ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ከ "ሀ" እስከ "ሃ"

ወንበርን የያዙት ~ ጉዳይ ተቀብለው
           ጉዳይ ሚያስጨርሱ
ይመስሉኝ ነበረ ~ ፊደል በስርዓት
            ቆጥረው የጨረሱ


ዳሩግን ወዲህ ነው~መማር ተምረዋል
ሙሉውን ባይሆንም~ጥቂት ግን ቆጥረዋል
             አዎ ሰምቻለው
            እንደውም አቃለው
ከፊደል ገበታ ~ መጀመሪያ መስመር
ከ '''' እስከ "'' ድረስ ~ ቆጥረው እንደነበር

              እና እኚ ሰዎች
            ሆነው ሰራተኞች
           ሲያስፈፅሙ ጉዳይ
አንድ ነገር አለ ~ ሁልጊዜ የማይቀር
             ሁልጊዜ የሚታይ

ምንድነው ካላችሁኝ~ የጥያቄው መልሱ
             ናቸው እና እነሱ
"" ብለው ጀምረው ""~ ላይ እንደቀሩ
                እዚህ የደረሱ
ጉዳይ አይፈፅሙም ~ "" ባለ አፋቸው
               ጉርሻ ካልጎረሱ::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍5030😁13🔥6🤩5😱2👎1
የፍቅራችን ቅኔ

በፍቅር ሰሌዳ በመዋደድ ቅኔ፣
የኔ ልብ ባንተ ያንተም ልብ በኔ።

የነፍስያችን ወግ ካሳባችን ሰርፆ፣
በልባችን ሀዉልት ፍቅራችን ተቀርፆ።

ደምህና ደሜ ፍፁም ተዋህዶ፣
ባንደበት ሊገለፅ በቃላት ተጋምዶ።

ቀና ብለህ እያት ዉቢቷን ጨረቃ፣
የብርሃን ዝናር በወገቧ ታጥቃ።

ተስፋ ልታድል ጽልመት ለጋረደዉ፣
በትዝታ ጋሪ ሞሽራ ልትሸኘዉ።

ያቺ ዉብ ጨረቃ ምስክር ትሁንህ፣
በሷ ብርሃን የኔ መልክ ይታይህ።

ከዋክብትን ስታይ ከደጃፉ ቆመህ፣
በአንተ ብርሃን ድምቀቴ ይታወስህ።

የኔና አንተ ፍቅር በወርቅ ይመሰላል፣
ካፈር ተደባልቆ ከሳት ይፈተናል።

ከጭቃዉ ይጠራል ነበልባሉን አልፎ፣
ከነፍስ ተራቆ ከህሊና ገዝፎ።
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍3718
"ሲያስጠላ.."
የአንደበቷ ቃል
"ሲያምር" .. የልቧ ትርጉም
ለዓመታት ከኔ ጋር ኖራም
እንዳታምን የከለላት ጉም
አልጠፋም ዛሬም ከፊቷ
ስወደው የአፍላነት መልኳን
ማትከጅል ታስመስላለች
አይኗ ላይ ባነበው እንኳን
"ሂድዛ.." ሳሞጋግሳት
"ሞ..ዛዛ" ..ጉንጯን ስስማት
ውልክፍክፍ እንዳልተሻለው
ተሰብራ እግሯን ሳክማት

ስቀርባት ጥርሷን አትከድን
ሳወራት አይኗን አትነቅል
ወይ ጠልታኝ እርቃ አትከስም
ወይ ወዳኝ አብራኝ አትበቅል
መንፈሷ ተብትቦ አስሮ
ከገጿ እየዳረገኝ
ውብ አይኗ ትቶኝ ሲዋትት
ሰው መሃል እንዳልፈለገኝ
ልሄድ ስል "ተው ግን" እያለኝ
እምባዋ ካይኗ ላይ ሞልቶ
እንዳልቀር እጇ እየገፋኝ
እንዳልሄድ አፏ ቃል አቶ
ልለያት ጉንጯን እየሳምኩ
በፍቅር ስትቃትት ነፍሷ
"ቆይ ትንሽ" ልቧ የሚለው
"ደህና ደር"
የአፏ ላይ መልሷ.

