የአብስራ ሳሙኤል
⁓⁓⁓
ልውደድስ ቢሉ ⁓ እንዴት ተደርጎ ይወደዳል
ደግሞ ልሽሽም ቢሉ ⁓ ከራስ ወዴት ይኬዳል
ብቻ ህያው ነፍሴ ⁓ በሁለት ባላ ተወጥራ
ለፍታ ደክማ ........ጥራ
♡⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯♡
ወዳንቺ ⁓ ትንጠራራለች
በለሆሳስ ⁓ ታወራሻለች
‧₊˚✧
አየሽ አበቦቹን ⁓ በሚወዷቸው ተከበው
ጸድቀው ⁓ ፈክተው ⁓ አብበው
❀ ❀ ❀
የመኖርን ጣዕም ⁓ ሲቀስሙ
በቢራቢሮ ⁓ ሲሳሙ
—⋅☾⋅—
በእኔ ቀጋ ገላ ⁓ ትል ያዣል
እንኳን ለሚወዱት ⁓ ለራስስ ምኑ ያስጎመዣል
⁂
እናም ⁓ ቢሳካልሽ ⁓ ቢሆንልሽ
ጭቃ ⁓ ጠፍጥፈሽ ⁓ በሀብና በአምሳልሽ
◌ ◌ ◌
ብትፈጢርኝ ⁓ መች ይከፋኛል
የአንቺ መሆን ⁓ ያስመኘኛል
⋯♰⋯
ቢሆንም ⁓ ሂጅ ⁓ ግድየለም
አንቺን ⁓ አትነፍግም ⁓ አለም
—⋆—
ህይወት ⁓ ቢረግፍም ⁓ በየመስኩ
ላይችል ⁓ አይሰጥ ⁓ ያለ ልኩ
⸻⸻⸻
እስጥሽ ምንም ⁓ የለኝም
እቸርሽ ⁓ አልሞላልኝም
ከኔ ዘንድ ⁓ አትጠውልጊ
ከፈካው ⁓ አበባ ⁓ ተጠጊ
⁓⁓⁓
@getem
@getem
@getem
⁓⁓⁓
ልውደድስ ቢሉ ⁓ እንዴት ተደርጎ ይወደዳል
ደግሞ ልሽሽም ቢሉ ⁓ ከራስ ወዴት ይኬዳል
ብቻ ህያው ነፍሴ ⁓ በሁለት ባላ ተወጥራ
ለፍታ ደክማ ........ጥራ
♡⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯⋯♡
ወዳንቺ ⁓ ትንጠራራለች
በለሆሳስ ⁓ ታወራሻለች
‧₊˚✧
አየሽ አበቦቹን ⁓ በሚወዷቸው ተከበው
ጸድቀው ⁓ ፈክተው ⁓ አብበው
❀ ❀ ❀
የመኖርን ጣዕም ⁓ ሲቀስሙ
በቢራቢሮ ⁓ ሲሳሙ
—⋅☾⋅—
በእኔ ቀጋ ገላ ⁓ ትል ያዣል
እንኳን ለሚወዱት ⁓ ለራስስ ምኑ ያስጎመዣል
⁂
እናም ⁓ ቢሳካልሽ ⁓ ቢሆንልሽ
ጭቃ ⁓ ጠፍጥፈሽ ⁓ በሀብና በአምሳልሽ
◌ ◌ ◌
ብትፈጢርኝ ⁓ መች ይከፋኛል
የአንቺ መሆን ⁓ ያስመኘኛል
⋯♰⋯
ቢሆንም ⁓ ሂጅ ⁓ ግድየለም
አንቺን ⁓ አትነፍግም ⁓ አለም
—⋆—
ህይወት ⁓ ቢረግፍም ⁓ በየመስኩ
ላይችል ⁓ አይሰጥ ⁓ ያለ ልኩ
⸻⸻⸻
እስጥሽ ምንም ⁓ የለኝም
እቸርሽ ⁓ አልሞላልኝም
ከኔ ዘንድ ⁓ አትጠውልጊ
ከፈካው ⁓ አበባ ⁓ ተጠጊ
⁓⁓⁓
@getem
@getem
@getem
❤41😢13👍3🔥2
✧የአብስራ ሳሙኤል ✧
ውበት ኪነ-ጥበብ ናት
ከታደሏት ያጌጡባታል
ካልታደሏት ይመኟታል‧‧‧
ያደንቋታል
የአፍንጫ አወራረድ ቤት ይመታል
የጉንጮቿ ስርጉድ ቤት ይደፉል
✧・゚゚:* ──── * ✧・゚:*
ውብ እግዜር የጻፋት ግጥም ትመስላለች
ልብ ብሎ ላያት ሁሉ እንደ ግሉ ትፈታለች
አሁን ለምሳሌ እሷን ያዪ ሴቶች
ቻፒስቲካቸውን አንስተው
የ'ሷን አይነት ቀለም ይቀባሉ
✦•≪───── ⋆⋅☽⋅⋆ ─────≫•✦
ውበት ተዋረሰ ማለት ይሄ አደለ ቅሉ
ልቡ የከጀላት ጎልማሳ ደሞ
"ሚስትማ እንደ እሷ አይነት ነበር እንጂ"
ብሎ ሚስቱን ይገፉል
ውበት አይኑን ሲያውረው
ከማማር ዝሙት ያተርፋል
