ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
.................


ኣላወቅሽም እንጂ፤ኣስቤሽ ነበረ
ሚስክን ልቤ የፍጥኝ፤ባንቺ እንደታሰረ
ላዘን ለእንጉርጉሮ፤ካረቄ ቤት ገብቶ
ንዴቱን ማብረጃ፤ትንሽ ተጎንጭቶ
ገና እንደሰከረ፤ስምሽን እንደጠራ
ኣይኔን ህመም ሞልቶት፤በእንባ ላያባራ
እቅፍሽን ለምዶ፤ከትቦ ስር ሲያድር
ኣላወቅሽም እንጂ፤ብታውቂማ ፍቅር
እቅፍ ድግፍ ኣርገሽ፤ኣዝነሽ በመውደቄ
ትንባሆ ሲጃራ፤መጠጥ አና ኣረቄ
በህጻን ልጅ ኩርፊያ፤ንዴትና ቁጣ
እንደምትገዝቺኝ፤ዳግም እንዳልጠጣ
ኣቅ ነበር ብትወጂኝ፤ኣጨክኝም በኔ
ግና እንዳታይኝ፤ጋረደሽ ኩነኔ
ፍቅርዬ ውድዬ፤ምናምን ምናምን
ከእቅፌ አንዳትወጪ፤ስማጸን ስለምን
ኣንቺን ማባበያ፤እንቡጥ ጽገሬዳ
መኖሪያ እንኳን የለኝ፤የማድረው ከሜዳ
የምሰጠው ባይኖር፤ሀብት እንኳ ቢጎለኝ
ከኔ ጋራ ሁኚ፤ለ ነገ አምላክ ኣለኝ
ብዬ ተማልጄ፤ችዬ እንዳላስቀራት
የማታውቀው ነገ፤ዛሬዋን ደለላት
.
..
...
ኣላወቅሽም እንጂ
አንቺን ኣጣው ብዬ፤ሳለቅስ ሳላዝን
ምን ጎሎኝ ነው ብዬ፤እራሴን ስመዝን
ከትቦ ስር ሀኜ፤የማየው ኣዲስ ጀንበር
ላንቺ የሚታይሽ፤ለካስ እሱ ነበር
ከትቦ ስር ሆኖ፤ማን ውበት ያደንቃል
ለተራበ ኣንጀት፤ጀንበር ሸከሰም እንጂ
መች ጌጥ ሆኖ ያቃል
ፍቅራችን ቢማርክ፤እንደ እንቡጥ ኣበባ
ቋንቋችን ኣይገጥም፤በምን እንግባባ
ከጎዳና ወድቃ፤ለምትማቅቅ ነፍሴ
ምን ያለ ምስጋና፤የፍቅር ውዳሴ
ቁስሌን ላያድነው፤ጠባሳዬን ላይሽር
ኣንቺን ኣጣሁ ብዬ፤እድሌን ሳማርር
ደርሶ ላያድነኝ፤ቁስሌን ላይፈውሰው
ከንፈር መጠጠልኝ፤ሳለቅስ የሚያየኝ ሰው
.
..
...
ኣላወቅሽም እንጂ፤ብታቂም ባታቂም
መኖሬ ኣስጨንቆሽ፤ስለኔ ኣጠይቂም
መውደቅ የለመደ፤መነሳት ይፈራል
ተጎዝ ያፈቀረ፤ሲከተል ይኖራል
ከመኖር ላይ ጎሎ፤የድራሻውን ያጣ
በውሲኪ በታጠብ፤ኣሬቄ ቢጠጣ
መውደዴን ታይ ብሎ፤ከደጇ ቢወድቅም
የሰካራም ፍቅር፤በመጠጥ ኣይለቅም

       @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍4111🔥11😢1
..............


