ርዕስ......እንጃጃጃጃጃጃ
እንዴት ነህ አለሜ ልቤ ላይ የነገስከው
ሳላስብ ሳልወጥን ጉዳዬ የሆንከው።
እንግዲህ ልንገረህ መውደዴን በግጥም
አንብበህ ሳትጨርስ ወዴትም አትሄድም።
ጀመርኩኝ እንግዲህ....
በተከዳ ልብ ላይ እምነት በጎደለው
መውደድ ላልሆነለት ተስፋ ላስቀረጠው
የሰው ነገር በቅቶት ብቻን ለመረጠ
አንተን ባየ ጊዜ ለምን ደነገጠ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ 🤷🏾♀
ማመን መታመን ከንቱ ብሎ ላለ
አውቆ መታለሉን ሞኝ ለተባለ
ሰው ለምኔ ብሎ ብቻውን የዋለ
ልቤ ካንተ መሆን ስለምን ከጀለ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
ፍቅር የለም ብሎ አምኖ የደመደመ
ላይለምድ እና ላይወድ ከልቡ ያደመ
ካንተ ጋር ለመኖር ስለምን አለመ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
ስለሰው መጨነቅ ማሰብ የሰለቸው
ለእኔ ብቻ ብሎ መኖር የጀመረው
ለደቂቃ ሲያጣህ ለምን አስጨነቀው?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
እንዳልኩህ ነው ውዴ
ምክንያት ልደረድር ልቤን ብጠይቀው
ሌላ መልስ የለውም እንጃ ነው የሚያውቀው
ያለ አንዳች ምክንያት እኔም በማለውቀው
በቃ ተወደሃል ቁርጥህን እወቀው።
ሌላው ይቅርና
በዚህ ውድቅት ለሊት ሰው ሁሉ ተኝቶ
ግጥም የሚያፅፈኝ እንቅልፌን አስትቶ
ምን ይሆን ምክንያቴ አንተን ማስብበት
ምንድን ነው የሚባለው ፍቅር ወይስ ልክፍት?
እንጃጃጃጃጃ🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀
#li_ya
@getem
@getem
@paappii
እንዴት ነህ አለሜ ልቤ ላይ የነገስከው
ሳላስብ ሳልወጥን ጉዳዬ የሆንከው።
እንግዲህ ልንገረህ መውደዴን በግጥም
አንብበህ ሳትጨርስ ወዴትም አትሄድም።
ጀመርኩኝ እንግዲህ....
በተከዳ ልብ ላይ እምነት በጎደለው
መውደድ ላልሆነለት ተስፋ ላስቀረጠው
የሰው ነገር በቅቶት ብቻን ለመረጠ
አንተን ባየ ጊዜ ለምን ደነገጠ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ 🤷🏾♀
ማመን መታመን ከንቱ ብሎ ላለ
አውቆ መታለሉን ሞኝ ለተባለ
ሰው ለምኔ ብሎ ብቻውን የዋለ
ልቤ ካንተ መሆን ስለምን ከጀለ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
ፍቅር የለም ብሎ አምኖ የደመደመ
ላይለምድ እና ላይወድ ከልቡ ያደመ
ካንተ ጋር ለመኖር ስለምን አለመ?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
ስለሰው መጨነቅ ማሰብ የሰለቸው
ለእኔ ብቻ ብሎ መኖር የጀመረው
ለደቂቃ ሲያጣህ ለምን አስጨነቀው?
እንጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃጃ🤷🏾♀
እንዳልኩህ ነው ውዴ
ምክንያት ልደረድር ልቤን ብጠይቀው
ሌላ መልስ የለውም እንጃ ነው የሚያውቀው
ያለ አንዳች ምክንያት እኔም በማለውቀው
በቃ ተወደሃል ቁርጥህን እወቀው።
ሌላው ይቅርና
በዚህ ውድቅት ለሊት ሰው ሁሉ ተኝቶ
ግጥም የሚያፅፈኝ እንቅልፌን አስትቶ
ምን ይሆን ምክንያቴ አንተን ማስብበት
ምንድን ነው የሚባለው ፍቅር ወይስ ልክፍት?
እንጃጃጃጃጃ🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀🤷🏾♀
#li_ya
@getem
@getem
@paappii
👍94❤41🔥14😁7🤩3🎉2
ተከሳሽ ልብ
አዬ ጉድ ዘንድሮ....
አዬ ጉድ ዘንድሮ.........
