ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሀሰት በከበባት ኢ ፍትሀዊ አለም ተከሳሽ በሙሉ ወንጀለኛ አይደለም

አይገርምም ...?

የሚታዘዙለት ሳርና ንፋሱ ሀጢአት የሌለባት ንፁህ ሳለች ነፍሱ
ወንጀለኛ ተብሎ ፤

ተከሳሽ ነበረ ክርስቶስ እራሱ፡፡

By Eyob Z Mariam

@getem
@getem
@paappii
118👍34😢8
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
የካቲት ወርሀ-ገብረ-ክርስቶስ ;

ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰአት በገብረ ክርስቶስ ሙዚየም 6 ኪሎ ፧ አመታዊው አለማቀፍ የገብረክርስቶስ ቀን በስነ ግጥምና ስነ ጥበብ ደምቆ ይከበራል። ገብረክርስቶስንና ድንቅ ስራዎቹን የምትወዱ ሁሉ ተጋብዛችሁዋል። ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።


ምንጭ
አርቲስት በቀለ መኮንን

@Seiloch
👍1510
ምኞት ምትጸንሰው

ምኞት ፀንሳ ሃጥያትን ትወልዳለች፣
ፑልም ተጀምራ ቁማር ትሆናለች።
ለመዝናናት በሚል በተልካሻ ምክንያት፣
ምኞት ትሄዳለች ወደ ትልቅ ሃጥያት።
ሃጥያት ሲተነተን በብዙ መንገድ ነው፣
እንደ ሃጥያቱ ብዛት በሲኦልም ሲኬድ የራስ ክፍል አለው።
ከሃሳቤ ሳልስት ከፑሉ ሳልወጣ፣
ቁማሩን ተወው እንጂ ከፑል ቤት አትውጣ።

By G.hanun

@getem
@getem
@getem
😁36👍184😱2🔥1🤩1
በግድ የፈለቀች
ጠብ አደረኩ እምባ
"በቃ ይፍቱኝ አባ"

ይሄ ነው ሀጥያቴ
ከእግሮ ስር ያራቀኝ
ምን ልስራ
ምን ላድርግ
አዚሙ እንዲለቀኝ?

አዩኝ ትክ ብለው
ቀረቡኝ
ቀረብኩኝ
መስቀል ተሳለምኩኝ

ከዛ ግን አላውቅም
ካልቾ .. ጥፊ .. ጨምቧ
".. ያማል እኮ አባ"

"ዝምበል"
"አባ ይፍቱኝ በል"

"አዎን አባ ይፍቱኝ"
አገላብጠው መቱኝ።

"ይኸው የኔ ጎበዝ
መንፈሰ ከርታታው
አንዲህ ነው ሚፈታው"
እስቲ ዝቅ
እስቲ ዝቅ
ከዛ አንዴ ድልቅ!

ወይኔ መድሃኒአለም
እጃቸው እንዴት ያማል፤
"የኔ ልጅ ይሰማል?"
በተዋጠ ልሳን
"አይሰማም አባ"
በድጋሚ ጨምቧ
የጠገበ ልጄን
ሳጠምቅ አልገኝም
እስቲ ከፍ ጨምቧ
ያንተማ አይጠፋኝም

እስቲ ከፍ ጥብስ
እስት ዝቅ ጨምቧ
"ይበቃኛል አባ!"

"ምኑ ነው ሚበቃህ?"
የኔን ትንሽ ዱላ
  ከሳር የቀለለ ፤
ንፅህና የታለ?
ድንግልና የታለ?

ከፍ ዝቅ ክልትው
ሸሸሁኝ በዳዴ ፤
አባ ይቅር በሉኝ
ተሳሳትኩኝ አንዴ
"ሰው አይደለው እንዴ?"

እሱማ ሰው ነበርክ
በእግዜር የሚፀና
ክህነቱስ ግና?
ድቁናውስ ግና?

ቀና በል  ያዝ ጧ!
አትወራጭ ፡ ድርግም!
"አይለምደኝም ዳግም"
እሱን ለግዜር በለው
ይኸው የኔ ፋንታ ፤
ከፍ ዝቅ ድርግም
"እባኮት የኔታ"

"ይቅር በሉ ይላል
ወንጌሉን አይርሱ
መመለሴን አይደል
ሚፈልገው እሱ?"
"እሱማ መተሃል
ዱላ ለወጉ ነው
ዳግም እንደማትሄድ
  .. ለማረጋገጫ ፤
"ይሄ ሁሉ እርግጫ?"

