ግጥም ብቻ 📘
66.7K subscribers
1.54K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ኗሪ.....
ቃላቶች ካፍህ ሲጠፉ
ከንፈሮችህም ተዘግተው በፀጥታ ክር ሲሰፉ
ማንነትህ ጎልቶ ወጥቶ በራሱ ድምጽ ካልተሰማ
ሀሳብህን እውቀትህን ይሉኝታህ ገዝፎ ከቀማ
አካፋን አካፋ -ማለት- ዶማውን ዶማ ሲያቅትህ
በምታልፈው ልክ ይሆናል ኗሪ የመሆን እድልህ
ኗሪ ማለት ሁሌም ተጓዣ ካገኘው ጋር ተሳፋሪ
እርዳኝ ብሎ ለጠየቀው ለምን? ሳይል ተባባሪ
ከ ሁሉም ጋር የሚቀልድ ሰዉ እንደ ህፃን የሚወደው
ምክንያቱም ኗሪ ሲኖር ሁሉንም አይቶ ዝም ነው።
ለሳቅ ጨዋታ ካልሆነ አንደበቱ ማይፈታ
ጽድቁን እያየ ፀጥ የሚል ኩነኔም አይቶ ዝምታ
ኗሪ መሆን በቃኝ ብሎ ሲደርስለት የሱ'ም ተራ
ትንሿን ነገር ቢሞክር ትልቅ ቁም ነገር ቢሰራ
ማን ጎበዝ ልክ ነው ይበል
ማን ጎበዝ ስህተቱን ያውራ ....

በሳሙኤል

@getem
@getem
@paappii
#Hiking_trip to Mount Mogle

The beautiful group of mountains, various types of trees and birds make the place an ultimate destination for hikers.

Hiking Date :- March 14, 2021 (megabit 5, 2013)

#Hiking_Cost 500 ETB only and for foreign 25 dollar

Departure Spot-piyasa (Tayitu Hotel)🍁
Departure Time - 12:30 Am LT 🍂🌴🍁

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 entrance with Guide
🍂 photography 📷
💐 Breakfast and lunch
🌷 Family Chilling & Talent performance ( if any)🙊🙊

🧗‍♂️ Trip grade: Medium
👉 Score Level: 8/25
👉 elevation: 3210 meter
👉 walking hour: 5-6 hour (8 km of walking)

suitable for:
- beginner
- walking of average fitness
- basic skill required

NB.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!

Brought to you by
💥#Sunset_Hiking_Group

for more join the
🔸channel @sunsethiking🍁
🔹the group @sunsethike🍁
🔻📷 @sunsetphotography🍁

🎫 tickets available at
@Paappii (0922303747)
1👍1
" መንቃት"
__________________
የተከደነው ዓይንሽን ...
በእርጋታ ሆነሽ ክፈቺ
ቀና ብለሽ ከአንገትሽ ...
ወደ አርያም ተመልከቺ
ደመናው ከሠማዩ ላይ...
ይገፈፍ ይከፈት ባንቺ፤
ብርሃን ፀዳልሽ ይፍካ...
ይርከፍከፍ በምድራችን ላይ
የውበትሽ ፍካት ድምቀት ...
ለፍጥረት ሁሉ ይታይ
ሸማ ለብሠሽ ወደኔ ነይ...
መብረቅ ፈገግታሽ ይምታኝ
"ሠላም" በይኝ እጄን ነክተሽ...
መላው አካሌን ይንዘረኝ ፤
"እመሪ " አምረሻል ደሞ ...
እኔም ልኑር በፍንደቃ
ትኩስ ትንፋሽሽ ይሠማኝ... ክው...ድርቅ...ልበል በቃ
ያረጀች የሞተች ነብሴ...
በከንፈርሽ "መሳም" ትንቃ !!!