የጸነሽው ባይወለድ
ያዳፈንሽው ጭሶ ባይነድ
ውጥናችን ባይሳካ
ሞት ደጃችን ሲያመሰኳ
ህይወት ሸክሞ ሲቀልልን
የዘራነው ሳይበቅልልን
ሲራገፍ ስጋ ከገላሽ
በስብሰሽ ምስጥ ሲበላሸ
የት እንደምቴጅ ባላቅም
ወደድኩሽ በሙታን ኣቅም
የሚኖር ማፍቀር ኣልሻም፤የማይቀልጥ የምድር ሻማ
ቢኩላት ኣያምርባትም፤ብጥስጣሽ ጨርቅና ሸማ
ኣፈር ነው የሷ ገላ ጌጥ፤ኣታቅም ተውባ በኩል
ኣትሻም ማድመቂያ ብረት፤ካንገቷ ከጆቿ በኩል
ጭንጋፍ ነው ቢሉም፤ተያቸው ለሷ ሞትን ተመኘ
ስታለቅስ ሳያስታምማት፤ስተለይ ጎኗ ተገኘ
ባቀው ነው የሀዘንሽን ጥግ፤በቃላት ኣይታበስም
ምን ያህል እንባ ቢፈስስ፤በጊዜ ኣይታፈስም
ቢገባኝ ነው መጠኑ፤ማቅሽን ብመቀምቀው
ልትሞት ነው ሲሉ የምስቀው
ውጥናችን ባይሳካ፤የጸነሽው ጭነጋፍ ሲቀር
ነገ ከሞትሽ እንዳራ፤ነገ ከሞትሽ እንፋቀር

     @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍1811🔥1
¹
ገና ወጣት ንፁህ ነበር .....
ያለ ግብሩ ወነጀሉት ፤
ይግባኝ ቢልም አልገባቸው
ግራ ቀኝ ሳይሉ ገ ደ ሉት ።
ከመሬት አጋድመው
አፈ ሙዝ ደግነው እየፎከሩበት
እሳት ያዘለ እርሳስ አርከፈከፉበት ።
²
የእሱስ ይሁን አንዴ ሄደ
እንደ ንፋስ ....ነፍሶ (ደርሶ)
አተረፈው ከሕይወቱ
(ከስቃይ አዳነው ሞቱ !)
ይብላኝ ለኗሪ እናቱ ።
³
ያኔ ፊትለፊቷ....
ልጇን በመስቀል ላይ የቸነከሩት ለት
ያሰረችበትን የወላድ አንጀቷን
አላቀበለቻት ማርያም መቀነቷን ።
ውስጥ ውስጡን ተከፍታ በሀዘን ዝላለች
ስዕሏ ፊት ቆማ እንዲህ ትላታለች

“ለደረሰበት ምኑ ሊነገር ?
ታውቂው የለም ወይ የልጅን ነገር !?
የልጅን ነገር ታውቂው የለም ወይ ?
አይተሽ የለም ወይ?
ወስደው ሲያዳፉት
አስረው ሲገርፉት
በምስማር ፊትሽ ሲቸነክሩት
አካል ገላውን በደም ሲነክሩት
አይተሽ የለም ወይ?
ታመሽ የለም ወይ?
.
.
.
«ያንቺስ ተነስቷል በሦስት ቀኑ
የኔ ግን ይሄው ስንት ዘመኑ
በአካል በስጋ መች ይገለጣል
ትዝታው ብቻ በሌት ይመጣል ።
እስኪ ንገሪኝ ?
እነዛ አይሁዶች አንቺን
እንደ
ኔ በድለውሻል?
ልጅሽን ገድለው
አታልቅሽ ብለው
ከልክለውሻል?»

የታወቀ ነው.....
ደስታ ቢታሰር በሳቅ ያመልጣል
ሀዘን ፈንቅሎ በእንባ ይወጣል
(እሷ ትላለች ....)
«አልበቃ ብሎ ልጄን የነሱኝ
ባዋጅ በሕጉ እየመለሱኝ
እንደው በወጉ አላስለቀሱኝ »

ብዙ ቀን ሄዶ....ብዙ ቀን አልፎ
ከሕይወት ዛፍ ላይ ዘመን ረግፎ
ጎረቤቶቿ አብረው ሚኖሩ
በየሰርጉ ዳስ በየማ
በሩ
ድግስ ሲጠሩ
ትታደማለች ፤
እንደ ተፅናና ፈገግ ትላለች ።
ሀዘኗ ሳይሽር አውልቃው ማቋን ፤
ዕምባ ዕምባ ይላል ቢቀምሱት ሳቋን ።
እየዋሸች ነው እያስመሰለች
"እንደ ሚኖሩት ልኑር" እያለች ።
(አልተፅናናችም )

