Kamest 4 Kilo
Yohannes_Lawgaw
✨"አሁን በዚ ሰአት ቀጭን ጓደኛዋን በስካር ደፍሬ ደውዬ ላናግራት?? ቀልዱን ድገሚልኝ እባክሽ እኔም ልሳቅ ብዬ ልለምናት??"
'ካምስት 4 ኪሎ ' አንድ ሺ...እርምጃ ነው!✨
የ ሰለሞን ሳህለን ፅሁፍ ዮሀንስ_ላውጋው በ ውብ አቀራረብ ከፍ ባለ ጥራት እንዲህ አቅርቦታል!✨
#High_quality
@getem
@getem
@getem
'ካምስት 4 ኪሎ ' አንድ ሺ...እርምጃ ነው!✨
የ ሰለሞን ሳህለን ፅሁፍ ዮሀንስ_ላውጋው በ ውብ አቀራረብ ከፍ ባለ ጥራት እንዲህ አቅርቦታል!✨
#High_quality
@getem
@getem
@getem
#የውብ ዳር !
.
ስቤ በምለቀው ጭስ መሀል
ገፅታሽ ተስሏል
ከጭሱ ቅርፅ ጋር ...
የኔዋ የውብዳር.. .
ትሽከረከሪያለሽ.. .
አንዳንዴም
ቀጥ ባለ መስመር ፏለሽ ትከንፊያለሽ።
.
ይሄ ጭሰት ማለት
ያንቺ ተምሳሌት ነው...
ከህይወት ኑባሬ የተቀዳ እውነት
አንዴ በቀጥታ አንዳንዴ በክበብ
ፔንዱለም ዓመልሽ የተከተበበት ።
.
#ይሄ ባንኮኒው አናት ላይ
ተቀምጦ የሚታይ
የድራፍት ብርጭቆ...
የአልኮል መጠጡን በአረፋው ደብቆ
ምሉዕ ነኝ እያለ ጎድሎ የቀረብኝ
ፍቅርሽ ነው መሰለኝ
ሳላጣጥመው ነው ቀድሞ ያለቀብኝ።
.
#አረፋው ሲከስም ...አየሁት ሲጋመስ
በዚህ ምልከታ ነው ቀዬሽ ዘንድ የምደርስ።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር !
ደግሞ በሁለቱ ... በሱሳቸው ስሌት
በስካር ስናውዝ.. . ስመሰጥ በጭስ ቤት
ካሰላሁት ሁሉ ገርሞ የሚደንቀኝ
ዛሬ አጭሰሀል
ዛሬ ጠጥተሀል ይበቃል የሚለኝ
ያ ክፉ ልማዴ.. .የርኩሰት መካሪ
ነገ አዲስ ሆኖ ... ሲልክብኝ ጥሪ
ትናንት አጭሻለሁ
ትናንት ጠጥቻለሁ
ብዬ አሻፈረኝ.. . አልደግምም አልልም
ፍቅርሽም እንዲያ ነው... መቋረጥ አይወድም
ትናንት ጭስ ነች እያልኩ እንዳጨስኩኝ ሁሉ
ትናንት ብርጭቆ ነች እያልኩ እንደጠጣሁ ሁሉ
.
ዛሬም ጭስ ቤቴ ውስጥ ዛሬም ግሮሰሪ
በፍቅርሽ ፖስታ በመውደድሽ ጥሪ
የሰው ነጭ በሞላው
መንገድ ዘንድ ፈልጌሽ ላትመጭ ስትቀሪ.. .
.
ድራፍት እየጠጣሁ ሲጃራ እያጨስኩኝ
አንቺን እየሳልኩኝ
ይህቹት የውብዳር
ይኸው ገፅታዋ
አቤት ከባድ ህመም የገዘፈ ዋይታ
ዋ !
እያልህ ትጮሀለህ ይለኛል ታዛቢ
የስካር መዝጋቢ !
።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር
አንቺ የኔ ጭሰት.. .አንቺ የኔ ስካር.. .
ከነ በስቲያም ላይ በሚኖረኝ አዳር
ደግሜ ልጮህ ነው እንደ እብድ መንገድ ዳር።
.
አላሳዝንም ወይ ?
...... ሚካኤል አስጨናቂ
@getem
@getem
@paappii
https://tttttt.me/MichaelAschenakipoems
.
