጇችንን ÷ ረጅም ክንፋቸው
ምስኪን አበባዎች ÷ ምን እንሁን ጨነቀን
እናያቸው ጀመር ÷ ድንገት አጮልቀን

አጮልቀን ድንገት ÷ ስናይ ቆየንና
ጨነቀን ምን እንሁን ÷ መልካም ስብእና
ለእኛ አይነት አበቦች ÷ በአይን አይለይምና
ግባ እንለው ዘንድ ÷ በራችንን ከፍተን
"መልኣክ"ን ከ"ሰይጣን" ÷ መለየት አቃተን

መለየት አቃተን ÷ አንድ ነው ገፃቸው
በራችንን ከፍተን ÷ እንዳናስገባቸው
ተመሳሰለብን ÷ረጅም ክንፋቸው
እንዴት እንለያቸው ÷ ልዩነት ተንትነን
አራት አይን የለንም ÷ምስኪን አበቦች ነን
ምናልባት አማልክት ÷ ታሪክን ሲፅፉ
ቀለም ደባልቀዋል ÷ መልካምን ከክፉ

አበቦች ነን ምስኪን ÷አንድ ቀን ረጋፊ
ተንትነን ልዩነት ÷የማናውቅ ለፊ
ቅጠላችን 'ሚወድቅ ÷ ባንድ ንፋስ ጥፊ
አነጋገራቸው
መጣሪያ ድምፃቸው
መልካምና ክፉ ÷አንድ ናቸው ለእኛ
እጅ ወደ ላይ የሚል
ገዳይ ወታደር ነው ÷አልያም ሙዚቀኛ ።
ስያሜ በማሰስ ÷ ማንነት ለሚሻ
የጫካ አዳኝና ÷ የመንደር ወጌሻ
ግብር ለያይቷቸው ÷ ባይመሳሰሉ
አንድ ነው ስማቸው ÷ "አዳኝ" ይባላሉ

ይንኳኳል ይንኳል
ይንኳኳል …በራፉ !
መለየት አልቻልንም÷ ፥መልካምን ከክፉ
ተጨንቀን ተጠበን ÷ በስተመጨረሻ
ቦግ እንዳለች ኮኮብ ÷ ከጨለማ ጢሻ
እንለያቸው ዘንድ ÷ በራችልን መላ
የያዙትን አየን
ሁለቱም እጅ ላይ ÷ ተገኘ ሻሞላ !

" እኛ ጠውልገናል
የሆነ መልአክ÷ ቢመጣ ሊረዳን
መኮትኮቻ እንጂ
ጎራዴ ይያዛል ÷ አበባ ለማዳን ?
ከሰማይ ነን ያሉ÷ መላእክቶች ሁላ
ምስላቸው ቢታተም ÷ ታጥቀው ነው ሻሞላ !
የውሀ ማጠጫ ÷ካልያዙ በእጃቸው
ለእኛ አበባዎች
ስእለ ገድሎ ነው ÷ ስእለ አድኗቸው ! "
ብለን በመማከር …
መልካም ዛፎች እንጂ ÷ ስላይደለን ሞኞች
በራችንን ዘጋን ÷ ለሁለቱም ፍጡሮች !!
.
( ናትናኤል ጌቱ )
.
.
የአፃፃፍ ስልቱ : በሳድስ ያለቁ ቤት መምቻና መድፊያ ሀረጋትን ሌላ አርኬ ላይ በመድገም ከሳድስ ውጭ ባለ ሀረግ እንዲያልቁ ማድረግ ነው ። የመጨረሻ ስንኞች ሳድስ ቢኖራቸውም ግጥሙ ካለቀ ባሉበት ሊተው ይችላሉ ። ጠንካራ ጎን : በግጥም ውስጥ የሚኖረውን የሳድስ መጠን በማረጋጋት ጥዑም ዜማን ይፈጥራል ። በሳድስ መጨረስ አመል ያለበት ገጣሚ ካለ ስልቱ ብቃቱን እየተፈታተነ ያዳብርለታል ። ደካማ ጎን : በሳድስ የሚያልቁ ቤት መምቻና መድፊያ ሀረጋት ስለሚደገሙ ገጣሚው ደካማ ከሆነና አንድን የሳድስ ሀረግ የሚደጋግም ከሆነ …ስልቱም ከስር ስለሚያስደግመው ግጥሙን አሰልቺ ያደርግበታል ።