"ዝምበል"
"አባ ይፍቱኝ በል"
"እሺ ይፍቱኝ አባ"
ቀና ሳብ ጨምቧ

ከዛን ተረጋጉ
አየር ሳብ አረጉ
"ይኸውልህ ልጄ
አድገህ አይደል በእጄ
አይንህ ልቤን ወጋው
ከእሳት ሳይህ ሰጋው
ለዛ ነው የተቆጣው
እስኪ እጅህን አምጣው"

"ይኸው" ብዬ አቀበልኩ
"ለበረከት እንጂ
አይሆኑም ለመርገም፤
እንካ ዳዊት ድገም
ይበቃል የስካሁን
አንተን ሳይ ፈራለው
.. ከእቶን ከእሳት፤
ከንግዲህ አትሳሳት"

ብለው አሳለሙኝ
ዝቅ ስል አመመኝ
ለንስሃ  ያልወጣ
እምባዬ ቀደመኝ

ዱላ ያጀገነው
ልቤን ብሶት ገፋው
ስብርብር እያልኩኝ
ከእግራቸው ተደፋው

"አሳፈርኮት አባ
አሰደብኮት አባ
አስተምረው መና
አሳደገው መና
አልበሰልኩም ገና
አልበቃውም ገና
ይቅር በሉኝ አባ
አፉ በሉኝ አባ"
ብዬ ጥምጥም አልኩኝ
ጉልበታቸው ግርጌ
ጎትተው አነሱኝ
አቀፉኝ ሳብ አርገው፤
"ይሄን ልጅነት ነው
ጌታ ሚፈልገው"።

አሁን ለርሱ ስጋ
ባለበሰህ ፀጋ
ስለምትበድለው
ግፍን ስትሰበስብ ፤
እኔማ በእጄ ነህ
ለሞተልህ አስብ!።

አልቅስ እዘን እንጂ
ተስፋ ለማይቆርጠው
የምትድንበትን
ምክንያት ሲገጣጥም ፤
የጠገብክ እንደሆን
እናትህ ሆድ እንኳን
እኔን አታመልጥም!።

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
77👍57🤩7🔥6😁6😱1
ወዬ ለኔ

ዘንድሮን ሁዳዴ
ሳልሰስት ለሆዴ
ንፍሮዉን አንፍሬ
ዳቤዉን ጋግሬ
ቢጫ ቆቤን ገዛዉ
መቋሚያም አሰራዉ
ዳሩ ምን ያደርጋል...........

ሠዉ'ነቴ አደፈ
ቃሌ ገረጀፈ
ሀሳቤ ሸፈፈ
ምን ያደርግልኛል ንፍሮ መቀቀሉ
ኑሽሮን እንብላ እስኪደርስ በአሉ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@Tizita21
@getem
@getem
👍6940😢4😁2👎1
ሩህሩ ነበር ልብሽ፣
የዋህ የጨው እቃ፣
የማይከብድ ቀንበር፣
ተመቺ ለጫንቃ፤
አቃፊ ደጋፊ፣
ፈገግታ መጋቢ፣
የምሕረት ገባር፣
ከእውነት አጋቢ፤
ተናፋቂ ውበት፣
ውስጣዊ ብርሓን፣
የማይጨልም ትጋት፣
የሚደነቅ ልሳን፣
አቆራኝቶ ይዞ፣
ሰውረሽ ይዘሽው፣
የመወደድ ፅዋን እንዳይጎል ሞላሽው።

By @tafachgitm

@getem
@getem
@paappii
30👍24🔥4
ይች በሰማይ ላይ
የተሳለች ፀሐይ
በዓለም ሰልጥና መንበሯን ዘርግታ
መኖሯ ቀን ቢባል ማዘቅዘቁዋ ማታ
ለኔ ምን ሊፈይድ እኔን ምን ቸገረኝ
አትገዛኝም ፀሐይ የራሴ ዓለም አለኝ።
ፀሐይ ለዘላለም ሳቶጣም ብትቀር
የት አይቶኝ ጨለማ የት ደርሶ ከኔ በር
ባንች መምጣት መኼድ ነው ቀኔ ሚቆጠር።
በኔ ዓለም ውስጥ ያለሽ የኔ ፀሐይ አንች
ስትመጭ ይነጋል ይመሻል ስትኼጅ።

By @yonas_sileshi

@getem
@getem
@paappii
28👍26🔥3😁2
[በሠላሳ ክረምት]
.
.
ከቦኛል ፍርሀት ከቦኛል እርጅና
የጉብዝናው ወራት
በወጉ በወጉ አላለፈምና።
ያወዛውዘኛል የአዝማናት ነፋስ
መደገፊያ ምርኩዝ ከማን ብርቱ ልዋስ?
እነሳ የነበርኩ ተስፈንጥሬ እንዳነር
እራመድ የነበርኩ በግሮቼ ጀግኜ
ክንፌን ቆርጬ ጣልኩ ከፍርሀት ወግኜ።

