ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
...ስወድህ
እኔ አንተን ስወድህ መስፈርት አላወጣው
መልክና ቁመና ምንህን አላየው
እኔ አንተን ስወድህ ፍቅርህን ነው ያየው
መልክህ ምግባርህ ነው ሁሉን የሚገልፀው
እኔ ምልህ ሆዴ መውደድክን ልውደደው

By
@Hanipia


@getem
@getem
@getem
17👍4
እደውላለሁኝ የሚል ቃል ሳይወጣሽ
ስልኬን በፍጥጫ ቀለሟን ገፈፍኩት
ያለምንም ተስፋ በባዶ ሜዳ ላይ ተስፋዬን ሰነኩት
ጉድ እኮ ነው....
ወይ ደውለሽ ልቤ አረጋም
ወይ ትተሽኝ ቀኔ አልነጋም
እንዲ ስብከነከን እንደ ሰረቀ ሰው
ባጉል ተስፋ ኖሬ ሆዴን እንባ ባሰው።

ጉድ እኮ ነው....

ትንሽ ቆየሁና ስልኬን አስቀመትኩት
እርሳሴን አንስቼ ሃሳቤን አማጥኩት
ልግጠም
ልሳል
ልፃፍ
መርጊያ ምስ አጣሁኝ የመድረሻዬን ጫፍ

ልግጠምላት.....ስለምኗ?
ጠባይ መልኳን ወይንስ ላይኗ

ምኗን ልሳል.....ቀይ ከንፈሯን?
ሰውነቷን ወይንስ ጠጉሯን

ጉድ እኮ ነው....
እንዴት ልፃፍ ምን አንስቼ
እሷን ላግኝ እኔን ትቼ?


እጄን ላብ ጠመቀው
በጨበትኩት እርሳስ
ቆይ...ብትመጣስ?

ልትመጣ ነው!
ምን እየሆንኩ ልጠብቃት?
ምን ነበርኩኝ እሷን ሳቃት?

ኧረ እኔንጃ
ጉድ እኮ ነው....

ወይ አትደውል ወይ አትመጣ
እንዲ አያበድኩኝ ቀልቤን ስንቴ ልጣ

አሃ!
አሃሃ
አሃሃ አሃሃ አሃሃ!

አይ የኔ ነገር
ለካ አታውቀኝም...ኧረ እኔም አላውቃት
ታድያ ምን ቤት ሆና ልቤ ሚጠብቃት?

ጉድ እኮ ነው....

የት ነበር ያየኋት...?
ጎንደር ሸገር ጅማ ሽረ
የት ነው ያገኘኋት ልቤስ ነት ነበረ?

ወይ አታውቀኝ ወይ አላውቃት
ለምንድንው ምጠብቃት?

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
68🔥11🤩6🎉4👍2
የኔን ልንገርሽ
       አፈቅርሻለሁ፣
እየኖርኩኝ ምቼ          
      እጠብቅሻለሁ።
የኔን ልንገርሽ
      ሀሳቤ ሆነሻል፣
አካሌ ተወርሶ
  ልቤ ልብ ሰቶሻል።
የኔን ልንገርሽ
  ባንቺ ሰግቻለሁ፣
ምን ሆነች እያልኩኝ
   የትም አስባለሁ።
የኔን ልንገርሽ
ለሰው አወራለሁ፣
የኔ ናት እያልኩኝ
  ቀኔን አረዝማለሁ።
የኔን ልንገርሽ
መወሰን ከብዶኛል፣
እያጠፋሽ መተሽ
    ይቅርታ ቀሎኛል።
የኔን ልንገርሽ
ሳላጠፋ ይቅርታ እላለሁ፣
አንቺን ባፈቀርኩኝ
    ጌታን መስያለሁ።
የኔን ልንገርሽ
   ጨጓራዬ በስሏል፣
በቀናሁኝ ቁጥር
    ጥላሸት ይመስላል።
የኔን ልንገርሽ
   ቃላት አብዝቻለሁ፣
ፍቅር ፍቅር እያልኩ
    መድረስ ጀምሬአለሁ።
የኔን ልንገርሽ
   ሰው ያለ አይመስለኝም፣
ሴትም ሰውም ውብም አንቺ
ሆነሽ ሌላ አይታየኝም።
የኔን ልንገርሽ
    አይቀረኝ ሙሉቀን፣
    አይቀረኝ ብዙአየሁ፣
    አይቀረኝ ታምራት፣
    አይቀረኝ ቴዲ አፍሮ፣
ማዳመጥ ነው ልምዴ
            እየሰጠው ጆሮ👂
  አያቅም እኔ ጋር ዘፈን ውሎ አድሮ ።
   የአንቺን ግን ንገሪኝ ?
         እንደኔ ሆነሻል፣
     ወይስ እኔ እንደፃፍኩልሽ
         ለአንዱ ሰው ፅፈሻል።


