ጀመኣው ቅድም ማታ ላይ ምርጥ ቀደዳ አለ ብያቹ ነበር በቃሌ መሰረት ይዤው መጥቻለሁ ያው #ግጥም ባይሆንም ሁላችንንም በቀጥታ የሚመለከት ስለሆነ ነው! #በደንብ ይነበብ!!
የሰንበት ረፋድ ምርጥ ቀደዳ!!
💚
.
.
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? የዚህ ሳምንት ቀደዳችን ደግሞ ይለያል! የፀዳ ነው! ይጠቅምሃል አንብበው!😀
.
.
ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ መጀመርያ ስልክህን አንስተህ "facebook" ቼክ ታደርጋለህ። ሽንት ቤት ቁጭ ብለህ "Instagram" ላይ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን "scroll" እያደረክ ትኮሞኩማለህ። ስልክህ ካርድ ከሌለው ቶሎ ገዝተህ "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ እስክትጣድ ያንቀለቅልሃል! የሆነ ፅሁፍ ለጥፈህ ምን ያህል "like" እና "comment" እንዳገኘህ ለማወቅ በየደቂቃው "Refresh" እያደረክ ታያለህ። የለጠፍሽው ፎቶ ምን ያህል "like" እንዳገኘ ለማወቅ ያቅበዘብዝሻል። የጠበቅሽውን ያህል "Reaction" ካላገኘ ተበሳጭተሽ ፎቶውን ታጠፊዋለሽ። "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ለተወሰነ ግዜ ሲጠፉብህ ይጨንቅሃል። ስማቸውን ሳይቀር ፅፈህ ትፈልጋቸዋለህ። ፎቶሽ ላይ ሁል ግዜ "...የኔ ቆንጆ፣ የኔ ልዕልት፣ ስታምሪ.." ምናምን እያለ "comment" የሚያደርግልሽ ልጅ በሆነ አጋጣሚ አዲስ የለጠፍሽው ፎቶ ላይ "comment" ካላደረገ ያሳስብሻል። የለጠፍከው ፎቶ ወይም ፅሁፍ "like" ብዙም ካላገኘ እራስህ "like" ታደርጋለህ። መስሪያ ቤትህ በሰጠህ ኮምፒውተር "facebook" ትጠቀማለህ። ከሰዓት ማስገባት ያለብህ ወሳኝ ስራ እያለ አንተ "tiktok" ላይ ትጣዳለህ። ጠዋት ተነስተህ ወደ ስራ መሄድ እንዳለብህ እያወቅ ማታ ላይ አንድ ሰላሳ ደቂቃ "Tiktok" ልይ ብለህ እስከ ለሊቱ 9 ሰዓት ድረስ ተጥደሃል። በንጋታው ስራ ረፍዶብሃል ወይም "Tiktok" ላይ ለሊቱን ሙሉ ተጥደህ በቂ እንቅልፍ ባለማግኘትህ ምክንያት ጠዋት ታክሲ ውስጥ አንቀላፍተሃል፣ ቀንህ ተጦልቧል። አንድ ቪድዮ "YouTube" ላይ አያለው ብለህ የገባህ ሰውዬ ሳታስበው "30 ቪድዮ" አይተሃል። "Facebook" ላይ ተጀናጅናችሁ፣ የባጥ የቆጡን ሳትተፋፈሩ አውርታችሁ፣ ተዋዳችሁ፣ ሳትገናኙ እዛው "Facebook" ላይ ተጣብሳችሁ በመጨረሻም በአካል ስትገናኙ ተሽኮርምመሃል፣ አፍረሃል፣ መሬት መሬት አይተሃል፣ ተንተባትበሃል። ከጓደኞችህ ጋር ምሳ ለመብላት ተገናኝታችሁ ምግቡ እስኪመጣ በፊት ስለ ውሏቹ፣ ገጠመኞቻችሁ፣ ስለ ቤተሰቦቻችሁ፣ ስለ ስራችሁ ምናምን