እሷ ብቻ ናት ማማሯን የማታውቀው
✧・゚: ゚:* ──── * ✧・゚:*
እንደ ግጥም ለራስ ተነባ
አትረካም ታዳሚ ትሻለች
አጀብ አጀብ ባይ አሞጋሽ ትፈልጋለች
ከስንኝ አኳላቶቿ
ግጥም እያዋቀረ የሚያወድሳት
ከሆነችበት ወዳ'ልሆነችበት
በምዕናብ የሚያደርሳት
✧・゚・゚:* ──── *✧・゚✧・゚:*
ምነው እንደጨረቃ
ባማርኩ ብሎ እንደትመኝ የሚያረጋት
ከመሆንና አለመሆን
በምኞት ወላፈን የሚያዋጋት
✦•≪───── ⋆⋅☾⋅⋆ ─────≫•✦
ታዲያ ይሄን ያዩ ቺኮች
አሁንም ገጻቸውን እንደ ጨረቃ ይቀባሉ
ስንቱን ተኩኖ ይቻላል
ስንቱን ይሆናሉ
ወደ ተንጠራራንበት ሁሉ
ፈጣሪ �|አይጠፋም
ቆርጦ የሚቀጥል ቀዶ
የሚሰፋ! አያለፋም ?
✧・゚: * ──── * ✧・゚:*
ታዲያ ውበት ማለት ምን ማለት ይሆን
ያላለቀ ግጥም
ያላለቀ ድርሰት
✾ መድረስ የሚችሉት ነው
ወይስ የቆሙበት
✧・゚: * ──── * ✧・゚:*
ሁሉም በሷ ከተለካ
እሷን ለመምሰል
ገጹን ሸራ ቢያደርገው
ምንድነው ክፋቱ
**ልኬቱ ሳይሆን
መለኪያው ነው ጥፋቱ**
✦•≪─── ⋆⋅☆⋅⋆ ───≫•✦
ቤት የማይመታ መልክ አለ ?
ቤት የማይደፋ ቁመና አለ ?
ገጣሚው ተሳሳተ
ላለማለት ለምን
ግጥሙ ይወቀሳል
ለምን ፊደል ይረክሳል
ሁሉም ስንኝ ቤት አይመታም
ልክ እንደዚህ ግጥም
✧・゚・゚:* ──── * ✧・゚:*
አያምርም ለማለት
መስፈርቱ ይህ ከሆነ
ቆርጣች ቀጥሏት
ቀዳችሁ ስፏት
✾ ❀ ስለሆነችው ሳይሆን
እንድትሆን ወደምትፈልጉት
ምዕናባችሁ ምሯት ❀
✦•≪──── ⋆⋅🌙⋅⋆ ────≫•✦
@getem
@getem
@paappii
ውበት ኪነ-ጥበብ ናት
ከታደሏት ያጌጡባታል
ካልታደሏት ይመኟታል‧‧‧
ያደንቋታል
የአፍንጫ አወራረድ ቤት ይመታል
የጉንጮቿ ስርጉድ ቤት ይደፉል
✧・゚゚:* ──── * ✧・゚:*
ውብ እግዜር የጻፋት ግጥም ትመስላለች
ልብ ብሎ ላያት ሁሉ እንደ ግሉ ትፈታለች
አሁን ለምሳሌ እሷን ያዪ ሴቶች
ቻፒስቲካቸውን አንስተው
የ'ሷን አይነት ቀለም ይቀባሉ
✦•≪───── ⋆⋅☽⋅⋆ ─────≫•✦
ውበት ተዋረሰ ማለት ይሄ አደለ ቅሉ
ልቡ የከጀላት ጎልማሳ ደሞ
"ሚስትማ እንደ እሷ አይነት ነበር እንጂ"
ብሎ ሚስቱን ይገፉል
ውበት አይኑን ሲያውረው
ከማማር ዝሙት ያተርፋል
እሷ ብቻ ናት ማማሯን የማታውቀው
✧・゚: ゚:* ──── * ✧・゚:*
እንደ ግጥም ለራስ ተነባ
አትረካም ታዳሚ ትሻለች
አጀብ አጀብ ባይ አሞጋሽ ትፈልጋለች
ከስንኝ አኳላቶቿ
ግጥም እያዋቀረ የሚያወድሳት
ከሆነችበት ወዳ'ልሆነችበት
በምዕናብ የሚያደርሳት
✧・゚・゚:* ──── *✧・゚✧・゚:*
ምነው እንደጨረቃ
ባማርኩ ብሎ እንደትመኝ የሚያረጋት
ከመሆንና አለመሆን
በምኞት ወላፈን የሚያዋጋት
✦•≪───── ⋆⋅☾⋅⋆ ─────≫•✦
ታዲያ ይሄን ያዩ ቺኮች
አሁንም ገጻቸውን እንደ ጨረቃ ይቀባሉ
ስንቱን ተኩኖ ይቻላል
ስንቱን ይሆናሉ
ወደ ተንጠራራንበት ሁሉ
ፈጣሪ �|አይጠፋም
ቆርጦ የሚቀጥል ቀዶ
የሚሰፋ! አያለፋም ?