ተፅናናች እንዴ?
ፀኣዳ ቢሆን ከላይ ቀሚሷ
የሀዘን ማቋን ካልጣለች ነፍሷ
ውስጧ እንዳዘነ....
ልቧ ተከፍቶ ዘቅዝቆ ጥለት
‘ሞቶ መኖር’ ነው ....
“መፅናናት” ማለት ?
------
@Bekalushumye
ነሃሴ 23 — 2016 ዓም

@getem
@getem
@getem
👍3522😢15🔥3🎉1
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ
ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣
ተጨነቀች ወዲያው ደሞ
ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣

ትፈጥናለች ለማግኜት
ልቤን አርጋው የቀበሌ  ፣
ታምር አርጋ ቆጠረችው
በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣

መቸኮልን አስለምዳኝ
ተጣድፎ ዝግታየን
አቻኩላ አገባችኝ
እይ ስትል እድሜየን ፣


ተቻኩላ አስለምዳኝ
ረጋ ያለ አረማመድ  ፣
ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ
ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@getem
34👍18😱3👎2🎉1
ይመስለኝ ነበር
ፍቅር አዳልጦት ውድቀት ያነቀው
መቼም የማይስቅ ሞትም ቢንቀው
ይመስለኝ ነበር
ሚወደውን ያጣ ትንፋሹ የሚርቅ
እንባ ሲቀለብ ማግኘትን 'ሚንቅ
ይመስለኝ ነበር
ዳግም ማያብብ አንዴ የረገፈ
እምነት ተስፋውን ቆሞ ያሰየፈ
ተሳስቻለሁ
ተጸጽቻለሁ
መምሰል መሆን ላይሆን ባ'ጉል ስጋት ቀንበር
መክሰምን ፍራቻ ወድቄ ለካ ነበር

ይለይልኝ ዘንድ
ትተሽኝ ስትቀዝፊ
ጥለሽኝ ስትከንፊ

ጽልመት ሳቅ አንጣፊ
ፍም እንባ አርጋፊ
እልህ ዘር አብቃይ
ሰው ሸሽቶ ጣይ
ልሆን ለዘላለም ራሴን ሳሰለጥን
አንሽዬ አንሺ ላከ ውድቀቴን የሚጥል
ተነሳሁ ተራግፌ
ተስፋን ታቅፌ

እንኳን ተውሽኝ እንኳን ጣልሽኝ
ጥሩ እጅ ላይ ገፍተሽ አኖርሽኝ

#ኤልዳን
tiktok ... ldan291

@getem
@getem
@getem
19👍8🔥1🤩1
እሺ ብያለሁኝ

ትዳር ለመመስረት አምኜህ አምነኸኝ
መርጠኸኝ ከሌላ እኔን ስትጠይቀኝ
የወግ ማዕረጉን የባህል ስርአቱን
ጠብቀህ ጠይቀህ ቤትህ ልታስገባኝ
ሚስትህ ልታደርገኝ አንተ ስጠይቀኝ
እኔም በተራዬ እሺ ብያለሁኝ
ተቀብያለሁኝ

@getem
@getem
@getem
@Eltene937
👍2711🔥2🎉2
...
ምን እንደምናፍቅ
አላውቅም አያውቅም የልቤ ዳርቻ
መሸት ሲል ቀኑ ደንገዝ ሲል ምሽት
ናፍቃለሁ ናፍቆት ጠብቃለሁ ብቻ

By Sirak Wondemu

@getem
@getem
@paappii
24👍9😢4🔥2
..............