@getem
@getem
@gebriel_19
Yaya Human Hair
Yaya Original Human Hair
አዳዲስ ባስመጣናቸው Quality የሆኑ
የItaly and Brazil products and with full Guarantee እንሸጣለን.እንዲሁም እቃችን ሙሉ ለ ሙሉ የማይነቃቀልና ቀለም የሚቀበል መሆኑን በደስታ እናበስራለን.
https://telegram.me/yayahumanhair
አስመስሎ መኖር
(በዮናስ ቦጋለ)

የሰው ሆድ ሰፊ ነው ይሞላል ይጎድላል
አሁን በቃኝ ብሎ ጨምሩልኝ ይላል::

ሰውም ለሆዱ ሲል ለአንዷ እንጀራ
እሷን ላለማጣት ይደክማል በስራ::

አንደኛው ሲነግድ ሌላው ይደልላል
ነጋዴው አትርፎ ካልሆነለት ከስሮ
ደላላው የላቡን ዋጋውን ያገኛል::

ሌላውም በፊናው መረብ ይዘረጋል
ገበሬ ጎተራን ተማሪም እራሱን አስፍቶ ይጠብቃል
ለላቡ የሚመጥን ነዶንም ያጭዳል::
አንዳዱ ይሰርቃል የሰውን ላብ ደፍሮ
ህሊናውን ሽጦ ማንነቱን ቀብሮ::
ሀኪሙም ያክማል ገበሬውም ያርሳል
ሁሉም በያለበት ኑሮንይታገላል፡፡

ደግሞ አንዳድ አለ ምንም የማይሰራ የሚኖር አጋድሎ
ወሬን በጨው አርጎ አጣፍጦ አቃጥሮ

ከአንዲት ክዳን ስር ክፍሎችን ከፍሎ
መውደቂያውን ማያውቅ ሚኖር አስመስሎ::

@getem
@getem
@gebriel_19
ኮለምላማየዋ!!!!!!!
ጥርሷ ጉራማይሌ፤ እጅ እግሯ ሶሪት ፤
ሃገሯ ቆቦ ነው ፤ መቅጃዋ ሆርማት ፤
ርስቷ ዋጃ ነው ፤ እርሻዋ ሮቢት ፤
የራያ ቅምጥል፤ የወሎ እመቤት ፤
መንገሌ በወተት፤ ያገማሸራት ፤
መገን ጃኖ ሸጋ ፤
የስበር እኩያ ፤ የጢነኛ እህት ፤
ባል የላትም ብለህ፤ አትከተላት ፤
ሰማይ የሚሰብር ፤
ባለ አጭር ምንሽር፤ ሸጋ ባል አላት ፤
መገን እሷ!!!!!

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
👍1
ስለረሳሁሽ ፡ ነው !
… …
" ሊረሳኝ ፡ አይችልም ! "
ብለሽ ፡ በአደባባይ ÷ ሰማሁ ፡ ስታውጂ
እረስቼሽ ፡ ነበር
ምናልባት ፡ ደግሜ ÷ አፍቅሬሽ ፡ ነው ፡ እንጂ።
………
እረስቼሻለሁ
ድንገት ፡ ስጋ ፡ ሁነሽ ÷ ነፍስ ፡ እንደምትሰብሪ
እረስቼዋለሁ
አበባ ፡ አይኖች ፡ ላይ ÷ እንባ ፡ እንደምትሠፍሪ
አላስታወስኩትም
ሁሉን ፡ ነገርሺን ÷ መርሳት ፡ ስለሚሻል
እርሳኝ ፡ ማለትሸን
ባስታውሰው ኑሮ ÷ 'ማፈቀርሽ ይመስልሻል ?