@getem
@getem
@paappii
#yonas_kebede
#ከራስ ጋር ንግግር!
...(ሚካኤል አስጨናቂ)...
.
ውሾችን ሳትሰማ
ግመል ሆነህ ተጓዝ
አጥብቅ መንገድህን
የፊት የፊቱን ያዝ ።
.
አትችልም ሲሉህ
በእሾህ ትብታባቸው ወርውረው ሲዶሉህ
እችላለሁ ብለህ ትብታብህን በጥስ
እንባ ያራሳቸው
የአይኖችህን ቦይ ... በወኔህ ክንድ አብስ።
.
ነገህ ማልዶ ይንጋ
የፅልመት ታሪክህ
በአዲቷ ጀንበር ተማርኮ ይወጋ።
.
ትናንት ኖረህ ታልፏል
ዛሬ ላይ ለመዋል
ቀንበርህን ግን ጣል !
.
እንዲያ ነው ዘመዴ
ይቀነሳል ሸክም አቀበት ለመውጣት
ሸቅንም ይጣላል ከእድፍ ለመንፃት
ሀሳብ መታሻ ነው ልብ ነው ሳሙና
መንፈስም ጥምቀት ነው በአርሞሞህ ተቃና
.
እንዲያ ነው ወዳጄ ...
ጆሮ ሰጥተህ ስትኖር
ለወጪ ወራጁ...
ሁሉም ልንዳህ ይላል ያሾርሀል በ'ጁ።
.
የራስህ ሹፌር ሁን ሰልጥን በገላህ ላይ
ነፃነት ነው መናህ ... የተቸረህ ከላይ
ውስጥህን ማመን ነው ... የንግስና ውሉ
ያመነ ይድናል
ብሎ እንዲናገር .... የመፅሀፍ ቃሉ ።
.
እንዲያ ነው ዘመዴ ...
የንፋስ ወጀቡ
ላስቲክ ሆነህ አይቶ ... በዛው ይዞህ እንዳይቀር
አትችልም ሲሉህ...
እችላለሁ ብለህ ... አንተን አምነህ እደር።

@getem
@getem
@paappii
Endaigermsh Wude
Dawit Tumay & Solodian
Medium Quality (128kbps) @getem
@getem
@paappii
2
#አንቺው_አንቺን_ሊጥል
#ነገር_ሲያብጠለጥል

እኔ በከንካናው
ዛሬም እንደትላንት ልቤን እያሞኘው
አልከዳህም ያለኝ ቃልሽን አምኜው
አማና ብሰጥሽ ፍቅሬን አንጠልጥዬ
አንቺን ለማወደስ እኔነቴን ጥዬ
በተስፍ ባህር ላይ ሰግሬ እየዋኘው
አንቺን ፊት አድርጌ ከኋላሽ ተገኘው

ከኋላሽ አድርጎ
ፍቅርሽ ያደከመኝ እኔ ብርቱ ድኩም
ማኗኗር ነው እንጂ መኖር አልታደልኩም

እይልኝ እንግዲ
ባልታደልኩት ኑሮ እኔነቴ ያልቃል
ከማጣቴ እልፍኝ
ህላዌ እንደጥላ እያደር ይርቃል

በራቀኝ ህላዌ
ከመጉደል ጎድዬ ከማጣት ስቀስም
መኖሬን ለመካድ ባለመኖሬ ስም
አልኖርኩም አልልም
አለው እንደምንም

ታዲያልሽ
ይህ ምስኪኑ ልቤን ማጣቱ ሳያንሰው
አልፈሽኝ ልቴጂ
ስትዘገጃጂ አይቶ እንዳላየ ሰው
በኔ በኩል ሄደሽ በኔው በኩል መጣሽ
ከዕድሌና ካንቺ ማን ይሆን ተወቃሽ ?
መፍትሔ ፍለጋ
ለፍርድ ስሯሯጥ ነገር ሳብሰለስል
ልውጣ ይለኛል ቁ-ዕጣሽ በወጉ ሳይበስል
ኩርፊያሽን ለማስከን
ቁ-ዕጣሽን ለማብረድ ወጌን ስሰትረው
ወግ ያልኩት ካባዬ ልቤን ሸነተረው

ግና
እኔውስ እኔው ነኝ
አንቺን ተከትዬ ያጣው የገረጣው
አልገባ ያለኝ ግን
አንቺኑ ለመጣል አንቺነት ምን ቃጣው?

