ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
አጃኢብ ነው አቦ
በቀደም ስስማት የእድሜ ልክ ስጋቴን ሞቴን ባንዴ ረሳሁ

ይሄው ዛሬ ስሜያት
ምድርም አልበቃችኝ ሰማየ ሰማያት ካምላክ ጋር ተገኘሁ

ጨዋታ ፈጥሬ የዓለሙን ፈጣሪ ሳስቀው አመሸሁ

በወጋችን መሃል ከ አምላኬ ጋራ

አንድ ሁለት ስንል ስንስቅ ስናወራ

እንዲሰምር ሃሳቡ ፍጥረትን አድምቆ ዉብ አርጎ እንዲሰራው

እፁብ ድንቅ እንዲሆን ፀሐይን አውርዶ ሳቅሽን እንዲሰቅለው

ከምድር አጥፍቶ አየር ነፋሳቱን

በዓለም እንዲናኘው እፁብ ትንፋሽሽን

ጨረቃን ሸሽጎ ሰማይ እንዲያኖረው አጃኢብ አይንሽን

ቤተስኪያን ተሰርቶ ፍጥረት እንዲሳለም እንዲስም ከፈርሽን

ስሸነግል ዋልኩኝ ሁሉም እንዲያሸተው ናርዶስ ጠረንሽን

                   ዘረ ሠናይ
              @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@paappii
👎4529👍22😁5😱1
ኑሮ ይባልና

ጤናዬን ጠየቁኝ አልኳቸው ደህና
አይደለሁም ብልስ ምን ይቀየርና
ሁሉም ነገር ከንቱ እየሆነ ወና
ደህና ነኝ እላለሁ ኑሮ ይባልና
እውነት ለመናገር እኔ ግን አሞኛል
ድርጊቶች በሙሉ ሰላሜን ነስቶኛል
እስቃለሁ እንጂ ደስታ እርቆኛል
ውስጤም ይረበሻል ቅር ቅር ይለኛል
በምንስ ልደሰት እንዴት ልሁን ደህና
ሰውን ማመን ከንቱ አልኩኝ እንደገና
ይሁና!!!
መልካም ቀናት አሉ እያልኩኝ ልፅናና
እታዛብ ይሆናል ይህም ቀን ያልፍና
ፀሀይም ቀን ወጥታ
ደግሞ ትለቃለች ለጨረቃ ማታ
ጊዜም ይቀየራል በጊዜ ይተካል
ቀናቶች ያልፋሉ ሌላም ቀን ይመጣል
ጨልሞ ይበራል በርቶም ይጨልማል
ለጊዜው ነው እንጂ ቢመሽም ይነጋል።
           
BY፦ LIONEL YOHANNES

@getem
@getem
@getem
43👍36🔥5😢3👎2🤩1
( ባዶሽን ..)
=============

ሰው ነኝና ....
ስጦታ ሳይ እረሳለሁ ደጉን ሰጪ
ይቅር አለም ከእጅ መንሻ አመሐ ጋር
ሁሌ አትምጪ
እስቲ አንዴ እንኳን ... መባ ትቼ
የምትበልጭው አንቺን ልይሽ
ባዶሽን ነይ
ቀልቤን ንዋይ እንዳይነጥቅሽ !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
28👍15🔥3
የተሰበረ ልብ

ጥፋት ሳይኖሮበት በደሉን ሳያውቀው
አካሌ ያለው ሰው በቅጽበት ሲርቀው
በህመም ላይ ክህደት ሲደራረብበት
የማይጠገን ልብ ይሰበራል ድንገት
የፍቅር ትርጉሙ ቅኔው ሳይገባቸው
ስንቶች ቶሎ ገብተው ሲወጡ አየናቸው
በሚያማልል ቅርበት ፍቅሩ እየጨመረ
ራስን በመክዳት ለሰው እየኖረ
በኢምንት ዘመን ነገር ተቀየረ
ያለፈው ትዝታ ጊዜያቱ ተረስቶ
ደካማው ሰውነት በፍቅር ተገዝቶ
ሲታመም አየነው ራሱን ሰውቶ
እምነት በማብዛቱ ለወደደው ሞቶ