✧・゚: * ──── * ✧・゚:*
ታዲያ ውበት ማለት ምን ማለት ይሆን
ያላለቀ ግጥም
ያላለቀ ድርሰት
✾ መድረስ የሚችሉት ነው
ወይስ የቆሙበት
✧・゚: * ──── * ✧・゚:*
ሁሉም በሷ ከተለካ
እሷን ለመምሰል
ገጹን ሸራ ቢያደርገው
ምንድነው ክፋቱ
**ልኬቱ ሳይሆን
መለኪያው ነው ጥፋቱ**
✦•≪─── ⋆⋅☆⋅⋆ ───≫•✦
ቤት የማይመታ መልክ አለ ?
ቤት የማይደፋ ቁመና አለ ?
ገጣሚው ተሳሳተ
ላለማለት ለምን
ግጥሙ ይወቀሳል
ለምን ፊደል ይረክሳል
ሁሉም ስንኝ ቤት አይመታም
ልክ እንደዚህ ግጥም
✧・゚・゚:* ──── * ✧・゚:*
አያምርም ለማለት
መስፈርቱ ይህ ከሆነ
ቆርጣች ቀጥሏት
ቀዳችሁ ስፏት
✾ ❀ ስለሆነችው ሳይሆን
እንድትሆን ወደምትፈልጉት
ምዕናባችሁ ምሯት ❀
✦•≪──── ⋆⋅🌙⋅⋆ ────≫•✦
@getem
@getem
@paappii
❤38🤩2🔥1
የሠው ጉርብትና
(የሞገሴ ልጅ)
ለመደጋገፉም-
ለመወራወሩም - ነፃ ፈቃድ ያለው፣
ራሱን አሳምኖ፣
ሲሻ የሚያነሳ - ሲሻ የሚጥለው።
ሠው የሚባል ፍጥረት-
በኅብረት በመኖር - ላንዱ አንዱ ሊደርስ፣
አንድነት መስርቶ፣
ጉርብትና ፈጥሮ - ሊማከር ሊዋቀስ።
ብዙ የኖረበት-
እየተጋገዘ - ዛሬን እየሰራ፣
ሊያቃጥል ይችላል፣
እንዲሞቅ ሲለኮስ - በርቶ እንዲያበራ።
ሲያክም የሚፈውስ-
ሲዋጋ ህመሙ -
ኃይሉ የሚጠና፣
ሲጠብቅ መከታ፣
ሲሻክር ስጋት ነው -የሠው ጉርብትና።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@paappii
(የሞገሴ ልጅ)
ለመደጋገፉም-
ለመወራወሩም - ነፃ ፈቃድ ያለው፣
ራሱን አሳምኖ፣
ሲሻ የሚያነሳ - ሲሻ የሚጥለው።
ሠው የሚባል ፍጥረት-
በኅብረት በመኖር - ላንዱ አንዱ ሊደርስ፣
አንድነት መስርቶ፣
ጉርብትና ፈጥሮ - ሊማከር ሊዋቀስ።
ብዙ የኖረበት-
እየተጋገዘ - ዛሬን እየሰራ፣
ሊያቃጥል ይችላል፣
እንዲሞቅ ሲለኮስ - በርቶ እንዲያበራ።
ሲያክም የሚፈውስ-
ሲዋጋ ህመሙ -
ኃይሉ የሚጠና፣
ሲጠብቅ መከታ፣
ሲሻክር ስጋት ነው -የሠው ጉርብትና።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@paappii
❤18🔥3
ነገር ስሩን ታውቂዋለሽ
አይጠበቅም የአፌ ቃል
አካኋኔ እንኳን ላንቺ
ላገር ምድሩ ያስታውቃል
ምን ስራ አለኝ ካንቺ ውጪ
ሌትም ቀንም ከደጃፍሽ
ሰርክ መዋል አይሰለቸኝ
ከጋላሽ ጋር ካንደበትሽ
ታውቂዋለሽ ስራ ጉዴን
አታጭኝም ከሄድሽበት
እኔን ማልፋት ደስ ይለሻል?