ሠማዩም መዝገብ ነው፤ምድርም ብርሀና
ገልጦ ላነበበው፤በኣይነ ልቦና
መዝገብ ነው ሠማይ፤ያልተነበበ
በፈራጅ ሚዛን የተከተበ
ብርሀና ነው ምድር
ንፁህ የበግ ቆዳ፤የተፈጥሮ ጽፈት
ስርዝ ድልዝ ያለው
ፍጹም ልክ ያልሆነ፤ፍጹምም ስህተት
ንባብ ነው መብረቁ፤የእንስሳቱ ድምፀት
የባህር የሸለቆው፤የኣዋፋቱ ዜማ
ለምጽ የሚፈው
ልብ የሚሰረስር፤በነፍስ የሚሰማ
የሚፈካው ኣበባ፤ደርቆ የጠወለገው
ስንዴ እንክርዳዱ
እንደ ኣዲስ ሊወለድ፤ወድቆ የበሰበሰው
የሀይቁ ፀጥታ፤የማዕበል ጩኀት
ቅንጣት እምነትና
ተራራን ያሰረው፤የተፈጥሮ እውነት
የዛፍ የቅጠሉ
የእሳት ነበልባሉ
መዝገብ ነው ይሄ ሁሉ
ፅህፈት ነው ይሄ ሁሉ
ገልጦ ላለበበው፤በኣይነ ልቦና
ሠማይም መዝገብ ነው
ምድርም ብርሀና
.
....
መጸሀፍ ነው ኑሮ፤መጸሀፍ ነው ህይወት
ነዋሪዋች በደም፤ጽፈው የከተቡት
በመስፈሪያው መዝገብ፤በህቡ የተፃፈ
ከትእዛዝህ ኣልፎ፤ሚዛን ያተረፈ
መፀሀፍ ነው ህይወት፤መፀሀፍ ነው ኑሮ
ንባብ ነው ፈገግታው፤ንባብ ነው እሮሮ
የሚስቀው ጥርስ፤ደም ተጎንጭቶ
የሚነባው ኣይን፤በሀዘን ታክቶ
ይህ ሁሉ ንባብ፤ይሄም ጽህፈት ነው
ይህ ሁሉ ኑሮ፤ይሄም ህይወት ነው
ያልደረስንበት እረቂቅ ምስጢር
ስውር ጽህፈት
ኑሮ ነው መጸሀፍ፤ህይወት ነው ህርመት
.
....
ግና ግና ግና
ይሄን ሁሉ ጽህፈት፤ገብቶት ያነበበ
ኣንዳች ጠቢብ ቢኖር፤በእውቀት ያበበ
እንዲ ነበር ቃሉ፤የሚል የሚናገር
መስፈርያ ሆኛለው፤ከሰፋሪዋች ሀገር
የመለስከው ሰይፍ፤ከሰገባው ኣምልጦ
ዲዳ ህዝብ ኣፍርቷል፤መኣት ጆሮ ቆርጦ
ታፈልገናለህ ተወለድ ከንደገና
የእዳ ደብዳቤያችን፤እጅግ በዝቷልና
እግዚኦ እግዚኦ
አድን ህዝበከ
ወባርክ ርስተከ


By @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍12🔥116
-----------ድንገት-----------
ድንገት ሳላስበው፣ ልቤ ዘልቆ ገብቶ፣
ጣፋጭ በሆኑ ቃላት ፣እራሱ ወትውቶ፣
ዓለምን እንደ አዲስ ፣ለማየት ሚረዳ፣
ፍቅር መነፅር እንደሆነ እያስረዳ፣
ንፍገት የለሽ ፍቅሩን ፣በልቤ አነጓግዶ፣
ድንገት ተሰወረ፣ ክፉ አስለምዶ።

እኔ ምልህ ፍቅሬ...
እንደው ምን ገጥሞክ ነው? ከዐይኔ የራቅከው
ታስባለች ሳትል ከእኔ የሸሸኸው?

በሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@getem
👍4415👎5🔥2🎉1
ዮኒ
    ኣታን @yonatoz


@getem
@getem
@getem
22👍12🔥1
................


ኣኩኩሉ ሲባል
እንደበቅ ደሞ
ሰው ከማይደርስበት፤መርጠን ስውር ቦታ
ከኑሮ እንቆቅልሽ፤ከፊደል ገበታ
ገሽሽ ግሳንግሱን፤የህይወትን እድፍ
ቀን ኣልፎ ከገላሽ፤ጠባሳ ለሚጽፍ
ኣልነጋም እያልን፤ባይጠይቁን እንኳን
መደበቂያ እንፈልግ፤መሸሸጊያ ድንኳን
መፈለግ ሲረክስ፤ፈላጊ ሲረሳ
ከተሸሸገበት ወድቆ ባይነሳ
ኣልነጋም ይለዋል፤በምስጋና ቅኔ
ደጅህ ተደብቆ፤ከኣለም ምናኔ
ሌትን ተቆራምተን፤ንቀነው ንጋቱን
ማስታመሚያ ሆነሽ፤ያኩኩሉ ህይወቱን
ይዞሽ ለመደበቅ፤ጭዋታ መረጠ
ኣልነጋም እያለ፤ሊሸሸግ እሮጠ
በቀንሽ ተዳራ፤ለሊትሽ ቢመስል
ቀለም ኣልባ ብእር፤ሌጣ እንደሚስል
ጨለማን ያማጠ፤ብርሀን አይወልድም
ንጋቷን የጠላ፤ተስፋዋን ኣይወድም
የኣኩኩሉ ትውልድ፤ያልነጋም ኣፍቃሪ
ነግቶ ላትፈልገው፤ከደጅህ ኣዳሪ
ጭዋታ ነው ብሎ፤በእንባው እየሳቀ
ኣልነጋም እያለ፤ደጅህ ተደበቀ


