ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
እርዕስ ስጡት!

ጦሩን አስከትሎ መጣ ገሰገሰ
ሊገዛን ባርነት ሀገሩን አሰሰ
እምዬ ሚኒሊክ ያ ቆራጡ ጀግና
ኢትዮጵያ ስትፋርስ ቆሞ መች ያይና
እቴጌ ጣይቱ ልበ ሙሉ መሪ
ለጦር ግንባር ሰጠች አይደለችም ፈሪ
ባልቻ አባ ነፍሶ የደግኖች አለቃ
ጠላት አንበርክኮ ህዝቡን የሚያነቃ
ነበሩ ሌሎችም የነፃነት ታጋይ
ለታላቋ ሰንደቅ የሆኑት ተጋዳይ
ለሶስቱ ቀለማት ደማቸውን አፍስሰው
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን አርማ ይዘው
ጉዳይ ሳይኖራቸው ከአንድ ሀገር በቀር
አድዋን ድል አረጉ ሳይጠቅሱ ብሔር ዘር
አድዋ ነፃነት ነው ላልገባው አስረዳው
የሰላማችን ጥግ የነፃነት ጌጥ ነው
ጣይቱ ስትመራው ጦሩን ከፊት ቀድማ
ደግሞ ድል አረገች ብልጠቷን ተጠቅማ
እናማ አትልፉ
አታስቡ ይቅር ህዝቦቿን አትንኩ!
የማይፋቅ የማይሻር የደም ነው ታሪኩ ።
                
BY፦LIONEL YOHANNES

@getem
@getem
@getem
👍4319🔥7👎1
የኔታ

ሀሁ አቦጊዳ
ከፊደል ገበታ
ጭራቸውን ይዘው
ሲያስቀኙን የኔታ
ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብ
ሂ ሳልስ ሃ ራብዕ
ብለን የቆጠርን ተቀምጠን ስራቸው
አንደበት ያስፈቱን ሊቀ ቀለም ናቸው
.
ወንጌለ ዮሀንስ ውዳሴ ማርያሙን
ቅዳሴ ሰዓታት ስርዓተ ፆሙን
ገድለ መልዓክትን ገድለ ቅዱሳናት
ህማመ ፋሲካን የስቃዩን ወራት
ሰብስበው ያሳዩን መንገደ ሥላሴን
ባህረ ሀሳብ ቀመር አቋጣጠር ጊዜን
.
በፈጣሪ ያሉ ዓለም ያልገዛቸው
የኔታ የሁሉም ባለውለታ ናቸው

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
69👍44🔥4
( እንደ ፎቶሽ...)
=============

አሳዩኝ ሰሞኑን በፎቶ ስትስቂ
ጨረቃ ስትከልይ
ጀምበር ስታስንቂ !
አሉኝ መመረጧ አቤት መታደሏ
በጨለማው ዘመን
ስትፈካ መዋሏ ....
( እውነት እውነት እውነት)
እኔም በአንክሮ አየሁ
ምስልሽን በጥልቀት

ሳቅሽ ያምራል በጣም
ወደር አቻም የለው ...
ግና
ልቤን የሚታገል አንድ ጥያቄ አለው

ኑሮሽም አለሜ ልክ እንደ ፎቶው ነው ?

By @kiyorna

@getem
@getem
@getem
62👍28😢8😁5👎4🎉2
አያልፉ ሚመስሉ ጨለማ ቀናቶች፤
እንቅልፍ የሚነሱ ረጃጅም ሌቶች፤

ሁሉም አለፉና....

ብርሃን ፈንጥቆ ፅልመቱ ተረታ፤
ማዘን መከፋቱም ስቃዩም ተገታ፤

በእንባ የጠቆረዉ ፊታችንም ፈካ፤
አሮጌዉ ተሸኘ በአዲስ ቀን ተተካ።

..............ተመስገን..........

By ዔደን_ታደሰ

@getem
@getem
@getem
63👍30👎4🔥3
ሳቄን ፡ ነው የቀማኝ ፡ ጥሎኝ ነው ፡ የሄደው ፣
የምበርበትን ፡ ክንፌን ነው ፡ የሰበረው ፣
ያጎረሰው ፡ እጄን ፡
ያጠባሁት ፡ ጡቴን ፡ እሱ ነው ፡ የነከሰው ፣
እምነቴን ፡ የሸጠ ፡ ቃሉን ፡ ሰባሪ ፡ ነው ፣
ያከበረው ፡ ደጄን ፡
የነገሰበትን ፡ የፍቅር ፡ አክሊሌን ፣
የተገዛለትን ፡ ቅዱሱን ፡ ገላዬን ፣
ጠብቄ ፡ ያቆየሁትን ፡ የመዉደድ ፡ ኪዳኔን ፣
እጅግ ፡ የከበረ ፡ መስታወት ፡ እምነቴን ፣
ሰብሮ ፡ ነው ፡ የሄደው ፡ አንካሳውን ፡ ልቤን ፣

እያልሽ ፡ የኔ ርግብ ፡ ስታወሪ ፡ ሰማሁ ፣
ቀድሜሽ ፡ ከሄድኩኝ ፡ እንዴት ፡ ኋላሽ ፡ ቀረሁ ?