@Tufaw_muhe
@getem
@getem
@getem
         #ማብራት እና #ማጥፋት !!
                      (ዳኙ ነኝ የሮማን ልጅ )

<ሰው ፀሀይን አምኖ ፋኖሱን ባይሰብርም >፣
ተሰባሪ እቃን ፡ ብርጭቆን ተስፋ አርጎ
አይኑን አይጨፍንም ፣
አውቃለሁ እውነት ነው ፥
ደርሶ በሚረግፍ ~ተሰባሪ አምፖል
አጥፊና... አብሪ ..ባለው ፥
ብርጭቆን ተማምኖ 'ሚተኛ ሞኝ ነው ፣
ምክንያቱም...!?    ምክንያቱም ....!?
መብራቱም...!¡
መጥፋቱም ....¡!
የፅልመትህ ፍካት ~ ደርሶ 'ሚወሰነው
የሌት እጣፈንታህ ~ ብርሃንህ ያለው ፣
ሲፈልግ አጥፍቶ ~ ሲያሻው ከሚያበራው
ማብሪያና ማጥፊያውን~ከጨበጠው መዳፍ
            አንድ ሰው እጅ ላይ ነው ።

          መጋቢት 2013 ዓ.ም ተፃፈ


@getem
@getem
@paappii

#dagnu_ye_Roman
#መንገድ_እና_ሰው
(አብርሽ)

ከመንገዱ ግርጌ፤
ወገብ ማሳረፊያ ፡ እልፍኝ ፈልጌ፤
ከወዲያ ማዶ ባይ ፡ አንገቴን አስግጌ፤

ኬንዳ እንደ ቆርቆሮ፤
ድንጋይ እንደ ማገር ፡ ዙሪያውን ደርድሮ፤
ከበታች ስስ ላስቲክ፡
ከላይ አዳፋ ጨርቅ፡ ገላው ላይ የጣለ፤
ረሀብ የገረፈው፡
አንድ ጎልማሳ ላይ ፡ አይኔ ተተከለ፤

በማረፊያ ግዜው ፡ ቤት በሚውልበት፤
ደጀሰላም ዘውትር ፡ አሜን በሚልበት፤
የፈጣሪን መምጣት፡
ወይንም የእሱን መሄድ ፡ በሚጠብቅበት፤
የፍስሃ አመት ፡ የደስታ ዘመኑ፤
የአለም ስጦታ ነው፡
ነገሯ የግልብጥ ፡ እዚህ መኳተኑ፤

ከቤት ቤት ማማረጥ፡
ለለመደ ጎኔ ፡ ሀገሩን ሳስሰው፤
ዘንግቼው ነበረ፡
ከአልጋ ፍራሽ ይልቅ ፡ እንደሚበልጥ ሰው።

@getem
@getem
@paappii
::::::::::::::እኛ እኮ...:::::::::::::

የደም ካርታ ቅላፅ
የልህቀት ማማ ምቅራዝ
.............................
ላልኖረልን ምላጅ
ላልሞተልን ሰጋጅ
የሰረዝ ስብሳብ ግማጅ
የተጣልን ምራጭ
ንፉግ ገፊ ቁራጭ
ያልባነንን ድንዙዞች
የመረቀዝን ትሎች
በዘረ የሰከርን ጅሎች

✍️ሳምሶን

@getem
@getem
@getem
በዋልክበት ፍሰስ
:
:
:
እውነትን ሰንቄ ብታትር ብለፋ
ሲበሉ እንጂ ማየው የምጎርሰው ጠፋ
መልካም የዋልኩለት ዞሮ በኔው ከፋ።
:
:
ድጡን አለፍኩ ስል ማጡ ተከተለ
ስንዴ እየተመኘው እንክርዳድ በቀለ።
የ ህሊናዬ ሰላም የክንዴም መፈርጠም
ከገዛ ጠላቴ ከሆዴ አልበለጠም።
:
:
ያ ቀናው ጎዳናም ትክክሉ መንገድ
አመላላሽ ሆኗል ሀረግ እና ዘመድ።
ትዝብት ዓይኔን ገልጦት ዞሬ ብመረምር
ያንዱ ቤቱ ሰማይ ያንዱ ቤቱ ምድር።
:
:
ወጥመዱ እንዲሰበር የባለጊዜው ጥልፍ
ሀቅ አንግቡ እያልኩኝ ነበር ስለፈልፍ።
ለካስ አካሄዱ ዓለም እንድትደላ የስጋክ እንዲደርስ
በዋሉበት ሞልተው በዋሉበት መፍሰስ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb
@getem
@getem
@getem
"መሰከረም" ላይ
.
.
በጋ ሲሆን ገና፤
አውልቆ ለመጣል የወበቁን ድባት፣
ነፍሴን ለማለምለም ፍቅር ለመጋራት፣
ቃል እየወለድኩኝ፤
ቀን እየማለድኩኝ፤
ፍቅሬን "ነይ" አልልም፡፡
ለሙቀት ሳልሰጋ፤
ወረተኛው በጋ፤
እኔን ሳያማክር እንደመጣ ያልፋል፣
ክረምት አስከትሎ ከፊት ይሰለፋል፡፡
.
.
ቁር እየወለደ፤
ብርዱ ሲደራረብ በክረምቱ ወራት፣
ፍቅር ብትጠማ ነፍሴን ሰው ቢርባት፡፡
ውርጩን ስረፈራሁ ጣፋጯን በማለም፣
ቃል እያሰማመርኩ ፍቅሬን "ነይ" አልልም፡፡