By @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍1513
ቋጠሮሽ


ዞሮ ዞሮ ከሀገር   ዞሬ ዞሬ ካንቺ
ካንቺ ሚስበኝን  ቋጠሮሽን ፍቺ

ከተሰደዱበት  ሀገር ቢመለሱ
እንደው ተጓዙ እንጂ  ድሮስ መች ደረሱ

እንደ አፈሯ ሽታ  እትብቴ ከተቀበረባት እኩል
እረቄ ከሄድኩት  ትጎትተኛለች በትዝታ በኩል

ሀገርስ እናት ነች  ብወድቅ ባላገግም
አልጋ ባትሰጠኝ   በረንዳን አትነፍግም

ያንቺ ግን ጥላ ነው  ወደ ፀሀይ ስዞር
  ከኋላ ይወድቃል
ተፈጥሮው ነውና  ስርቀው ይቀርባል
ስቀርበው ይርቃል

የኔ ፍላጎቴ  መራቅ ብቻ ካንቺ
በቃ ልሂድበት  ቋጠሮሽን ፍቺ

የታመመን ትናንት  ዛሬ ባማርርም
መድረስ ከሌለበት  ነገን አልገብርም


by kerim
@poem2513

@getem
@getem
@getem
26👍26😱1🎉1
-----------ፍቅር------------

እንዲያውቀው
መውደዴ ጥግ የለው፣ ሁሌ ናፍቃለሁ
ቀን በሀሳቤ ፣ሌሊት ደሞ በህልሜ እሱን አስባለሁ
ሱስ ሆኖብኝ፣ መላ አጥቻለሁ
እያሉ መጃጃል፣ በቅርቡ ትቻለሁ

አለ አይደል...
ቢተውት የማይተው፣ ቢርቁት የማይርቅ
ፍቅር ሚባል ልክፍት፣ ከሰዎች እሚያርቅ
ትቼዋለሁ፣ ፍቅራችን አብቅቷል
እያልኩ ስወስን፣ ደሞ ሳብሰለስል
ይህ ጅሉ ልቤ ፣እንዲ ይሟገታል
ያፈቅርሻል ብሎ ፣ሊያሞኘኝ ይቃጣል።

ስማኝ ልቤ አፍቃሪማ..

ቢሸሹት የማይሸሽ ፣ቢተውት የማይተው፣
የፍቅር ዋጋ፣ በእርግጥም የገባው፣
ንጭንጭ ንትርክ ፣ክፋት እማይመስለው፣
ለደስታ ስኬትህ ፣እራሱን ለጋስ ነው።

ሳምሪ የዝኑ ልጅ

@getem
@getem
@getem
33👍15🔥3🤩2
..............