ምንጭ፡- የሷን መልስ በመጠበቅ ላይ ሆኜ የተፃፈ
ማጀቢያ ሙዚቃ ፡- ልዑል ሲሳይ ( የኔ አመል )
ገጣሚ፡- ፓፒኤል

@getem
@getem
@getem
52👍6🔥3🤩2
ልቡ ለከነፈ ፥ ለናፈቀ ወዳጅ
ምን ያደረጋል ታክሲ ?
ምን ያደረጋል ባጃጅ ?
ወራጅ !
የመኪናው ጎማ ፥ ሺ ጊዜ ቢፈጥን
መውደዴን ላያክል
ጉጉቴን ላይመጥን !
ወራጅ !
ወራጅ !
ናፍቆቷ እንዳልደክም ፥ ይሆነኛል ነዳጅ ።

ጫማዬን አስሬ ፥ ወደ ቤቷ ላዝግም
አጋዥ አልፈልግም ።

መኪናም ይቅርብኝ ፥ ፈረስም አልጋልብ
እግር ይቀርባል ላሳብ
እግር ይቀርባል ለልብ ።

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
53👍6🔥4
( የሚያጋጥም )
============

ኤዲያ ....
:
ልክ አብሮ እንደሚሄድ
አብሮ እንደሚመጣ
አብሮ እንደሚበላ
አብሮ እንደሚጠጣ
አብሮ የሚያጋጥም
ደህና ወዳጅ ልጣ .. !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
45👍6😁3🔥1
አታውቋትም።።
(የሞገሴ ልጅ)
እህት ማለት-
ወንድምነት እንዲታወቅ - ወንድ መሆን ልኩ እንዲታይ፣
መስታወት ናት፣
በታየበት በኩል ሆና - ያልታየውን አይታ አሳይ።

የወላጆች-
ዘር አጋምዷት ሤትነቷ - ችግኝ ሆኖ የሚጠበቅ፣
እርስት ናት-
ውብ ስጦታ ከጎን ሆና - በየ እለቱ የምትናፍቅ።

እያላችሁ-
እህትነት የኅዝብ ሆኖ - በወል ሚዛን ብትለኳትም፣
እናት መሆን,
ለእህትነት ካልተሰጠ - የኔን እህት አታውቋትም።

አታውቋትም።።.
እንደእድሏ-
ነጋ መሸ በልጅ አቅሟ - ልጅ ማሳደግ እጣ ደርሷት፣
ለወንድሟ፣
እናት መምሰል መሆን ጋርዶት - አቻ ላቻ ከእህትነት።

የአንድ ሁለት-
የሁለት አንድ ምስጢር ሆና - ያለልብ አይን ብታዩአትም፣
አለም ሲኖር፣
በሚአይበት መነጽሩ - የእኔን እህት አታዩአትም.
አታዩአትም..
ስም ነው እና፣
እንበል እንጂ ለእህቴ - እህትነት አይገልጻትም.

By @tafachgitm

@getem
@getem
@getem
57👍6🔥4
ሀገር ሲሰርቅ

ጀግኖቹ ዘማቾች!
በገደል፣ በደኑ፤
ሌባ ሲያሳድዱ፣ ቀማኛ ሲያድኑ።

ጀግኖቹ ዘማቾች!
ከጫካው፣ ከዱሩ፤
ነጣቂ ሲያስሱ፣ ሽፍታ ሲያባርሩ።

ከዘመቻው ብዛት፣
ከዘማቹ ብዛት − አንድ ‘ዕውቀት’ ተረፈን፤
ለካስ!
ሽፍቶች መሀል በቅሎ ‘ጫካው’ ነው ‘ሚዘርፈን።
------
በረከት በላይነህ

@getem
@getem
@paappii
32👍10🔥5🎉2😁1
( ልመርቅሽማ ... )
===============

እማ .....
የተረሳው ማንነቴን
እንዳወጣሽ ከጨለማ
ልትጠይቂው ያሰብሽውን
ቃል ሳይወጣሽ ጌታ ይስማ

እንደሸፈንሽ ገመናዬን
ስሜ ባገር ሳይ'ታማ
ኃፍረት አሳር ያገኘሽ ለት
ትከልልሽ ጸሐይ ጸልማ

ቀን ሲጥለኝ ላጽናናሽኝ
እስኪረሳኝ ክፉ ግብሬ
የሰማይ ዘብ መላዕክታን
ያረጋጉሽ በዝማሬ ... 