በወፍ ጎጆዬ ውስጥ፤
በወፍራም ሹራብ ላይ ካቦርቴን ደርቤ፣
ቦት ተጫምቼ፤
ጋቢ ወይ ብልኮ አንዱን ተከንቤ፡፡
ሸንቁር ምድጃ ላይ፤
እሳት አያይዤ እሸት እየጠበስኩ፣
ውርጩን እያሟሸሁ ብርዱን እየሰበርኩ፣
~ክረምቴን አልፋለው፣
ለሊት በህልም አክናፍ፤
ካንዱ ምዕዋር ላይ ሙቀት እቀዝፋለዉ፡፡

ይልቅ፤
በዘመን ማለዳ፤
በፀደይ ተወልዳ፤
ደመናው ተንዶ ጀምበሯ ስትወጣ፣
እንደ መልካም እድል፤
እንደ መስቀሏ ወፍ ባ'ደይ ተንቆጥቁጣ፣
ያምላኬ ስጦታ፤
የምወዳት ፍቅሬ "መስከረም" ላይ ትምጣ፡፡

ትምጣ ትዝታዬ፤
ታሽረኝ ከመድከም፤
ዝለቴን ታክመው ተሽጣ ከጎኔ፤
የናፈቁት ገላ "እቅፍ" ሲያረጉት ፋሲካ ነው ያኔ፡፡

ዐብይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
*805*ፍቅር♥️#
ፅሁፍ leul Haile
በ Yohannes

@getem
@getem
@paappii
🤩1
"ከደህናው እንጀራ አፈር ስሆን ጉረስ"

እኔን አፈር ልግባ ጉድጓድ ይሁን ቤቴ
እኔ ልጨማደድ ትል ይብላኝ እናቴ

እናቴ አይኔ አበባ
የሴትነት ካባ..
ምስር ቀሚስሽን በእንባዬ እስከሚርስ
አይንሽን እያየሁ ነገን ዛሬ ላልቅስ
ስቅስቅ ይበል ሆዴ
ላንቺ ጉድጓድ ስምስ ነገ ይዝላል ክንዴ

ድንገት ክው እላለሁ
እርግማን ሆነና ነገን አጣሻለሁ
ከዛ ብቻዬን ነኝ
አንድ አለሜ አንቺ ነሽ ሌላ ምን አንድ አለኝ?

ክፉ ቀን ቅርብ ነው
የእናት ሞት ክፉ ነው
የፈጣሪን ቁጣ የሰውን እርግማን
አንድ አለምን ማጣት
አንድ እናትን ማጣት
የት ይደበቁታል?
ወዴት ይሸሹታል?
በምን ይሽሩታል?

ከመልክሽ ላይ መልኬ ተንዶ እስከሚፈርስ
ከአንቺ እድሜ ላይ ልኬ ቁጥሩ ዜሮ እስኪደርስ
አይንሽን እያየሁ ነገን ልመርቅሽ..
አፈር ያቅልልልሽ