ስቤ በምለቀው ጭስ መሀል
ገፅታሽ ተስሏል
ከጭሱ ቅርፅ ጋር ...
የኔዋ የውብዳር.. .
ትሽከረከሪያለሽ.. .
አንዳንዴም
ቀጥ ባለ መስመር ፏለሽ ትከንፊያለሽ።
.
ይሄ ጭሰት ማለት
ያንቺ ተምሳሌት ነው...
ከህይወት ኑባሬ የተቀዳ እውነት
አንዴ በቀጥታ አንዳንዴ በክበብ
ፔንዱለም ዓመልሽ የተከተበበት ።
.
#ይሄ ባንኮኒው አናት ላይ
ተቀምጦ የሚታይ
የድራፍት ብርጭቆ...
የአልኮል መጠጡን በአረፋው ደብቆ
ምሉዕ ነኝ እያለ ጎድሎ የቀረብኝ
ፍቅርሽ ነው መሰለኝ
ሳላጣጥመው ነው ቀድሞ ያለቀብኝ።
.
#አረፋው ሲከስም ...አየሁት ሲጋመስ
በዚህ ምልከታ ነው ቀዬሽ ዘንድ የምደርስ።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር !
ደግሞ በሁለቱ ... በሱሳቸው ስሌት
በስካር ስናውዝ.. . ስመሰጥ በጭስ ቤት
ካሰላሁት ሁሉ ገርሞ የሚደንቀኝ
ዛሬ አጭሰሀል
ዛሬ ጠጥተሀል ይበቃል የሚለኝ
ያ ክፉ ልማዴ.. .የርኩሰት መካሪ
ነገ አዲስ ሆኖ ... ሲልክብኝ ጥሪ
ትናንት አጭሻለሁ
ትናንት ጠጥቻለሁ
ብዬ አሻፈረኝ.. . አልደግምም አልልም
ፍቅርሽም እንዲያ ነው... መቋረጥ አይወድም
ትናንት ጭስ ነች እያልኩ እንዳጨስኩኝ ሁሉ
ትናንት ብርጭቆ ነች እያልኩ እንደጠጣሁ ሁሉ
.
ዛሬም ጭስ ቤቴ ውስጥ ዛሬም ግሮሰሪ
በፍቅርሽ ፖስታ በመውደድሽ ጥሪ
የሰው ነጭ በሞላው
መንገድ ዘንድ ፈልጌሽ ላትመጭ ስትቀሪ.. .
.
ድራፍት እየጠጣሁ ሲጃራ እያጨስኩኝ
አንቺን እየሳልኩኝ
ይህቹት የውብዳር
ይኸው ገፅታዋ
አቤት ከባድ ህመም የገዘፈ ዋይታ
ዋ !
እያልህ ትጮሀለህ ይለኛል ታዛቢ
የስካር መዝጋቢ !
።
.
#ይታይሽ የውብ ዳር
አንቺ የኔ ጭሰት.. .አንቺ የኔ ስካር.. .
ከነ በስቲያም ላይ በሚኖረኝ አዳር
ደግሜ ልጮህ ነው እንደ እብድ መንገድ ዳር።
.
አላሳዝንም ወይ ?
...... ሚካኤል አስጨናቂ
@getem
@getem
@paappii
https://tttttt.me/MichaelAschenakipoems
👍1
አምሮ መቅረት
***
አልበቃኝም ገላ
አልበቃኝም ምድር
አልበቃኝም ጊዜ
አልበቃኝም አየር
አልበቃኝም ሐሳብ
አልበቃኝም ታ'ምር
ለአጉል አለሁ ብቻ
ሁሉም አምሮ ሊቀር።
@ዲበኩሉ ጌታ
#የምድር_ዘላለም
@getem
@getem
@getem
***
አልበቃኝም ገላ
አልበቃኝም ምድር
አልበቃኝም ጊዜ
አልበቃኝም አየር
አልበቃኝም ሐሳብ
አልበቃኝም ታ'ምር
ለአጉል አለሁ ብቻ
ሁሉም አምሮ ሊቀር።
@ዲበኩሉ ጌታ
#የምድር_ዘላለም
@getem
@getem
@getem
👍1👎1
" #መልካም_የእናቶች_ቀን !!!"
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
.
.
የሽሽግ መውደዴ፤
የክፉ ቀን ስንቄ ፍላፃ ውበቴ፣
እልፍ ዘመን እንጂ፤
አንድ ቀን 'ማይበቃት እኝኋት እናቴ፡፡
.