ሳዘግም
እግሮቼ ሲርዱ
ስተኛ ጭኖቼ ሲበርዱ
የገላዬ ሙቀት ሲሸሽ ቀን ጠብቆ
ቆፈን ሲዳበለኝ እንደስም ተጣብቆ
እትቱ ዘፈኔ
ፀደይ እንዳልወጣ በጋን እንዳልገፋ
ግንባሩ ላይ ይዟል የማለፍ ወረፋ።

በሰላሳ ክረምት በሰላሳ በጋ
ገሚሱ የርግማን ጥቂቱ የፀጋ
ተብዬ ብጠየቅ “ምን አደረክበት?”
መልሴ
እንደሞላለት ሰው ዝም ብዬ ኖርኩበት።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
40👍27😱3🔥2🎉1
.......


የሄዱትን ሁሉ
የገፋንን ሁሉ
ስቀን ሸኘናቸው
ስመን ጠቆምናቸው
በተዘጋ ጎጆ
በእንባ እየተራጨን
ከመገፋት ጽዋ
በቀል ተጎነጨን
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን
መልከጥፋ መልካም
ብጉራም ቀፋፊ
ጎባጣ አንገት ደፊ
ነን ብለን አመንን
ውበትን ለመንን
የሄዱትን ሁሉ
የገፋንን ሁሉ
ስቀን ሸኛናቸው
በእናባ ጸለይናቸው
ፍቅርን ተሳልን
በበቀል ቆሰልን
ሳሚ ያጣ ከንፈር
አቃፊ ያጣ ገላ
የወደድነው ሁላ
ጸጸት አስጎነጨን
ስቆ ለእንባ እያጨን
አሸሸ መዳፋን
ነፈገን እቅፋን
ጸደቁብን በቃል
ውበት ልብ ይበቃል
ብለው ልብን ሸሹ
ገፍተው አቆሸሹ
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን
መልከጥፋ መልካም
ብጉራምም ቀፋፊ
ጎባጣ አንገት ደፊ
ጉለት ሆንን ያምላካቸው
ያምላካችን
በመልካችን
ለወደድነው አነስን
ለአፈቀርነው እረከስን
ተጎነጨን መገፋትን
መተፋትን
ጠላናት ተፈጥሮን
ከእይታ ሰውሮን


By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3010🔥9👎1
| በዚህ አለም፥ በዚህ ህይወት ፍቅር እስካ'ለ -
ለህልም፥ ለመሻት፥ ለምኞት ሁሌ መንገድ አለ።
ለእያንዳንዱ ድቅድቅ ለሊትም ብሩህ እለት አለ።

እውነቱን ስነግርሽ፦ ፈተና ነበረ በየዕለቱ፣
ሰኞ ተሰብሬ - ተነሳሁ በነጋታው በጠዋቱ።

ማክሰኞ በተስፋ እያለምኹ ዋልኹና
ረቡዕ ከሰርኹ - የእጄ ስራ ቀረ መና።

ሐሙስ ቆምኩኝ፥ ፍቅርሽን ጥበቃ
ለአማልክቱ ምስጋና ይግባቸውና -
አርብ ላይ ደረስኹ መንገዴ ነውና!

ቅዳሜን ነደድኹ ጨስኹ -
ፍቅሬን አንቺን እየጠበቅኹ፥
ሰንበትን ከመቅደሱ ቀረኹ!

ውዴ

የፍቅርሽን መንገድ እጓዛለኹ! እጓዛለኹ!
ሰንበት ሰንበት ሲሆን ቆሜ ጠብቃለኹ!

በመጠበቅም ቆሞ፥
|
በመፈለግም ሄዶ፥
|
እኔ አፈቅርሻለኹ!


•°•°•°•°•°•°••°°••°•°•°°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•
በዚህ ምድር፥ በዚህ ህይወት ፍቅር እስካለ
የሚረታኝ፥ የሚያቆመኝ፥ የሚይዘኝ ማን አለ?