.bin
@NyctophiliaBin.
@getem
@getem
@getem
👍1
# የእግዜር_ስህተት ¡
````

"እግዜር ብፁዕ ነው
ከእንከን የጸዳ ከስህተት
ፍጹም"
ብለን ብናምንም
መጽሐፍት ሁሉ ይሄን ቢገልጹም፤
ልብ ያላልነው
ቢያንስ ሁለቴ እግዜርም ስቷል¡
በሰራው ሸክላ ለትችት ታጭቷል።
# አንድ
በአምሳል ቀንብቦ ፣ ሰውን ፈጠረ፣
ሰውም ታብዮ
'ራሱን ካምላክ ጋር አነጣጠረ።
ከአምላኩም ትዕዛዝ እያደር ሸሸ፣
ቃል ተላለፈ
ወንድሙን ገድሎ እጁ ቆሸሸ።
ከአፈር ቆንጥሮ
ባይፈጥረው ኑሮ ፣ በአምሳል ባይሰራው፣
ለሌላው ጥፋት
መች ይሆን ነበር ፣ የሰው ልጅ ሴራው።
ስለዚህ እመን እግዚአብሔር ስቷል¡
ፍጹምነቱን ሰው ሲሰራ አጥቷል።
# ሁለት
መቀመቅ ሲወርድ
ቃሉን በመጣስ በመሻር ህጉን፣
እግዜር ምን ነካው?
ዳግም መምጣቱ ፣ ሊታደግ በጉን።
በጉን ቢታደግ
ቢሆን ከለላ ቢሰጠው ተገን፣
በጉ ያለቀው
በራሱ ተኩላ ፣ በራሱ ወገን።
በጉ ነው ተኩላው
ሰው ነው አሳዳጅ ፣ ሰውን የፈጀው፣
ክብሩን የሚያረክስ
'መቅደሴ' ብሎ ፣ በአምሳል ቢያበጀው፣
ከአብራኩ ወጥቶ
ሲያድግ ያጋያል ፣ ወገኑን በእሳት፣
ራሱን ሰቅሎ
ሰውን ማዳን ነው ፣ የአምላክ መሳሳት።
ሰውን ሲወጥን
ትሁት ይሆን ዘንድ
ካላላበሰው የግብር ጸጋ፣
ጧቱን ሲፈጥረው
ኋላም ቢያድነው
እርባነ ቢስ ነው ፣ የሰሪው ዋጋ።


መጋቢት 6፣ 2013 ዓ.ም

@getem
@getem
@paappii

#Biruk
በሱራፌል ጌትነት ሱራቢራቢሮ
እሷን ሳስብ part #2

ደራሲ ና አንባቢ
ሲራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ
🦋

@getem
@getem
@getem
#የአዝማሪው_እሮሮ
.
.
.
ተቀበል ይለኛል መሸታ ቤት ገብቶ
ምኑን ልቀበለው ሁሉን ተቀራምቶ
በባዶ መሸለል በባዶ ፉከራ
የልብን ጠባሳ አጥቦ ላያጠራ
ልፋ ቢለኝ እንጂ እንደው የኔ ነገር
ቃላት ተደርድሮ አይገነባም ሀገር

@Tufaw_muhe
@getem
@getem
@getem
👍2
ሼክስፒርዝም
.
(አብርሀም ሙሉ ሰው)

ደስተኛ ለመሆን ፤ አትሁን የተከፋ
የሌለህን ፈልግ ፤ ያለህ እንደ-ጠፋ
ከተራብክ ብላ ፤ ከተጠማህ ጠጣ
ከዛሬ አትራቅ ፤ ነገ ራሷ ትምጣ።
ከቸገረህ ጠይቅ ፤ ግን ከሰው አትጠብቅ
የሰው ትንሽ አትሁን ፤ ሁንም ለሰው ትልቅ
በአይኖችህ ከማልቀስ ፤ በጥርሶችህ ፈግግ
ያማረህን ሳይሆን ፤ 'ሚያምርብህን አድርግ።
ከመፃፍህ በፊት ፤ ምትፅፈውን አስብ
ከመፅሀፍት በላይ ፤ ራስህን አንብብ
መጨረሻ መልስ ፤ ጠይቅ መጀመሪያ
ወዲ አትጨነቅ ፤ አታስብም ወዲያ።
ሳትሞት መኖርህን ፤ አረጋግጥ በስራ
ትልቅነት ካሻህ ፤ በትንሹ አትኩራ።

@getem
@getem
@paappii