ልቤን ፡ ልብ ፡ አይባሰው ÷ ኸረ ተይኝ እቱ
የሚያፈቅሩትን፡ ሰው ÷ ቀላል ፡ ነው መርሳቱ
ከነ ፡ ፍጥርጥርሽ
ከነ ፡ መፈጠርሽ ÷ እርሳኝ ፡ አይደል ፡ ያልሽኝ ?
ረስቼሻለሁ
አላፍቅርሽ ፡ እንጂ ÷ አዲስ ሴት መስለሽኝ ።

( ናትናኤል ጌቱ )


@getem
@getem
@lula_Al_greeko
አየ እንጀራ???!!!!!

በስምንተኛው ሺህ፤
ከራማ ነጠፈ ፤ሰውነት ገረጣ ፤
ገመድ አፍ በሙሉ ፤
ልበ ሞኙ ሁሉ ፤ እንደራሴ ሊሆን አደባባይ ወጣ ።
ተብታባ ምላሱን፤
ዝርክርክ ቃላቱን ፤
በሃቅ ሳይሸምን በጥበብ ሳይገራ ፤
ያመለውን ዱቄት፤
ለውሶ ከልሶ፤ ከሞተ እርሾ ጋራ ፤
የግድ አጎረሰን ፤
ያረረ መንገሌ የሻገተ እንጀራ ።
አየ እንጀራ......???!!!!
(( ጃ ኖ )💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
ወተት የጠማት ባለወተት(ልዑል ሀይሌ)
.
ላም አላት በሰማይ
ወተቷ የሚዘንብ
ግን ዝናቡን ፈርታ ተጠልላ ምታይ
.
በተጠለለች ልክ ወተቱ ጎርፍ ሆኖ
ሀገር ምድሩን ሁሉ ፆም እያስገደፈ
እሷ ሰማይ አስራት
ባልታቆረ ወተት ያመጣችው ጣጣ ለመንደር ተረፈ
.
ይህቺ!
በስስታምነት ላሚቷን አርቃ ሰማይ ላይ ያሰረች
ዝናቡን ፍራቻ ሲሳይዋ የራቃት ወተት ያላቆረች
.
ወይ ዣንጥላ የላት በጥላ ተጋርዳ ፀጋዋን አትቀርበው
ወይ ትታ እንዳትተው ልጅ አለ ጀርባዋ ወተቱ የራበው
.
ይህቺ የጨነቃት
ከዶፉ ከወተት ከልጇም ያልሆነች
"እምቧ በይ!
እምቧ በይ!
እምቧ በይ ላሚቱ!" ብላ ታዜማለች
.
"እምቧ በይ ላሚቱ!
እምቧ!
እምቧ በይ ላሚቱ!
አርቄ አስሬሽ ነው ሳላገኝ የቀረው ከቅቤ ወተቱ"
.
"እምቧ በይ ላሚቱ!
እምቧ!
እምቧ በይልኝ!
ከሰማይ አስሬሽ ረሀብ ገደለኝ!"
ብላ ታዜማለች
ወተቷ ቢጎርፍም ወተት ተጠምታለች

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👉👉👉ፍቅርና ፍርሀት፡፡


ፈሪ ሰው ጠላሁኝ ፍቅሩን የደበቀ፡
ከተፈጥሮ ሽሽት ህሊናን የራቀ፡
አውቆ እንዳላወቀ ተመሳስሎ ኗሪ፡
እነ ሆድ ንጉሱ አባሮ አባራሪ፡
የፈጣሪን ትዕዛዝ በጣኦት ቀያሪ፡፡

