ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
.............


በምን ሀቅ ጠየከኝ
በዕጣ ፋንታ ጽፈህ፤ከትከሻህ መስቀል
መዳን ያላቃተው፥ቃልህን ለመስቀል
ፈቅደህ ለሰየምከው፤ላኖርኩብህ ችንካር
በምን ሀቅ ጠይቀህ፤አጨኀኝ ለአሳር
ወዳ የተኛችና፤ፈቅዶ የዘሞተ
መዳን እየቻለ፤ለማዳን የሞተ
ደፈረኝ አትልም፤ቀሚሴን ገፈፈ
ገደለኝ ጥሰት ነው፤መሞቱን ለጻፈ
በዝሙት ሞግተኝ
ለረከሰች ነፍሴ፤ልማጸንህ ምላሽ
ፈቅዶ ለሚሰቀል፤ማን ሊሆነው ደራሽ
ይክደኛል ብለህ፤መዝነህ እምነቴን
ውሸቴን እያወክ፤ለሸሸህ እውነቴን
ሞቱኩ ብለህ አድነህ
ገለህኛል ብለህ፤የሰየምከኝ ሸንጎ
በምን ቃል ለሟገት
ከመስቀልህ ጀርባ፤ሀቄ ተሸሽጎ
በምን ልብ ልማልድህ፤በየቱ ልማጸን
ገዱ ለተጻፈ ገና ከማህጸን
ሳይወልዱት ለማይድን
ተወልዶ ለሚያድን
የተሰዋ ሀቄን፤የከተቡት እድል
በምን ሀቅ ጠየከኝ፤እዲያው ምን ብበድል


   By   @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
19👍11🔥3
ለምን ፣ ለምን ፣ ለምን?
(ሚካኤል አ)

(ጠዋት)

እኔ ያንቺ ባካኝ
ብርድ ፣ ቁር ሳይረታኝ
ወረቀት ሳይበቃኝ
ሳልሰስት ለቀለም
በፍቅርሽ ስታመም
እንዴት እንደከረምኩ
አንቺን ለማስረዳት
ግጥም መፃፍ ጀመርኩ።

ጻፍኩኝ ብዙ ፣ ብዙ
“ ስለ ዓይንሽ መዘዙ
ስለ ትንሽ ጣትሽ
ልክ እኔ ሳፈቅርሽ
ነክሳሽ ነበር ቢንቢ
ከጥፍርሽ ግርጌ…
ሰው መሆኔን ጠላሁ
ቢንቢነት ፈልጌ ።

ደግሞ ካንገትሽ ስር
ማርያም የሳመችሽ
ጥቁር ፣ አንድ … ነጥብ
በማርያም ቀናሁኝ
አንቺን መሳም ሳስብ።

ዝቅ አልኩኝ ለጥቆ
ሎሚ ተረከዝሽ
እንሶስላ ሞቆ
በነጠላ ጫማ
ባየው አሸብርቆ
ጫማ መሆን ፈለ’ኩ
ብረገጥ ከእግርሽ ስር
:
ሰው መሆን ሲደብር ! “

የሚል ስንኝ ቃላት
ጀምሬ በጠዋት
እንዲህ እንዲያ እያልኩኝ
በብዙ ብፅፍም

(ማት አመሻሽ ላይ )

“ግጥም አትወድም “
ብላ ነገረችኝ ፣ ጓደኛሽ በሀዘን
ከቅፅበት በኋላ
ባዶ ሆነ ፍቅርሽ ፣ ከልቤ ሲመዘን ።

ለምን ጠላሽ ቅኔ?
ለምን ጠላሽ ግጥም?
:
አንቺን አልፈልግም።

@getem
@getem
@getem
👍44😁2119🤩1
( የማራት ... )
===============

ብዘረግፈው ብሶቴን
ታፍኖ የኖረ ህማሜን
የአይኖቼ ቀላይ ተከፍቶ
ባዘንበው የዘመን ሸክሜን
ዕምባዬ ደራሽ ጎርፍ ሆኖ
በጠራረገው አዳሜን ...