ከማበዴ በፊት፤ኣንድ ቃል ልንገርሽ
ላንቺ ብዬ ኣይደለም፤ጨርቅ የምቀድልሽ
ስለተውሺኝ ብዬ
መራቅ መገፋቴን፤መቻል ስላቃተኝ
ፍቅርሽ እንደ ቅዘት፤ስለሚያቃትተኝ
ከምቀደው ልብሴ፤ከገላዬ ካለው
ትዝታሽ ብቻ ነው፤በውብ የተሳለው
ጠረንሽ ነው ያለ፤ከገላ ከጨርቄ
የሄድሽ ቀን ጣልኩት፤ሀፍረቴን ኣውልቄ
    ከማበዴ በፊት
ኣንድ ቃል ለናገር፤ፍቅርዬ ባንቺ ፊት
  ኡ ኡ ብዬ ብጮህ
እንዳትጠብቂ ከጬኀቴ መሀል
ከቶም ስምሽ የለም
የኔ ውድ የኔ ኣለም
ለኔ ኣይነቱ ኣፍቃሪ
እብደት ጤንነት ነው ከእስሩ መፈቻ
ኣንቺን አንቺን ብቻ
ማለቱን እረስቶ
ፍቅርን እንደጨርቅ፤ከገላው ለይቶ
     ከገረባው መሀል
ተግቶ ሊፈልጋት፤የጠፋችው ፍቅሩን
ቅጠሏ ኣመርቅኖ
ግንዷ የበከለ ሰማይና ምድሩን
    ቅጠሏ ፍቅር ነው፤ሙትን የሚባብል
ግንዷ ደሞ ግፍሽ፤በቁም የሚገድል
  ለዚህ ይሆን ? እብድ ሁሉ
ገረባ የሚያነሳ፤ገረባ የሚጥለው
የጠፋችው ፍቅሩን፤ስለምትመስለው
       እናም ፍቅርዬ
    ላብድ ስለሆነ እንዳትጸጸቺ
ኣንቺን ፍለጋ ነው፤የማበዴ ፍቺ
ከሰው መሀል ባጣሽ፤ካትሮንስ ባትገኚ
ኣብጄ ፈለኩሽ፤ገረባ ስትሆኚ


      By  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
30👍24😢8👎6🤩3🔥2
የቱ ፍቅሬ ስቦህ እንደምንፈታኸኝ
እኔኮ ብኩንነኝ
አንተ ስትሰቀል ከዐይሁድ ጋር የምገኝ
እኔኮ ምንም ነኝ ተራ የህመም ሰው
ጌታዬ እንድትምረኝ ምክንያትህ ምንድነው ?
በከሀሊነትህ ብቆምም የኔ አሳር
ከደግነት ደጅህ የቆረጥኩኝ ምሳር
ብቶደኝ ብትምረኝ እኔ ምን ታድዬ
ከሰቀሉህ ጋር ልስቀልህ ጌታዬ
እንዲህ ነኝ መፃጉ ውለታ ምረሳ
ስወድህ እንድኖር ህመሜን አትፈውስ
ቀንበሬን አታንሳ ።
ስንኩር ነው የኔ እግር ለሀሰት ያጋደለ
ጠማማ ነው ልቤ ፍቅርህን የጣለ
ቀጤማ ነው እጄ ክፋት ያቃጠለው
ያዙት ያን ክርስቶስ ብሎ ሚጠቁመው
እውር ነው ብሌኔ እያየ ሚከዳ
ከደግነት ኩሬ መዐት የሚቀዳ
እዳ ነኝ ለራሴ እዳ ነኝ ለአለም
ሲጀመር ነው የካድኩህ ሲፈፀም አይደለም
አልጋን ተሸከሚ ስትለኝ የኔ አባት
ልቤን አናተበው የመራመድ ክፋት
አትማረኝ መዳኑ አትማረኝ ጌታዬ
አልጋን መሸከሜ ለኔ መጥፋት
እንጂ መፈወስ አይደለም
እጆቼ ላንቺ ነው ትለኝም አነበረም
እናማ
ይቅር በለኝ እና ከመቅደስህ ልፅና
እጆችህን ስጠኝ ብርታት ሁነኝና።

By bline asefa


@getem
@getem
@getem
45👍26🔥3🎉2👎1🤩1
ሁሉም እያነሳ
ብረት እና ዘገር
ሰው ህግን ሲተካ
ሂደት እርቃን ሲቀር
ውጊያው ሁለት ሲሆን
በነፍስና ፣ ሥጋ
ምሽት አይኑን ከድኖ
ቀንቶለት ያነጋ
ይቅረብልን ባዋጅ
ይዘገብ ፣ ይነገር ...
ማሸነፍ ነውና
ሰላም ውሎ ማደር!!

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
32👍25🔥7
............