ለካ እራስ ይተዋል የሰው ሰው አፍቅሮ
ከሳሽ አእምሮ
ፅድቅ አይሉት ሀጥያት ፍቅር ነው ሽፋኑ
መቀደሙን እረስቶ ደረቅ በመሆኑ
ስቃይ ተፈርዶበት ይዘጋ ውጥኑ
ዳኛ
ከሁለቱም ወገን እውነት እስከሚገኝ
ቀጥሉ ክርክሩን እስክታሳምኑኝ
ተከሳሽ ልብ
ተናገር ከተባልኩ እድል ከተሰጠኝ
ብዙ ምናገረው ምተርከው አለኝ
ባለሰብኩት ሰአት ምንም ባላቀድኩት
ከራሴ አስበልጬ አፍቅሬው አረፍኩት
ከሱ አንደበት የኔን ያህል ፍቅር ስላልነበረ
ከሳሽ ተብዬው ሲወቅሰኝ ውሎ ሞግቶኝ አደረ
ዳኛ
እሺ ከሳሽ ቀጥል
ከሳሽ አእምሮ
ለኔም እድል ካለኝ ከተሰጠኝ ተራ
ምኑንም ሳላስቀር ልዘርዝር በተራ
አልክድም እውነት ነው ከልብ ነው ማፍቀሩ
ከልብ መሆኑ ነው ትልቁ ችግሩ
በወደደው መጠን ፍቅር ካላገኘ
በፍቅር ማእበል ብቻውን ከዋኘ
እራሱን ዝቅ አርጎ ገዢ ካላገኘ
ታድያ ልክ አድለው...
የሰው ሰው አፍቅሮ ነው የተገኘ
ዳኛ
ተከሳሽ ምትለው አለ
ተከሳሽ ልብ
እንደው በኔ ቦታ ለእንዴ ብትቆሙ
ይገባቹ ነበር ጉዳትና ጥቅሙ
መች እኔ መሰለኝ የአስቅሮቱ ይሁዳ
አሎደውም ነበር እራሴን እስክከዳ
አለማመን ሆኖ እንጂ እራሴ የራሴን ነገር
ደስታዬን አጥቻለው እኔ እሱን ሳፈቅር
ከዚ በላይ ስቃይ ቅጣት ስለሌለ
በሉ ፍረዱብኝ ከሳሹ እንዳለ
ዳኛ
ምን ትላለህ ከሳሽ
ከሳሽ አእምሮ
ያው ባዝን ነው እንጂ ቢከፋኝ ብናደድ
ጭካኔ የለኝም በርሱ ላይ የሚፈርድ
ያሁኑ ጉዳቱ ከባድ ስለሆነ
ዳግመኛ እንዳይወድ የራሱ ያልሆነ
በትንሹም ቢሆን ይፈረድበትና
ይሰተካከል እንደው እናየዋለና
የመጨረሻ ፍርድ
ዳኛ
ሁሉን ሰምቻለው ሁሉን ታዝቢያለው
ለዚህ አይነት ጥፋት ቅጣቱን አውቃለዉ
እንደ እራሱ አርጎ የማይወደውን ሰው በመውደዱ
ቀላል አይምሰለው ይከብደዋል ፍርዱ
የጠፋውን ጊዜ እና እንባ ታሳቢ ተደርጎ
እራሱን እንዲያፈቅር እንደ ሰው አድርጎ
ያጠፋውን ጊዜ ለራሱ እየሰጠ
እራሱን እንዲወድ እጅግ የበለጠ
ስል ፈርጄበታለው ተገቢ ቅጣት
ይግባኝ የለሌው ነው በል እስቲ ተወጣት
መዝገብ ቤት ይመለስ ተዘግቷል ጉዳዩ
ድጋሚ አስኪከስ አፍቃሪ ነኝ ባዩ።
#Li_Ya
@getem
@getem
@getem
አዬ ጉድ ዘንድሮ....
አዬ ጉድ ዘንድሮ.........
