ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
" መንቃት"
__________________
የተከደነው ዓይንሽን ...
በእርጋታ ሆነሽ ክፈቺ
ቀና ብለሽ ከአንገትሽ ...
ወደ አርያም ተመልከቺ
ደመናው ከሠማዩ ላይ...
ይገፈፍ ይከፈት ባንቺ፤
ብርሃን ፀዳልሽ ይፍካ...
ይርከፍከፍ በምድራችን ላይ
የውበትሽ ፍካት ድምቀት ...
ለፍጥረት ሁሉ ይታይ
ሸማ ለብሠሽ ወደኔ ነይ...
መብረቅ ፈገግታሽ ይምታኝ
"ሠላም" በይኝ እጄን ነክተሽ...
መላው አካሌን ይንዘረኝ ፤
"እመሪ " አምረሻል ደሞ ...
እኔም ልኑር በፍንደቃ
ትኩስ ትንፋሽሽ ይሠማኝ... ክው...ድርቅ...ልበል በቃ
ያረጀች የሞተች ነብሴ...
በከንፈርሽ "መሳም" ትንቃ !!!

@getem
@getem
@paappii
#yonas_kebede