.
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ረጅም እድሜና ጤና ለእናቶቻችን !!!
🙏🙏🙏
✍ "ዐብይ"
@getem
@getem
@abiye12
.
.
የሽሽግ መውደዴ፤
የክፉ ቀን ስንቄ ፍላፃ ውበቴ፣
እልፍ ዘመን እንጂ፤
አንድ ቀን 'ማይበቃት እኝኋት እናቴ፡፡
.
.
ረጅም እድሜና ጤና ለእናቶቻችን !!!
🙏🙏🙏
✍ "ዐብይ"
@getem
@getem
@abiye12
👍1
የፍቅር መድረሻው!
(አኑ)
ሂድ ስትለው መጣ፣
ውረድ ሲባል ወጣ፣
ውጣ ሲባል ሲወርድ፣
አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣
ከራሱ ተጣልቶ፣
ከራሱ ተኳርፎ፣
ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ
(ያቺ ሴት)
የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች
በፍቅሩ የከነፈች፣
ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት!
እሱም የሚያፈቅራት
ከጎና ማይጠፋ
ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት!
አንድ'ዜ በሀይቅ
አንድ'ዜ በየብሱ
አንድ'ዜ በአየር
ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር።
(ዛሬ)
ተጣልተው
ተኳርፈው
ደግሞም ተለያየተው
አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው
ጎጆውን አፍርሰው
ተነጣጥለው አሉ
ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ።
(እሱ)
ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ
ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ
( ሁለት ነው ያዘዘው)
አንደኛው ለራሱ
ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ
እርግጥ ነው የለችም
በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ
(እንዲኽ ነው ሀሳቡ)
ትዕዛዙ እስኪመጣ
ጋዜጣ ያነባል
የጋዜጣው ርዕስ
ጥያቄ ይጠይቃል
(ጥያቄው)
ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል?
ከርዕሱ በታች
የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣
(እዚህ ጋር)
ቄሱም ሆነ ሼኹ
የፃፉትን ፅህፈት፣
የሰበኩት ስብከት፣
ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት!
(እውነቱ)
የቄሱም የሼኹም
የኣላህም የእግዜሩም
ቃሎች ሲመረመር
ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣
( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል
ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል)
ሳይጠጣው ተነሳ
ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ
ሚጓዝበት መንገድ
ማይሽር ፣ የማይጠፋ
ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ።
እርምጃው ፈጠነ
ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል
ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣
በሯን ደበደበ፣
እየሮጠች ወጣች፣
የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል
የምትለው ጠፋት
ፍርሀት ነብሷን ዋጣት
እ
ሱ
ተንበርክኳል
እግሯ ስር ተገኝቷል
በስስት ፣ በፍቅር
ሽቅብ አይኗን ያያል
ይቅርታ የሚል ቃል
ከአንደበቱ ይፈልቃል
እ
ሷ
አለቀሰች
አይኗን እንባ ወረሰው፣
አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣
ተነሳ አቀፈቹ
ሲያያት ሳመቹ
አ
ፈ
ቅ
ር
ሀ
ለ
ው
አለች
እየሳቀች
ጋዜጣውን አየ
ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣
ይኽን አስታውሶ
ፊቱን ብርሀን ሞላው።
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
(አኑ)
ሂድ ስትለው መጣ፣
ውረድ ሲባል ወጣ፣
ውጣ ሲባል ሲወርድ፣
አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣
ከራሱ ተጣልቶ፣
ከራሱ ተኳርፎ፣
ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ
(ያቺ ሴት)
የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች
በፍቅሩ የከነፈች፣
ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት!
እሱም የሚያፈቅራት
ከጎና ማይጠፋ
ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት!
አንድ'ዜ በሀይቅ
አንድ'ዜ በየብሱ
አንድ'ዜ በአየር
ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር።
(ዛሬ)
ተጣልተው
ተኳርፈው
ደግሞም ተለያየተው
አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው
ጎጆውን አፍርሰው
ተነጣጥለው አሉ
ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ።
(እሱ)
ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ
ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ
( ሁለት ነው ያዘዘው)
አንደኛው ለራሱ
ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ
እርግጥ ነው የለችም
በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ
(እንዲኽ ነው ሀሳቡ)
ትዕዛዙ እስኪመጣ
ጋዜጣ ያነባል
የጋዜጣው ርዕስ
ጥያቄ ይጠይቃል
(ጥያቄው)
ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል?