በዚህ አለም በዚህ ህይወት ፍቅር እስካ'አለ
ለህልም ለመሻት ለምኞት ሁሌ መንገድ አለ
ለእያንዳንዱ ድቅድቅ ለሊት ብሩህ እለት አለ

•°•°•°••°•°•°•°•°°••°•°•°•°•°•°•°•°°•°•°

By ናኹ

@getem
@getem
@paappii
👍3026
ቃለኛ ናት ለእግዜር ወጉ
ልባም ትጉህ
ኪዳን አዛይ ልበ ብርቱ
ዳር እስከ ዳር ከአስረቱ
ንቃ አተኛም ለሰዓቱ

ወተቲቱ!

ለ ሶስት ለስድስቱ
ለዘጠኝ ሰዓቱ
ቁሞ ጠላይ ለእግዜር
ነጣላ አንጋቢቱ
ተንበርካኪ ካፈር ከስነ ስዕሉ
አሜን ቃለ ከንፈር ለመረቃት ሁሉ
ጦም ኣዳሪ አትወላውል
አታውቀውም የላት ስልቱ
ወድቃ ማትገዛ ለነገረ ከንቱ

ወተቲቱ!

ዮኒ
      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍198🔥1
ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ

ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ

ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)

አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ

እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር

በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)

ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ

#ኤልዳን
@marda129

@getem
@getem
@getem
20👍17🔥2
ላረፈድሽው


እኔማ ጠባቂሽ
ማርፈድሽን አላይም መምጣትሽን ብቻ
ድረሽልኝ እንጅ
በዘመኔ ማብቂያ በዕድሜዬ መባቻ

ፀጉሬ ቢሸበባብት ስጋዬ ቢጃጅም
ይበስል እንደሁ እንጅ
መንፈስ አያረጅም
ነይ ፍቅሬ ወጣት ነው ልቤም እቶን እሳት
የተገላቢጦሽ ቢያደርገውም ቅሉን
የዘመን መሳሳት
ከመቅረት ይሻላል ከመጣሽ ቢረፍድም
ፅልመት ካልገፈፈ ወትሮም ጎህ አይቀድም

By @poem2513

@getem
@getem
@getem
36👍20😢3🔥2
..........



አላቅም
አታቅም
የልቧን ተናግራ
ዝምታ ሰብራ
ጭምት ነበረች
እኔን ስታገኝ
ቃላት ፈጠረች
የፊደል አይደል
የቋንቋ በደል
ውሸት ነው የሚሉት
ነገ ላይ ደርሰው
ክደው
አፍርሰው
የቋንቋ አይደለም
በፍቅር ቀለም
ከገጽ ከአካሏ
ምልክት ስላ
ከሩቅ ነበረ ያናገረቺኝ
ደምቃ የታየቺኝ
አታቅም
አላቅም
ሴት አሽኮርምሜ
ከንፈር ተስሜ
ገላን በጠረን
ናፍቆት በዘፈን
አላባበልኩም
አላጫወትኩም
ጭምት ነበርኩኝ
ሰው የሚሞቀኝ
ወሬ የሚርቀኝ
ጥርሶቼ ስቀው
እግሬ ቦርቀው
ቀን ያላለፉ
አንቺ ጋር ደርሰው
ተኮላተፉ
መሳም አማረኝ
ያማረ ጉንጯን
አገጭ.....አገጯን
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
መኖር እየሳሙ
ከእቅፏ
ከአፏ
ህይወት ታዘንባለች
መኖር ታስርባለች
እየደጋገሙ
እየደጋገሙ
ክፉዋን ሳይሰሙ
አምላክ እንደው ጨካኝ
ክፉ
ዐዕላፍ ሳይረግፋ
የሰው መንጋ
ሞት ከደጇ ላይጠጋ
ገዝቼላት ሞትን
መለየትን
ከዘር እዳ ልነጥላት
እኔው ሞቷን ልሙትላት
ዕድሜ አውሼ
ተውሼ
ከእባብ ከሚዳቆ
ከዛፍ ከሸንበቆ
ትንሽ ዕለት
ትንሽ አመት
ተመጽውቼ
ልሙትላት
ሞቷን ትቼ
አላቅም
አታቅም
ብቻ በሰው አቅም
አኛን አንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን
የጭምቶች ፍቅር
የአይናፈሮች ሀገር
ማገር
ሆነልኝ አለማወቋ
አታቅም እንጂ
ያሰግራል ሳቋ
ሀቋ
ከፊቷ ላይ ቅራኔ የለም
የኔ አለም
ባታቅም
ባላቅም
በሰው አቅም
እኔና እሷን እንደገባን
መፋቀር ነው ብለን
አንድ ጎጆ ገባን