By @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
64👍30🔥3
እርግጡ ይሄው ነው
ግርም እያለኝ ነው እራሴን ሳስበው
ጉድፍ ማንነቴን ውስጤን ስነካካው
ዛሬ ነው በጠዋት ከእንቅልፍ ተነስቼ
ነጠላ ደርቤ ዳዊቱን አንግቼ
ነጭበነጭ ሁኜ ልክ እንደ መላዕክ
ሄድኩኝ ቤተክርስቲያን ላደርስ ብየ ፀሎት
የሊቁን ምስጋና ከዘውትር እስከለት
....................አቤትአቤት......
ከውጭ ሁኖ የሚያይ ስንጎራደድማ
'ሊቀ መልዐክ ነው የመጣ ከራማ
ጥበብን የያዘ ያለው ሞገስ ግርማ '
እያሉ ሚያወሩ ይመስለኝ ጀመረ
ውዳሴ ከንቱውም ገፋ እየከረረ
.
ድንገት ጩኸት መሰል ከሀሳቤ አነቃኝ
ዞር ብየ ሳይም ቀለቤን ሁሉ ገዛኝ
እብድ የምንላቸው አዛውንት ከሰፈር
ጎርነን ባለ ድምፅ ይሰጣሉ ምክር
ሳላስበው እኔም ሆነ ትኩረቴ በሙሉ
ተግሳፅ ከሚሰጡት እንዲህም እያሉ
'ራስህን ሁን የሌላውን አትፈልግ
ትዕቢትን አስወግደህ ዓላማህን አንግ
መምሰልን ሳይሆን መሆን እሻ
ያን ጊዜ ነው የብስለትህ መነሻ'
.
ተግሳፅናምክሩ አንድበአንድ ሳይቀር
ባሳለፈዉፍኩት ሂወት ይመላለስ ጀመር
  ........አይየኔ ነገር.........
መምሰል የምፈልግ የፈጣሪ አገልጋይ
በቃ...በዝግጅት ጊዜ በሰዎች እንድታይ
መሆን የማልፈግ ውስጣዊ ልቤ ላይ
.........እርግጡ ይሄው ነው .......
ደግሞኮ በዛ ላይ ራሴን ምስለው
ጥሩና አስተዋይ ባህሪውም ያለው
ሲናገር እራሱ አንደበተ ርቱ
ፈሶ የሞላበት ትህትና ዕምነቱ
ፍቅርን ያዘለ ሀይማኖቱንየሚያቅ
የሚያነብ የሚጥር ሊቅና ረቂቅ
ለቤተሰብ ታዛዥ ተናፋቂ ደስታ
ካፋ የማይጠፋ ጨዋታ ፈገግታ
ይመስለኝ ነበረ  እንደዚህ መከታ
...ለካ
የሚመስለኝ ሌላ የሚሆነው ሌላ
       

በዳግም ጌታቸው @Ruzand29

@getem
@getem
@getem
25👍23👎5😁1
( እንዴት ብትወደኝ ነው .. )
===================

እየሳሳህ እንጂ
እንዳልቀር ጠፍቼ .. ቅስሜ እንዳይሰበር
በደሌን ለመጻፍ
ግምባሬ ብቻውን መች ይበቃህ ነበር

እንደአባትነትህ ስትተጋ ዘወትር
ልትገስጽ ልጅህን ....
እንዴት ብትወደኝ ነው
በግብሬ ተመርረህ
ስትቀጣኝ እንኳ አያለሁ ፍቅርህን !!!

እንዴት ብትወደኝ ነው ?