ከርዕሱ በታች
የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣
(እዚህ ጋር)
ቄሱም ሆነ ሼኹ
የፃፉትን ፅህፈት፣
የሰበኩት ስብከት፣
ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት!
(እውነቱ)
የቄሱም የሼኹም
የኣላህም የእግዜሩም
ቃሎች ሲመረመር
ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣
( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል
ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል)
ሳይጠጣው ተነሳ
ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ
ሚጓዝበት መንገድ
ማይሽር ፣ የማይጠፋ
ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ።
እርምጃው ፈጠነ
ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል
ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣
በሯን ደበደበ፣
እየሮጠች ወጣች፣
የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል
የምትለው ጠፋት
ፍርሀት ነብሷን ዋጣት
እ
ሱ
ተንበርክኳል
እግሯ ስር ተገኝቷል
በስስት ፣ በፍቅር
ሽቅብ አይኗን ያያል
ይቅርታ የሚል ቃል
ከአንደበቱ ይፈልቃል
እ
ሷ
አለቀሰች
አይኗን እንባ ወረሰው፣
አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣
ተነሳ አቀፈቹ
ሲያያት ሳመቹ
አ
ፈ
ቅ
ር
ሀ
ለ
ው
አለች
እየሳቀች
ጋዜጣውን አየ
ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣
ከፍቅር ለራቀ
የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣
ይኽን አስታውሶ
ፊቱን ብርሀን ሞላው።
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
👍2
#ማነው?
፡
፡
፡
በፈጣሪ አምሳል የተበጀን ገላ
ህይወቱ እንድታልፍ በቃታ በቢላ
ካሰቃዩት ቧላ
የመዳንን ምስጢር ፍቅርን ወዲያ ጥለው
ቤንዚን አርከፍክፈው በቁም ሳለ አቃጥለው
ሞቶ ያሸነፈን ያን መሲ ዘንግተው
የተሰጣቸውን ህያው ቃሉን ትተው
ግዳይ እንደጣሉ ደረት እየነፉ
ጎምለል ቀብረር ብለው በአደባባይ ሲያልፉ
ከትቢያ ተናንሶ የሰው ሰውነቱ
ሀገሬ ላይ ባየው ባይኔ በብረቱ
የወገኔ ሲቃ ከአርያም ሲደርስ አድማስ ሲያስተጋባ፣
ወደ ውስጤ አልቅሶ ልቤም የደም ዕምባ፣
እንደዚህ የሚቀኝ መልስ ያጣ ጥያቄ ከነብሴ ውስጥ ገባ።
፡
፡
እንዲ ይላል ጥያቄው
መልሱን ምን አውቄው
፡
፡
እስኪያስረሳን ድረስ የመቅደሱን እጣን
እውን ግን ሚያባላን ስልጣን ነው ወይ ሴጣን?
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb
@getem
@getem
@getem
፡
፡
፡
በፈጣሪ አምሳል የተበጀን ገላ
ህይወቱ እንድታልፍ በቃታ በቢላ
ካሰቃዩት ቧላ
የመዳንን ምስጢር ፍቅርን ወዲያ ጥለው
ቤንዚን አርከፍክፈው በቁም ሳለ አቃጥለው
ሞቶ ያሸነፈን ያን መሲ ዘንግተው
የተሰጣቸውን ህያው ቃሉን ትተው
ግዳይ እንደጣሉ ደረት እየነፉ
ጎምለል ቀብረር ብለው በአደባባይ ሲያልፉ
ከትቢያ ተናንሶ የሰው ሰውነቱ
ሀገሬ ላይ ባየው ባይኔ በብረቱ
የወገኔ ሲቃ ከአርያም ሲደርስ አድማስ ሲያስተጋባ፣
ወደ ውስጤ አልቅሶ ልቤም የደም ዕምባ፣
እንደዚህ የሚቀኝ መልስ ያጣ ጥያቄ ከነብሴ ውስጥ ገባ።
፡
፡
እንዲ ይላል ጥያቄው
መልሱን ምን አውቄው
፡
፡
እስኪያስረሳን ድረስ የመቅደሱን እጣን
እውን ግን ሚያባላን ስልጣን ነው ወይ ሴጣን?