የበቀል ጥፍሬ ተመዞ
ስስ ገጿን ስላልቧጭራት
የሀዘኔ ድርሳን ተነብቦ
በጸጸት ስላልጠፈራት

ከኃያሉ ከእግዚአብሔር በታች
ይችን ምድር በመታገሱ
ማን አለ እንደኔ የማራት ???

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
👍2820🔥2
ተታግለናል እጣ ፈንታን
አብሮ የመሆን  ተስፋ እንዳለው፥
እንዳይቆጭሽ ስንለያይ፡
ሞክረሻል
ሞክሪያለው!።

by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
50👍11🔥3😢3
Audio
9 ሰአት ስትቀጥረኝ

እንዴት ሆኜ ልጠብቅህ?

መልከ ዑራኤልን እየደረስኩ
ወይስ
መልከ ገፅህን እያሰብኩ?

ትዝታ ወልዴ(Tizita21)💕

@getem
@getem
36👍7🎉1
\ ዱ ባባ /

ሁለት ሰው ነበሩ...
በገንገን ወንዝ ዳር
በዱባባ ገጠር ፣
አንዱ እንዲፈቀር
ላንዱ የሚፈጠር ፣
አንዱ እንዲቆጠር
አንዱ የሚሰበር ፣
አንዱ እንዲራመድ
አንዱ ነፍስ የሚበር፣

ደሞ አንዱ አለ...
አንዱን ለመሆን
ከአንድ የሚሰፋ ፣
ሻማውን አቅልጦ
በስንጥር ክብሪት
በሰከንድ ሚጠፋ ፣
ላያወጣው ነገር
የሻርኩ ጉንጭ ላይ
ምራቅ የሚተፋ ፣

አንደኛዋ አለች
እናት ምትባል
ወላድ የምትባል ፣
በጉምዝ  አንቀልባ
ልጇን ከወንዝ ሰዳ
እሷ እየሳቀች
ባሏ ቤት ያነባል ፣
እነሱ እያሉ
ማች ልጇ ይረባል ፣

ዱ ባባ ብትልም
ልጇን ደራሽ ወስዶ
ከውሃ ስትጠማ ፣
ቀን ከፈረደ
በህፃን ትጠራለች
የአንዲት ገጠር ስሟ፣

ዳስ ቢሆንም ከቶ
ያገሩ ኩራቱ
ከአንድ እጅ ቢበልጥም ፣
ሁለት አለኝ ተብሎ
ተአምር ቢፈጠር
ልጅ ሞቱን አይሰጥም ፣

እዳ እና እፍርቱ
በጉምዟ ሲናሻ
በዱ'ባባ መሃል ፣
አንድ ህፃን አለ
ከገንገን ወንዝ ላይ
ሬሳው ይጮኻል፣

በቀጭን ታሪክ ስር
የሚጠና ስም ላይ
ገጠር እንዲባል ፣
መቀንጨር ነው መልሱ
ላልተወለደ ልጅ
መኖርም ያባባል፣

ሁለት ሚባል የለም
ሞትም አንድ ነው ስሙ፣
በገዛ ከንፈር የገዛ ጉንጭን
እንዴት ነው ምትስሙ

ለዚህች እናት ታዝኖ
በህፃኗ ሞት ላይ
ሁለት ስሜት የለም
ወይ አልቅስ ለስቃይ
ወይ ገርሞህ ሳቅ ይታይ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት 🦘

@getem
@getem
@getem
👍398😱2
(ድንገት)
አንዱን ወጣት አየሁት ፤

አይኔ እስኪፈቅድ ተከተልሁት ።

እያየሁት ... እየሄደ ...
እያየሁት ... እየሄደ ...
በሰው ማዕበል ተጋረደ ።
ጠፋ ፥
ተሰወረ ደብዛው ።

እንግዲህ ...
አዕምሯችን ታሪክ ፈጥሮ ካላንዛዛው
ወይ በምናብ ካላወዛው
ሰው መነሻው አይታወቅም
መጨረሻውም እንደዛው ።

By HAB HD

@getem
@getem
@paappii
36👍25🔥3👎2😱1
Audio
20👍6🔥3😢3👎1
አንዴ ብቻ ይድላኝ
አንዴ ብቻ ልረፍ
አንዴ ብቻ ልኑር
አንዴ ብቻ ልትረፍ
ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገው
እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማውቀው ።