ወድቄ አይተሽ እንዳልናቅሽኝ
ከሰው ተራ በታች ስገኝ
ቀን ሰምሮልኝ ከብሬ እንኳ
አገልጋይሽ ሎሌሽ ያርገኝ ...

አሜን !!!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
105🔥15🤩6😱2👎1
🕊️  የአብስራ ሳሙኤል  🕊️ 


ተይኝ ሞቴን ልሙት ትውልድ ምናምን አትበይኝ 
በፏፏቴ በተራራው በሳር በቅጠል አደልይኝ 
እማ ልጄን አትበይኝ 

የታሪክ ስንክ ሳር ኋላ ታላቅነትሽን 
የድል የድሎት ዘመንሽን 

አባይ ሆኖ ጅረት ፈሶ ለሌላ እንጂ የሚ'ደርሰው 
ለኔ ብኩን ደካማ ሰው 
የዕንባ ብናኝ የደም ወዜን 

ግልገል ወንዝሽ መች አርሶት 
ለምለም ጤዛሽ መች አብሶት 

መቼም ከተራራሽ ብብት 
ድንጋይ ቢፋጭ ውሀ ቢላተም 
እጇን በዘረጋች እናት አለም 

ጸሎት ምልጃዋ ያውጣት እንጂ 
ማን እጁን ወዳንቺ ይሰዳል 
ምኞት ተስፋሽ ይማግዳል 

እናም አልችለውና በሰው አቅም በሰው ገላ 
ስጋ ነፍሴን ከ'ነ ህልሟ መሀጸንሽ ተቀብላ 
ጸጸት ብሶቷን ታምጥ ግድ የለም 
ልጄ አትበይኝ እናት አለም 

ተይኝ ሞቴን ልሙት እማ ሆዴን አታባቢው 
ተስፋ ምኞት አቀልቢው 

መቼም ትታዘቢኝ ይሆናል ያዝናል ወላድ አንጀትሽ 
ይነጥፋል ያጠባ ጡትሽ 

ሽል ሆኜብሽ የዘር አምሳል አደራሽን ብሸሽም 
እማ ትሙች ብሞት �ንጂ ኖሬም ምንም አልጠቅምሽም 

እናም አንቺ ውለጅ መውለድ ይክሳል 
የኔ አይነት እልፍ ተቀብሮ ከትቢያሽ ህይወት ይነሳል 

የምኞትሽን ልጅ ይስጥሽ የተመኘውትን አትንሺኝ 
አለወለድኩም ብለሽ እርሺኝ 

ለ'ኔ አልሆነም ይሄ ትግል 
ምልጃሽ ያውጣኝ በግልግል 

ተይኝ ሞቴን ልሙት ትውልድ ምናምን አትበይኝ 
በፏፏቴ በተራራው በሳር በቅጠል አደልይኝ 
እማ �ጄን �ትበይኝ 

      _ንሸጣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን_ 
      _ተወኝ_

@getem
@getem
@getem
33👍2🔥2🎉1🤩1
( ተደብቆ )
=========

ጠብ ካልሻቱ በቀር
እድሜ አይጠየቅም .. ሄዋንን አጥብቆ

መፈላለግ እንጂ
ፈገግታዋ መሐል ካለ ተደብቆ !!!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
44😁18🔥3😢1🎉1
"ፀሎት ወምኞት"
              (ግዮናይ ነኝ)!፧

ከሐምሌ ጨለማ  ከክረምቱ ቆፈን፣
ከበጋው በረሃ   ከግንቦት ወላፈን፣
እኔና አንችን ብቻ  አምላክ ያሳልፈን።
                  ......
ካሉባልታ ወሬ  ከምቀኛ ሐሜት፣
ሰይጣን ለሚጠራ  ካልተገራ ስሜት።
መንታ ምላስ ይዞ   ከሚሰነጥቀን፣
የፍቅራችን ጌታ   እሱ ይጠብቀን።
                  .......
ትዳር ስንክሳሩን  የሳልነው በምናብ፣
ከላይ ይፈሰስልን  እንደ ሐምሌ ዝናብ።
በህይወተ-ፍካት በኔና አንቺ ማማር፣
መስከረም ይቅናብን  ጥቅምት ከኛ ይማር።