By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍6626😁3
መለያየት ማለት

እየው ትላንትና ከትላንትም በስቲያ
ያዩሽ ሰዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ ዓለም ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው
ለእኔ እና ለአንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
ያለመተያየት መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ሕይወት
ዘወትር ዘወትር ምናልባት
ምናልባት እያለች የምትኖር ሕይወት
በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት
በተስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው
ልቤና ልቡናው ተጣብቋል በያቸው
እንጂ በእኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት

By Efrem seyoum

@getem
@getem
@paappii
38👍17😢8🔥1🎉1
መለየት

የለም ! የለም !
መለየት ሞት አይደለም
ሞትም መለየት አያክለው
መለየትም ሞትን አይመስለው
ትርጓሜያቸው ለየቅል ነው
አንቺም እኔም ጅረት ኾነን
ከራሳችን ምንጭ ፈልቀን
በራሳችን ፈለግ ፈስሰን
አገር ምድሩን አድርሰን
ሄደን ! ሄደን ! ሄደን ! ሄደን
ወርደን ! ወርደን ! ወርደን ! ወርደን !
ሞት በሚሉት ውቅያኖስ
አንድ ስንኾን ተዋሕደን
ተገናኘን 'ንጂ መች ጨርሰን ተለያየን
የለም ! የለም !
መራቅ መለየት አይደለም
ሰው በሰዎች ግዞት
ችግር መከራ ይዞት
አገር ቀዬውን ጥሎ
ስልቻውን በጫንቃው አዝሎ
ቅሉን ጨርቁን አንጠልጥሎ
ብቻውን ሄደ ብለው ሰፈርተኛው ተጃጅሎ
እርሱ በልቡ ሕንፃ በማይዘመው በማይፈርሰው
ከተጓዘ አኑሮ ሰው
አሁን ይኼ መለየት ነው ?
የለም የለም !
መለየት ይህ አይደለም
ትርጓሜያቸው እንቀይረው
ላ 'ንቺና ለ'ኔ ሌላ ነው
ከፊቴ ቁጭ ብለሽ
ከፊትሽ ቁጭ ብዬ
ክንድሽን ከአንገቴ ጥለሽ
ክንዴን ከአንገቴ ጥዬ
የምታወሪው ሳይገባኝ
የማወራሽ ሳይገባሽ
ለይስሙላ ጥርስሺ ሲሥቅ
ቻው ቻው ሲለኝ ቀልብሽ
ደህና ኹኚ ሲልሽ ዐይኔ
መለየት ይህ ነው ለ'ኔ፡፡

By እውቀቱ ስዩም

@getem
@getem
@paappii
52👍30😢9🔥6🎉2
የ'ግዜርን ነፍስ ሴጣን ልብን አድሏታል
ላይዋ ታቦት ታቿ ጣዖት ተዋርሷታል

ልጅ እያለች ስትድህ ገና ያወቀችዉ
አፏን ገና ስትፈታ በቀል የሚል ቃላቶች ነዉ ያወጣችዉ

በ።ቀ።ል
እልል...............

በእናቷ እቅፍ ገብታ በአንቀልባ ዉስጥ እያለች
ስለአባቷ መርዛማነት በጡጦ አርጋ ጠብተዋለች

ጥ።ላ።ቻ
እልል..................

እሹሩሩ አታዉቅ እናት
አባቷን ነዉ ምጠራላት

ህ።መ።ም
እልል...................

እልል
ዛሬ
ነፍስ አወቀች
ፍቅርን ሻተች
ምን ታደርገዉ ሴጣን ልብን ተዋርሳለች
የአዳም ፍጥረት ትጠላለች።


@Tizita21


@getem
@getem
@getem
31👍23😢7🤩2🔥1🎉1
ተራማጅ ነን እኛ!
.
በመንገዱ ኹሉ - እሾህ እየወጋው፣
ባዕድ እየኾነ - የከረመ ሥጋው፣
(እንዴትም ቢያሰጋው፣)
እየተገጫጨ፣
ደም እየተረጨ፣
ያብሮነት ሕልማችን - ቁስል ቢያስነክሰው፣
ተስፋ አይቆረጥም - በ’ርምጃና በሰው።

By abere ayalew

@getem
@getem
@paappii
👍3318🔥6
*
የሚበድላት ሰው
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።

የትኛውን ትመን?

መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!

ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።


by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
👍3521😢7🔥5
ተለያይቶ ማፍቀር
በህልም እንቆቅልሽ ዘላለም ማሽቀርቀር
ይህም ይቅር ፍቅሬ በኑሮ መታጠር
ታሰረ ፍቅራችን ልክ እንደዘራችን
ዘመመ ቀናችን

by almseged wolde

@getem
@getem
@getem
👍37😢128