በሰፊው የምትቀዱ ሰዎች አሁን ሁላችሁም ስልካችሁ ላይ አቀርቅራችኃል። እየበላችሁ ሳይቀር ከስልኩ ጋር የሚበላ ከመካከላችሁ አይጠፋም። ስልክህን አብዝተህ ከመውደድህ የተነሳ ትራስህ ስር ወሽቀኸው ትተኛለህ። መብራት ሲጠፋ መጀመርያ የሚያሳስብህ ምግብ ማብሰል አለመቻልህ፣ ቴሌቪዥን ማየት አለመቻልህ ወይም ጨለማ መሆኑ ሳይሆን ስልክህን ቻርጅ ማድረግ አለመቻልህ ነው። ስልክህ ላይ ተጥደህ በመዋልህ ምክንያት ለሚስትህ የምትሰጣት ግዜ ቀንሷል፣ የምትተኙበት እና የምትነሱበት ሰዓት ተለያይቷል፣ ከልጅህ ጋር የምትጫወትበት ግዜ ወርዳል። ማህበራዊ ህይወትህ ተመቷል። ሰዎችን በአካል አግኝተህ ከምታወራቸው ይልቅ በ "Telegram" ወይም "Messanger" ብታወራቸው ይቀልሃል፣ በአካል መገናኘት ይጨንቅሃል። ጆሮህ ላይ የምትተክለው "Earphone" መገለጫህ እስኪሆን ድረስ ተጣብቆብሃል። የ "Internet' መቋረጥ ሞት እስኪመስልሽ ድረስ ያስጨንቅሻል። ብቻ ምን አለፋህ ስልክህ ህይወት ሆኗል!
አባዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!
ዓለማችን ካላት ወደ 7 ቢልዮን ከሚገመት ህዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 3 ቢልዮን የሚሆነው ማህበራዊ ሚድያ(facebook, Instagram, snapchat, twitter, tiktok.....) ይጠቀማል። በቅርቡ በ"Netflix" የተሰራ "The Social Dilemma" የሚል ዶክመንተሪ አየሁ። ተራ ዶክመንተሪ አይደለም ጌታዬ! እዚህ ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ግለሰቦች ከባድ ሚዛን ናቸው። "Instagram" መጀመርያ ላይ ሃሳቡ ሲጠነሰስ አብረው የነበሩ ፣ "Twitter" ውስጥ ለአመታት በኢንጅነርነት ያገለገሉ፣ "pintrest" የመጣ ሰሞን ፕሬዝዳንት ሆኖ የሰራ፣ "Facebook" ውስጥ የ "monetization" ክፍል ዳይሬክተር የነበረ፣ "Google Drive"ን የፈጠሩ፣ "Facebook" ላይ ያለችውን "Like button" የሰራ፣ "Google" ውስጥ በዲዛይነርነት የሰሩ ፣" Gmail" መጀመርያ ሲፈጠር አብረው የነበሩ እና የ "Facebook" ስራ አስፈፃሚ(Executive) ቡድን ውስጥ ሳይቀር የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ከነዚህ ከባባድ ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በፍቃደኝነት ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰሩት ትውልድን ሽባ የሚያደርግ ስራ ስለቀፈፋቸው ተጣልተው ወይ ተባረው የወጡ ናቸው።
የሚያስደነግጥ ነገር!
ሁሉም የሚያወሩት አንድ አይነት ነገር ነው። ምን ይላሉ መሰለህ ጌታዬ!