ባታደክሚኝ ምናለበት።
ቃሌን መስማት ከምላሴ
ካሻሽ እንደው የትርጉሙን
ልብሽ ያውቃል ሁሉን ነገር
የኔን ስቃይ ጥግ ህመሙን
ኪዳን ይዘሽ መጠየቁን
ትችያለሽ ካላመንሽው
ዳሩ ፍቅር ዳሩ መውደድ
ከልቤ ነው የታደልሽው
ንግስት አርጎ ሰርክ ያኖረሸ
ይህ ልቤን ነው ያላመንሽው።
እውነት እውነት ስሜት አለው
ያንቺን ፍቅር ያነገበ
ወትሮ ጊዜው መጨናነቅ
ሌላ አካልን አልደረበ
ድምም ይላል ውስጥ መንፈሴ
ቃል ስምሽን እየሰማ
ሻማ ማብራት አስጀምሯል
ባወቀሽ ቀን እየጠራ
ለሊት አይሉት ወይ ቀትር ላይ
አትታጪም ከሃሳቡ
ሁሌም አለሽ በ ህልሙ ውስጥ
ልቤ አፍቅሮ ባክኖ ልቡ።
ተይ አታስደክሚኝ
ካወክሽው እከሚኝ!
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
አይጠበቅም የአፌ ቃል
አካኋኔ እንኳን ላንቺ
ላገር ምድሩ ያስታውቃል
ምን ስራ አለኝ ካንቺ ውጪ
ሌትም ቀንም ከደጃፍሽ
ሰርክ መዋል አይሰለቸኝ
ከጋላሽ ጋር ካንደበትሽ
ታውቂዋለሽ ስራ ጉዴን
አታጭኝም ከሄድሽበት
እኔን ማልፋት ደስ ይለሻል?
ባታደክሚኝ ምናለበት።
ቃሌን መስማት ከምላሴ
ካሻሽ እንደው የትርጉሙን
ልብሽ ያውቃል ሁሉን ነገር
የኔን ስቃይ ጥግ ህመሙን
ኪዳን ይዘሽ መጠየቁን
ትችያለሽ ካላመንሽው
ዳሩ ፍቅር ዳሩ መውደድ
ከልቤ ነው የታደልሽው
ንግስት አርጎ ሰርክ ያኖረሸ
ይህ ልቤን ነው ያላመንሽው።
እውነት እውነት ስሜት አለው
ያንቺን ፍቅር ያነገበ
ወትሮ ጊዜው መጨናነቅ
ሌላ አካልን አልደረበ
ድምም ይላል ውስጥ መንፈሴ
ቃል ስምሽን እየሰማ
ሻማ ማብራት አስጀምሯል
ባወቀሽ ቀን እየጠራ
ለሊት አይሉት ወይ ቀትር ላይ
አትታጪም ከሃሳቡ
ሁሌም አለሽ በ ህልሙ ውስጥ
ልቤ አፍቅሮ ባክኖ ልቡ።
ተይ አታስደክሚኝ
ካወክሽው እከሚኝ!
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤43👍4😢1
የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
By bewuketu seyoum
@getem
@getem
@paappii
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
By bewuketu seyoum
@getem
@getem
@paappii
❤71😁22🔥13👍6😢2
የአብስራ ሳሙኤል
ከቤትሽ በር ላይ
ትንሽ ዘምበል ብሎ ቅጠሉ የረገፈ
አንቺ ስትወጪ የተንዘፈዘፈ
በአራራይ ዜማ
ጎንበስ ቀና ብሎ ውዳሴ የሚያሰማ
ዛፍ ካየሽ.......እኔ ነኝ
ደሞ ጮራ ከቦሽ
የጸሀዪ ንዳድ ገላሽን አልቦሽ
ማረፊያ ፍለጋ የተቀመጥሽበት
ስራ የፈታ ድንጋይ የዱርዬ መንበር
የኔ ገላ ነበር
ወይም ባለፈው 'ለት
በዕለተ ሰንበት ልደታን ስትስሚ
የተሽኮረመምሽው ምርቃት ስትሰሚ
ምንም ሳትሰጪ ሳትመጸውቺ
ህይወት ህይወት ጸዳል ለምትሸቺው ላንቺ
አሜን ሳትይ እንኳ የመረቀሽ ለማኝ
እኔ ነኝ
እናልሽ መቅደሴ
ሴያሻሽ እንደ ታዛ ሲያሻሽ እንደ ወንበር
ደጀ ሰላም ወድቆ ሲመርቅ የነበር
ከጎጆሽ ባይመጥን ከልብሽ ባይሞላ
በሄድሽበት ሁሉ በአምሳል እያጠላ
እንደ ንፍቀ ክበብ ሲዞርሽ የሚገኝ