ቢኒያም ዘ አንጾኪያ፡፡

@getem
@getem
አትዮጵያ!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
,
,
ይብላኝለት እንጂ...
በዘር ተከፋፍሎ ፣ ለፈረሰው ቤቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ተሸርፎ ተሸርፎ ፣ ላለቀ መሬቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ደረቷን ስትደቃ ፣ ለወረደው ጡቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ባዘን ፀጉሯን ስትነጭ ፣ ለገጠበ አናቷ
ይብላኝለት እንጂ..
ቁንጅናውን ላጣ ፣ ማድያታም ፊቷ...
፡፡፡፡፡፡፡
ከዚ ሁሉ ኋላም
የዘመን ጥላሸት ፣ መልኳን ተለቅልቃ
ቁንጅናዋ ርቋት ፣ ፉንጋነትን ታጥቃ
ልንጠላት አንችልም ፣ ውብ ሀገር ነች በቃ!!!
።።።
ኢትዮጵያዊነት የሰው ዘር መሰረት የዓለም ውሃ ልክ ነው!!!ክብር ፍቅር
እውነት ለኢትዮጵያዊነት!!!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
(ለካ ተንብየን ነበረ)
።።ሰለሞን ሳህለ።።

ያዝ እንግዲህ …
እናት አባቶችህ አያት ቅድመ አያትክን
በዘመን ንቃት ስም አሽቀንጥረው ጥለው
ለጠማጁ ሰጋጅ
ለበይው አጎብዳጅ
ለቀነኛ ፍጡር ጭፍን አጨብጫቢ
አንተም የነርሱ ልጅ
የወሬ ምድጃን እሳት አርገብጋቢ
አላዋቂ ሳሚ ሲያዝዙህ አጨብጫቢ
ያዝ እንግዲህ …
ራዲዎን ክፈት ቲቪውንም አብራው
ቱልቱላውን አድምጥ አቶስቷሹን እየው
‹"ወሬኛው እንቶኔ በወሬ ውድድር
አሸንፎ ስለመጣ
ሊሸለም ነው ዛሬ ማታ…"
ሂድ አጨብጭብለታ….
የአራጆች ጉባኤ ባሰናዳው ግብር
ምስኪን የኔ ቢጤ…ተቀልቶ ሲዘረር
አደባባይ መሃል የሰው አራጅ ካየህ
መዳፍህ እስኪላጥ አጨብጭብ እባክህ
አጨብጭብ… አጨብጭብ…
አጨብጫቢ ሁሉ ያጨብጫቢ መንጋ
አጨብጭብ ለሀጥአን
አጨብጭብ ለሞቱት
አጨብጭብ ላስመሳይ
አጨብጭብ ላድርባይ
በጭብጨባ ብዛት በጭብጨባ መአት
የተዘጋው ልብህ ምናልባት ቢከፈት !!!
አጨብጫቢ ሁላ.......!

ያማል የግጥም መድብል
ገፅ 14

@getem
@getem
@lula_al_greeko
በደሞዝ ሞት እንዳትጨርሰው!!!!!!!