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
50👍22
ሰላም እንዴት አላችሁ ሶስተኛ ስራዬ የሆነዉ "እየዳነ ሄደ" የተሰኘ የአጫጭር ልቦለድ ስብስብ መጽሐፌን አዘጋጅቼ የጨረስኩ ሲሆን በሚታወቀዉ የህትመት ዋጋ ችግርና ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት በቅድመ ክፍያ ለማሳተም አስቤያለሁ።

ገፅ :- 280
ዋጋ :- 450

መጽሐፉ ቢኖረን እንወዳለን ለምትሉ ለሕትመት ዝግጁ የሆነ መጽሐፍ ይዤ እየጠበቅኋችሁ ነው።
     

     CBE Account :- 1000394805924 ሶስና ሰይፉ

በቴሌ ብር 0933304772 

ከላካችሁ በኋላ screenshot ላኩልን

#ምግባር_ሲራጅ

@getem
@getem
👍262🔥1🤩1
ያኔ ...ትምህርት ቤት ሳለን፤
ሰዓት አሳለፉ አረፈዱ ተብለን፤
በደረቅ አርጬሜ እንገረፋለን፤

ነገር ግን በህይወት.....

ይደርሳል እያልን፤
ጥቂት ካረፈድን፤

ህይወታችን ሁሉ ይመሰቃቀላል፤
ዳግም ላይመለስ ይዘበራረቃል።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍70🔥14🤩5😢1
ስለፋ ለዋልኩት ስወጣና ስወርድ
አገኝህ ይሆን ብዬ ዱካህን ሳሳድድ
ጥዬህ የማልበላው ክፍት ውሎ ገበታው
አይዋጥልኝም አንተ ያልባረከው አንተ ያልቀደስከው
ተስፋ ሳልቆርጥብህ ጥሎሽ ሄደ ስባል
ይመጣል እያልኩኝ አይኔን ሳልከድን ስዉል
የውሃ ጥም አቃጥሎኝ ሳልጠጣ ጾም ውዬ
ነገም ሌላ ቀን ነው በእንቅልፍ ያልፋል ብዬ
ድንገት ሸለብ ቢያረገኝ ለቅፅበት ለአንዳፍታ
በእውን የጠፋኸው የሆንክ የውሃ ሽታ
አየውህ በህልሜ ባመረ ፈገግታ
ገበታችን ቀርቦ ቤታችንም ደምቆ
የፍቅራችን ነገር ከነበረው ልቆ
መጣሁልሽ ፍቅሬ አላሳፈርኩሽም
ከእግዲህ በኋላ ላፍታ አልለይሽም
በይ እንኪ ጉረሺ በሞቴ እባክሽ
እኔም ደስ እያለኝ ሳልፈራ እና ሳልሸሽ
ድንገት ልጓርስ ስል ከእንቅልፌ ነቃው
ውዴ የኔ አለም መጠሪያህ ብዙ ነው
በአካል ብትቀርም በህልሜ ትመጣለህ
ይሄን አምኛለው
እርቦኛል በቃ ጥዬህ ልበላ ነው።

By #li_ya

@getem
@getem
@getem
31👍15👎5😱3🔥2
የሞተ ቢናገር
.
ስንኖር ያልተረዳን ስንሞት አለቀሰ
በቁም ያልጎበኘን ለቀብር ደረሰ
በአንቋሸሸን መዳፍ ፅድቅን ተቆናጀን
በእኔ ያርገው ለቅሶ ከአፈር ተወዳጀን
አብረን ካልተቀበርን የሚለው ጎረፈ
ከሀውልታችን ግርጌ ስማችን ተፃፈ
ሊሾን አለበሱን ቆመው በእየተራ
ሞትን ያጣጣለ በእኛ መሞት ፈራ
.
ፍትሀት እግዚኦታ ላኩ ለነፍሳችን
ይማረኒ ብለው ለሰራን ጌታችን
እሪታ እና ዋይታው ቆመ በሰዓታት
የመጣን መቻል ነው! በማፅናኛ ቃላት
ታሪክ ሆነን ቀረን የቀናት ትዝታ
በሰው የታሰረ በአምላክ ተፈታ
.
በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
47👍29🤩3
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- -----
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- -----

