ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ኑ ትውልድ እንገንባ!

#ሰበታ የምትገኙ 0932540523/ያሬድ ለማ/ ፣ 0921421493/ያብስራ ካሳ/

#አዲስ_አበባ የምትገኙ 0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/፣ 0924140293/መባ/

#መቐለ የምትገኙ 0912178520/ኤርሚያስ ደጀኔ/: 0923602445/ፊራኦል መስፍን/


#ድሬዳዋ የምትገኙ 0915034762/መሃሪ/

#አዳማ የምተገኙ 0949377735/ሰላም/

#ደብረብርሃን የምትገኙ 0941907303/ሄኖክ ዳኜ/


#ሀዋሳ የምትገኙ +251926429534/ተስፋ/፣ +251935932153/ብስራት/

በሁሉም የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630

የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች በትልቁ አሻራችሁን እንደምታሳርፉ ምንም አንጠራጠርም!


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ ቅንድል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር
@KendelM
@KendelM
👍1
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_2_|_Kendel_edited10.pdf
6 MB
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት
#ቅፅ-2 #ቁጥር-1

#አዲስ ይዘት፣
#ልዩ አቀራረብ
#ሚያሸልሙ_ጥያቄዎች_የተካተቱበት



💵ፓኬጅ ከገዙ 60 ሳንቲም ብቻ💵

ቅን ፣ ምክንያታዊ እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ !!!
@KendelM
@KendelM
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_2_|_Kendel_edited10.pdf
6 MB
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት
#ቅፅ-2 #ቁጥር-1

#አዲስ ይዘት፣
#ልዩ አቀራረብ
#ሚያሸልሙ_ጥያቄዎች_የተካተቱበት



💵ፓኬጅ ከገዙ 60 ሳንቲም ብቻ💵

ቅን ፣ ምክንያታዊ እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ !!!
@KendelM
@KendelM
#አዲስ_ቀን_ይመጣል
እስከዚያው ግን ፈ ገ ግ.....
.
.
.
ሰሞኑን ሰሞኑን፤
ሳቅሽ ግራ ገባኝ፤
ኩርፊያሽ ግራ ገባኝ፤
እንደ ህፃል ልጅ አመል ይገለባበጣል፣
እንባሽን አይቼ፤
ላባብልሽ ስቀርብ ያ ሳቅሽ ይመጣል።

ሰሞኑን ሰሞኑን፤
ያ ገራገር አይንሽ፤
እልፍኝ ቤቴ ልብሽ፤
ልጅ ነፍሴን የገራ በፍቅር የጠመደ፣
በሂያጅ እግር ሊዳኝ፤
መንገድ ላይ ተገኘ ሌላ እንደወደደ፣
.............................ሌላ እንደለመደ።

እኔ እንደሁ እኔ ነኝ፤
በድርድር ጥርሶችሽ በሳቅ ለዛሽ በኩል፣
በአይን አከዳደንሽ በአፍንጫሽ ትክክል፣
በከንፈርሽ ጣዕም ነፍሴን የምፈልግ፣
ቅፅበት ስትስቂ ሶስት ቀን የምፈግግ።
ሚስኪንሽ ነኝ ባዶ ምርኮ ለአይንሽ ቀለም፣
በሳቅ ተጀምራ፤
በማኩረፍ የምታልፍ አንቺን ናት የኔ አለም።

እንጂማ፤
እንጂማ፤
ፀሃይ ሳቅሽ ገርበብ፣
ሙቅ ፈገግታሽ ለዘብ።
አይንሽ እርግብ እርግብ ሸሸት ሸሸት ካለ፣
ከእንባዬ መሃል፤
ለአይን የከበደ ጠብደል እንባ አለ።
ጠብደል ህመም አለ።
በመኖር የታሸ፤
ከህማም የሸሸ መዳን የሚመስል፣
ከቁስሌም ማዶ፤
አድሮ የሚደማ አለ ሌላ ቁስል።

እኔ እንደሁ እኔ ነኝ፤
አንቺን ከለመደው፤
ከገላዬ በላይ፤
መዓዛሽ ካወደው፤
ከግምጃዬ በላይ።
በላብ የነተበ ሌላ ያደፈ ግምጃ፣
ጥርስሽ ፊት ከነሳኝ፤
መሰንበትስ ወዴት መክረሜንም እንጃ።

ከኖረበት ጎሬ፤
መቼስ ቀን ካመጣው የእትብቴን እጣ፣
አምላክ ካበደረሽ፤
ነፍስ የሚያርገበግብ እንዲህ ያለን ቁጣ።
እንቢ አይባል ነገር፤
አርምሞ እያበዛሁ እኖራለሁ ግዴን፣
"አዲስ ቀን ይመጣል፤"
"ያልፋል" እለዋለሁ ሆድ የባሰው ሆዴን።
.
.
"አዎ ይህም ያልፋል ይመጣል አዲስ ቀን፣
እስከዚያው ድረስ ግን......
ሞት ያከለን ህመም እናልፋለን ስቀን።"
".............እስቲ ትንሽ ፈገግ...........😊"

ዓቢይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
33👍31🔥2😢2