በደሞዝ ሞት እንዳትጨርሰው ፤
ፉከራው ብዙ ፤
ቀረርቶው መቶ ፤ የጨነቀው ሰው ።
እንባጮው ሁላ ፤
እገላለሁ ሲል እየፎከረ ፤
በደሞዎዝ ሞት ፤
ልግደልህ ያለው፤
በየሸለቆው ተቀብሮ ቀረ ።
በደሞዝ ሞት እንዳትጨርሰው ፤
ምን እጠላለሁ ፤
በባዶ ሜዳ ፤
በምላስ ሞይዘር ፤ የሚጎራ ሰው ።
እገላለሁ ሲል ምላስ አሹሎ ፤
ጀግና ቀደመው ፤
ያንን መቀጣ ያንን አብሽሎ ።
ዋትስ up በል ፤ በእንግሊዝኛ ፤
በደሞዝ ሞት ፤
የቡከን ወሬ ፤ አንወድም እኛ ።
ደግሞ እንደገና ፤
በደሞዝ ሞት ፤ ዋትስ up ጓዴ ፤
ያን አሽቃራሪ፤ ያነን መደዴ ፤
ሸኘሁት ዛሬ ፤
ባርባ ዙር ዝናር ፤ በረጅም ጓንዴ ።
ያነ ወበሎ ጅል ፤
ልግደልህ እያለ፤ ሰርክ እየሸለለ ፤
በአጀብ በቀረርቶ፤ በአፉ እየፏለለ ፤
ፎክሮ ሳይጠግብ ፤ እየተማለለ ፣
ያነ የቡከን ልጅ ፤
የወሳንሳ ከፈን ፤ ገላው ላይ ተጣለ ።
ወንድምአለሜ ፤ በደሞዝ ሞት እንዳትጨርሰው ፤
በጉራ ብቻ ለሚደንሰው ፤
በራያ ሽመል ፤
ሃበከው ብለህ ፤ አፈር አልብሰው ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
Forwarded from SPACE COMPUTER
እንድቅትዩን የስነፅሁፍ ምሽት

ምርጥ ምርጥ የጥበብ ሰዎች ስራቸውን ያቀርባሉ
በዋቢ ሸበሌ ሆቴል
መግብያ 50 ብር
ሐሙስ ታህሳስ 18/2011 አ.ም

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
#ውሀዬ
:
:
አሳ ከውሀ ከወጣ
እስትንፋሱን ስለሚያጣ
ልክ እንደ ደሀ
አይጣላም ከ ውሀ።
የፍቅርሽ ደሀው እኔም እንደ አሳ
ህይወቴ ከህይወትሽ ካልተወሳ
ከተለየው ካንቺ ከውሀዬ
ሞት ነው ሚሆነው እጣዬ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
ለአስተያየቶ @henokbirhanu

@getem
@getem
ግጠም ያሉኝ ጊዜ!!!

እስቲ ቅኔ ልዝረፍ፤
ቅኔ ዛር አለብኝ፤ ደርሶ የሚነሳ፤
ና ግጠም የሚለኝ፤
ና ብረር የሚለኝ፤
ብድግ የሚልብኝ፤ ደርሶ እንደግሪሳ።
እኔም አያስችለኝ፤
መቼም አይሆንልኝ፤ የቅኔ ወግ ነገር፤
እየተዘረፉ፤
እየተዛረፉ፤
ደግሞ እየዘረፉ፤ በሚበሉት ሃገር፤
ጭቁን ምን ይዘርፋል፤
ከዘለላ ግጥም፤ ካንዲት ቅኔ በቀር።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ! !!!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
አሳዛኝ ዜና

ጋዜጠኛ፤ ተርጓሚ እና ደራሲ #ግርማ_ለማ ደሳለኝ ህይወታቸው አለፈ፡፡

★የቅርብ ዘመድ፤ ወገን ስለሌላቸው በማዘጋጃ ቤት ሊቀበሩ ነበር ተብሏል፡፡

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ “እንዲህ ቢሆንስ” “ድሮና ዘንድሮ” “ሃሳብ አለኝ” የተባሉ አምዶች አዘጋጅ ነበሩ፤ የዘመን መፅሄት መስራች እና የአምድ አዘጋጅ ነበሩ፤ ከ1983 በኋላ መፅሄቶች በብዛት ለገበያ መውጣት በጀመሩበት ወቅት “አፍሮዳይት” እና “ዛቬራ” በተሰኙ መፅሄቶች ላይ በ ዋና አዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡

በሬዲዮ ፋና በአስተዳዳሪነት ና በ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ተወዳጅ የነበረውን “ታቦት ፍለጋ” በሚል ርዕስ በተከታታይ ይወጡ የነበሩ የግርሃም ኩክ ስራዎችም የእሳቸው ትርጉሞች ነበሩ፡፡

