ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#አንቺው_አንቺን_ሊጥል
#ነገር_ሲያብጠለጥል

እኔ በከንካናው
ዛሬም እንደትላንት ልቤን እያሞኘው
አልከዳህም ያለኝ ቃልሽን አምኜው
አማና ብሰጥሽ ፍቅሬን አንጠልጥዬ
አንቺን ለማወደስ እኔነቴን ጥዬ
በተስፍ ባህር ላይ ሰግሬ እየዋኘው
አንቺን ፊት አድርጌ ከኋላሽ ተገኘው

ከኋላሽ አድርጎ
ፍቅርሽ ያደከመኝ እኔ ብርቱ ድኩም
ማኗኗር ነው እንጂ መኖር አልታደልኩም

እይልኝ እንግዲ
ባልታደልኩት ኑሮ እኔነቴ ያልቃል
ከማጣቴ እልፍኝ
ህላዌ እንደጥላ እያደር ይርቃል

በራቀኝ ህላዌ
ከመጉደል ጎድዬ ከማጣት ስቀስም
መኖሬን ለመካድ ባለመኖሬ ስም
አልኖርኩም አልልም
አለው እንደምንም

ታዲያልሽ
ይህ ምስኪኑ ልቤን ማጣቱ ሳያንሰው
አልፈሽኝ ልቴጂ
ስትዘገጃጂ አይቶ እንዳላየ ሰው
በኔ በኩል ሄደሽ በኔው በኩል መጣሽ
ከዕድሌና ካንቺ ማን ይሆን ተወቃሽ ?
መፍትሔ ፍለጋ
ለፍርድ ስሯሯጥ ነገር ሳብሰለስል
ልውጣ ይለኛል ቁ-ዕጣሽ በወጉ ሳይበስል
ኩርፊያሽን ለማስከን
ቁ-ዕጣሽን ለማብረድ ወጌን ስሰትረው
ወግ ያልኩት ካባዬ ልቤን ሸነተረው

ግና
እኔውስ እኔው ነኝ
አንቺን ተከትዬ ያጣው የገረጣው
አልገባ ያለኝ ግን
አንቺኑ ለመጣል አንቺነት ምን ቃጣው?

@Tufaw_muhe
@getem
@getem
@getem