እኔ ነኝ
@getem
@getem
@paappii
ከቤትሽ በር ላይ
ትንሽ ዘምበል ብሎ ቅጠሉ የረገፈ
አንቺ ስትወጪ የተንዘፈዘፈ
በአራራይ ዜማ
ጎንበስ ቀና ብሎ ውዳሴ የሚያሰማ
ዛፍ ካየሽ.......እኔ ነኝ
ደሞ ጮራ ከቦሽ
የጸሀዪ ንዳድ ገላሽን አልቦሽ
ማረፊያ ፍለጋ የተቀመጥሽበት
ስራ የፈታ ድንጋይ የዱርዬ መንበር
የኔ ገላ ነበር
ወይም ባለፈው 'ለት
በዕለተ ሰንበት ልደታን ስትስሚ
የተሽኮረመምሽው ምርቃት ስትሰሚ
ምንም ሳትሰጪ ሳትመጸውቺ
ህይወት ህይወት ጸዳል ለምትሸቺው ላንቺ
አሜን ሳትይ እንኳ የመረቀሽ ለማኝ
እኔ ነኝ
እናልሽ መቅደሴ
ሴያሻሽ እንደ ታዛ ሲያሻሽ እንደ ወንበር
ደጀ ሰላም ወድቆ ሲመርቅ የነበር
ከጎጆሽ ባይመጥን ከልብሽ ባይሞላ
በሄድሽበት ሁሉ በአምሳል እያጠላ
እንደ ንፍቀ ክበብ ሲዞርሽ የሚገኝ
እኔ ነኝ
@getem
@getem
@paappii
❤46🔥5👍1
" በረከተ-መንግስት"
( ግዮናይ ነኝ)!፧
ምስኪን ያገሬ ሰው...
ቀኑን ሲሮጥ ውሎ ሌሊት ይሸሸጋል፣
ተፈጥሮ ነውና...
በወፎች ዝማሬ አይቀርም ይነጋል።
ይኸው ደሞ ነጋ...
መስከረም ይመስል መድፉ ተተኮሰ፣
ከምንሸሽበቱ...
እየተከተለን ውጊያው ተለኮሰ።
* * * * * * * * *
ይኸውና ሞርተር...
አዲሱን ቆርቆሮ ባንድ'ዜ ቀደደ፣
እናት ታለቅሳለች...
የዘመናት ወዟ ቤቷ እየነደደ።
ሰብአዊነት ጠፋ...
እንደ ውሻ ሆነ የህዝቤ ክቡር ደም፣
ለቀብራችን እንኳን...
በነጋሢ ቄሳር ለቅሶ አልተፈቀደም።
* * * * * * * * *
እርሻ የሄደ ሰው...
ቀንበር ተሸክሞ በወጣበት ሲቀር፣
ምን እናደርጋለን...
ለላይኛው ጌታ ከማዳኘት በቀር።
@getem
@getem
@getem
( ግዮናይ ነኝ)!፧
ምስኪን ያገሬ ሰው...
ቀኑን ሲሮጥ ውሎ ሌሊት ይሸሸጋል፣
ተፈጥሮ ነውና...
በወፎች ዝማሬ አይቀርም ይነጋል።
ይኸው ደሞ ነጋ...
መስከረም ይመስል መድፉ ተተኮሰ፣
ከምንሸሽበቱ...
እየተከተለን ውጊያው ተለኮሰ።
* * * * * * * * *
ይኸውና ሞርተር...
አዲሱን ቆርቆሮ ባንድ'ዜ ቀደደ፣
እናት ታለቅሳለች...
የዘመናት ወዟ ቤቷ እየነደደ።
ሰብአዊነት ጠፋ...
እንደ ውሻ ሆነ የህዝቤ ክቡር ደም፣
ለቀብራችን እንኳን...
በነጋሢ ቄሳር ለቅሶ አልተፈቀደም።
* * * * * * * * *
እርሻ የሄደ ሰው...
ቀንበር ተሸክሞ በወጣበት ሲቀር፣
ምን እናደርጋለን...
ለላይኛው ጌታ ከማዳኘት በቀር።
@getem
@getem
@getem
😢32❤27😱1
ምን አጥፍተን ይሆን
.
.
ዳገቱን ስንወጣ ወድቀን ተነስተናል፤
ከተራራው አናት አብረን ተጉዘናል፤
የጠዋቷን ፀሐይ በደስታ ሞቀናል፤
በዉቧ ጨረቃ በፍቅር ደምቀናል።
ግና ናፍቆቴዋ................
በዛች የቀን ምራጭ ሰይጣን ሹክ ቢልህ፤
ፈጥነህ ተቀበልከዉ እሺታህን ሰጥተህ።
ከእግዜር ተጣልቼ ቀኒቱን ጠላኋት፤
ባትፈጠር ብዬ አምርሬ ረገምኳት።
እናም አካላቴ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
አትፈልጊኝ ስትል ሀዘን ገብቶህ ይሆን?