በናሆም

@getem
@getem
@getem
👍5327🔥6😢6🎉1
❤️❤️የግራ ጎኔ❤️❤️

አንድ ያለኝን ልቤን
ሰርቀሽ ወስደሽብኝ

ቀልበ ቢስ ደንባራ
ልፍስፍስ አረግሺኝ

ልቤስ ይሁንልሽ
ውሰጂው ግዴለም

የግራ ጎኔን ግን
መልሺው የኔ አለም።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍4213😁11👎3
ለማታዉቀኝ
.
በቀናት መካከል ገና ያየሁህ 'ለት"፣
በሴኮንዳት እድሜ በትንሿ ቅፅበት፣

በሰዎች ተከበህ ስትስቅ አይኔ ገባህ፣
በዝምታ ሆኖ ልቤ አዜመልህ፣
የፍቅርን ሸማ ፈጥኖ ሸመነልህ፣

እዉነቱን ልንገርህ........

ከዛች ቀን ጀምሮ ጤናም የለኝ እንጃ፣
ሀሳቤ አንተዉ ነህ አወይ የኔ ፍርጃ፣

ለማታዉቀኝ ላንተ ደብዳቤ እፅፋለሁ፣
አልሳካ ቢለኝ ደግሜ እቀዳለሁ፣

ደግሞ ስትናፍቀኝ፣
ሳቅህ ትዝ ሲለኝ፣

ከቃኘሁህ ቦታ እመላለሳለሁ፣
አገኝህ ይመስል እጠባበቃለሁ።
........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍4415😁2
።።።።። እጠብቅሀለዉ።።።።።።።።።

እጠብቅሀለዉ ባረጅም ግድ የለኝ ፣
እጠብቅሀለዉ ህያዉ ፍቅር አለኝ።
ድንገት ብትቀር ወይንም ብታረፍድ፣
እጠብቅሀለዉ ቃሌ ሳይሰደድ።
አንተን ከህይወቴ ለማስወጣት ብጥር፣
እዉነት እሱ አ'ይበለኝ ይቅር።
አትምጣ ስትፈልግ እኔ ልጠብቅህ፣
ዘላለም አለሜን በህልሜ እንኳን ልይህ።
እጠብቅሀለዉ እስካለሁ በዚህ አለም፣
አንተን በመጠበቅ የሚያስቆመኝ የለም።

ጥያቄዉ ተመለሰ😊

ገጣሚ: freye ለ papiel

@getem
@getem
@getem
28👍15😁3👎2🔥2😱1😢1
የቱ ይሻልሻል ዘፈን ወይስ መዝሙር?

ባለም እንደሚኖር እልፍ ጭንቀት ከቦት
መከራና ስቃይ ጠዋት ማታ አዋክቦት
ህመሙን ለመርሳት ወይ ደግሞ ለማፈን
የቱ ይሻልሻል መዝሙር ወይስ ዘፈን?

ባለም እንደሚኖር በግዜሩ ተማምኖ
ቀን እንደሚገፋ ተማፅኖ ለምኖ
ትንሽ ለማራራት ይህን መሳይ አሽሙር
የቱ ይሻልሻል ዘፈን ወይስ መዝሙር?
ካለም ቀሽም ድብርት
ከጀሊሉ ቅጣት
ከሚሰማት እንቅልፍ
ተስፋ እያባነናት ነፍስሽ እንድትነቃ
የቱ ይሻልሻል መንዙማ? ሙዚቃ?

አዜምልሻለሁ
ባበቦች ፅሞና
በወፍ የሌት ጻማ
በልብ ትርታ
በቅጠል ሹክሹክታ
በነፋሳት ፉጨት በመብረቅ እልልታ
በወንዞች ፏፏቴ በንቦች ቅዳሴ
በብርሃን ድምጾች በፅልመት ቅላጼ
አዜምልሻለሁ
እዘፍንልሻለሁ
ዘምርልሻለሁ
በፍቅር እርምጃ
ገዳም ገብቶ ዘፈን
ባለም ሆኖ መዝሙር
የጽድቅ የኩነኔ የለውም ስልቻ
የመኖር ዓላማው
የመውደድ ዓላማ ው
ነፍስ ማትረፍና ተስፋን ማዳን ብቻ።