@getem
@getem
@paappii
39👍8🔥2🎉2🤩2
ደርሷል ያልሽኝ ፍሬ
በሳል ያልኩሽ ጥሬ
ሰላ ያልሽኝ ፍቅር
ፀና ያልኩሽ ውቅር
ተንዶ በድንገት
ለኔም ላንቺም እብለት
ላንቺም ለኔም ውሸት
እንጭጭ ሳለ ጥሬ
ለቀጠፍነው እሸት።
       

By @poetkidus

@getem
@getem
@getem
22👍9🔥2
የአብስራ ሳሙኤል

ዘመን ባይቀድምም እዚህ ህይወት አለ 
ከመኖር ወጀብ በመውደድ ሰበዝ የተከለለ 

❀   ❀
እዚህ እናት አለች 
ልጇ ሲመጣ ፈገግ ትላለች 
እዚህ አባት አለ 
ደቂቅ ትከሻው ዝግባ ያከለ 
❀    ❀


እዚህ . . . . . 
እኔና አንቺ ባለንት 
ነፍስ በዘራንበት 

ጠባብ ጎጆ ድንክ ማገር 
ታሪክ አለ ለዘመናት የሚሻገር
ከገሀድ ጮራ ፈንጥቀን 
በፈጠርናት ህብረ ቀለም 

መዋደድ ነው የህይወት ቋንቋ 
ቤተሰብ ነው የ'ኛ አለም 

እዚህ በምታይው 
በመኳረፍ እልህ ጥልቅ ፍቅር አለ 
የጊዜን ግሳንግስ በሳቅ ያቀለለ 
ዕልፍ ተሰብስቦ ቡራኬ የሚቋደስ 

እዚህ �ህይወት አለ 
አንተ ብላ በሚል ጥጋብ የሚታደስ 

እንዴት እንዲህ ይወደዳል 
እንዴት እንዲህ ይዋደዳል 

የመኖርን �አጸድ በአንዱ ዳና መትከል 
ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ላመኑት መከተል 

እዚህ ብቻ ነው ያለው 
ለ'ኛ ብቻ ነው ያደለን 

እዚህ ውስጥ ሁላችን አለን 
እናት ሆነን አባት ሆነን 
ወንድም ሆነን እህት ሆነን 

አንድ የመሆን ብዙ መልኮች 
የአንድ ሰፌድ ህብራዊ ሰበዝ ገጾች 

የህይወት መርህ ያጠላለፈን 
የመዋደድ ቅጽ ያደጋገፈን 

እዚህ . . . . . 
እኔና አንቺ ካለንበት 
ህያው ታሪክ አለበት

@getem
@getem
@paappii
34🔥6
---

የአብስራ ሳሙኤል 
*・꙳・꙳・꙳・꙳・・*

እጠራሀለው 
በስምህ አቤት በለኝ ከሰማኀው
"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልከው 

ከፀሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ከህይወት አድማስ ባሻገር 
ሞት የህይወት ፍጻሜ ነው? 
ወይስ ድልድይ የሚሻገር? 
አላዛር ያኔ ቢጠየቅ 
የሞተ ግዜ የት ነበር? 

ወዴት ነው 
የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 
ነፍሴን የማጽናናበት 
ምኞቴን የምዳኝበት 
ምን አለ ከጸሀይ ጀርባ? 
ወዴት ነው ነፍሴ የምትሸሸው? 

ይብቃህ እረፍ ተብዬ 
የስቃይ ቀኔ የሚያመሸው 
አውቃለሁ እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*"ጠይቁ?" ብለህ አልነበር・・・ራባይ* 
―☾―

አየሁኝ 
እውር አንበሣን 
አንካሳ ነብር ሲመራው 
እንዲህ ነው መንግስት የሚዘልቅ 
እንዲህ ነው ፍጡር የሚመራው 

ካልተማመነ 
መንገዱን በነብር አይን ተረድቶ 
መጠራጠር ይገላል 
አንዱን ከአንዱ አባልቶ 
ይኀው ነው የነፍሴ ጣሯ 
አታምነኝ ወይም አላምናት 
ማ? በለኝና ማን ልበል 
በየቱ ቃልህ ላባብላት 

ማመን ነው 
የተስፋ ምርኩዝ 
መከተል የአይኑ ብርሀን 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ይሆን የመራኀን? 
―✦―

እጠራሀለው 
በስም አቤት በለኝ  ከሰማኀው
ጠይቁ ብለህ አልነበር 
እጠይቃለሁ አንተ እንዳልኀው 

ከጸሀይ ጀርባ  ምን አለ?
ኦና'ነት ወይ ፍጻሜ 
የት ይሆን ጅምር መቋጫው? 
ስንት ይሆን የመኖር እድሜ? 
ወዴት ነው የመኖር ማብቂያው? 
ወዴት ነው መጠናቀቂያው? 