እኔማ ናፍቆቴ.................
ምክንያቱን ሳላዉቀዉ፤
አንተም ሳትረዳዉ።
እንለያይ ብለህ ከጎኔ ስትርቀኝ፤
በላዬ ተንዶ ምድር ተደፋብኝ፤
የማደርገዉ አጣሁ ቀኑ ጨለመብኝ፤
ብልሀቴ ጠፍቶ ማጣፊያው ራቀኝ።
ትናንት የቀኑብን ዛሬ እያሸሞሩ፤
ተለያዩ ብለዉ እንዲሰማ ሀገሩ፤
በቡና ሸፋፍነዉ ለፍፈዉ ነገሩ።
ሙጫ ነች እያሉ ፍርድ ይበይናሉ፤
ህመሜን ሳያዉቁ እንዲህ ነች ይላሉ።
ካንተ ጋ አብሮ ሄዷል ፈገግታና ስቄ፤
ዘወትር የምኖር ብሶቴን አምቄ።
ምን አጥፍተን ይሆን ?
እንዲህ የተቀጣን ?
እንደዉ በደፈናዉ በቃችሁ የተባልን፤
በናፍቆት ችንካራት የተቸነከርን።
መንገድህን መርጠህ ከእኔ ብትሸሽም፤
ተስቶህ ነው እንጂ በደልከኝ አልልም።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
ዳገቱን ስንወጣ ወድቀን ተነስተናል፤
ከተራራው አናት አብረን ተጉዘናል፤
የጠዋቷን ፀሐይ በደስታ ሞቀናል፤
በዉቧ ጨረቃ በፍቅር ደምቀናል።
ግና ናፍቆቴዋ................
በዛች የቀን ምራጭ ሰይጣን ሹክ ቢልህ፤
ፈጥነህ ተቀበልከዉ እሺታህን ሰጥተህ።
ከእግዜር ተጣልቼ ቀኒቱን ጠላኋት፤
ባትፈጠር ብዬ አምርሬ ረገምኳት።
እናም አካላቴ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
አትፈልጊኝ ስትል ሀዘን ገብቶህ ይሆን?
እኔማ ናፍቆቴ.................
ምክንያቱን ሳላዉቀዉ፤
አንተም ሳትረዳዉ።
እንለያይ ብለህ ከጎኔ ስትርቀኝ፤
በላዬ ተንዶ ምድር ተደፋብኝ፤
የማደርገዉ አጣሁ ቀኑ ጨለመብኝ፤
ብልሀቴ ጠፍቶ ማጣፊያው ራቀኝ።
ትናንት የቀኑብን ዛሬ እያሸሞሩ፤
ተለያዩ ብለዉ እንዲሰማ ሀገሩ፤
በቡና ሸፋፍነዉ ለፍፈዉ ነገሩ።
ሙጫ ነች እያሉ ፍርድ ይበይናሉ፤
ህመሜን ሳያዉቁ እንዲህ ነች ይላሉ።
ካንተ ጋ አብሮ ሄዷል ፈገግታና ስቄ፤
ዘወትር የምኖር ብሶቴን አምቄ።
ምን አጥፍተን ይሆን ?
እንዲህ የተቀጣን ?
እንደዉ በደፈናዉ በቃችሁ የተባልን፤
በናፍቆት ችንካራት የተቸነከርን።
መንገድህን መርጠህ ከእኔ ብትሸሽም፤
ተስቶህ ነው እንጂ በደልከኝ አልልም።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤41🔥4👍2
የአብስራ ሳሙኤል
፩.
ከቀጠራት ካፌ
የአባቧዋን ገላ እየቀነጠሰች
ጥሏት ከሄደበት
በሀሳብ ተከትላው በሀሳብ ተመለሰች
ያልጠጣውን ቡና እንፋሎት ታየለች
ጠረኑን ቀላቅሎ ብን'ብሎ ሲጠፋ
እንደ ጠዋት ጤዛ እንደ ቀቢጸ ተስፋ
የመሄዱን ዳና እያመሳሰለ
ከመኖር ጎደለ
―✦―
፪.
እንባ አቅርሯል አይኑ
ዞር ብሎም ለማየት አልቀናም ልቡናው
ያውቀዋል ህሊናው
ሰው አልመጠናትም
ያቀፈችው ሁሉ ትከሻው አልሞቃትም
አትገባም ለሱ
ሰው አልሆነም እሱ
ቢጽፍላት ቢቀኝላት
እልፍ ግጥም እልፍ ቅኔ
መልኳን ተሳልሞ መመለስ ነው
ቃል አያቅም የ'ሱ ወኔ
―✦―
፫.