"....የየትኛውም ማህበራዊ ሚድያ የ " Business Model" እንዴት ተጠቃሚዎቻችንን ስክሪን ላይ ማቆየት እንችላለን የሚል ነው! አንድን ተጠቃሚ "Facebook" ወይም "Youtube" ላይ ለማቆየት እና በይበልጥ ትኩረቱን ለመሳብ ምን እናድርግ? የህይወቱን ስንት አመታት ለኛ እንዲሰጠን እናድርግ? የሚለውን ታሳቢ አድርገው ነው የሚሰሩት! እነዚህ "Tech ካምፓኒዎች" ተጠቃሚዎቻቸው "Online" የሚመለከቱትን ማንኛውንም ነገር ያያሉ፣ ይከታተላሉ፣ ይመዝናሉ፣ ያጠናሉ። አንድን ፎቶ ለምን ያህል ደቂቃ ቆም ብለህ እንዳየህ እና የሆነን ቪድዮ እስከ ስንተኛው ደቂቃ ድረስ እንደተከታተልክ ሳይቀር ያውቃሉ! ሲከፋህ ያውቃሉ፣ ሲጨንቅህ ያውቃሉ፣ ስትጓዝ ያውቃሉ፣ ማታ ማታ ምን እንደምታይ ያውቃሉ፣ ቀን ቀን ምን አዘውትረህ እንደምታይ ያውቃሉ። እኛ ከምናስበው በላይ እነዚህ ካምፓኒዎች ጋር ስለኛ ብዙ መረጃ አለ!...."
አባዬ! "Youtube" ልትገዛው ያሰብከውን እቃ መሃል ላይ አስተዋውቆት አስደንግጦህ ያውቃል? የሆነ ልትማር ያሰብለውን ትምህርት በምታየው "Video" መሃል በማስታወቂያ መልክ አምጥቶብህ አልተገረምክም? "Facebook" የዛሬ 10 ዓመት የምታውቀውን እና ከዛ በኃላ አግኝተኸው የማታውቀውን ሰውዬ "people you may know" ላይ ገጭ አድርጎት አይተህ ገርሞህ አታውቅም? "Google" ላይ የሆነ "lipstick" "Search" አድርገሽ ከወጣሽ በኃላ በንጋታው ሌሎች ማህበራዊ ሚድያዎችን ስትከፍቺ የ"lipstick" ማስታወቂያዎች አስሬ እየመጡ አዝገውሽ አያውቁም?
ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!
"...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ ድርጅቶች የኛን መረጃ(data) ይሸጡላቸዋል!...በቀላሉ ካሌንደርህ ላይ በቀጣይ ወር መነፅር እንደምትገዛ ከፃፍክ ቀኑ እየቀረበ ሲመጣ ብዙ የመነፅር ማስታወቂያዎች ይመጡብሃል! ኢሜልክ ላይ የሆነ ሃገር የምትሄድበት ትኬት ካለ እዛ የምትሄድበት ሃገር ላይ ያሉ የሆቴሎች ማስታወቂያ

👍2
ይመጣብሃል!..."
ጌታዬ! "Algorithm" የሚባል ነገር አለ! በአጭሩ አዘውትረህ የምትመለከታቸውን ቪድዮዎች፣ ዜናዎች፣ መረጃዎች እና ፅሁፎች እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች በደንብ ካጠኑ እና ከመዘገቡ በኃላ ማንነትህን የሚያውቁበት መንገድ ማለት ነው። ለምሳሌ "Youtube" ከፍተህ አንድ ሁለት ቪድዮ ስለ የሆነ ነገር ካየህ በቀጣይ "YouTube" ላይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ተመሳሳይ 100 ቪድዮዎችን " Recommended" ላይ ያመጣብሃል! "Facebook" ላይ ስለ አንድ ጉዳይ በተደጋጋሚ የምታነብ ከሆነ በቀጣይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ብዙ መረጃዎችን ያዘንብብሃል! የአንድ አካባቢ ሰዎችን ጓደኛ ካደረክ በቀጣይ እዛ አካባቢ ያሉ ብዙ ሰዎችን ጓደኛ እንድታደርግ ያመጣልሃል! ለምሳሌ "Tiktok" ላይ ገብተህ ተገላልጠው የሚደንሱ ሴቶችን አንድ ሁለት ቪድዮ ካየህ ከዛ በኃላ "tiktok" ተቆጥረው የማያልቁ ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ያዥጎደጉድልሃል! የ "Tiktok" "Algorithm" ደግሞ ይለያል! ፍላጎትህን ለመለየት አንድን ቪድዮን ለምን ያህል ደቂቃ እንዳየህ ሳይቀር ያሰላሉ!
ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!