መለያየት ሞት ነው፤ብላኝ እንዳልነበር
ይኀው ተለያየን፤ሞታ ስትቀበር
አፈር ስትለብስ፤መሬት ሲደብቃት
የኣዳም ዘር እዳ፤ከቅፌ ሲነጥቃት
ጩኀት ለቅሶ ዋይታ፤ኣጅቧት ስጠፋ
ነፍስ ይማር የሚል ቃል፤ጆሮ ላይ ሲከፋ
ሞታ ስትቀበር
መለያየት ሞት ነው
ሞት መለያየት ነው
ብላኝ እንዳልነበር
ይኀው ተለየቺኝ፤ኣፈር ስትለብስ
እንባም ኣይበቃኝም፤ላንቺ በምን ላልቅስ
የቀብርሽ እለት
በልብሰተ ክህኖ፤ገጡን ያሳመረ
ጠይም ደርባባ ቄስ፤
ስለ ሞትሽ ትርጉም፤እንዲ ተናገረ
ተው ኣይለቀስም
ምን ሰራህ ተብሎ እግዜር ይወቀሳል
ኣፈር የተጫማ
ሊበሰብስ እንጂ፤ተጉዞ የት ይደርሳል
ህይው ልትሆን እንጂ
ከፈራሽ ገላዋ፤ነፍሷን የነጠቀ
ያልሞተ ኣያፈራም፤ዘር ሆኖ ያልወደቀ
ትድን እደሆነ
ተዝካሯን ኣውጡላት፤ነድያን መግቡ
እሱ እንደው ሩህሩህ፤ኣይጨክንም ልቡ
ብለው ቢናገሩ
ከበደኝ ቀብሩ
ኣንቺስ ፍቅርዬ
መለያየት ሞት ነው፤ብለሺኝ ኣልነበር
በመሞት ከሆነ፤ህይወት የሚጀመር
ውልደትሽ ምን ነበር?
ከኔ ተለይተሽ
ገነት ብትገቢ፤ብትቆሚ በቀኙ
ያንቺን እጣ ማግኘት፤ሙታን እዲመኙ
ውይ ሲኦል ተጥለሽ፤እልፍ ብትቀጪ
ለየለት ሀጥያትሽ፤ፀፀት ብታምጪ
ከልብሽ ላይ ችለው፤እኔን ላያወጡ
ስፍር ኣልባ ጋኔል፤ባንቺ ላይ ቢቆጡ
ብታማትቢ እንኳ
የማይጠፋ ሴጣን፤ከሲኦል ቢገጥምሽ
ኣውቃለሁ ፍቅርዬ
የሀጥያት ሰንሰለት፤እንደማይገድብሽ
ስለዚህ ለኣንቺ
ፍጹም እንቀይረው፤የመሞትን ፍቺ
ኣንቺ እንደነገርሺኝ፤እኔም እንደማቀው
ካሀዘናቸው ብዛት፤ባይቀብሩሽም ስቀው
ስለመለየትሽ እንባ አሰያፈሰሱ
መኣት ለቀስተኞች፤ከለቅሶሽ ደረሱ
እኔም ከንቱ ኣፍቃሪሽ
ሞት ህያውነት ነው፤ብዬ እያመንኩኝ
ህያው ሆኜ እንኳ፤ካንቺ የተነጠልኩኝ
ሳስስ ስፈልገው፤የሞትሽን ትርጉም
ከእንባ ላይ ኣየሁት፤የሚተን እንደ ጉም

  By  @Mad12titan

@getem
@getem
@getem
👍3823😢7🔥3🎉2
እልልታ
ጭብጨባ
ከአውደ ምህረቱ ተነስቶ ይነፍሳል፤
የሰማእቷ ታ'ምር እንደ ጉድ ይወሳል።

"ሰምታኛለች እናቴ..."
"ታውቃለች አርሴማ..."
ክብሯን የሚመጥን
ይገባል ስለት - ጧፍ፣ ጥላ፣ ብር፣ ሻማ።

ሰው ይጸልያል
ሰው ይለምናል ክፍተቱን አይቶ፣
እኔ ከንቱ ግን
የጎደለኝን አላውቅም ከቶ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፣
ደጅሽን ስረግጥ እታደሳለሁ።

እዪኣት ያቺን ሴት
ከአትሮንሱ ጀርባ የምትዘምረው
ስምሽን ደጋግማ የምታነሳው፤
እኔ እስከማውቃት
ፊደል የሚያንቃት
ኩልትፍ አንደበት - ነው የነበራት።