i
#ሳቅሽ የኔ ብርታት!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ብዬሽ አልነበረ ?
ስትስቂ ሁሉን እረሳለው...
የባህሩን ጡዘት
በፈገግታሽ ዥረት ፏልዬ አልፈዋለው።
አያስጨንቀኝም የመንደሩ ወሬ
አዲስ ነኝ ለዛሬ !
ሀገር በቋፍ ገመድ ስትማቅቅ ታስራ
እዚም እዛም ባለው ስጋት ተወጥራ
መሪያችን ግን ማነው?
ፓርቲውስ ምንድነው? እላለሁ ሳልፈራ።
ሰዎች ሲገረሙ
ከወዲህ ወደዛ የሚነፍስ አየር ተግተው ሲቃርሙ
በኑሮ ውድነት አዝነው ሲያማርሩ
ሩቅ ነኝ ለሀዘን ባይተዋር ለሀገሩ።
አሁን የዚህ ኑሮ!
ከአምናው ዘንድሮ
መናር መወደዱ ... ክንዱን ማበርታቱ
ከፈገግታሽ በልጦ
እኔን የሚጎዳኝ የታለ ክፋቱ?
የቱ ጋር ነው ደዌ ? የታለስ ኮረና?
እንኳን አንዲት ጉንፋን ...
ብዙ ህመም አልፋለሁ በጥርስሽ ስቃና።
አያሳስበኝም!
ወበቅ ቅዝቃዜው የኦዞን መሸንቆር
እተነፍሳለሁ ...
ካንቺ ጉያ ሳርፍ ... በፍቅርሽ ስኖር ።
#ብዬሽ አልነበረ ?
እንደ ዓለሙ ክፋት.. . እንደ ኑሮው ክብደት
እንደ ዘረኝነት.. . እንደ ዜጋው እብደት
እንደምንሰማው ሰቅጣጭ ዘግናኝ ወሬ
በዚህ ሁሉ እሾህ .... ዙሪያዬን ታጥሬ
ከፍቶኝ የማላድረው.. . የማልቆርጠው ተስፋ
ባንቺው ፈገግታ ነው የተቀደደውን ቅስሜን የምሰፋ።
#እንዲያ ነው የኔ ዓለም !
የሐሴቴ ምንጩ
ሁሉ ምሉዕ ሆኖ አስር ደፍኖ አይደለም
ለዘጠኝ ኑሮዬ ...
ዘመኔን ቀንሼ.. .
ከፍቶኝ ተናንሼ
ሲነጋና ሲመሽ ... ለሀዘን አልዳርም
ብቻ አንቺ ሳቂልኝ.. . ሌላው አይገርመኝም
ከሳቅሽ አይሎ ... የማይተርፈው መዓት
እኔን አይጥለኝም! !

@getem
@getem
@paappii
በሀምሌ መናፈቅ

የውበት ጥግጋት የመዋብ መስፈሪያ
የልቤ ላይ ጥማት የዘመኔ ማብቂያ
የመውደዴ አሀዱ የፍቅሬ ቃል ሀሁን
የሀሴት ማጥመቂያን ካልተገራው ፀዳል ከቁንጅናሽ ፈሰስ ካንቺ አጊንቻለሁ
እናምልሽ እቴ እንቆቅልሽ ሆኖ አካሌ ሲባዝት
ሰማይ አስገምግሞ በጭልመት ሲዳፈን ምድር ሲርበተበት
ፍጥረታት ሸሽገው ከጎጇቸው ጓዳ
ፀሀይቱ ጠልቃ ሞቃታማ ጮራዋን ከምድር ብታካዳ
ከዋክብቱ ፈዘው ደምቀው ባይታዩ
የሀምሌው ደመና ክስለቱን ነስንሶ ቢጋርድ ሰማዩን
የእኔነቴ ምሳል ደቂቅ ጠብታዎች
እምባ አዘል ፈሰሶች
ሊያሰሙ ይመስለኛል ለምድር ሊያረዱት የሰማዩን ብሶት
አስር ወር አርግዞ የቂሙን ቋጠሮ ሸሽጎ ብሶቱን
.
.
.ሲለፍፍ ይከርማል....
ቁጣው ያየለ እንደው መብረቁን ያማታል
ሰሚ አገኝ ብሎ በግርማው አይሎ ለፍጥረት ይጮሀል
እንኳን ልብ የሚለው የሚያስተውል ሊያገኝ
ፍጥረት ይሸበራል ይደነባበራል በሰማይ ውርጅብኝ
ሁሉም የራስ ብሶት ቁስሉ አይሎበት
ውስጡን ያደምጠዋል በሚያነባው ሀምሌ በሩን ቸንክሮበት