ለካ እራስ ይተዋል የሰው ሰው አፍቅሮ
ከሳሽ አእምሮ
ፅድቅ አይሉት ሀጥያት ፍቅር ነው ሽፋኑ
መቀደሙን እረስቶ ደረቅ በመሆኑ
ስቃይ ተፈርዶበት ይዘጋ ውጥኑ
ዳኛ
ከሁለቱም ወገን እውነት እስከሚገኝ
ቀጥሉ ክርክሩን እስክታሳምኑኝ
ተከሳሽ ልብ
ተናገር ከተባልኩ እድል ከተሰጠኝ
ብዙ ምናገረው ምተርከው አለኝ
ባለሰብኩት ሰአት ምንም ባላቀድኩት
ከራሴ አስበልጬ አፍቅሬው አረፍኩት
ከሱ አንደበት የኔን ያህል ፍቅር ስላልነበረ
ከሳሽ ተብዬው ሲወቅሰኝ ውሎ ሞግቶኝ አደረ
ዳኛ
እሺ ከሳሽ ቀጥል
ከሳሽ አእምሮ
ለኔም እድል ካለኝ ከተሰጠኝ ተራ
ምኑንም ሳላስቀር ልዘርዝር በተራ
አልክድም እውነት ነው ከልብ ነው ማፍቀሩ
ከልብ መሆኑ ነው ትልቁ ችግሩ
በወደደው መጠን ፍቅር ካላገኘ
በፍቅር ማእበል ብቻውን ከዋኘ
እራሱን ዝቅ አርጎ ገዢ ካላገኘ
ታድያ ልክ አድለው...
የሰው ሰው አፍቅሮ ነው የተገኘ
ዳኛ
ተከሳሽ ምትለው አለ
ተከሳሽ ልብ
እንደው በኔ ቦታ ለእንዴ ብትቆሙ
ይገባቹ ነበር ጉዳትና ጥቅሙ
መች እኔ መሰለኝ የአስቅሮቱ ይሁዳ
አሎደውም ነበር እራሴን እስክከዳ
አለማመን ሆኖ እንጂ እራሴ የራሴን ነገር
ደስታዬን አጥቻለው እኔ እሱን ሳፈቅር
ከዚ በላይ ስቃይ ቅጣት ስለሌለ
በሉ ፍረዱብኝ ከሳሹ እንዳለ
ዳኛ
ምን ትላለህ ከሳሽ
ከሳሽ አእምሮ
ያው ባዝን ነው እንጂ ቢከፋኝ ብናደድ
ጭካኔ የለኝም በርሱ ላይ የሚፈርድ
ያሁኑ ጉዳቱ ከባድ ስለሆነ
ዳግመኛ እንዳይወድ የራሱ ያልሆነ
በትንሹም ቢሆን ይፈረድበትና
ይሰተካከል እንደው እናየዋለና
የመጨረሻ ፍርድ
ዳኛ
ሁሉን ሰምቻለው ሁሉን ታዝቢያለው
ለዚህ አይነት ጥፋት ቅጣቱን አውቃለዉ
እንደ እራሱ አርጎ የማይወደውን ሰው በመውደዱ
ቀላል አይምሰለው ይከብደዋል ፍርዱ
የጠፋውን ጊዜ እና እንባ ታሳቢ ተደርጎ
እራሱን እንዲያፈቅር እንደ ሰው አድርጎ
ያጠፋውን ጊዜ ለራሱ እየሰጠ
እራሱን እንዲወድ እጅግ የበለጠ
ስል ፈርጄበታለው ተገቢ ቅጣት
ይግባኝ የለሌው ነው በል እስቲ ተወጣት
መዝገብ ቤት ይመለስ ተዘግቷል ጉዳዩ
ድጋሚ አስኪከስ አፍቃሪ ነኝ ባዩ።
#Li_Ya
@getem
@getem
@getem
👍57❤17😢4🎉3😁2
ስለፋ ለዋልኩት ስወጣና ስወርድ
አገኝህ ይሆን ብዬ ዱካህን ሳሳድድ
ጥዬህ የማልበላው ክፍት ውሎ ገበታው
አይዋጥልኝም አንተ ያልባረከው አንተ ያልቀደስከው
ተስፋ ሳልቆርጥብህ ጥሎሽ ሄደ ስባል
ይመጣል እያልኩኝ አይኔን ሳልከድን ስዉል
የውሃ ጥም አቃጥሎኝ ሳልጠጣ ጾም ውዬ
ነገም ሌላ ቀን ነው በእንቅልፍ ያልፋል ብዬ
ድንገት ሸለብ ቢያረገኝ ለቅፅበት ለአንዳፍታ
በእውን የጠፋኸው የሆንክ የውሃ ሽታ
አየውህ በህልሜ ባመረ ፈገግታ
ገበታችን ቀርቦ ቤታችንም ደምቆ
የፍቅራችን ነገር ከነበረው ልቆ
መጣሁልሽ ፍቅሬ አላሳፈርኩሽም
ከእግዲህ በኋላ ላፍታ አልለይሽም
በይ እንኪ ጉረሺ በሞቴ እባክሽ