"...ስራችን የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ልክ እንደ "ማሽን/ኮምፒተሮች" "program" ማድረግ ነው። ሰዎች አዲስ ማንነት እና ባህሪን እንዲላበሱ ማድረግ ነው። አንተ ለኛ ልክ እንደ የላብራቶሪ አይጥ ነህ። ዓለም ላይ ሁለት ኢንደስትሪዎች ብቻ ተጠቃሚዎቻቸውን "users" ብለው ይጠራሉ። አንደኛው የአደንዛዥ እፅ ኢንደስትሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማህበራዊ ሚድያው ኢንደስትሪ ነው። ሌሎች ኢንደስትሪዎች ተጠቃሚዎቻቸውን "Customers(ደንበኞች)" ወይንም "Buyers(ገዢዎች)" ነው የሚሉት!
"Refresh" ባደረክ ቁጥር አዲስ ዜና፣ አዲስ መረጃ፣ አዲስ ፎቶ እንድታይ ነው የሚፈልገው። ምክንያቱም ግባቸው አንተን ከስልክህ አጣብቆ ማቆየት ነው።
እቅዳቸው ተጠቃሚዎቻችን "perfection(ፍፁማዊነት)" እና "Social Approval(ማህበራዊ ተቀባይነት)" እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።አንዲት ሴት ዝም ብላ አንድ የራሷን ፎቶ ምንም ሳትጨምርበት ብትለጥፍ የምታገኘው "like" ያንሳል። ነገር ግን የተለያዩ የውበት መጨመርያ ፊልተሮችን ተጠቅማ ፎቶዋን ብታሳምር፣ ሻዶው ብትጨምር፣ የቆዳ ቀለሟን ፈካ ብታደርግ እና ፊቷ ላይ ያለውን ብጉር ብታጠፋ የምታገኘው "like" እና "comment" ይበዛል። "...ቆንጆ፣ ስታምሪ፣ ከንፈርሽ፣ ፊትሽ..." ምናምን የሚሏት ሰዎች ይጨምራሉ። ግባችን የተወደደች፣ ሰዎች በውበቷ የሚቀኑባት፣ ከሌሎች ጓደኞቿ የተሻለ ተከታይ እና "social approval" ያላት ሴትን መፍጠር ነው። የሚያሳዝነው ልጅቷ ያንን ሁሉ "comment" እና "like" ያገኘችው እሷን ሆና አይደለም! የውሸት/የተጋነነ ማንነትን እንድትፈጥር አድርገናታል። ትክክለኛ መልኳን እና ማንነቷን እንድትጠላው አመቻችተናል! ለዛም ነው ብዙ ሴቶች ጭንቀት እና የአዕምሮ መታወክ የሚያጋጥማቸው። የሚለጥፉትን ፎቶ ለመምሰል ብዙ ሴቶች ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል!ማህበራዊ ሚድያዎች ዋነኛ አላማቸው የተጠቃሚዎችን "Social Media Engagement (ማህበራዊ ሚድያ ቆይታ)" ማሳደግ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወደ 214 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች የማህበራዊ ሚድያ ሱሰኞች ሆነዋል። የማህበራዊ ሚድያ ሱስ ከ "Cocaine" ሱስ ጋር አንድ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ "Dopamine" የሚባል የደስታ ስሜትን የሚረጭ ሆርሞን አለ! ሱሰኛ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮኬይን ወይም ሌላ አደንዛዥ እፅን ሲያስቡ አዕምሮዋቸው "Dopamine" ይረጫል፣ ደስታ ይሰማቸዋል። ማህበራዊ ሚድያም እንደዛ ነው! ማህበራዊ ሚድያን ከፍተህ ለማየት እንድትንቀለቀል የሚያደርገህ ወደ ሰውነትህ የሚረጨው "dopamine" ነው! በአማካይ ሰዎች በቀን 2 ሰዓት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅማቸውንም የማይጠቅማቸውንም ነገር በማየት ግዜያቸውን ያጠፋሉ! ይህ ማለት ከአጠቃላይ እድሜያቸው ድፍን አምስት አመታትን ያባክናሉ ማለት ነው! አሁን ላይ ከሶስት ፍቺዎች ውስጥ አንዱ ከማህበራዊ ሚድያ ሱስ ጋር በተያያዘ ሆንዋል!...." እያሉ ይቀጥላሉ! ከዚህ በላይ ከቀጠልኩ ሙሉ ዶክመንተሪውን መጨረሴ ነው!😀
ማጠቃለያ!