አውቃለሁ 
እንደ ነገርከኝ 
ብረዳም ከድርሳን ቅጽህ 
ማ? በለኝና ማን ልመን 
ብዙ ነው ስምና ገጽህ 

*・☽・・・☾・・・*

@getem
@getem
@paappii
47🔥7👎2
( ተይ ጡር አለው ... )
=================

መቅረት እኮ ብርቅ አይደለም
መጣሁ ያለ ሁሉ አይመጣም
መተው እኮ ጥንትም ነበር
አንዳች እክል ሰው አያጣም
አይደንቀኝም ወዶ ማጣት
አልከፋኝም በመጥፋትሽ
ግን ንገሪኝ ....
እንደማትመጭ እያወቅሽው
ለምን ይሆን ማስጠበቅሽ ?

አንድ ህይወት ነው የተሰጠኝ
የማልኖረው ደጋግሜ
ግፍ አይደል ወይ ..  ከዚችም ላይ
በጥበቃ መስረቅ እድሜ ??

ቅርብ አሳቢ ምስኪን ልብሽ
ባያስተውል ልብ ባይለው
በወደደው ለጨከነ
ላልራራለት ለከጀለው
የዘሩትን የሚያሳጭድ
ፍቅርም እኮ ተይ ጡር አለው !

By @kiyorna

@getem
@getem
@getem
49😢14🔥6👍5👎1
ብዙ ሳይጣጣር
እምብዛም ሳይለፋ
ከዓይን የራቀ
ከምናብ የሰፋ
ይህን ዓለም ሠራ
ያለ ጭንቀት ጥበት
ሆነለት “ሁን” ሲለው
እንዲሁ በዘበት

ሕዋውን በሙሉ
ግዑዙን ተፈጥሮ
በቃሉ ትዕዛዝ
እንዲህ አሳምሮ
ለድንጋዩ ራርቶ
የንብ መንጋ መርቶ
አበባን አፍክቶ
ወፊቱን አብልቶ

እኔ ትንሽ ነገር
ከሕይወት ቢጨንቀኝ
አደራህን ብለው
“እሺ ቆይ” እያለ
ይህን ሁሉ ዓመት
የሚያጠባብቀኝ
እንዴት ብከብደው ነው
ወይ እንዴት ቢንቀኝ ?
….

By henok bekele

@getem
@getem
@paappii
45👎20😱5😢3🔥2👍1😁1
ሀ...ለ...ሐ...መ
ነገር አከተመ

ጥበብ በሁለቱ
በግጥም ስዕሉ
        ስታወናብደኝ
ህይወት ሚሉት ቋንቋ
ካንቺ ስር አዋለኝ።

መልክሽን በስዕል
መልክሽን በግጥም
       አተራመስኩልሽ
ይኸው አበድኩልሽ።

ጥበብና ህይወት...
ካንቺ ጋር አጋብተው ላያኖሩኝ ነገር
ለምን ይሰጣሉ
"ስሜት" ብለው ማፍቀር

አቤት አኳኋንሽ
አቤት አሳሳቅሽ
አቤት አረማመድ
ምንድነው መላመድ?
ለጥበበኛ ሰው መላመድ ትርፍ ነው
አይቶ ማፍቀር ብቻ ጥበብ እያረገው።

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!

የማልጨብጣትን ከምናብ አለም ሰው
        በፍቅር ሰቀልሽኝ
       ይኸው አሳበድሽኝ።

ሀ...ለ...ሐ...መ
በቃ ተፈፀመ።

ታሪክ ልስራ ብዬ...ታሪኬን ጨረስኩት
          ኑሮዬን አበድኩት

አይ ጥበብ አንዳንዴ
ደስ አለሽ ማበዴ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
52🔥10🤩1
ጭውውት ከአይኖቿ
ጠ..ጠ..ር
እንደ ዳዊት ጠጠር፤
ወርወር፤
ጎላ ደግሞ ደመቅ፤
ደመና መሰንጠቅ፤
ጠንቀቅ፤
ወጋ ደግሞ ነቀል፤
ስሜትን መፈንቀል፤
ቀልቀል፤
ከብለል ከዛ ረጋ፤
ትንፋሿን ፍለጋ፤
ጠጋ።