እኔማ.... በትመጪ ተስፋ የሚጠብቅ ልቤ ደጅ ደጁን ይለኛል
ሮጦ ላይደርስብሽ ከቆመበት ቆሞ ሊጠብቅሽ ሚሻ
እግሬ ከበራፌ ፍንክች ብሎ አያውቅም ከሌላም ለመክረም አልባጀም መሸሻ
ያልተዘጋው በሬ በወጭፉ መብዛት አልተቀረቀረም
ዛሬም እንደትላንት ትመጣለች በሚል ጥበቃ አልታከተም
ይሄኔ ነው እቴ የሰማዩን መፅለም የደመናውን ክልል አቅንቼ ያስተዋልኩት
ከደጄ እንዳለሁ አንቺን በመፈለግ ብሶቱን ያየሁት
ይሄኔ ነው እቴ የሰማዩን ምስጢር ለመፍትት ስዳክር ውስጤን ያገኘሁት
አንቺን ስፈልግ ነው ከሀምሌው ደመና ራሴን የፈታሁት
ከጨለማው መሀል ከአመሻሹ ተርታ
ተቃጥረን ስትመጪ በለሆሳስ ፀዳል ተጣምቀን በደስታ
ሰሚ አልነበረንም ተግባብተን ስንከንፍ በፍቅር ሹክሹክታ
ትሰሚውም ነበር ከደረቴ ፈልቆ ሊሸሸኝ ሲዳዳው የልቤ ትርታ
ዛሬ.. ከጭፍግጉ ሰማይ ፈልጌ አጣሁሽ
ከቅጥራችን ስፍራ መቅረትን ካስቆጠርሽ ቀናቶች አለፉሽ
ልቤም እንዲ እያለ ለማልመልስለት ጭንቅ ያወርድብኛል
በጥያቄ ገመድ ነፍሴን አስተሳስሮ ይተበትበኛል
ትመጣለች...? አትመጣም...?
በተፈጥሮ ቀመር በቀናት ውርርድ
መምጣት መሄድ እንጂ ከስሜቱ ጎድሎ አይጠፋም መዋደድ
በትመጣ አትመጣ በሚወልል ልቤ
ከምሽት ቅጥራችን ለማይቀር አካሌ
ምላሼ ዝም ነው ፀ..ጥ.. በምንም ቃል
የውስጤም ስብራት የፍቅር ተማፅኖ ከአይኖቼ ይታያል
ያቀረሩት እምባ እንደጠቆረ ጉም ዙሪያን ይከልላል
ከአይኖቼ በሚወርድ ናፍቆት ሙሊት እምባ ብረሳሽ እያልኩኝ ገላዬን አጥባለሁ
ሰማዩም ብሶቱን ሰሚ አገኘ መሰል እያልኩ አስባለሁ

የወረደ እምባዬ ፊቴን ከማጠቡ
ጠብታ ውሀዎች ከምድር ተዋሀዱ

ጠብ..ጠብ.. ጠብጠብ..ጠብ
በትዝታ ፈረስ ካንቺ ዘመን ቅኝት የሗሊት መጋለብ
ከፍቅር አድባራት አንቺን ይዞ መክነፍ
.
.
አካሌ ረጠበ ዙሪያዬም ጨቀየ
የሰማዩም ድባቅ የእኔም ጥሪ ጩኸት ምድሪቱን አጋየ
ትመጣለች..?አትመጣም..?

በእምኒ የጨረቃዋ

@getem
@getem
@paappii
👍1
~~~~~~~~~~~~~~~ //~~~~~~~~~~~~~

"ሰው"ነት
.
.
የቱርኩ ሶላቶ፤
ክብሬን ተመኝቶ፤
ሊበላኝ ጎምጅቶ ሊገዛኝ ሲቃጣው፤
አርፎ የተኛውን፤
የአንበሳ መንጋ ነብሩን አስቆጣው፡፡

ያ ነጩ ወንድሜ፤
ዘረኝነት አንቆት "ሰው"ነት ሲያማታው፣
ሰው መሆን የገባው፤
"እምዬ"ያሉት "ሰው"
ዋጀኝ እንደገና እግረ ሙቄን ፈታው።
"አሉላ" ያሉት "ሰው"
ያ "ባልቻ" ያሉት "ሰው"
በጦር በጎራዴ እያንገረገበ መገፋቴን 'ረታው፡፡

ክብር ሀገር ላቆዩልን ሁሉ ይሁን !!!
..............💚💛❤️.................


ዐብይ ( @abiye12 )


@getem
@getem
@getem
1