ፀጉሬ ሸብቶ፤ ነጥቶ ከበረዶ
ጀርባዬ ጎባብጦ፤ አጥንቴ ተወላግዶ
ጨብጬ ምርኩዜን፤ ጉልበቶቼ ፈሰው
በድዴ እየሳኩኝ፤ ጥርሶቼ ረጋግፈው
ተሸልመው አጉሊ፤ አይኖቼ ታክቷቸው
አንቱ እየተባልኩኝ ፤ እያሉኝ እሳቸው
.
.
.
እኔን የሚያሰጋኝ፤ እጅግ የምፈራው
በስተርጅና ዕድሜዬም፤ እንዳልከጅልሽ ነው።

        ✍️ ኒቆዲሞስ
                        @niko_nikodimos1

---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
---- ---- ---- ---- ---- ----- ----- ----- ----- ----- ----
     @getem
                   @getem
                                  @getem
👍36🔥87🤩1
ባልጀራዬ ላልኩት ሚስጥር ብዬ ብነግረዉ ፤
እሱም ለባልንጀራዉ አትንገር ብሎ ነገረዉ፤

ሲቀንስና ሲጨምር ለራሱ እንደተመቸዉ፤
ዞረ ዞረና ሚስጥሬ እኔ ጋር ደርሶ አረፈዉ።
................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍4510😁10
ብቻ አንተ ተናገር
.
( ለባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ
- በአፈ እሱ በአፈ እኔ )

ሠናይ ቅዳሜ !
.
( ሰሎሞን ንጉስ )
...
አጀብ የሱ ነገር
ደማም የሱ ነገር
ጨርሶ እሚወጥን
ፈጽሞ እሚጀምር
አንተ ያገር አድባር
አንተ የቅኔ ዛር
እስኪ አንተ ተናገር...
ኩለሄ ዘጥበብ ግጥማዊ መለኮት
እንክት !!
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
በብርህ ስትለቁጥ
ተሽሞንሙና መጣች
አስያ ጨብራሪት፡፡
ተመልከት በእነሆ መለኮት...
.
ዛሬ...
ተራው የኛ ነው ብለን
እቅኔ ቤት ገብተን ...
ስንጽፍ ስንገጥም እንበለ ቅኔ አጽም
ስንቱን ስንደጉሰው ለታይታ ለዝናው ፣
ምኑን አስችሎህ ተኛኻው ?
አንተ ያገር አድባር
እስኪ አንተ ተናገር
እንዳንባሰል መጣሁ ስትል
እንዳስያ ጨብራሪት ተወስውሰን
በራሳችን ቅኔ ታመን ፣
ምናለ ፣ ቅኔ ልከህ ብትፈውሰን
አቦ አንዴ ዘይረን፡፡
እስኪ አንዴ ተመልከት
ማነው ያስተማረህ የግጥም መለኮት፡፡
ታዲያ አውርድ በረከት
በእነሆ መለከት...
ይለኛል መለኮት ... በህሊና መስኮት
የናንተን አላውቅም ..የኔን የፈንታዬን
ድርሻዬን ልመልከት፡፡
ባልከኝ ቀኝ ቁሚያለሁ
ያንተን ለመመልከት፡፡
ብቅ በል በወዲህ...
እንደ ቅኔ መንገድ
እንደ መጥኔ ሞገድ
ታውቅ እንዲሁ ሌላ አገር
ሱሪ ማን ይጥፋል አንተ ስትናገር፡፡
አያ ሙሌ ነፍሴ ፣
ሰርክ አዲስ ነህ አንተ - የጠዋት ቅዳሴ፡፡
እርካብና መጣብር..ለጊዜው ቢያጥበረብር
አይን ሸብቦ ምላስ ቢያስገብር ...
ማን እንደ ነፍስ ክብር
ማን እንደልብ ...ድልብ ግብር ?
ብለኽኝ ስንቱን ጥፈኽው
ምኑን አስችሎህ ተኛኻው ?
ምን ጎሎበት ነፍሴማ
ካንተ የቅኔ ዛር ከተስማማ
አያ ሙሌ ነፍሴ የነግህ ቅዳሴ
አልረካሁትም ጣዕሙን
ብሰግር አግድሙን
ፍቅር ዘውዘው መውደድ ሽሙንሙን
እና...ምን ይሁን
አያ ሙሌ ጓዴ ፣
የነፍሳችን ምንዳ ሰማይ አረብቦ
ለምን ጎንበስ ቀና ለቁጣና ለርቦ '
እስኪ አንዴ ዘይረኝ ባለህበት አቦ ፡፡
.