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb
@getem
@getem
@getem
👍1
እናት አለሜ
(አኑ)
እናቴ፣
የመኖር ቅደመ መስፈርቴ፣
የፍቅር ህይወት እውነቴ፣
አንቺ ነሽ ፋኖስ መብራቴ፣
ሌላውማ፣
ሌላውማ፣
ሌላውማ፣ ጥሎኝ ሄዷል ፣
ውድቀቴን አይቶ ሸሽቶኛል ፣
አይንህን ላፈር ብሎኛል፣
******************
አለም ሁሉ እኔን ሲገፋኝ፣
ፍጥረት በሙሉ ሲያስከፋኝ፣
አንቺው ነሽ መሸሸጋዬ፣
ከአለም መደበቂያዬ ፣
እናቴ
ፋኖስ ፣ መብራቴ
የእዝነትሽ ልኬት ስፍር ፣
ለኔ የምትሰጭኝ ፍቅር ፣
በምን ቋንቋ በምን ፊደል በየትኛው ቃል ይገለፃል?
ከእድሜዬ ስንቱን ልስጥሽ? ስንቱን ብሰጥሽ ይካሳል?
አለሜ እናት ህይወቴ፣
የእስትንፋስ መሰረቴ፣
ምን አድርጌ ላስደስትሽ?፣
ምን ሰርቼ ላስደንቅሽ?፣
ምን ገዝቼ ላ'ዘንጥሽ?፣
ትዝ ይልሻል ደግሞ አለሜ፣
ህፃን ሳለሁ
ከትንሿ ጎጇችን በር ልወጣ ስል ተላትሜ፣
ከጭንቅላቴ ደም ፈሶ፣
ያለቀስሽው የስስት ለቅሶ፣
መላ ደሜ ቢንጠፋጠፍ
ከቶ አይቻለው ሊክስሽ ፣ ፈፅሞ አይችልም ሊገልፅሽ፣
አጥንቴ እንኳ ቢከሰከስ
አደናቅፎኝ እኔን ላልሽው ፣ ቅንጣት እንኳ አይደርስብሽ።
ብቻ ግን አንቺ ኑሪልኝ።
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
(አኑ)
እናቴ፣
የመኖር ቅደመ መስፈርቴ፣
የፍቅር ህይወት እውነቴ፣
አንቺ ነሽ ፋኖስ መብራቴ፣
ሌላውማ፣
ሌላውማ፣
ሌላውማ፣ ጥሎኝ ሄዷል ፣
ውድቀቴን አይቶ ሸሽቶኛል ፣
አይንህን ላፈር ብሎኛል፣
******************
አለም ሁሉ እኔን ሲገፋኝ፣
ፍጥረት በሙሉ ሲያስከፋኝ፣
አንቺው ነሽ መሸሸጋዬ፣
ከአለም መደበቂያዬ ፣
እናቴ
ፋኖስ ፣ መብራቴ
የእዝነትሽ ልኬት ስፍር ፣
ለኔ የምትሰጭኝ ፍቅር ፣
በምን ቋንቋ በምን ፊደል በየትኛው ቃል ይገለፃል?
ከእድሜዬ ስንቱን ልስጥሽ? ስንቱን ብሰጥሽ ይካሳል?
አለሜ እናት ህይወቴ፣
የእስትንፋስ መሰረቴ፣
ምን አድርጌ ላስደስትሽ?፣
ምን ሰርቼ ላስደንቅሽ?፣
ምን ገዝቼ ላ'ዘንጥሽ?፣
ትዝ ይልሻል ደግሞ አለሜ፣
ህፃን ሳለሁ
ከትንሿ ጎጇችን በር ልወጣ ስል ተላትሜ፣
ከጭንቅላቴ ደም ፈሶ፣
ያለቀስሽው የስስት ለቅሶ፣
መላ ደሜ ቢንጠፋጠፍ
ከቶ አይቻለው ሊክስሽ ፣ ፈፅሞ አይችልም ሊገልፅሽ፣
አጥንቴ እንኳ ቢከሰከስ
አደናቅፎኝ እኔን ላልሽው ፣ ቅንጣት እንኳ አይደርስብሽ።
ብቻ ግን አንቺ ኑሪልኝ።
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትዝታን ገጣሚ
(አኑ)
እቴ
ውዴ
ሆዴ
ፍቅሬ ፣ መውደዴ
እነኚህ ቃላቶች
ገጣሚ ህይወት ላይ ዘውትር ሲጎርፉ
የግጥሙ ሀሳብ
የግጥሙ ይዘት ትዝታ ነው ትርፉ!