እናም እሷም ካለችበት እሱም ከሄደበት
በቀስተ ደመና አድማስ የሚያጣምር
የማይኖሩት ፍቅር
ለምትኖረው ህይወት እስትንፋሱን ቸረ
ሄደ ያለችው ገላ ሲመራት ነበረ
―☾―
@getem
@getem
@getem
፩.
ከቀጠራት ካፌ
የአባቧዋን ገላ እየቀነጠሰች
ጥሏት ከሄደበት
በሀሳብ ተከትላው በሀሳብ ተመለሰች
ያልጠጣውን ቡና እንፋሎት ታየለች
ጠረኑን ቀላቅሎ ብን'ብሎ ሲጠፋ
እንደ ጠዋት ጤዛ እንደ ቀቢጸ ተስፋ
የመሄዱን ዳና እያመሳሰለ
ከመኖር ጎደለ
―✦―
፪.
እንባ አቅርሯል አይኑ
ዞር ብሎም ለማየት አልቀናም ልቡናው
ያውቀዋል ህሊናው
ሰው አልመጠናትም
ያቀፈችው ሁሉ ትከሻው አልሞቃትም
አትገባም ለሱ
ሰው አልሆነም እሱ
ቢጽፍላት ቢቀኝላት
እልፍ ግጥም እልፍ ቅኔ
መልኳን ተሳልሞ መመለስ ነው
ቃል አያቅም የ'ሱ ወኔ
―✦―
፫.
እናም እሷም ካለችበት እሱም ከሄደበት
በቀስተ ደመና አድማስ የሚያጣምር
የማይኖሩት ፍቅር
ለምትኖረው ህይወት እስትንፋሱን ቸረ
ሄደ ያለችው ገላ ሲመራት ነበረ
―☾―
@getem
@getem
@getem
❤37👍5🔥1
⁂
የአብስራ ሳሙኤል
⁂
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ
ማለፊያ ምግባር ምን ሰራህ
በኖርክባት ስንዝር እድሜ
ምን'ን ዘርተህ ምን አፈራህ
እንዴያው ሲያስበው ይጨንቀኛል
ነፍሴን እንዳል'ጥላት እፈራለሁ
ፈራሽ ገላ ተጫምቼ
ስንት ዘመን እኖራለሁ
የእንባ ብዕር ከሚጠቀስበት
መዝገብ እንዳላሰፍር
መሾ ከሚወርድበት
ክብሬን እንዳላሳፍር
ለመንግስትህ እጨኝ ባልልም
ከመከራው ጠብቀኝ
የኔ እውቀት አያድነኝም
መልካሙን አንተ አሳውቀኝ
ለማትሞላ ጎደሎ ምድር
ህልም ነው ወዳልከው ስትለፋ
ተስፋ ነው ወዳልከው ስትገፋ
ማረፍ አይቀርምና ታርፋለህ
መሞት አይቀርምና ትሞታለህ
ማለፊያ ምግባር የሚሆን
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ
የበገና ክር መወጠር
ለዜማው መጣም ነው'ና
ምስገና መባ እንዲሆን
የህይወትህ ጥኡም ቃና
ለመንግስትህ እጨን ባንልም
ከመከራው አንተ ጠብቀን
የ'ኛ እውቀት አያድነንም
መልካሙን አንተ አሳውቀን
⁂
ለነፍስህ ቅሪት ምን አለህ ?
@getem
@getem
@getem
❤50🔥3🤩1
.
ከገነት ላለኸዉ
.
የ'ግር እሳት ሆኖ ቢገርፈኝ መለየት ፍም እሳቱ፤
ልቤን አቀጣጠላት የናፍቆትህ ስር ግለቱ፤
በዛች የቀን ጎዶሎ ጥቁር ሞት አንተን ሲጠራ፤
እኔንም ጠርቶኝ በነበር ብጓዝ ከፍቅሬ ጋራ፤
ካንተ መራቅ አይሆንልኝ፤
ሌጣ ሆኜ አያምርብኝ፤
ዘወትር..መቃብርህን አቅፌ ስስም 'ዉላለሁ፤
ነጋ ጠባ..ስምህን ስደጋግም አድራለሁ፤
ያዩኝ በሙሉ.........
አበደች እያሉ ሲያሸሙሩብኝ፤
ከመቃብር አድራ ተለከፈች ሲሉኝ፤
መች ጆሮ ሰጠሁኝ መች አዳመጥኳቸዉ፤
ሞቷል እርሽዉ ሲሉኝ ላይኔ ጠላኋቸዉ፤
አይገባቸዉማ..........