በእኔ አንተ ተናገር...
እኔም ባንተ ልሳን እስኪ አንዴ ልናገር
ልምጣ ወይስ ልቆይ የቱ ይሻለኛል
ከነበረ ይልቅ የሞተ ይለያል
ሙሌ አንዴ ይለኛል አብርሃም ወንድሜ
ቆሞ የሚጠብቀኝ እኔ ተጋድሜ
ሰፋ አርገው ቦታውን መቼም መምጣቴ አይቀር
ከሞት አያስጥልም ወትሮም ኑዋሪን ማፍቀር..
ሙሌ ያገር አድባር
ሙሌ የቅኔ ዛር
ዝም ብለን እንስማህ
ብቻ አንተ ተናገር፡፡
..
አልረካሁትም ጣዕሙን
ብሰግር አግድሙን...
ፍቅር ዘውዘው መውደድ ሽሙንሙን
እና...ምን ይሁን
አያ ሙሌ ጓዴ ፣
የነፍሳችን ምንዳ ሰማይ አረብቦ
ለምን ጎንበስ ቀና ለቁጣና ለርቦ '
እስኪ አንዴ ዘይረኝ ባለህበት አቦ ፡፡
-/-

@getem
@getem
👍4215
ለማታዉቀኝ 2
.
በጥላሁን ዘፈን እጅግ ተመሰጬ፤
አንተኑ ስጠብቅ ከዳር ተቀምጬ፤

የማታዉቀዉ ፍቅሬን በልቤ አጥሬ፤
አለሜን ረሳሁ ሌላ አለም ፈጥሬ፤

ብትዘገይም እንኳ ዛሬ መጣህልኝ ፤
ፈገግ በልና ናፍቆቴ ይዉጣልኝ፤

አሁን ተነስቼ ማፍቀሬን ልንገረዉ፤
ልተንፍሰዉና መዉደዴን ይወቀዉ፤

እያልኩኝ.........

ከገዛ ልቤ ጋር ክርክር ገጠምኩኝ፤
ከራሴ ስሟገት መፍትሔን አጣሁኝ፤

ከሰመመን ማያልፍ የህልም ላይ ፍቅር፤
ተመልሶ አይምጣ በቆመበት ይቅር፤

ብዬ ወሰንኩና.......

የህልሜን እንጀራ ከመንገድ ጨርሼ።
ወደመጣሁበት ሄድኩኝ ተመልሼ።
.....................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍6733😢3👎1
እናርክሳት ወርቄን
.
የዓለምን ነገር - ከመናቁ ጽናት - ሊገልጽሽ ቃል ያጣ፥
ያ መናኝ ደራሲሽ - ይገርመኛል በጣም - እግዜርን ሲቆጣ።

ለሠዓሊሽ ሲባል - ስንት ዘር ይዘራ - ስንት ዛፍ ይገንደስ፥
ባ’ገር ሙሉ ሸራ - ጫካ፥ ሜዳ ሲሳል - አንቺን ለማወደስ?