@getem
@getem
@paappii

By Yadel Tizazu
👍5620🔥4👎3😢1🎉1
ካጣሁሽ በኃላ ተለያይተን ከራቀሽ
ከሃሳብሽ ጠፍቼ ከሞትኩኝ በልብሽ
የኔን ገላ ከሻርሽ የአዲሱን አንግሰሽ
ከሰው ከተገኘሽ ትዝታሽን ረስተሽ
ሌላ ክንድ ካቀፍሽ የኔን እቅፍ ገፍተሽ
ባዳ ካስዳበስሽው ትንሽ መዳፍሽን
የተመኘሽ ሁሉ ካወቀው  ጠረንሽን
ላፍታ የከበበሽ ከሳመው ከንፈርሽን
የመጣ የሄደው ካልከሰከሰው ጣዕምሽን
ተፈፀመ አበቃ ከእንግዲህ ምን ቀረው
ብቻውን አይመጣም ሞትም ዘጠኝ አለው

                   ዘረ ሠናይ
              @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
👍3213🔥1
ስላለው መች ኖረ
                              
ሁሉም ያያል እንጅ ጣፋጭ መራራውን
በፈረቃ ሕይወት ማጣት ማግኘትን
ስላጣም አልጠፋ ስላለው አልኖረ
የከፋው ሰው ሞቶ የደላው መች ቀረ።

በ ናሆም

@getem
@getem
@getem
66👍19😢13
▷መለኪያ(ሲጠብቅ)◁

የሚለካበት ሰው ፤ የያዘው መስፈሪያ፤

በፈገግበት  ልክ ፤ ባረከው እራፊያ።

ካላየ እመባ ካይንህ ፤ ደም ካልሞላው አፍህ

ፊቱ መሬት ወድቀህ፤ ካልጨቀየ ልብስህ፤

ከሌለህ ማስረጃ ፤ለመምህ ምስክር ፤

መች ታመሀል ይላል...
እሱ የገመተህ፤

በሳከው ፈገግታ፣ በለበስከው ጫማህ።


      by @Kas_4set

@getem
@getem
@getem
👍277😢2
እኛን ሚዘክረን ቀናትን ሰይሞ
ከውልደት አንስቶ አላየን ፈፅሞ
ከግራ አጥንታችን እንዳልተገኛቹ
ለዝከረ በዓላት ስያሜ በቃቹ
.
8 ቁጥር ደላ ለአጥንቴ ክፋይ
ቀኗን ስታከብር እኔ ምለው ጠፋኝ
ለካስ ቀን የለኝም እኔ ምስኪን አዳም
ወትሮስ መች ሊታወስ የደኸየ አመዳም
.
ይኸው ደስ ይበልሽ ላጫፍር በብርቱ
ወንድ ልጅ አያውቀም አይደል ቀን ልደቱን
ፍኪበት ሸብርቂ ዕለትሽ ይቀደስ
ታሰጪኝ ይሆናል "የኔን ቀን" የደስ ደስ
.
እንኳን አደረሰሽ ሴትዬ ሴታችን
ለእኛም ቀን ይመጣል ከእርሱ ከአምላካችን
.
ለማንኛውም እንኳን አደረሳቹ 😏

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
👍3116👎8🤩5🔥1
/እስቲ አንቺ አውሺኝ/
ስንቱን ለንግግር ለሳቅ ለጨዋታ
ደግሞም ለመግባባት የቃላት ሁካታ፤
እንዳልደረደርኩኝ ከወሬ ማዕድ ላይ
እንዳደራረብኩኝ ነገረ በላይ በላይ፤
ልቤ የወደደሽን ዛሬ አንቺን ባገኝሽ
ልጥር ብከጅልም በቃል ላሳምንሽ፤
ከየት ይምጣ ቃሉ እንዲያ የዘረገፍኩት
ዛሬ ጠፋኝ ቅኔው ያኔ የዘረፍኩት፤
በምን ብናገር ይሆን አንቺን ምማርከው
ከምንስ ብጀምር እዴትስ ብተርከው፤
ላወራሽ እልና ምለው ይጠፋኛል
ስደርስ ካንቺ አጠገብ መናገር ያመኛል፤
ደሞ ሚያሳስበኛል!
በአፌ ተናግሬ ባይሽማማሽ ያልኩት ቃል
መዉደዴስ ባጭሩ ሳልጀምር ያበቃል፤
እላለው ከራሴ ጋር እያብሰለሰልኩኝ
ቆሞ ለታዘበኝ እብድ እየመሰልኩኝ፤
እና አንቺየዋ!
ከሆነ እስኪመጣ ቃል ከኔ ምትሸሺን
የሚያስማማንን ቃል እስቲ አንቺ አውሺኝ
#መሳይ ግርማ