ዘውትር ትዝታ
ዘውትር መናፈቅ
ዛሬን እየኖረ
ትላንትን መማቀቅ
በሀሳብ መንፏቀቅ
እንዲህ ነው ገጣሚ..
ድንገት በአጋጣሚ
ውድቅ ሌት ተነስቶ
ታጥቦ የተተኮሰ ሸሚዙን አንስቶ
በጎራዳ አፍንጫው ጠረኑን አሽትቶ
እንዲህ ሲል ይፅፋል
ሌት ነው ጨለማ ነው
የቀን ሰራተኛ ድካም ያናወጠው
ሚስኪን ደሀ አባት
ልጅ የሞላው ቤቱን በላቡ የሚያኖረው
የሞቀ ትዳሩን
ፍቅር የሞላበት ፍቅር ቤተሰቡን
አቅፎ በተኛበት
በዛ ወድቅ ለሊት
እኔ ተነስቼ
ታጥቦ የተተኮሰ ሸሚዜን አንስቼ
ጠረኑን ስምገው
ያልጠፋው መዐዛሽ መንፈሴን አወደው!
ትዝ ይልሻል አይደል?
መዐዛሽ ሸሚዜን ያወደበት ቅፅበት
አብረን ያደርን ለት
የ21 አመት ልደትሽ ሲከበር
ምሽት ጨለማ ቤት
በሻማ አድምቀነው
ወይን እየጠጣን በፍቅር ስንበር
ስትስሚኝ ስስምሽ
ስግል ደግሞ እየጋልሽ
ከራሳችን አለም በስሜት ስንሸሽ
እንዲያ ስንተሻሽ
ያ የፍቅር ሲቃሽ
ድንገት አባነነኝ
በገዛ ሸሚዜ መዐዛሽ ሲያውደኝ
ትላንት ላይ ጣለኝ!
ለሊት ነው
ሊያውም 10 ሰዐት
ሸሚዜን ታቅፌ ውድ አንቺን እያሰብኩ
አንቺን እየናፈቅኩ
አንቺን ብቻ እያለምኩ
ሌላው
ረብጣ ዶላሩን በኪሱ ላይ ሞልቶ
ጭፈራ ቤት ገብቶ
በቆነጃጂቶች ዙሪያውን ተከቦ
እንስት እንደ ካባ ደርቦ ደራርቦ
ከሙዚቃ ጋራ
ከቆንጆዎች ጋራ
ከውድ አልኮል ጋራ
ሌቱን ያሳልፋል ሲጨፍር ሲዳራ
አየሽ ልዩነቱን
የሚደንቅሽ ነገር
በዚች ውድ ለሊት
በኔ በአፍቃሪሽ ፣
በደሀ አባትና በዚህ ሰው መካከል ልዩነት ይጎላል
ተቃራኒ ይመስላል
ሶስታችን ህይወት ላይ
አንደ የማይለያይ
ታላቅ እውነት አለች ከኛ ጋር ያደረች
ሴት ልጅ የተባለች!
ሌሎቹ ሲያቅፏት
እኔ በትዝታ ሌቱን የማስባት
ሸሚዝ እያነሳሁ
ቲሸርት እያነሳሁ
ጠረኗን ምመገብ ሌት እየተነሳሁ!
እንዲህ ነው ገጣሚ!
ትዝታን የሚፅፍ ለሊት በአጋጣሚ!
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
(አኑ)
እቴ
ውዴ
ሆዴ
ፍቅሬ ፣ መውደዴ
እነኚህ ቃላቶች
ገጣሚ ህይወት ላይ ዘውትር ሲጎርፉ
የግጥሙ ሀሳብ
የግጥሙ ይዘት ትዝታ ነው ትርፉ!
ዘውትር ትዝታ
ዘውትር መናፈቅ
ዛሬን እየኖረ
ትላንትን መማቀቅ
በሀሳብ መንፏቀቅ
እንዲህ ነው ገጣሚ..