የገላሽ አዝማሪ፥
የዜማ ተማሪ፥
አንድ ‘ያዜመልሽ - ቢራ ልፎ፥ ልፎ፥
አንጀት አበላሉ - ያለ’ድሜ ገርጅፎ።

ባ’ይን ካ’ካላትሽ - ዘግነው በሚኼዱ፥
ገላ ተመጽዋቾች - ምን ሞላው መንገዱ?

ይደንቀኛል በጣም - ይህ ኹሉ ግሳንግስ - በፍቅርሽ ሲማሰል፤
እኔስ ያንቺ ፍቅር - አይሞቀኝ፥ አይበርደኝ - አግኝቼሽ ነው መሰል።

By abere ayalew

@getem
@getem
@getem
24👍17
አውግተን ነበረ ጨዋታ በአይነቱ
ቀኑ እስኪጨልም እስኪነጋ ሌቱ
ዛሬ በአይኔ ላይ ድንገት ዞር አልክና
ትናፍቀኝ ጀመር ዳግም እንደገና።
ታማኝ ይሆን ውዴ ይህቺ ክፉ ብለህ
የጥላቻህን ሳር ስሜ ላይ ጎዝጉዘህ
ቀረሁባት እንጂ መቼ ቀረችብኝ
በሀሰት ሸንግላ ተጫወተችብኝ
ልቤን ባቀርብላት ገፍታ ነው የተወቺኝ
ወይስ ወይስ ልክ እንደኔ ባለፈ ትውስታ
ያ ሳቅ ደስታችንን አስበህ ለአንዳፍታ
ታስታውሰኝ ይሆን ሽረህ በይቅርታ
እኔ ግን ስምህን በክፉ አላነሳም
ባደረኩት ነገር እራሴን ብወቅስም
ተስፋ አደርጋለሁኝ በእኔ ቂም አቲዝም
ወሬ ከማበዛ በአጭር ቃል ልቋጨው
በውብ ቃል የተፃፍክ ሁሌ የማነብህ
የምወደው ድርሰት የትላንት ታሪኬ ነህ።

By #li_ya

@getem
@getem
@getem
25👍23😁4
የጠፋዉኝ መስሎኝ መራቄን አስቤ፣
።።።። ።።።።።። ጭራሽ።።።።።።።።
እየቀረብኩ መጣሁ መዓዛሽን ስቤ።
ፍፁም ፍፁም አልጠላሽም ፣
???????????ለምን??????????
ሰይጣን አልገዛሽም።
እውነት ፍቅር አለሽ ፣
ዉለታ የሚያሸሽ።
ድንገት በፍቅርሽ በር ፣
ሻማ አጥፍቼ ብቀር።
ለምን?እንዳትይ ከቶ እንዳትከፊ ፣
ሁሌም ሳትቀሪ ፍቅሬን ትተሽ ጥፊ።
እያፈቀርኩት ለምን እሸሻለዉ ፣
የምወደዉን ሰዉ ለምን እርቃለዉ።
እንዳትይይ ከቶ አታቀርቅሪ ፣
መሬት አልተጎዳም በሰማይ ስባሪ።

ገጣሚ :- papiel

@getem
@getem
@getem
👍3014🔥5👎3😱1🎉1
ይሄን አዳም አልነበርኩም (በ ይቴ)