                   ዘረ ሠናይ
              @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
👍5916🔥4
አየሽ!
ሁላችንም
"ሰው ታከተኝ" - ብለን የምንተነፍሰው
ሰው እንዲሆንልን - ለምንፈልገው ሰው።
.
.
አየሽ!
ሁላችንም - እንደዚህ ዝለናል
ሰዎች ሲሰለቹን - ሰው ይናፍቀናል።
.
.
አየሽ!
ለኔና አንቺም
ርቀቱ የሰፋው - አልግባባ ያልነው
ምናልባት ስገፋሽ - እየፈለግሁሽ ነው።
.
.
እንግዲህ እወቂው!
ማኩረፍ መቆጣቴ - ብሶ ተባብሶ
ፈጣሪ ሲረሳኝ - ሰባት ሰማይ ለብሶ
ለመቅረብ ሳስፈራ
አስታውሺኝ አደራ!
.
.
በሬን ከሌላው ቀን አጥብቄ ስዘጋ!
መግባት ባትችይ'ንኳ ስታንኳኪ ይንጋ።


____
The last Eulogy
By Henock Bekele

@getem
@getem
@paappii
59👍47🤩2
አንድ ሞኝ አፍቃሪ.....
.
.
ጥርቅምቅም እዉቀቱን እያንጠፈጠፈ፤
ለሚወዳት እንስት እንዲህ ብሎ ፃፈ፤
.
አንቺ የኔ ፀሐይ....
.
ጨለማ ህይወቴን ፈንጥቀሽ ያበራሽ፤
ከልቤ ምጥገጥሚ ግጣም ኮከቤ ነሽ።
.
ከአፈር ያበጃጀሽ እግዜር እጁን ታጥቦ፤
ከሁሉም አብልጦ የሰራሽ አስዉቦ።
.
እንዲህ እንዲህ እያለ......
.
ቃላት አሰካክቶ ይገጥማል ይፅፋል፤
ዉበቷን ለመግለፅ ሲዳክር ይዉላል።

ከመቼ ጀምሮ?
.
እግዜሩም ላንድ ሰዉ ማድላትን ያወቀዉ ፤
እጁን ዉሃ ታጥቦ መፍጠር የጀመረዉ።
....................................
በዔደን ታደሰ ..@topazionnn

@getem
@getem
40👍33🔥8🤩5😱2😢2
"እማ" እና "አባቴ" ዘይቤው ተቀይሮ
የፍቅረኛ ዲስኩር ሆኖ አርፏል ዘንድሮ
.
ትላንት ላወቃት ሞትኩልህ ላለችው
የፍቅር ቴክስቶች ለደረደረችው
ውሉ ካልተስማማት የፍቅራቸው መንገድ
ሌላውን ፍለጋ ለምትረማመድ
አምጥቶ ይችራታል የእናቱን መጠሪያ
ትላንቱ በልጦበት ካለው መጀመሪያ
ደክሟት ሳትታክት ለዚህ እንዳላበቃች
በመጪ አጅ ሁሉ ሺ ጊዜ ተተካች
.
ሴቷም ለጥሪዋ ቃል ጠፍቶ ይመስል
አንዱን ጎረምሳዋን ከአባቷ እኩል ስትስል
ሞትኩኝ አበድኩልሽ ብሎ ለጠቀሰ
ያሳደገ አባት መጠሪያው እረከሰ
አዝሎ ባያጠባ ፀንሶ ባይወልድም
የአባት መጠሪያ ላወቁት አይሰጥም
.
ግና ምን ያደርጋል ግልብጥብጥ ዘመኑ
ካሳደጉት በላይ መጪዎች ገነኑ
ጊዜው አልበቃ ብሎ ስያሜ ነጠቁ
ካጎረሰው እኩል ጎራሾች መጠቁ

ሚገባውን ለማይገባው አትስጡ

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
96👍67🔥9😁5👎4😱2
እልፍ ደራሲያን.....