@getem
@getem
@getem
👍4410😁4
ፆም
.
የነፍስ ቁስልን ፈዋሽ፣
ፀጋ መንፈስን አልባሽ፣

ላወቀባት ፍቱን መድኃኒት፣
የበጎ ምግባር ቱሩፋት፣

የስጋን ፍላጎት ፣
ምኞትና አምሮት፣

ክፋትን አክሳሚ ፣
ፍቅርን አታሚ ፣

ከጸሎት የምታዋድድ ፣
ፅድቅን የምታስለምድ ፣

የምትገራ አንደበትን ፣
የምትገስፅ ፍላጎትን ፣

ከአርምሞ ምታፋቅር ፣
ተጠራቅማ የምታስምር ።
.......................................
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
45👍13🔥2🤩1
#ለወንዶች_👨‍🦱

የተፈጠርሽባት ቀን💖💖

በዛች ቀን ነበረ አምላክ ለኔ ብሎ

ከግራ ጎኔ ላይ አጥንቴን ነጥሎ

           አንቺን የፈጠረሸ
   
በረቂቅ ጥበቡ ተጠቅሞ  የሰራሽ

ከውበት ደምግባት ከመልካሙም ምግባር   
                 አንዱንም ሳይነሳሽ::
:
:
:
እኔም ለዛች ቀን ምስጋናዬን ላቅርብ
              ለአምላክ ኃያሉ

አንቺን ለኔ ፈጥሮ  የህይወት ዘመኔን
             ስላረገው ሙሉ::

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️


               ✍️ @BEGITIMENAWGA


@getem
@getem
@getem
42👍30👎3🤩2
አልሃምዱሊላህ እግዚአብሔር ይመስገን
ከብዙ ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን
ጀመርነው በጋራ በፀሎት በሰላት
በፍፁም አብሮነት ሳንለይ በቀናት
.
ፆመን አስቀድሰን ማልደን ልናፈጥር
ወትሮም በለመድነው ባቆራኘን ፍቅር
ምህረትን በጋራ ልንለምን ከእርሱ
ፋሲካ ወ ረመዳን ይመስገን ደረሱ
.
ለሀገራችን ሰላም ለነፍሳችን ዕረፍት
በዱዓ በፀሎት የምንጠይቅበት
ዲኑን እንዲያወርሰን አላህ ፈጣሪያችን
ገሀነም እንዳይሆን ጥልቁ ማረፊያችን
.
በህብረት እንድንቆም እንዳንርቅ ከእሱ
ፋሲካ ወ ረመዳን ይመስገን ደረሱ

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
93👍40🔥5
▪️▪️ሳልሞት ተረሳው▪️▪️

ድካም ድካም ሲለኝ ሲያስቸግረኝ እንቅልፍ

ትንሽ ጋደም ብል ጎኔን ለማሳረፍ

አለመኖሬን ሚያይ አስታዋሽ ስላጣው

ሳልሞት እየተነፈስኩ በቁሜ ተረሳው::
:
:
:
ይሁና

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍7416😢11🔥8👎5
በቃኸኝ፤
በቃሽኝ፤

ብለን ብንዘጋዉ አርስቱን፤
የቡና መጠጫ መተረቻ አረጉን።

እንዳልተዋደዱ እንዳልተፋቀሩ፤
ከተማዉን ሁሉ አብረዉ እንዳልዞሩ፤
ምኞታቸዉ ከስሞ ተለያይተዉ ቀሩ።

እንዲህ እንዲህ እያሉ........
በጨዋታቸዉ ላይ ሲያሙን ይዉላሉ፤

ግና ያልገባቸዉ ፍፁም ያላወቁት፤
በጥሞና ሆነዉ ወርቁን ያልተረዱት፤

የማስመሰል ፍቅርን ዘዉሮ ከመምራት፤
መልካም ተመኝቶ እንዳልነበር መርሳት።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍6228🔥3😢3
❤️ አይጠፋም ❤️

ፀሀይ ብትጠልቅም
ጨረቃን ጠብቃ ተራዋን ብትለቅም

ቀናት ወራት ሆነው
ጊዜ ጊዜን ወልዶ አመታት ብከርምም

ዘመንም እንዳሻው
በፈለገው ፍጥነት ቶሎ ቢቀያየር

መቼም አይቀንስም
በፍፁም አይጠፋም ላንቺ ያለኝ ፍቅር

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
31👍27👎8