በፍቅር ተቃኝተን
               ስለስሜት አብደን ባደረግነው ነገር
ከየት አመጣሽው
             ሴትነቴን ጣልኩት የሚል መደናገር
ይቺን ሴት ግን አልነበርኩም
ክት ነበር አካላቴ ማንም ደርሶ የማይገልጠው
ጨዋ ነበር ውብ ቀሚሴ በእማ ጥለት የተጌጠው
ላንተ ሲሆን ባንተ ምክንያት ተሰበረ የልቤ ቃል
ሽፍንፍኑን ገላለጥኩት ካንተ ምኔ ይደበቃል
ይችን ሴት ግን አልነበርኩም
ትይኛለሽ በመፀፀት ውስጥሽ እንጃ ምን እንዳለ
ከኔ ጋራ ባሳለፍሽው ምንን አጣሽ ምን ጎደለ
አየሽ
ማንነቱን ቃል እምነቱን 
               ሰው በምድር ባይለውጥም
እንዳመጣው እንዲመልስ 
               ለሰው አመል አይሰጥም
የቀሚስሽን ወግና ህግ 
                ፍቅር ገልጦ ቢሽረውም
ልብሽ ለምን ይከፋዋል 
             ላያስችለው አልሰጠውም
ባደባባይ ስታገድሚ 
              እልፉ በአይኑ ቢዘልፍሽም
በገላችን ተክሰሻል 
             መፅናኛውን አላጣሽም
አለነበርኩም ብሎ ማለት
              ከመሆንሽ አያርቅም
ያንቺው ብቻ አልነበረም
              የኔም ገላ ሌላ አያውቅም
ከምንሽ ተነሳሁ በምንሽ አበቃሁ
ህልም መስሎኝ ነበር ባንኜም አልነቃሁ
እንዳንቺ ለማለት 
ያሄን አዳም አልነበርኩም
              የሚል ሃረግ ስገነባ
አይኔ እንዳየው ይናፍቃል 
               ተናነቀው ጥቁር እንባ
ያሄን አዳም አልነበርኩም!
ቡታንታየን ከሄዋን ፊት 
               ስለስሜት አላላላም
ጨዋ ቀሚስ አራክሼ 
                በክብር ደም አላቀላም
እንጃ ብቻ ባንቺ ሲሆን 
                ያልነበርኩት ሆኜ አረፍኩት
የፈቀደው ውብ ገላሽን 
                   ልዳብሰው እጄን ላኩት
የሳመኝን ከንፈርሽን 
                 ደጋግሜ እኔም ሳምኩት
ግን 
ያሄን አዳም አልነበርኩም

እንዳልካድሽን የማልክደው 
                    ያረሳሽው የማረሳው
በፍቅራችን ድርሳን መጻ'ፍ 
                      በፊደሌ የማወሳው 
ያልነበርነው አዲስ እውነት
                       በገላችን የፈጸምነው
ይሄን አዳም እኔ ባልሆን
ይቺን ሴትም ባትሆኚ
                   የእድሜአችን ስጦታ ነው
ይሄን አዳም አልነበርኩም።

ይታያል ጌቴ (@gtmwustie)

@getem
@getem
@getem
@Yitayal05
👍8023🔥6
ትብረር

አገኘች መሰለኝ የልቧን ፍላጎት
ወፌ በራ ቀረች ኣልመጣች ከመስኮት.....
ቅር ቢለኝ እንጂ ለምጄ ያንን ሰዓት
ደስታዋ ነዉ ትብረር እርሷ ወፍ እኮ ናት።
ሁሉም ያስቀድማል ህልምና ምኞቱን፣.......
ለካስ መሽቷል ?
ታድያ ምን ልጠብቅ፣ ዘግቼ ልተኛ በር እና መስኮቱን።

By ፊራ ኦል

@getem
@getem
@paappii
47👍25🤩8🔥7
እንባ ሞልቶት አይኔን ፣
ሲያጨልመዉ ቀኔን።
ስትናፍቂኝ ጊዜ ህልሜ ይበላሻል።
ንግግሬ ለዛዉ ሀሳቤ ይጠለሻል።
ስትናፍቂኝ ጊዜ እበድ ያሰኘኛል ፣
ያላንቺ መተንፈስ ማልችል ይመስለኛል።
ግን የኔ ፍቅር ዉሸት ነዉ አይደል ፣
ያላንቺ ይሆናል ኑሮ መደላደል ?
እውነት እችላለሁ ?
እኔ አይመስለኝም ናፍቆትሽ ናፍቆኛል ፣
ይሄዉ ከናፈቅሽኝ 1 ቀን ሞልቶኛል።
እኔስ ብሶብኛል።


ገጣሚ:-papiel

@getem
@getem
@getem
57👍32😁13🔥8🤩1