በድኔን አስቀርታኝ መከረኚት ልቤ፤
አብራህ እንደሄደች አያዉቁም አሳቤ፤
ነፍሴ ከነፍስህ ጋር እንደተሳሰረች፤
ዳግም ላትነጠል እንደተጋመደች፤
ከጎኔ ባለገኝህም አይዞሽ ባትለኝ አንዴ፤
ጠረንህ ቢናፍቀኝም ባታባብለኝ ዉዴ፤
መቼም ላይጠፋ ከእኔነቴ፤
ዛሬም ህያዉ ነው ፍቅርህ ናፍቆቴ።
በዔደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn
@getem
@getem
❤21😢8🤩2👎1
መኖሬ ከሆነ
እግሬ እንዳይራመድ
ልቤ ሲያጠምድ ወጥመድ
ልርቅ ስል ከሁሉ
ሲቀርቡኝ በሙሉ
አሉልኝ ያልኩኝ ለት
ብትንትን ሲሉ
በቅፅበት ደስታ
ስረሳው ሀዘኔን
ትንሽ ፈገግ አልኩኝ
ላነባው ዘመኔን
ወይ አለምን ንቄ
አልመነንኩ ከደብሩ
ወይ አልተሳካልኝ
አልተመቸኝ ምድሩ
መኖሬ ከሆነ ይቅርብኝ
ግድየለም ውሰደኝ እግዜሩ ።
By ኢዮብ_ዮሚን
@getem
@getem
@paappii
እግሬ እንዳይራመድ
ልቤ ሲያጠምድ ወጥመድ
ልርቅ ስል ከሁሉ
ሲቀርቡኝ በሙሉ
አሉልኝ ያልኩኝ ለት
ብትንትን ሲሉ
በቅፅበት ደስታ
ስረሳው ሀዘኔን
ትንሽ ፈገግ አልኩኝ
ላነባው ዘመኔን
ወይ አለምን ንቄ
አልመነንኩ ከደብሩ
ወይ አልተሳካልኝ
አልተመቸኝ ምድሩ
መኖሬ ከሆነ ይቅርብኝ
ግድየለም ውሰደኝ እግዜሩ ።
By ኢዮብ_ዮሚን
@getem
@getem
@paappii
Telegram
✍ዮ_ሚን
ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
@Yob_minn
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
@Yob_minn
❤45😢7🤩1
" አሜን"
( ግዮናይ ነኝ)!፧
አንቺ ጋር ለመኖር...
ሺ ቁልቁል ወርጄ ብዙ ዳገት ወጣሁ፣
ዳኛ ሳይፈርድብኝ...
እንደ ወንጀለኛ በኑሮ ተቀጣሁ፣
ያ'ርባ ቀን ዕድሌን እጣ ፈንቴን አጣሁ።
* * *
ህይወትን ተራብኩኝ...
እንጃ ስለ ፍቅር ጥላቻን ተጠማሁ፣
ይኸው ደሞ ዛሬ...
እንለያይ የሚል ካ'ንደበትሽ ሰማሁ።
አሜን ያደርግልኝ...
እዛ ማዶ ልጓዝ ፍቅርሽን አልፌ፣
(አልጋዬ የት ነበር?)...
እስኪ ጋደም ልበል ናፍቆኛል እንቅልፌ።
* * *
ሰውነቴ ሁሉ...
እንደ ብሉይ ኃጢያት ለምጻም ሰው መሰለ፣
ፈጣሪ ያውቀኛል...
ህይወቴ ላ'ንቺነት ብዙ እንደ ቆሰለ።
ልሽሽ ካለሽበት...
ምድር እስከምታልቅ በሌትና ቀትር፣
ባህር እንኳን ባገኝ...
ሙሴ ይሰጠኛል የመክፈያ በትር።
@getem
@getem
@paappii
( ግዮናይ ነኝ)!፧
አንቺ ጋር ለመኖር...
ሺ ቁልቁል ወርጄ ብዙ ዳገት ወጣሁ፣
ዳኛ ሳይፈርድብኝ...
እንደ ወንጀለኛ በኑሮ ተቀጣሁ፣
ያ'ርባ ቀን ዕድሌን እጣ ፈንቴን አጣሁ።
* * *
ህይወትን ተራብኩኝ...
እንጃ ስለ ፍቅር ጥላቻን ተጠማሁ፣
ይኸው ደሞ ዛሬ...
እንለያይ የሚል ካ'ንደበትሽ ሰማሁ።
አሜን ያደርግልኝ...
እዛ ማዶ ልጓዝ ፍቅርሽን አልፌ፣
(አልጋዬ የት ነበር?)...
እስኪ ጋደም ልበል ናፍቆኛል እንቅልፌ።
* * *
ሰውነቴ ሁሉ...
እንደ ብሉይ ኃጢያት ለምጻም ሰው መሰለ፣
ፈጣሪ ያውቀኛል...
ህይወቴ ላ'ንቺነት ብዙ እንደ ቆሰለ።
ልሽሽ ካለሽበት...
ምድር እስከምታልቅ በሌትና ቀትር፣
ባህር እንኳን ባገኝ...
ሙሴ ይሰጠኛል የመክፈያ በትር።
@getem
@getem
@paappii
❤32👍2🔥2🤩1