By @poetkidus

@getem
@getem
@paappii
38🤩21👍3🔥3
🌹 የአብስራ ሳሙኤል🕊


▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
መለያየት ሞት ነው ብላኝ እንዳልነበር 
ይኀው ተለያየን ሞታ ስትቀበር 
✞ አፈር ስትለብስ መሬት ሲደብቃት 
   የአዳም ዘር እዳ ከቅፌ ሲነጥቃት 
ጩኀት ለቅሶ ዋይታ አጅቧት ስጠፋ 
   ነፍስ ይማር የሚል ቃል ጆሮ ላይ ሲከፋ 

   ሞታ ስትቀበር 
   መለያየት ሞት ነው 
   ሞት መለያየት ነው 
ብላኝ እንዳልነበር 
   ይኀው ተለየቺኝ አፈር ስትለብስ 
   እንባም አይበቃኝም ላንቺ በምን ላልቅስ 


▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
የቀብርሽ እለት 
   በልብሰተ ክህኖ ገፁን ያሳመረ 
ጠይም ደርባባ ቄስ 
   ስለ ሞትሽ ትርጉም እንዲ ተናገረ 
  ተው አይለቀስም 
   ምን ሰራህ ተብሎ እግዜር ይወቀሳል 
   አፈር የተጫማ 
   ሊበሰብስ እንጂ ተጉዞ የት ይደርሳል 

 
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
ህይው ልትሆን እንጂ 
   ✞ ከፈራሽ ገላዋ ነፍሷን የነጠቀ 
ያልሞተ አያፈራም ዘር ሆኖ ያልወደቀ 
   ትድን እደሆነ 
   ተዝካሯን አውጡላት ነድያን መግቡ 
   እሱ እንደው ሩህሩህ አይጨክንም ልቡ 
ብለው ቢናገሩ 
     ከበደኝ ቀብሩ 


▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
አንቺስ ፍቅርዬ 
   መለያየት ሞት ነው ብለሺኝ አልነበር 
በመሞት ከሆነ ህይወት የሚጀመር 
   ውልደትሽ ምን ነበር? 
   ከኔ ተለይተሽ 
   ጀነት ብትገቢ ብትቆሚ በቀኙ 
   ያንቺን እጣ ማግኘት ሙታን እዲመኙ 
🔥 ወይ ሲኦል ተጥለሽ እልፍ ብትቀጪ 
      ለየዕለት ሀጥያትሽ ፀፀት ብታምጪ
   ከልብሽ ላይ ችለው እኔን ላያወጡ 
   ስፍር አልባ ጋኔል ባንቺ ላይ ቢቆጡ


▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
ብታማትቢ እንኳ 
     የማይጠፋ ሴጣን ከሲኦል ቢገጥምሽ 
አውቃለሁ ፍቅርዬ 
     የሀጥያት ሰንሰለት እንደማይገድብሽ 
ስለዚህ ለአንቺ 
  🕊 ፍጹም እንቀይረው የመሞትን ፍቺ 
አንቺ እንደ ነገርሺኝ እኔም እንደማውቀው 
   ከሀዘናቸው ብዛት ባይቀብሩሽም ስቀው 

  🕊
▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔▔
ስለመለየትሽ እንባ እያፈሰሱ 
    መአት ለቀስተኞች ከለቅሶሽ ደረሱ 
እኔም ከንቱ አፍቃሪሽ 
     ሞት ህያውነት ነው ብዬ እያመንኩኝ 
ህያው ሆኜ እንኳ ካንቺ የተነጠልኩኝ 
   💧 ሳስስ ስፈልገው የሞትሽን ትርጉም 
   ከእንባ ላይ አየሁት የሚተን እንደ ጉም 

┗━━━━•❃🌹    🌹❃•━━━━┛

@getem
@getem
@getem
62👍10🔥4🤩3🎉1
መቼ ነው አንድ ቀን ??
===============

ስንጠጋው ሚሸሽ
ስንቀርበው ሚርቀን
ዕድሜያችንን ሁሉ
ስንኖር ሚናፍቀን
በተስፋ ጠቅልለው ይመጣል የሚሉን
መቼ ነው ' አንድ ቀን ' ??

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
80🔥9😢7👍2