ይህንን ሁሉ ካወሩ በኃላ እንደ መፍትሄ ከሚያስቀምጧቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ላስቀምጥ እና ልውጣ!
"Notification" የሚባል ነገርን "off" ማድረግ! በየደቂቃው ስልክህ ላይ "እንትና አዲስ ፅሁፍ ለጠፋ፣ እንትና አዲስ ፎቶ ለቀቀች፣ እገሌ እንዲህ ሆነ..." እያሉ "Notification" የሚልኩልህ ትኩረትህን ለመሳብ ነው። የቆይታ ግዜህን ለማሳደግ ነው። ያንተን "Algorithm" በደንብ ቀርጥፈው ስለበሉት ነው። አንተ ተቆጣጠራቸው እንጂ እነሱ እንዲቆጣጠሩህ አታድርግ! ማየት ስትፈልግ እራስህ ግባ እንጂ "Notification" አይቆስቁስህ!
ጌታዬ! ተጨማሪ መፍትሄዎቹን ማወቅ ከፈለክ ዶክመንተሪውን እይ! ትጠቀማለህ፣ ታተርፋለህ፣ ብዙ ነገር ትባንናለህ! በይበልጥ ማንበብ ከፈለክ እዛው ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከል "Jaron Lanier" የሚባል ፀዴ ሰውዬ የፃፈው መነጋገርያ የሆነ "Ten Arguments for deleting your social Media accounts right now!"የሚል መፅሃፍ አለ! አንብበው! ከፈለክ እንደ ሁል ግዜው በውስጥ መስመር አቀብልሃለሁ!
ፀዴ የሰንበት ምሽት ይሁንልህ፣ ፈታ ብለሽ አምሺ!😀
መልካም ምሽት!🙏
✍ወንድዬ እንግዳ
#በሀሳቡ ላይ ሀሳብ አለኝ የሚልም ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን
@getem
@getem
@Nagayta

👍1
#አንቺን_ያየሁኝ_ለት
.
.
አንቺን ያየሁኝ 'ለት፤
ከደርባባ ፊትሽ፣
ቁጥብ ፈገግታሽን በስስት ገበየሁ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
የጥርሴ ሲገርመኝ ፊቴም ሲስቅ አየሁ፡፡
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ተፈጥሮ ቀረበኝ ዝኑፌ ቀጥ አለ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ልቤ ልብ አገባ በደስታ ዘለለ፡፡
አንዳች የማላውቀው፤
የማልገልፀዉ ሰሜት፤
ከልቤ ማማ ላይ ድቤውን ደለቀ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ከልቤ ተስማምቶ አይኔም ሰው ናፈቀ፡፡
አንቺን ያየሁሽ ለት፤
ታጌጣለች ነፍሴ አንቺ ነሽ ውበቷ፣
አንቺን ያየሁሽ ለት፤
ሶሪት አትናፍቀኝ ጣዖስ ምናባቷ።
.
.
አንቺን ሳላይ ብቀር፤
አዘጋገመብኝ ምን ነክቶት ነው ቀኑ፣
ኧረ የምን ጉድ ነው፤
ከቤትሽ ስትገቢ ከዋክብት ያዘኑ ?፡፡
የሰማዩ ድምቀት፤
ወዴት ሸሸች ደሞ የታለች ጨረቃ፣
አንቺን ስላላየች፤
አኮረፈች መሰል አልወጣችም ደምቃ፡፡
አንቺን ካላየሁሽ፤
ምስኪኑ ታዛዬ ቤቴም ያስጠላኛል፣
አንቺን ካላየሁሽ፤
ደስታ እንዴት ሊታሰብ ