እስቲ ላፍቅር ደሞ…
ሰው አጥር ወጥቼ - ፅጌረዳ ልቅጠፍ፥
አበባዬን ይዤ - እግሯ ሥር ልነጠፍ፤
ጨረቃ ላይ ላፍጥጥ - ከዋክብትን ልቁጠር፥
የቦይ ውኃ ልምታ - በለቀምኩት ጠጠር፤
በመስኮት ላማትር - በሚወርደው ዝናብ፥
ቀን ተሌት ልተክዝ - በፈጠርኩት ምናብ።…
እስቲ ደሞ ላፍቅር…
እሷው ፖለቲካ - እሷው ሰበር ዜና፥
እሷው ባለንዋይ - እሷው ባለዝና፥
እሷው የ’ምነቴ ቄስ - እሷው ቅድስና፥
ዓለም በቃኝ ብዬ - በሷው ወሬ ልጽና።
ከፈገገች ልሣቅ - ካለቀሰች ልሙት፥
እኔ አለኹ ለቀልዷ - ደደቦች ባይሰሙት።…
እስቲ ላፍቅር ደሞ…
መንገድ ስሟን ልጥራ - አበደ ይበሉ፥
እሷ ውስጥ እንዳለኹ - የማያውቁ ኹሉ፤
ጥዑም ዜማ ይኹን - የምትጨቀጭቀኝ፥
የሰለቸኝ ኹሉ - ባ’ንድ አዳር ይናፍቀኝ፤
እንዴትም ትስደበኝ - ስሜን ታጥፋው አኹን፥
ብቻ ስሜን ትጥራ - ብቻ ካፏ ይኹን።…
እስቲ ላፍቅር ደሞ…
ዘፈን ትርጉም ይስጠኝ - ደሞ ላንጎራጉር፥
ስለመቃ አንገት - ስለሀር ጸጉር፤
ላንዲት እንስት ልውደቅ - ሎሌነቴን ልግመድ፥
የያዝኩትን ልጣል - ዐዲስ ጌታ ልልመድ።
እስቲ ላፍቅር ደሞ!
By abere ayalew
@getem
@getem
@paappii
ሰው አጥር ወጥቼ - ፅጌረዳ ልቅጠፍ፥
አበባዬን ይዤ - እግሯ ሥር ልነጠፍ፤
ጨረቃ ላይ ላፍጥጥ - ከዋክብትን ልቁጠር፥
የቦይ ውኃ ልምታ - በለቀምኩት ጠጠር፤
በመስኮት ላማትር - በሚወርደው ዝናብ፥
ቀን ተሌት ልተክዝ - በፈጠርኩት ምናብ።…
እስቲ ደሞ ላፍቅር…
እሷው ፖለቲካ - እሷው ሰበር ዜና፥
እሷው ባለንዋይ - እሷው ባለዝና፥
እሷው የ’ምነቴ ቄስ - እሷው ቅድስና፥
ዓለም በቃኝ ብዬ - በሷው ወሬ ልጽና።
ከፈገገች ልሣቅ - ካለቀሰች ልሙት፥
እኔ አለኹ ለቀልዷ - ደደቦች ባይሰሙት።…
እስቲ ላፍቅር ደሞ…
መንገድ ስሟን ልጥራ - አበደ ይበሉ፥
እሷ ውስጥ እንዳለኹ - የማያውቁ ኹሉ፤
ጥዑም ዜማ ይኹን - የምትጨቀጭቀኝ፥
የሰለቸኝ ኹሉ - ባ’ንድ አዳር ይናፍቀኝ፤
እንዴትም ትስደበኝ - ስሜን ታጥፋው አኹን፥
ብቻ ስሜን ትጥራ - ብቻ ካፏ ይኹን።…
እስቲ ላፍቅር ደሞ…
ዘፈን ትርጉም ይስጠኝ - ደሞ ላንጎራጉር፥
ስለመቃ አንገት - ስለሀር ጸጉር፤
ላንዲት እንስት ልውደቅ - ሎሌነቴን ልግመድ፥
የያዝኩትን ልጣል - ዐዲስ ጌታ ልልመድ።
እስቲ ላፍቅር ደሞ!
By abere ayalew
@getem
@getem
@paappii
❤71👍32🔥3😁1
እልፍ አዕላፍ ሰዎች.....
ይኖሩ ይመስል በምድር ዘላለም፤
ዳግም ላይፋቱ ተጋብተው ከአለም፤
የጊዜን ምንነት ወርቅነት ሳያዉቁ፤
ከእድሜያቸዉ ላይ ዘመናት ሰረቁ።
............................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
ይኖሩ ይመስል በምድር ዘላለም፤
ዳግም ላይፋቱ ተጋብተው ከአለም፤
የጊዜን ምንነት ወርቅነት ሳያዉቁ፤
ከእድሜያቸዉ ላይ ዘመናት ሰረቁ።
............................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍55❤27🔥11
( ማስረጃ .. )
===========
የኢያሱ ገባኦን
የሙሴ ቀይ ባህር
የጽዮን ተራሮች
የፈጣሪ ተአምር ... ምናምን ምናምን
ሰው የፈበረከው
የአፈታሪክ ክምር ..
(ብዬ ስፈላሰፍ )
(ብዬ ስመረምር)
ኤዲያ ....
ጸሐይ ከመች ወዲህ
የምትቆም ለበቀል
ባህር ምን እሆን ሲል
ለሁለት የሚከፈል
ተራራስ ምን ቆርጦት
እንደ ህጻን የሚዘል
(እያልሁ ስጀነን)
ታሪክ ዘመን አልፎ
ወደኔ አዘመመ
አንዲት ቆንጆ አይቼ .. ልቤ ድንገት ቆመ
በቆመበት ቅጽበት
ወዲያው ተከፈለ
ስንጥቁ ሳይገጥም
ደግሞ እንደ ልጅ ጊደር ወደላይ ዘለለ
ደረቅ እንዳልነበር ለሷ ብቻ ረጥቦ
ታጥቦ ተሰቀለ ...
ወዮ .. የሴት መፈጠሯ
ለካ ለእግዜር ታምር ማስረጃ ነበረ !
(ከዚያ ወዲያ መልሴ)
ጸሀይ ምን አቆመው ?
የኢያሱ ውበት
ባህር ምን ከፈለው ?
የሙሴ ቅንነት
ተራራስ የሚዘል ?
ግርማው አይሎበት ...
(ጎበዝ)
ለካ አላምን ያልሁት
ያ ሁሉ ታምራት መልሱ ነበር ውበት 😁
By @kiyorna
@getem
@getem
@getem
===========
የኢያሱ ገባኦን
የሙሴ ቀይ ባህር
የጽዮን ተራሮች
የፈጣሪ ተአምር ... ምናምን ምናምን
ሰው የፈበረከው
የአፈታሪክ ክምር ..
(ብዬ ስፈላሰፍ )
(ብዬ ስመረምር)
ኤዲያ ....
ጸሐይ ከመች ወዲህ
የምትቆም ለበቀል
ባህር ምን እሆን ሲል
ለሁለት የሚከፈል
ተራራስ ምን ቆርጦት
እንደ ህጻን የሚዘል
(እያልሁ ስጀነን)
ታሪክ ዘመን አልፎ
ወደኔ አዘመመ
አንዲት ቆንጆ አይቼ .. ልቤ ድንገት ቆመ
በቆመበት ቅጽበት
ወዲያው ተከፈለ
ስንጥቁ ሳይገጥም
ደግሞ እንደ ልጅ ጊደር ወደላይ ዘለለ
ደረቅ እንዳልነበር ለሷ ብቻ ረጥቦ
ታጥቦ ተሰቀለ ...
ወዮ .. የሴት መፈጠሯ
ለካ ለእግዜር ታምር ማስረጃ ነበረ !
(ከዚያ ወዲያ መልሴ)
ጸሀይ ምን አቆመው ?
የኢያሱ ውበት
ባህር ምን ከፈለው ?
የሙሴ ቅንነት
ተራራስ የሚዘል ?
ግርማው አይሎበት ...
(ጎበዝ)
ለካ አላምን ያልሁት
ያ ሁሉ ታምራት መልሱ ነበር ውበት 😁
By @kiyorna
@getem
@getem
@getem
❤49👍40🔥3😱3
አልመጣም ስትይኝ
አልመጣም ስትይኝ ትመጫለሽ እያልኩ
እራሴን ሳታልል
መንገዱ ማለቂያው ገና ነው እያልኩኝ
ዘመናት ሳካልል
ስንቶች ተፋቀሩ ስንቶች ተዋደዱ
ስንት ፀደይ ተተካ አመታት ነጎዱ
ስንቶቹ ተፋቱ ስንቱ ወልዶ ሳመ
ደስታው ከሀዘኑ አለፈ አገደመ
እኔ ግን እዛው ነኝ ያልሽኝን ሳላምን
ላንቺ ሚበቃሽን በመጠን ሳልተምን
ሁሉንም ነገሬን ሁሉንም ሰጥቼሽ
እዬጠበኩሽ ነው
እንደማትመጭ ባውቅም ማወቄን አላምነው
...................................እዬጠበኩሽ ነው
by kerim
@getem
@getem
@getem
አልመጣም ስትይኝ ትመጫለሽ እያልኩ
እራሴን ሳታልል
መንገዱ ማለቂያው ገና ነው እያልኩኝ
ዘመናት ሳካልል
ስንቶች ተፋቀሩ ስንቶች ተዋደዱ
ስንት ፀደይ ተተካ አመታት ነጎዱ
ስንቶቹ ተፋቱ ስንቱ ወልዶ ሳመ
ደስታው ከሀዘኑ አለፈ አገደመ
እኔ ግን እዛው ነኝ ያልሽኝን ሳላምን
ላንቺ ሚበቃሽን በመጠን ሳልተምን
ሁሉንም ነገሬን ሁሉንም ሰጥቼሽ
እዬጠበኩሽ ነው
እንደማትመጭ ባውቅም ማወቄን አላምነው
...................................እዬጠበኩሽ ነው
by kerim
@getem
@getem
@getem
👍58❤27😢12👎4🔥2
ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)
ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤
ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤
የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥
የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤
ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:
@getem
@getem
@paappii
(በእውቀቱ ስዩም)
ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤
ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ ዘበት፤
የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥
የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤
ለካ ሰው ቢማር፥
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:
@getem
@getem
@paappii
❤73👍43🤩6😱5🔥2
....
አሁን በእኛ ዘመን ፍቅር የምንለዉ፤
በቅዱስ መፅሐፍ ሠርክ የምናነበዉ፤
ካፋችን ማይጠፋ ቀን በቀን ምንጠራዉ፤
ፍቺዉ የጠፋብን ፍቅር ግን ምንድነዉ?
..................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
አሁን በእኛ ዘመን ፍቅር የምንለዉ፤
በቅዱስ መፅሐፍ ሠርክ የምናነበዉ፤
ካፋችን ማይጠፋ ቀን በቀን ምንጠራዉ፤
ፍቺዉ የጠፋብን ፍቅር ግን ምንድነዉ?
..................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤57👍24
ተአምር
"""""""""
ዘንዶ ሳይውጠኝ - ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ
ሽቅብ ቢወስደኝ - ወደ ደብረ ዳሞ፤
አንችን ከጎኔ - ፈፅሞ ካላየሁ
ተአምር ነው ብዬ … መች እቀበላለሁ፡፡
፡
ድንገት ተከብቤ - በአንበሳ መንጋ
ሊበሉኝ ሲጥሩ - አፋቸው ቢዘጋ፤
አንችን በዙሪያዬ - ቆመሽ ካላየሁ
የመዳኔን ሚስጥር
ከተአምር ጋር … መች አያይዛለሁ፡፡
፡
ግዙፉ ጎልያድ - ጥሩር ለብሶ
ህይወቴን ሊነጥቅ - ሲመጣ ገስግሶ፤
ወንጭፍ ወንጭፌ - በጠጠር ስጥለው
ከጎኔ ሁነሽ - ስታይኝ ካላየሁ
የድሌን መገኛ
ተአምር ነው ብዬ … መች አስባለሁ፡፡
፡
እመቤቴ
ከድርጊቴ በስተጀርባ - አንችን ካላየሁ በቀር፤
ተአምር አይመስለኝም - የተደረገው ነገር፡፡
፡
በህይወት እያለሁ … ተአምር ምለው እኔ፤
አንችን ማግኘት ነው - ሁልጊዜም ከጎኔ፡፡
፡
(ሌላው ጥንቅር ብሎ ይቅር¡¡¡)
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
"""""""""
ዘንዶ ሳይውጠኝ - ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ
ሽቅብ ቢወስደኝ - ወደ ደብረ ዳሞ፤
አንችን ከጎኔ - ፈፅሞ ካላየሁ
ተአምር ነው ብዬ … መች እቀበላለሁ፡፡
፡
ድንገት ተከብቤ - በአንበሳ መንጋ
ሊበሉኝ ሲጥሩ - አፋቸው ቢዘጋ፤
አንችን በዙሪያዬ - ቆመሽ ካላየሁ
የመዳኔን ሚስጥር
ከተአምር ጋር … መች አያይዛለሁ፡፡
፡
ግዙፉ ጎልያድ - ጥሩር ለብሶ
ህይወቴን ሊነጥቅ - ሲመጣ ገስግሶ፤
ወንጭፍ ወንጭፌ - በጠጠር ስጥለው
ከጎኔ ሁነሽ - ስታይኝ ካላየሁ
የድሌን መገኛ
ተአምር ነው ብዬ … መች አስባለሁ፡፡
፡
እመቤቴ
ከድርጊቴ በስተጀርባ - አንችን ካላየሁ በቀር፤
ተአምር አይመስለኝም - የተደረገው ነገር፡፡
፡
በህይወት እያለሁ … ተአምር ምለው እኔ፤
አንችን ማግኘት ነው - ሁልጊዜም ከጎኔ፡፡
፡
(ሌላው ጥንቅር ብሎ ይቅር¡¡¡)
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
❤53👍37👎2
CBE
ሀገር ሰላም ብየ በተኛሁበት ሌት ህልሜን እያለምኩኝ
በደረቀው ሌሊት ስልኬ ድንገት ጮሆ ከእልቅልፌ ባነንኩኝ
ደግሞ ምናባቱ ሰው አይተኛ እንዴ የሚደውልብኝ
የሚበጠብጠኝ እረ ምን ጣለብኝ
ግራ እየተጋባሁ
ሄሎ
አቤት ጓደኛየ ምነው ምን ሆነህ ነው ምነው በዚ ሰአት
ምን ቢገኝልኝ ነው በድቅድቅ ጨለማ በደረቀው ሌሊት
ወደኔ የደወልክ ብየ ስጠይቀው
ሁሉም ሀብታም ሆነ ገንዘብ ታፈሰልህ ይሄንን እወቀው
የትም ሳትለፋ ወዴትም ሳትደክም ባለህበት ቦታ
መበልፀግ መጣልህ አሁኑኑ ሞክር ነቃ በል በል በርታ
ሲለኝ ስለሰማሁ እኔም ከመ ቅፅበት ስኩን አቋርጬ
ወደ ስልኬ ማውጫ በፍጥነት አፍጥጬ
ኮኮብ ስምንት ስምንት ዘጠኝ መሰላል
ስደውል ስሞክር ልቤ ይጠረጥራል
ይሰራል አይሰራም? ብየ ስደናበር
አንዴ እስኪገባልኝ አላመንኩም ነበር
ከዛ
ስሞክር ሲገባ ስደግም ሲደመር ገንዘብ ሲጠራቀም
የተሰማኝ ደስታ ከዚ በፊት ጭራሽ ተሰምቶኝ አያውቅም
እየተጯጯህን የኔ እንደዚ ሆነ የኔም ይሄው ጨመረልኝ
በዚ ገንዘብማ ነገ የማደርገው ብዙ ነገር አለኝ
እየተባባልን እየተመካከርን ድንገት ተቋረጠ
ወይኔ ብዙ ሳይሆን
በሚል ሌላ ጩኸት ዶርሙ ተቀወጠ
ከዛ
ትንሽ እምደቆየን ነገ እንዳይወስዱት የሚል ስጋት ስለመጣ
በደረቀው ሌሊት ከግቢያችን ወጣን ብሩን ልናወጣ
ጨለማን አልፈራን ብርዱም አልበገረን ሰንጥቀነው ወጣን
በኪስ ሙሉ ገንዘብ እየተሳሳቅን አፋፍሰነው መጣን
ልክ ዶርም ስንደርስ
ተበተነ ብሩ ወለሉ በሙሉ ገንዘብ አጠገበው
ብርቅ ሆኖብናል እጠግብ አይመስለው እጅጉን የራበው
ስንጫወትበት ጮቤ ስንረግጥ መንጋት አይቀር ነጋ
በጠዋት ገባነው ብሩን መጨረሻ መዝናኛን ፍለጋ
ተገዛዛ እቃው ተጠጣ በበቃም ደግሞ ለዚ ገንዘብ
ዝም ብለህ ብላ እስከ ጥግ ተዝናና የምን ማገናዘብ
እየተባባልን ብሩ ሲገፋፋ ለማለቅ ሲቃጣው
ያንን ሁሉ ገንዘብ መልሱ ተባለ አሁን መጣ ጣጣው
አቤት መኮሳተር አቤት መኮስመን ያንን ስንሰማ
በጠራራው ፀሀይ የሚያሞቀን ቀትር ሆነብን ጨለማ
ስልኬ ይጠራና ባነሳሁት ቁጥር ገንዘብ አትመልስም
የሚል ነው ምሰማው ፍዳ ነው በእግዜር ስም
ይሄው ግራ ሲሆን በበላሁበት ብር የመኖር መንገዴ
ሁሉን እርዱኝ አልኩኝ ወይ እዳ ወይ ጉዴ
የተገዛው እቃ በርካሽ ተሸጠ አወየው ኪሳራ
ያንን ሳስብ ውየ ህይወቴ ሲናጋ እንዴት ስራ ልስራ
ቁጥር ባየሁ ቁጥር እዳ ትዝ እያለኝ
ባንክ የሚል ስሠማ እያብሰለሰለኝ
እንዴት ኑሮ ይሁን በተክለፈለፉ
ሆኖ በአፍ ይጠፉ
እርሜን ይሁን አልኩኝ ከእንግዲህ በሌሊት ስልኬን አላነሳም
ሆኦኦኦ ደሞ ምን በወጣኝ የሆንኩትን ነገር ዘላለም አረሳም
አመት ከምተክዝ ለአንድ ቀን ሳቄ
ይሻላል ሁሉንም ያኔ አለማወቄ
ሆሆሆሆ
ደሞኮ ባልነቃ ህልሜ ባይቋረጥ ምናል በጨረስኩት
የህልሜን አጫዋች ያንን የውብ ከንፈር ምናለ በሳምኩት
ጨለምለም ባለው ብርሀን ያጠረው ግንቡን ተጠልለን
እየተለፋፋን እየተሟዘዝን ይሉኝታንም ጥለን
ጠጋ ጠጋ ስላት እሷም ስትጠጋኝ ልክ ልስማት ስል
ማቋረጤ ቆጨኝ እንዴት ካይኔ ይጥፋ የውበቷ ምስል
ስልኬ ከሚጠራ ሳልስማት ሳልነካት ያኔ ከምነቃ
ምናለ ባይደውል ብሩስ ቢቀርብኝ አሁን ቆጨኝ በቃ።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@yiatayl05
ሀገር ሰላም ብየ በተኛሁበት ሌት ህልሜን እያለምኩኝ
በደረቀው ሌሊት ስልኬ ድንገት ጮሆ ከእልቅልፌ ባነንኩኝ
ደግሞ ምናባቱ ሰው አይተኛ እንዴ የሚደውልብኝ
የሚበጠብጠኝ እረ ምን ጣለብኝ
ግራ እየተጋባሁ
ሄሎ
አቤት ጓደኛየ ምነው ምን ሆነህ ነው ምነው በዚ ሰአት
ምን ቢገኝልኝ ነው በድቅድቅ ጨለማ በደረቀው ሌሊት
ወደኔ የደወልክ ብየ ስጠይቀው
ሁሉም ሀብታም ሆነ ገንዘብ ታፈሰልህ ይሄንን እወቀው
የትም ሳትለፋ ወዴትም ሳትደክም ባለህበት ቦታ
መበልፀግ መጣልህ አሁኑኑ ሞክር ነቃ በል በል በርታ
ሲለኝ ስለሰማሁ እኔም ከመ ቅፅበት ስኩን አቋርጬ
ወደ ስልኬ ማውጫ በፍጥነት አፍጥጬ
ኮኮብ ስምንት ስምንት ዘጠኝ መሰላል
ስደውል ስሞክር ልቤ ይጠረጥራል
ይሰራል አይሰራም? ብየ ስደናበር
አንዴ እስኪገባልኝ አላመንኩም ነበር
ከዛ
ስሞክር ሲገባ ስደግም ሲደመር ገንዘብ ሲጠራቀም
የተሰማኝ ደስታ ከዚ በፊት ጭራሽ ተሰምቶኝ አያውቅም
እየተጯጯህን የኔ እንደዚ ሆነ የኔም ይሄው ጨመረልኝ
በዚ ገንዘብማ ነገ የማደርገው ብዙ ነገር አለኝ
እየተባባልን እየተመካከርን ድንገት ተቋረጠ
ወይኔ ብዙ ሳይሆን
በሚል ሌላ ጩኸት ዶርሙ ተቀወጠ
ከዛ
ትንሽ እምደቆየን ነገ እንዳይወስዱት የሚል ስጋት ስለመጣ
በደረቀው ሌሊት ከግቢያችን ወጣን ብሩን ልናወጣ
ጨለማን አልፈራን ብርዱም አልበገረን ሰንጥቀነው ወጣን
በኪስ ሙሉ ገንዘብ እየተሳሳቅን አፋፍሰነው መጣን
ልክ ዶርም ስንደርስ
ተበተነ ብሩ ወለሉ በሙሉ ገንዘብ አጠገበው
ብርቅ ሆኖብናል እጠግብ አይመስለው እጅጉን የራበው
ስንጫወትበት ጮቤ ስንረግጥ መንጋት አይቀር ነጋ
በጠዋት ገባነው ብሩን መጨረሻ መዝናኛን ፍለጋ
ተገዛዛ እቃው ተጠጣ በበቃም ደግሞ ለዚ ገንዘብ
ዝም ብለህ ብላ እስከ ጥግ ተዝናና የምን ማገናዘብ
እየተባባልን ብሩ ሲገፋፋ ለማለቅ ሲቃጣው
ያንን ሁሉ ገንዘብ መልሱ ተባለ አሁን መጣ ጣጣው
አቤት መኮሳተር አቤት መኮስመን ያንን ስንሰማ
በጠራራው ፀሀይ የሚያሞቀን ቀትር ሆነብን ጨለማ
ስልኬ ይጠራና ባነሳሁት ቁጥር ገንዘብ አትመልስም
የሚል ነው ምሰማው ፍዳ ነው በእግዜር ስም
ይሄው ግራ ሲሆን በበላሁበት ብር የመኖር መንገዴ
ሁሉን እርዱኝ አልኩኝ ወይ እዳ ወይ ጉዴ
የተገዛው እቃ በርካሽ ተሸጠ አወየው ኪሳራ
ያንን ሳስብ ውየ ህይወቴ ሲናጋ እንዴት ስራ ልስራ
ቁጥር ባየሁ ቁጥር እዳ ትዝ እያለኝ
ባንክ የሚል ስሠማ እያብሰለሰለኝ
እንዴት ኑሮ ይሁን በተክለፈለፉ
ሆኖ በአፍ ይጠፉ
እርሜን ይሁን አልኩኝ ከእንግዲህ በሌሊት ስልኬን አላነሳም
ሆኦኦኦ ደሞ ምን በወጣኝ የሆንኩትን ነገር ዘላለም አረሳም
አመት ከምተክዝ ለአንድ ቀን ሳቄ
ይሻላል ሁሉንም ያኔ አለማወቄ
ሆሆሆሆ
ደሞኮ ባልነቃ ህልሜ ባይቋረጥ ምናል በጨረስኩት
የህልሜን አጫዋች ያንን የውብ ከንፈር ምናለ በሳምኩት
ጨለምለም ባለው ብርሀን ያጠረው ግንቡን ተጠልለን
እየተለፋፋን እየተሟዘዝን ይሉኝታንም ጥለን
ጠጋ ጠጋ ስላት እሷም ስትጠጋኝ ልክ ልስማት ስል
ማቋረጤ ቆጨኝ እንዴት ካይኔ ይጥፋ የውበቷ ምስል
ስልኬ ከሚጠራ ሳልስማት ሳልነካት ያኔ ከምነቃ
ምናለ ባይደውል ብሩስ ቢቀርብኝ አሁን ቆጨኝ በቃ።
✍✍✍ ይታያል ጌቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@yiatayl05
👍89😁54❤6👎5
እባክሽ አትሳቂ
ከንፈሮችሽ ሸሽተው ጥርሶችሽ ሲገለጥ ገነት ስለሚታይ
ሰማይ እና ምድሩ መላዕክቱም ሰውም ወዶሽ ከሚሰቃይ
ፈገግ እንዳትይ በጨረፍታም ቢሆን ጥርስሽ እንዳይታይ
ያለም ባለፀጋ ሀብት በሀብት ቢያደርግሽ ብትንደላቀቂ
ጥበበኛ ከቦሽ ጨዋታ አሳምሮ መሳቅ ብትናፍቂ
ደስ ብሎሽም ቢሆን ለኔ ካልሆነ እባክሽ አትሳቂ
መድሃኒት ነው ቢባል ሳቅሽ ለታመመ በሞት ለተጠራ
አንድም ሰው አያይም ይሞታታል እንጂ ሁሉም በየተራ
በተራ በተራ ጠብ ጠብ እያለ ፍጥረት ካለም ቢያልቅም
የሷን ሳቅ ፈገግታ ካለእኔ በቀር ማንም አያያትም
ብዬ ስለፎከርኩ እኔ ያንቺ ሱራፌል እኔ ጠባቂ
ደስ ብሎሽም ቢሆን ለኔ ካልሆነ እባክሽ አትሳቂ
ዘረ-ሠናይ
@Prince_Zeresenay
@getem
@getem
@getem
ከንፈሮችሽ ሸሽተው ጥርሶችሽ ሲገለጥ ገነት ስለሚታይ
ሰማይ እና ምድሩ መላዕክቱም ሰውም ወዶሽ ከሚሰቃይ
ፈገግ እንዳትይ በጨረፍታም ቢሆን ጥርስሽ እንዳይታይ
ያለም ባለፀጋ ሀብት በሀብት ቢያደርግሽ ብትንደላቀቂ
ጥበበኛ ከቦሽ ጨዋታ አሳምሮ መሳቅ ብትናፍቂ
ደስ ብሎሽም ቢሆን ለኔ ካልሆነ እባክሽ አትሳቂ
መድሃኒት ነው ቢባል ሳቅሽ ለታመመ በሞት ለተጠራ
አንድም ሰው አያይም ይሞታታል እንጂ ሁሉም በየተራ
በተራ በተራ ጠብ ጠብ እያለ ፍጥረት ካለም ቢያልቅም
የሷን ሳቅ ፈገግታ ካለእኔ በቀር ማንም አያያትም
ብዬ ስለፎከርኩ እኔ ያንቺ ሱራፌል እኔ ጠባቂ
ደስ ብሎሽም ቢሆን ለኔ ካልሆነ እባክሽ አትሳቂ
ዘረ-ሠናይ
@Prince_Zeresenay
@getem
@getem
@getem
❤63👍37😁10🔥6👎5😱1😢1
👑👑እንጀራ ልጅ👑👑
ገና በልጅነት ሲወርስ ይቺን ምድር
ጥሩ ይመስል ነበር የዋህ እና ገራገር::
:
:
:
ሆኖም በዓመቱ የፊት ጥርስ ሲያወጣ
ያገኘውን ሁሉ መጋጥን አመጣ::
:
:
አሁን ከፍ ብሎ ስድስት አንደሞላ
ለማይጠግበው ሆዱ ስላጣለት መላ
አብይ ፆም ሳይል ስጋ ነው ሚበላ::
✍️ @BEGITIMENAWGA
( መጋቢት 24 2016 በድጋሚ ተሻሽሎ የቀረበ።)
🎈🎂 መልካም ልደት ለማለት ያክል ነው በዛሬዋ ቀን እቺን ምድር ለረገጣቹት።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
@getem
@getem
@getem
ገና በልጅነት ሲወርስ ይቺን ምድር
ጥሩ ይመስል ነበር የዋህ እና ገራገር::
:
:
:
ሆኖም በዓመቱ የፊት ጥርስ ሲያወጣ
ያገኘውን ሁሉ መጋጥን አመጣ::
:
:
አሁን ከፍ ብሎ ስድስት አንደሞላ
ለማይጠግበው ሆዱ ስላጣለት መላ
አብይ ፆም ሳይል ስጋ ነው ሚበላ::
✍️ @BEGITIMENAWGA
( መጋቢት 24 2016 በድጋሚ ተሻሽሎ የቀረበ።)
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
@getem
@getem
@getem
👍56❤18😁14😢6😱4👎3🤩1
☀️ፀሃይ ልጠይቅሽ☀️
ሰማሽኝ ወይ ፀሃይ
ያለሽ ከሰው በላይ
ከዛ ከከፍታ ከዛ ከሩቅ ስፍራ
ሆነሽ ከሰማይ ስር
ሚታይሽ ከሆነ ከጥግ እስከጥጓ
የኛ ሰዎች ምድር
ስሚኝ እባክሽን አንዴ ተባበሪኝ
እኔ ከርታታውን
ውሃ አጣጬን እንደው አይተሻት ከሆነ
አገናኚኝ አሁን።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
ሰማሽኝ ወይ ፀሃይ
ያለሽ ከሰው በላይ
ከዛ ከከፍታ ከዛ ከሩቅ ስፍራ
ሆነሽ ከሰማይ ስር
ሚታይሽ ከሆነ ከጥግ እስከጥጓ
የኛ ሰዎች ምድር
ስሚኝ እባክሽን አንዴ ተባበሪኝ
እኔ ከርታታውን
ውሃ አጣጬን እንደው አይተሻት ከሆነ
አገናኚኝ አሁን።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
👍56❤23😁7🔥6🤩4😢2
( ያ ሰው ... )
=================
አውቀዋለሁ እኮ ....
ሁሉን ቻል ባረኩ ፈርቼ እንዳይመስለው
መች ተረሳኝና ልቤን ስንቴ ከአመድ እንዳንደባለለው
ወደአምና ቁጭቴ .....
ጎትቶ አይጨምረኝ ተው በለው ይሄን ሰው
በደል አመርቅዞት የመረረ ቁስሌን ይቅር አይቀስቅሰው
(እያልሁ ጠላቴን ጌታ ፊት ስከሰው ..)
ከዘርፉፉ ልብሱ ገለጠና አካሉን
ዘመን ያላጠፋው አሳየኝ ችንካሩን
የደም ላብ ያወዛው አስነካኝ ግንባሩን
ትኩስ ደም ያዘለ ዳሰስኩኝ ሰምበሩን
አለቀስሁ በብርቱ ...
ህማሙ መከራው ሆዴን አላወሰው
ዳግም ዘምበል አለ ዝንጉ ልቦናዬን ሊመክር ሊወቅሰው
" ልጄ ...
በደል አትቋጠር ይቅር አትክሰሰው
አልታወሰህ እንጂ ያኔም ' ውደድ ' ያልኩህ
ነበር ይሄንን ሰው !!! "
By @Kiyorna
@getem
@getem
@paappiii
=================
አውቀዋለሁ እኮ ....
ሁሉን ቻል ባረኩ ፈርቼ እንዳይመስለው
መች ተረሳኝና ልቤን ስንቴ ከአመድ እንዳንደባለለው
ወደአምና ቁጭቴ .....
ጎትቶ አይጨምረኝ ተው በለው ይሄን ሰው
በደል አመርቅዞት የመረረ ቁስሌን ይቅር አይቀስቅሰው
(እያልሁ ጠላቴን ጌታ ፊት ስከሰው ..)
ከዘርፉፉ ልብሱ ገለጠና አካሉን
ዘመን ያላጠፋው አሳየኝ ችንካሩን
የደም ላብ ያወዛው አስነካኝ ግንባሩን
ትኩስ ደም ያዘለ ዳሰስኩኝ ሰምበሩን
አለቀስሁ በብርቱ ...
ህማሙ መከራው ሆዴን አላወሰው
ዳግም ዘምበል አለ ዝንጉ ልቦናዬን ሊመክር ሊወቅሰው
" ልጄ ...