እንዲሁም አሁን ከህትመት በወጣችው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ላይ በ “ማህደር” አምድ ተወዳጅ የነበረውን እና በኋላም በመፅሃፍ ታትሞ ለአንባቢ የቀረበውን “የንጉሱ ገመና” የተሰኘ ፅሁፍ እና ሌሎች ስራዎችንም ያስነበቡት አንጋፋው ጋዜጠኛ ፣ጸሃፊ፣ ደራሲና አማካሪ የነበሩት ግርማ ለማ ደሳለኝ በዛሬው እለትሰ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህዝብ አስተዳደር በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ የተመረቁት ጋሽ ግርማ “ የንጉሱ ገመና” ከተሰኘው መፅሀፍ በተጨማሪ “የካህሊል ጅብራን ምርጥ ስራዎች” የተሰኘ ትርጉም ስራ ለአንባቢ ያቀረቡ እና ለህትመት ያልበቁ አምስት ያህል የትርጉምና የራሳቸው ወጥ ስራዎች ነበሯቸው፡፡ባለሙያው ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ የትርፍ ሰዓትስራዎቻቸው ሲሆኑ በመደበኛነት የሂውማን ሪሶርስ ማኔጅመንት አማካሪ ነበሩ፡፡

በህይወታቸው መጨረሻ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን በጠና ታመው አልጋ ላይ ከዋሉ መቆየታቸውን የገለጹልን ምንጮቻችን በዛሬው እለት በተከራዩበት ቤት ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የቅርብ ዘመድም ሆነ ወገን ስለሌላቸው አስክሬናቸው በመንግስት( ማዘጋጃ ቤት) ሊቀበር እንደነበርም ታውቋል፡፡

ጉዳዩን ከሰሙት መካከል የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ለማ እና ባለሙያውን የሚያውቁ ጥቂት ወዳጆቹ ሁኔታውን ለፕሬስ ድርጅት እና ለ ቀድሞ ባልደረቦቹ በማሳወቅ እና በማስተባበር በመንግስት እንዳይቀበር ያደረጉ ሲሆን በነገው እለትም በ6፡00 አዲሱ ገበያ በሚገኘው እግዚአብሄር አብ ቤተክርስትያን የቀብር ስነ ስርዓቱ የሚፈጸም መሆኑን ገልጸው በሙያው ላይ ያሉ ሁሉ ለአንጋፋው ባለሙያ ሽኝት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ታይምስ
--------------------------------------

ሰው እያለ አጠገባችን ፤
መልካም ስሙን ፣ መጥራት ሲያመን
<< ሰው ካልሞተ ፣ ወይ ካልሄደ
አይነሳም >> እንላለን።


እንዲህ እያልን ፣
አበባውን ቀጥፈን ጥለን
አበባ እናስቀምጣለን።

((( ነብይ መኮንን )))

እስከመቼ ይሆን ..??? ዛሬም የነብይ መኮንን ግጥም እንደ #ትንቢት እኛ ሀገር በደንብ ይሰራል

ግርማ ለማ ግን አበባ ቀርቶበት....በወጉ የሚቀብረው የለም .....? ዘመድ ይቅር..ወገን ምን ማለት ነው.....?

እስከዛሬ የፃፈልን ነገሮች ስናነበብ የነበርነው ለባዳ ህዝብ ነበር?

እዚህ ሀገር ዘፋኝ እና አርቲስት ብቻ ነው አሸሼ ገዳሜ ሚበዛለት...? ደራሲዋቻችን ከሰጡን ነገር አንፃር የሚኖሩት ኑሮ ለነሱ ሚገባ ነው..? አሁን ጭራሽ ሲሞቱ ሚቀብራቸው .....ከዚህ በላይ ልብ የሚሰብር ነገር አለ..?😭😭😭😭😭😭😭😭😭

@balmbaras
@getem
@getem