By Habtamu Hadera

@getem
@getem
@getem
😢8846👍27😁3
ይቅርታዬ


ምን ቢሰማኝ ሰላም ወይ ጥል ምን ብኳትን ያለው ሊሆን ምን ብታመም ለማገግም ምን ብሰቃይ ዳግም ልስቅ ይታየኛል ፋኖሶቹ ከዐይኔ ሳይርቅ ይታየኛል ሙሉ ተስፋው እኔን ሊያደምቅ፤ ይታየኛል ከስሬ ነው ከልቤ ስር አድማስ ያለው፤ ከእግሮቹ ነኝ ከመዳፉ መቼም አርቅ ከበራፉ፤ እሱን ይዤ ያጣሁበት እሱን ብዬ ያፈርኩበት፤ ቀን አላውቅም ብጠይቁኝ ግን .......... ምስክር ነኝ ላመንኩበት ልንገራችሁ እጁን ያዙት ችላ ቢልም አትልቀቁት፤ ምክንያት አለው ሲፈትንም እያዳነኝ ዝም አልልም ።

By bline asefa

@getem
@getem
@getem
63👍26🤩3
Forwarded from վohaŋŋes Lawgaw
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
21👍8🔥3🎉3😱2🤩1
‘’ይሄስ ቀን ባለፈ
ፅልመት በገፈፈ
ጥለሽኝ ብትሄጂ
በወጣሽ ከቤቴ
ጉዷ ባለቤቴ …
እህህ እያልኩኝ
እንዲህ እያማጥሁኝ
አደባባይ መኃል
የማልናገረው …
ብዙ ህመም ነበረ
ደሜን ያመረረው ።’’
በማለት የፃፈ
አንድ ባል ነበረ !
‘ምን ሆነህ ነው? ‘ ስለው
እየተማረረ …
'ላንተ ከተናገርኩ
ስንቱን እንደቻልሁት
ይሄን ግጥም ታድያ
ለምን ነው የፃፍኩት ? '

ብሎ መለሰልኝ !

(ፈርቷት ነው መሰለኝ🙄)

#ሚካኤል

@getem
@getem
@getem
30👍14😁12
Forwarded from Sami Alemu
ጣዕሙን የሚያውቀው
(ሳሙኤል አለሙ)

እንደ ሌላው
እንደ ሌላው፤
ሰርክ...
ጉንጭሽ ጋ አይደረስም
ረ------ጅም ነው ኬላው።

እያዩት...
ያስውላል።
ዕሮብ ለት
እያዩት...
ያፆማል።
አርብ ዕለት

እንደ እኛው
እንደ እኛው፤
አንቺ...
ከቶ አልተፈጠርሽም
በቀን ስድስተኛው።

ለምን...?
አይባልም።
አይጠየቅም።
እንዴት...?
አትለውም።
አትከራከርም።

ከአፈሩም ፣ ከውኃውም
ከእስትንፋሱም ፣ ሌላም
አለው... ሌላም...ሌላም
ሌላም አለው ያከለበት፤
ወተቱን እንዳ---
ፈሰሰ---
---በት
ጉንጭሽን የሳመው።
ጣዕሙን የሚያቀው።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem
@getem
👍3919🔥1🤩1
...........


ኢትዮጵያዬ ልጄን ውለጅ
አንደወጣ ቀረ ከደጅ
አፈር ምሶ የቀበረ
ውለጅ ይላል እያረረ
ከገጠሩ
     ከመንደሩ
          ከጎዳና ከድንበሩ
ለዘላለም ለማይደላው
ለምን ? ልጄን ልጅሽ በላው!