ቃላት አሽሞንሙነዉ ፤
ሐረጋት ጠንስሰዉ ፤

ፍቅርን ተረኩ፤
አብዝተዉ ሰበኩ።

እልፍ ሰዓልያን....

ባማረ ሸራቸዉ፤
ቀለማት ደባልቀዉ፤
በብሩሽ አቅልመዉ፤

ፍቅርን ተረኩ፤
አብዝተዉ ሰበኩ።

ምሁራን ተምረዉ፤
ጠቢባን ተጠበዉ፤

አብዝተዉ ቢፅፉ፤
ፅፈዉ ቢለፍፉ፤

ግና አንዳቸውም.....

ባለፉበት ዘመን፤
በለፈፉት መጠን፤

ፍቅር አያዉቁም፤
ኖረዉ አልተገኙም።
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍6823🔥6
ለስጦታ ሥዕል ማሳል ምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።

ወይም @gebriel_19 ላይ አናግሩኝ

@seiloch
@seiloch
👍4918😁5😱1
አድዋ
.
አንድ ተአምር አለ ከሶሎዳ ሰማይ ከተራሮቹ ስር፤
በሰዉኛ ልማድ በልሒቃን ምጥቀት የማይመረመር፤

የማንነት ስፍር ወሰን የተቸሩት፤
በአጥንትና በደም ከፍለው ያሰመሩት፤
አድዋ ድንበር ነው ደፍረው የማይረግጡት።

ከወይን ይልቅ ጣፍጦ የሚደጋግሙት፤
በግጥም አዋዝተው የሚያቀነቅኑት፤
አድዋ ዜማ ነው ሁሌ እየታደሰ የሚያንጎራጉት።

የህብረቃል ድምር ሰሙን የታጠቀ፤
በኩታ አከናንቦ ዕዉቀትን ያጨቀ፤
አድዋ ቅኔ ነው ወርቁን የደበቀ።

በባህረ ሀሳብ ያልተገኘ ስሌት፤
የአለት ምሰሶ የጊዜ ድንቅነት፤
አድዋ ዘመን ነው የትናንት ዛሬነት።

ባንዲራዋን አዝሎ ጦርሜዳ የወጣዉ፤
ቅንጣትም ሳይሰስት ራሱን የሰጠዉ፤
አድዋ ሰው ክቡር የሰው ልጅ ነው።
.............................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
42👍25
, ( ዓድዋ )


በጀመሯት ሴራ ችለው ላይወጧት
በነገር ነካክተው ንግስቷን አስቆጧት
የንጉስ ሳቁ እንጅ ጠቡ አይወደድም
ታጥቆ ከተነሳ ቁጣው አያራምድም

ፈረንጅ ወዳጅ መስሎ ገብቶ በጥበቡ
ታላቅ ሀገር ሊወርስ ሲያልም በምዕናቡ
የፍቅር ውል ሊያስሩ ፅፈው ሲያስነብቡ

ከንባቡ መሀል አንዲት አንቀፅ ልቃ
ጎልታ እየታዬሽ ከሁሉም ተልቃ
ውስጥን ስትከነክን በጀግና ልብ ጠልቃ
አልገዛም ስትል በድል መስኮት ዘልቃ
የንጉስ አዋጅ ተሰማ
ከዳር እስከዳር ዎኔው እዬታው
ጦሩን ቀድሞ አሰልፎ
ሀገሬው ከቶ እንዲቆዬው
ያገሬ ሰው እያለ ባማላጅ ስም ጠየቀው
ጦሩን ቀድሞ ሲመራ ፊት አውራሪ ገዬው
በሊቀ መኳስ አብሪነት
የድል ብርሃን ፈንጥቆ ታዬው
ኢጣሊያን ወሽመጡ መድፉ እስከሚሰበር
ድል አድርገው መጡ ጀግኖች ባንድ ጀንበር

ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን

@getem
@getem
@getem

By @Habtishe01
24👍17🔥1😱1
ነይ አስኪ ግቢብኝ


ገደል ግቢ ስልሽ 
    መልስሽ ነው የት ገደል
መሞትን መች አውቀሽ
    የለመድሽው መግደል
የለመድሽ ማኮስመን
     ያመቅሺው ማጠውለግ
መሻትን መፈለግን እንጂ  
     መች ለመድሽ መፈለግ