ድንገት በአጋጣሚ
ውድቅ ሌት ተነስቶ
ታጥቦ የተተኮሰ ሸሚዙን አንስቶ
በጎራዳ አፍንጫው ጠረኑን አሽትቶ
እንዲህ ሲል ይፅፋል
ሌት ነው ጨለማ ነው
የቀን ሰራተኛ ድካም ያናወጠው
ሚስኪን ደሀ አባት
ልጅ የሞላው ቤቱን በላቡ የሚያኖረው
የሞቀ ትዳሩን
ፍቅር የሞላበት ፍቅር ቤተሰቡን
አቅፎ በተኛበት
በዛ ወድቅ ለሊት
እኔ ተነስቼ
ታጥቦ የተተኮሰ ሸሚዜን አንስቼ
ጠረኑን ስምገው
ያልጠፋው መዐዛሽ መንፈሴን አወደው!
ትዝ ይልሻል አይደል?
መዐዛሽ ሸሚዜን ያወደበት ቅፅበት
አብረን ያደርን ለት
የ21 አመት ልደትሽ ሲከበር
ምሽት ጨለማ ቤት
በሻማ አድምቀነው
ወይን እየጠጣን በፍቅር ስንበር
ስትስሚኝ ስስምሽ
ስግል ደግሞ እየጋልሽ
ከራሳችን አለም በስሜት ስንሸሽ
እንዲያ ስንተሻሽ
ያ የፍቅር ሲቃሽ
ድንገት አባነነኝ
በገዛ ሸሚዜ መዐዛሽ ሲያውደኝ
ትላንት ላይ ጣለኝ!
ለሊት ነው
ሊያውም 10 ሰዐት
ሸሚዜን ታቅፌ ውድ አንቺን እያሰብኩ
አንቺን እየናፈቅኩ
አንቺን ብቻ እያለምኩ
ሌላው
ረብጣ ዶላሩን በኪሱ ላይ ሞልቶ
ጭፈራ ቤት ገብቶ
በቆነጃጂቶች ዙሪያውን ተከቦ
እንስት እንደ ካባ ደርቦ ደራርቦ
ከሙዚቃ ጋራ
ከቆንጆዎች ጋራ
ከውድ አልኮል ጋራ
ሌቱን ያሳልፋል ሲጨፍር ሲዳራ
አየሽ ልዩነቱን
የሚደንቅሽ ነገር
በዚች ውድ ለሊት
በኔ በአፍቃሪሽ ፣
በደሀ አባትና በዚህ ሰው መካከል ልዩነት ይጎላል
ተቃራኒ ይመስላል
ሶስታችን ህይወት ላይ
አንደ የማይለያይ
ታላቅ እውነት አለች ከኛ ጋር ያደረች
ሴት ልጅ የተባለች!
ሌሎቹ ሲያቅፏት
እኔ በትዝታ ሌቱን የማስባት
ሸሚዝ እያነሳሁ
ቲሸርት እያነሳሁ
ጠረኗን ምመገብ ሌት እየተነሳሁ!
እንዲህ ነው ገጣሚ!
ትዝታን የሚፅፍ ለሊት በአጋጣሚ!
@getem
@getem
@getem
@anu_yesua
👍2❤1
✏️ አሪፍ እይታ ያለው የሚሸጥ 127,000 Subscriber ያለው የቴሌግራም ቻናል አለን
ቻናሉን መግዛት የሚፈልግ ትክክለኛ ገዥ ካለ
@Miki_Mako ላይ ይናግረኝ
ቻናሉን መግዛት የሚፈልግ ትክክለኛ ገዥ ካለ
@Miki_Mako ላይ ይናግረኝ
👍1
#ተውበሽ በቀላል !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
በተውሶ ፀጉር ...
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው!
ያዩት ከሆናቸው...
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
.
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
.
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
.
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
ያንቺ ወዳጅ ልቤ
ርጋታ ተስኖት ... በስጋት በራደ !
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#አስቢው.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉም አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
ታድያ ...
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. .
እኔ ያንቺው ፈቺ ፥ በወርቅ ልደምቅ ነው።
@getem
@getem
@paappii
(ሚካኤል አስጨናቂ)
በተውሶ ፀጉር ...
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው!
ያዩት ከሆናቸው...
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
.
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
.
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
.
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
ያንቺ ወዳጅ ልቤ
ርጋታ ተስኖት ... በስጋት በራደ !
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#አስቢው.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉም አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
ታድያ ...
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. .
እኔ ያንቺው ፈቺ ፥ በወርቅ ልደምቅ ነው።
@getem
@getem
@paappii
👍4❤1