By @mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍47😢2512🔥2
ህይወት ሞልታ አትሞላም
    ወይ ጎላ አትጎድል
ቁልፉ ስኬት ሲሆን
ውድቀት ዋነኛው ድል

ስቃይ እና ደስታ...ድሎት እና ችግር
       ምን ቢሆን ጣዕሙ
ሁሉም እርግፍ ይላል
       ባንቺ ከተሳሙ
"ደስታ ምንም ነው
ስቃይ አይታሰብም
ለእንደኔ እና እንዳንቺ
ብቻ ሳሚኝ አንቺ"

ብዬ ነበር ብዬ ነበር

ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እያየሁት ዛሬ ባይኔ
አትረሳህም እለዋለው
ለተጎዳው ባንቺ ጎኔ
የቀን ሳቄን ከሳቅሽ ጋር
እንዳልሳቅነው ተያይዘን
ሲመሽ ሲጠልቅ ሁሉም ነገር
ስንቱ ቀናት ደበዘዘን
አይኔ ይበቃል ለመረዳት
ባላወጣው የፍቅሬን ቃል
እንደወደድኩሽ ነው...
ድፍን ሐገር ያውቃል

ውድቀት ቢሆን ሲመሽ ጊዜው
ይበቃኛል ለቀኑ ዕድል
ህይወት እንደዚህ ነች
ወይ ሞልታ አትሞላም
ወይ ጎላ አትጎድል።

አሳየሽኝ ስቃይ ድሉን
ከዚም ከዛም እያጣቀሽ
ተኮሳትረሽ ያው ወርቅ ነሽ
ትገያለሽ ደግሞ ስቀሽ

አስረዳሁሽ በአይን ወሬ
ልብሽ ከቶ ምኑን ነቃ
አንቺም ሂጂ ይለይልኝ
እኔም ደግሞ ልርሳሽ በቃ።


ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍316😢3🤩2
የደስታ ሰማይ - በር መክፈቻ፣
ይገኛል መስሎሽ - በመብረር ብቻ፣

በተዋስሽው ክንፍ - ሽቅብ ስትመጥቂ፣
የደመና ሆድ ስትሰነጥቂ ፣
(ድንገት ከአየር ላይ)
በባለ ክንፉ - ስትነጠቂ፥

በማይገመት - በማይጠበቅ ፣
በእድል ጨፈቃ - በጊዜ ለበቅ፣
በጊዜ ለበቅ - በማይመከት፣
ስትገረፊ -
ደንግጠን ሽቅብ - ስንመለከት፣
ስንመለከት የማታ ማታ፥
ያዘልሽው ላባ -
የአንቺ እንዳልሆነ - ትዝ ያለሽ ለታ፥

ወዮ የዛን 'ለት - ለመንደራችን፤
ወዮ ለመሬት፥
ወዮ ለጆሮ - ወዮ ለዐይናችን፤

By Michael Minassie

@getem
@getem
@paappii
👍2018🔥2
..........