በደል አትቋጠር ይቅር አትክሰሰው
አልታወሰህ እንጂ ያኔም ' ውደድ ' ያልኩህ
ነበር ይሄንን ሰው !!! "
By @Kiyorna
@getem
@getem
@paappiii
👍50❤35😢5🔥2
❤️❤️🔥💔የልቤን ብታዪ❤️❤️🔥💔
አይኔ እንደ ቆራጥ አንቺን ባያይሽም
ሞልቶት ትንሽ ኩራት
አፌም ጀነን ብሎ አሻፈረኝ ቢልም
ስምሽን ለመጥራት
ጆሮዬም ቢያስመስል ከቶ እንደማይሰማ
አንቺን የሚል ወሬ
በሄድሽበት መሄድ ሁሌ መከተሉን
ባይሞክረው እግሬ
በይ ልንገርሽ ዛሬ
ሞኝ ልብ እንዳለኝ ማያውቅ ማስመሰል
ጠዋትና ማታ ስራው አድርጎታል
አንቺን ማሰላሰል።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
አይኔ እንደ ቆራጥ አንቺን ባያይሽም
ሞልቶት ትንሽ ኩራት
አፌም ጀነን ብሎ አሻፈረኝ ቢልም
ስምሽን ለመጥራት
ጆሮዬም ቢያስመስል ከቶ እንደማይሰማ
አንቺን የሚል ወሬ
በሄድሽበት መሄድ ሁሌ መከተሉን
ባይሞክረው እግሬ
በይ ልንገርሽ ዛሬ
ሞኝ ልብ እንዳለኝ ማያውቅ ማስመሰል
ጠዋትና ማታ ስራው አድርጎታል
አንቺን ማሰላሰል።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
👍65❤27🔥1😱1
ቂቤሽ ጭፍ እያለ
ቅጫማም ፀጉርሽን እንዳልደባበስኩኝ
እናትዬ ብዬ
ግንባርሽን ስሜ ሻሽ እንዳላሰርኩኝ
ድንገት ብንገናኝ ሳልፍ በመንገድሽ
አላስቀምጥ አለኝ ግልምጫ ንቀትሽ
.
ከአንቺም ብሶ ደግሞ
ወይራ እንደ ተጠገበ እንደ ጠላ በርሜል
ጭሰኛ ብብትሽ የአፍንጫ ጋንኤል
መሆኑን ባውቅ እንኳን ጎንሽ ተኝቻለው
ከስሜት ህዋሴ አንዱን ሰውቻለው
.
እናም ይኸው ዛሬ
የሀብታም መንጋጋ መንጭቆ ቢያወጣሽ
ያሳለፍነው ሁሉ ቀልድ ሆኖ ተረሳሽ
ሀር ፀጉሬን ንቀሽ መላጣ መርጠሻል
ከእኔ ደረት ይልቅ ቦርጩ ተስማምቶሻል
እሱን እያሻሸሽ እለቢው እንደ ላም
ስለ አንቺ ባወራ ጊዜውም አይበቃም
.
ለዛም ተመኘውኝ ደግ ደጉን ላንቺ
ቅጫምሽን ትተሽ
አረተፊሻል ዉጊውን ማንጠልጠሉን በርቺ
By በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr
@getem
@getem
@getem
ቅጫማም ፀጉርሽን እንዳልደባበስኩኝ
እናትዬ ብዬ
ግንባርሽን ስሜ ሻሽ እንዳላሰርኩኝ
ድንገት ብንገናኝ ሳልፍ በመንገድሽ
አላስቀምጥ አለኝ ግልምጫ ንቀትሽ
.
ከአንቺም ብሶ ደግሞ
ወይራ እንደ ተጠገበ እንደ ጠላ በርሜል
ጭሰኛ ብብትሽ የአፍንጫ ጋንኤል
መሆኑን ባውቅ እንኳን ጎንሽ ተኝቻለው
ከስሜት ህዋሴ አንዱን ሰውቻለው
.
እናም ይኸው ዛሬ
የሀብታም መንጋጋ መንጭቆ ቢያወጣሽ
ያሳለፍነው ሁሉ ቀልድ ሆኖ ተረሳሽ
ሀር ፀጉሬን ንቀሽ መላጣ መርጠሻል
ከእኔ ደረት ይልቅ ቦርጩ ተስማምቶሻል
እሱን እያሻሸሽ እለቢው እንደ ላም
ስለ አንቺ ባወራ ጊዜውም አይበቃም
.
ለዛም ተመኘውኝ ደግ ደጉን ላንቺ
ቅጫምሽን ትተሽ
አረተፊሻል ዉጊውን ማንጠልጠሉን በርቺ
By በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr
@getem
@getem
@getem
😁66👍35😱6❤3👎2🤩2
🥲ትናንት እና ዛሬ🥲
አላወቅሺም እንጂ አፍቅሬሽ ነበረ
ዳሩ ምን ያረጋል
ሌላው ይዞሽ ሲሄድ ልቤ ተሰበረ።
የሆነው ሆነና እንዳሰብኩት ሳይሆን
ከጎኔ ባጣሽም
በትናንት ሀዘኔ የዛሬው ህይወቴን
ከቶ አላበላሽም።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
አላወቅሺም እንጂ አፍቅሬሽ ነበረ
ዳሩ ምን ያረጋል
ሌላው ይዞሽ ሲሄድ ልቤ ተሰበረ።
የሆነው ሆነና እንዳሰብኩት ሳይሆን
ከጎኔ ባጣሽም
በትናንት ሀዘኔ የዛሬው ህይወቴን
ከቶ አላበላሽም።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
❤49👍24🔥10🤩2