ግና ልግባ ካልሽኝ
ገደል ከጠዬቅሽኝ
ገብተሽ የማትወጭው
ቀድተሽ የማትጠጭው
በፍኝ የማትዘግኝው
እንደ ምፅአት ቀን ቶሎ ማተገኝው
ገደልስ አለልሽ  የኔ ልብ አዘቅት
ከእንጦሮጦስ  የተሻለው ጥልቀት

በያ 
እስኪነይ ግቢብኝ
በግርማሽ አስውቢኝ
በመንፈስሽ አሳብቢኝ
በታምርሽ ላፍራ
በገደልነቴ ልኩራ
አስኪ ነይ  ግቢብኝ 

ውስጤ የታመቀው  እሳት ሳይፈነዳ
ነይ እስኪ አረጋጊኝ  አድርጊኝ ባለ እዳ
ነይ አስኪ ግቢብኝ  ክፋት ሆኜ  ሳልፈስ 
ነይ አስኪ ግቢብኝ  ከንቱ ሆኜ ሳልፈርስ
አንች ውጨ ልርጋ   አኔን ሆኜ  ልርከስ
ነይ እስኪ ግቢብኝ.......

By kerim

@getem
@getem
@getem
43👍32👎7😱3😁2
#ለወንዶች 👨‍🦰

❤️ካጠገቤ❤️

አንቺን አንቺን ሲለኝ

መተኛት ቢከብደኝ

አይኔን እከድናለው
      እዚው ካጠገቤ
        ያለሽ እንዲመስለኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍3512😁9👎4
#ለሴቶች 👩

❤️ካጠገቤ❤️

አንተን አንተን ሲለኝ

መተኛት ቢከብደኝ

አይኔን እከድናለው
      እዚው ካጠገቤ
        ያለህ እንዲመስለኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍3922👎12😁9🔥3🤩2
#ለወንዶች 👨‍🦰


ጥያቄ አለኝ🙋‍♂

አይኔ ሲያይሽ......ስደነብር
ስታዪኝም..........ሳቀረቅር
ምፍለቀለቅ........ሀይ ስትዪኝ
ጎኔ ኖረሽ.........ምትናፍቂኝ
ኸረ እስቲ እንደው ልጠይቅሽ
መቼ ይሁን........ምትረጂኝ

አፈቀርኩሽ.........አልረሳሽም
ባፌ ብዬ...........ባልነግርሽም
አንዴት አንቺ እስከዛሬ
የኔ ስሜት.....አልገባሽም??

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
29👍17🤩10👎6🎉2
#ለሴቶች 👩


ጥያቄ አለኝ🙋‍♀

አይኔ ሲያይህ......ስደነብር
ስታየኝም..........ሳቀረቅር
ምፍለቀለቅ........ሀይ ስትለኝ
ጎኔ ኖረህ.........ምትናፍቀኝ
ኸረ እስቲ እንደው ልጠይቅህ
መቼ ይሁን........ምትረዳኝ

አፈቀርኩህ.........አልረሳህም
ባፌ ብዬ...........ባልነግርህም
አንዴት አንተን እስከዛሬ
የኔ ስሜት.....አልገባህም??

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
61👍26😁7👎2🔥2
🤔🤔ለልጄ ቸገረኝ🤔🤔

ለወለድኩት ልጄ ለሆንኩት አባቱ

የእውነት ከብዶኛል ለሱ ስም ማውጣቱ

ይህንን ስላቹ
ከሆነ ገብቷቹ
ያገር ፓለቲካ

ከእምነት ከብሄር የማይነካካ

ያንዱ ባለጊዜ ሲቀየር ስርዓት

ሰውን የማይዳርግ ለሞት እና እስራት

እንዲሁም ለስደት

ስም ታቁ እንደሆን ልጄን ምጠራበት

እስቲ መላ በሉኝ

እኔንም ከሀሳብ ከጭንቀት ገላግሉኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
👍81🔥1816😢9🎉2🤩2
ቃየልን ባስናቀ እርኩስ ተፈጥሯችን
እያለን ስንጮህ ተው ስማን ጌታችን
አወይ ድፍረታችን!!
.
አወይ ድፍረታችን
ሳንነፃ መባ ሳንነፃ ፀሎት
ቢወደን ነው እንጂ ያለነው በህይዎት
ሞተን ምናርፍበት
ቆመን ምንረግጥበት ግራ ገብቶን ሳለ
በየትኛው ልባችን ነፍሳችን ተሳለ?
.
እንቆቅልሽ ሆነን ሚፈታንን ቀብረን
ልክ እንደ ብፁሀን እንለምናለን
.
ግና ብናስተውል
ለዳቢሎስ እንኳን እናሳዝናለን

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@paappii
46👍29🤩2🔥1