በመዳፌ ጠፈር ዳሳሽ
በኣይኖቼ ህዋን አሳሽ
አፈር ድንጋዩን መርማሪ
ፀሀይን በጥፊ ኣብራሪ
ጨረቃን በኩርኩም ቀባሪ
በውርቅያኖስ የምግሞጠሞጥ
ከንፋስ እጥፍ የምሮጥ
ጉም ዘጋኝ በመዳፌ
በኖህ መርከብ ቀዝፌ
ከጥፋት ውሀ ተርፌ
ቅንጥብ ዘንባባ ቀጥፌ
ኣዲስ ምዕራፍ የማበስር
ብኩርናዬን የማልሸጥ በምስር
በኮከብ ወደም ምጫወት
የማድር ከኣብርሀም ቤት
እንግዳ ያልሆንኩኝ እንግዳ
የሩቅ ዘመድ የቅርብ ባዳ
ከጲላጦስ ሸንጎ የምፋረድ
በደመና ይምራመድ
   ከሰባሰገሎች ኣንዱ
ወርቅ እጣን ከርቤ የገበረ
ንጉሱን ከበረት ኣይቶ እረኛውን ያከበረ
ከድንጋይ ከህጻናት ጋር
ሆሳእና ብሎ የዘመረ
እኔ ነኝ ብኩኑ ባሪያህ የጥበብህ ማሳያ
የሀዲስ ኪዳን ነብይ የኦሪት ሀዋርያ
   በሀሳቤ እሩቅ ተጎዝ
ባካሌ ከቅርብ የማድር
ቅንጣት እምነት የጎደለኝ
የሚነቅል የተራራን ስር
እንኳንስ በደመና ላይ
በጠፈር ሰማይ ምድሩ
ሸክም ሆኖ የከበደኝ
የኣካሌ ክፋይ ኣፈሩ
ጉም መጨበጥ የምመኝ
የእጄን መና ለቅቄ
በሀሳብ ከኣብርሀም ያደርኩ
ከመንገድ መሀል ወድቄ
በኮከብ ወደሙ ቀርቶ
ጠጠር ማንሳት ያቃተኝ
ፍቅር መስቀል ይመስል
በየቀን የሚያቃትተኝ
አንድ ቀን ጠግቦ ለማደር
ብኩርናዬን የምሰዋ
ባገሬ መኖር ያቃተኝ
እንኳን በጠፈር ህዋ
ኣንድ ጉንጭ ውሀ የምለምን
ውርቂያኖስ መሉ ተፍቼ
ከሰገባ የማድር
ከስልክ እንጨት ስር ተኝቼ
ከጥፋት ውሀ ታዳሚ
ወይ ኣልድን ወይ ሰጥሜ ኣልሞት
እስትንፋስ አልባ የሆነ
የምኖሮ ትርጉም ኣልባ ህይወት
የኖህም መርከብ የራቀኝ
ለምግብ ጥንብ ኣንሳ የነቀኝ
መሲህ ፍለጋ ወጥቼ
ነብይ ይዜ የተመለስኩ
ሰባሰገል ተብዬ
ከሄሮድስ ጭፍሮች ያበርኩ
እንኳንስ ፀሀይ በጥፊ
ውቧን ጨረቃ በኩርኩም
ዝንብ ሽ ማለት ያቃተኝ
ሀሳቤ ብናኝ እንደ ጉም
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
በህልሜ ሁሌ ከደጅህ
ስነቃ ከተራራው ስር
ደራሽ በሌለበት ምድር
በሲቃ ድምጽ የምጣራ
ከመብረቅም በሚያስፈራ
የቅንጣት እምነቴ ተራራ ኣነቅል ቢለኝ
ተራራ ያሸከመኝ
ከገነት ያላደርኩ ከሲኦል ያልገባው
መሲሁን ጠቋሚ ኣንድ ኮከብ ያጣው
ወይ ድኜ ኣልድን ከስሜ አልጠፋ
ከፈራጅ ችሎት ዳኛ የማስከፋ
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
ወድቄ ያለው ከግርህ
ፍቅርህን የምሻ ልቤን ኣሽችቼ
ልክ እንደ ኣይሁድ ጎኑን ወግቼ
ከእቅፍህ ውስጥ ማደር የምመኝ
ብኩኑ ልጅህ
ባሪያህ እኔ ነኝ


   By  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3216😱5🔥3
ድልድይ ቢሆን ልብህ
ወደ ህይወት መሄጃ
ሞቼ አለመቅረቴን
መነሳቴን እንጃ
ማሻገርህን ያየ
ቢመሰክርም ሰው
ትረፍ ለሌላ ሟች
እኔ እንደሁ ሳይህ ነው
የምትፈራርሰው

By ዘማርቆስ

@getem
@getem
@paappii
22👍16🔥2
የዚች አለም ችግር
     ሁሌም ወደኋላ
የተራበው ቀርቶ
     የጠገበው በላ
እንዲህ ነው ምሳሌው
ሲተነተን ፍቺው
አንቺም የሌላ ሰው
እኔም ደግሞ ያንቺው

አወይ የኔ ህይወት
አወይ የኔ ተድላ
የማፈቅርሽ እኔ
የሚበላሽ ሌላ

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍3911😁9🔥5😱1🤩1
👍74🔥2😱1