እኔም ደስ እያለኝ ሳልፈራ እና ሳልሸሽ
ድንገት ልጓርስ ስል ከእንቅልፌ ነቃው
ውዴ የኔ አለም መጠሪያህ ብዙ ነው
በአካል ብትቀርም በህልሜ ትመጣለህ
ይሄን አምኛለው
እርቦኛል በቃ ጥዬህ ልበላ ነው።
By #li_ya
@getem
@getem
@getem
አገኝህ ይሆን ብዬ ዱካህን ሳሳድድ
ጥዬህ የማልበላው ክፍት ውሎ ገበታው
አይዋጥልኝም አንተ ያልባረከው አንተ ያልቀደስከው
ተስፋ ሳልቆርጥብህ ጥሎሽ ሄደ ስባል
ይመጣል እያልኩኝ አይኔን ሳልከድን ስዉል
የውሃ ጥም አቃጥሎኝ ሳልጠጣ ጾም ውዬ
ነገም ሌላ ቀን ነው በእንቅልፍ ያልፋል ብዬ
ድንገት ሸለብ ቢያረገኝ ለቅፅበት ለአንዳፍታ
በእውን የጠፋኸው የሆንክ የውሃ ሽታ
አየውህ በህልሜ ባመረ ፈገግታ
ገበታችን ቀርቦ ቤታችንም ደምቆ
የፍቅራችን ነገር ከነበረው ልቆ
መጣሁልሽ ፍቅሬ አላሳፈርኩሽም
ከእግዲህ በኋላ ላፍታ አልለይሽም
በይ እንኪ ጉረሺ በሞቴ እባክሽ
እኔም ደስ እያለኝ ሳልፈራ እና ሳልሸሽ
ድንገት ልጓርስ ስል ከእንቅልፌ ነቃው
ውዴ የኔ አለም መጠሪያህ ብዙ ነው
በአካል ብትቀርም በህልሜ ትመጣለህ
ይሄን አምኛለው
እርቦኛል በቃ ጥዬህ ልበላ ነው።
By #li_ya
@getem
@getem
@getem
❤31👍15👎5😱3🔥2
አውግተን ነበረ ጨዋታ በአይነቱ
ቀኑ እስኪጨልም እስኪነጋ ሌቱ
ዛሬ በአይኔ ላይ ድንገት ዞር አልክና
ትናፍቀኝ ጀመር ዳግም እንደገና።
ታማኝ ይሆን ውዴ ይህቺ ክፉ ብለህ
የጥላቻህን ሳር ስሜ ላይ ጎዝጉዘህ
ቀረሁባት እንጂ መቼ ቀረችብኝ
በሀሰት ሸንግላ ተጫወተችብኝ
ልቤን ባቀርብላት ገፍታ ነው የተወቺኝ
ወይስ ወይስ ልክ እንደኔ ባለፈ ትውስታ
ያ ሳቅ ደስታችንን አስበህ ለአንዳፍታ
ታስታውሰኝ ይሆን ሽረህ በይቅርታ
እኔ ግን ስምህን በክፉ አላነሳም
ባደረኩት ነገር እራሴን ብወቅስም
ተስፋ አደርጋለሁኝ በእኔ ቂም አቲዝም
ወሬ ከማበዛ በአጭር ቃል ልቋጨው
በውብ ቃል የተፃፍክ ሁሌ የማነብህ
የምወደው ድርሰት የትላንት ታሪኬ ነህ።
By #li_ya
@getem
@getem
@getem
ቀኑ እስኪጨልም እስኪነጋ ሌቱ
ዛሬ በአይኔ ላይ ድንገት ዞር አልክና
ትናፍቀኝ ጀመር ዳግም እንደገና።
ታማኝ ይሆን ውዴ ይህቺ ክፉ ብለህ
የጥላቻህን ሳር ስሜ ላይ ጎዝጉዘህ
ቀረሁባት እንጂ መቼ ቀረችብኝ
በሀሰት ሸንግላ ተጫወተችብኝ
ልቤን ባቀርብላት ገፍታ ነው የተወቺኝ
ወይስ ወይስ ልክ እንደኔ ባለፈ ትውስታ
ያ ሳቅ ደስታችንን አስበህ ለአንዳፍታ
ታስታውሰኝ ይሆን ሽረህ በይቅርታ
እኔ ግን ስምህን በክፉ አላነሳም
ባደረኩት ነገር እራሴን ብወቅስም
ተስፋ አደርጋለሁኝ በእኔ ቂም አቲዝም
ወሬ ከማበዛ በአጭር ቃል ልቋጨው
በውብ ቃል የተፃፍክ ሁሌ የማነብህ
የምወደው ድርሰት የትላንት ታሪኬ ነህ።
By #li_ya
@getem
@getem
@getem
❤25👍23😁4