ምን ጸልያ ነው አፏ የተፈታ?
ምን ብላሽ ይሆን
ቃል አቅሙን አጥቶ ለእሷ የተረታ?
የእኔማ ምላስ አግድም ለፋፊ
ለ'ንቶ ፈንቶ እንጂ ለጸሎት ታጣፊ።

እይው ያንን ሰው
ኑሮ የደቆሰው
የደስታን እንባ ሞልቶ ሚያፈሰው፤
እኔ እስከማውቀው
ሞት 'ሚናፍቀው
ማጣት በዝቶበት ገዳይ ሚፈልግ
ተስፋን ተነጥቆ
አለመኖርን የሚያነበንብ።
ምን ሰጥተሽው ነው ፊቱ የፈካ?
ምን አግኝቶ ነው
የደስታው መጠን ጣሪያ የነካ?
እኔ ሳቅ አላውቅ እንባም አይገደኝ
መኖርም መሞት ትርጉም አይሰጠኝ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፤
ደጅሽን ስረግጥ ነፍስ እገዛለሁ።

#ኤልዳን
tiktok - ldan291

@getem
@getem
@getem
54👍34🔥3
መቼስ ልብ የለኝም
ልብ እንዳለው ስሆን

መቼስ ነፍስ የለኝም
ነፍስ እንዳለው ስሆን

መቼስ ህዝብ የለኝም
የጥንድ አልቃሽ ምሆን

እና ምኑ ይገርማል
እየኖርኩኝ እንኳ
እንዳልኖርኩኝ ስሆን

በትንንሽ ድምፆች አምላኬ በሚሉት
ሶቆቃ ብቻ ነው ምእመን ሚያሰሙት

በጨቅላ ህፃናት ቆመው በሚሰግዱት
ጫንቃቸው ሞትን ነው ነጠላ ያረጉት

ይሄ ሁሉ ምእመን
ለአምላክ የሚነግረው
ኑሮን አቅል ነው
ወይ መሪን ቀንሰው

እኔ ግን ደስታ ነው
ላንተ የማቀርበው
እኔ ስለት አለኝ
ልሞት ስለሆነ
ጥላ አለኝ ማስገባው

ኑሮ በሚያስፈራው
ዋይታ በደፈረው
በጭንቅ ለቅሶ ድምፅ
ዝምታ ይበላል
ያለምንም ፍትህ
ከኖረ እንደምስፅ

አለም ትንሽ ገብታኝ
ሀገር በደንብ ገብታኝ
እኛሳ ስላልናት
ስትጋረፍ አየሁ
በምእመን ልጇ
ጨካኝ ሁና እናት

እናት በጨከነች አባት በደበቃት
በግራ እግር ሀገር
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ ተሳቆ ከማደር

እናማ ጌታዬ በዚህ ሺህ ምእመን
የጭንቅ መሃል ለቅሶ
አንዲት ነፍስ አለች
ደስታ ያፈነዳት የሞት ክሬም ልሶ

ኗሪው በሚፈራት
መሪው በሚንቃት
በግራ እግር ሀገር፣
ሞት ቀጠሮ ማወቅ
ደስታ ሆኖ ቀረ
ተሳቆ ከማደር ፣

@geez_mulat

ግዕዝ ሙላት

@getem
@getem
@paappii
👍4114😢2🔥1
ማን ልበልህ አንተስ እሺ ዛሬ ኮስተር ነገ ፈገግ በቃ ይሄው ነው የኔ አቅም አንተስ እሺ እኔ ልበል ላንተ ፍግም ። ይሻልሀል እያወከው የኔን አቅም ወይስ ልራቅህ እንድረሳው የአንተን አቅም አላውቅም በምን ይሆን መፈወሻህ ገዳም ፀበል ይዤህ ልሂድ መጥፎው ነገር ጥሎህ እንዲሄድ ። ምን ላድርግልህ....... ለኔስ ይሁን ክርክርህ ሱስ ይዞኛል እንዳርቅህ ። በጨዋታ እያዋዛህ አደረከኝ እንድወድህ የኔ ፍቅር ....... ማን ልበልህ ቃላት ጠፋኝ በምን ልጥራህ ስሱን ጎኔን እየነካህ እያስለቀስክ እያዋዛህ ተራ ህመም አደረከው አስጠፋኸው የኔን ለዛ ።

By bline asefa

@getem
@getem
@getem
23👍10🔥5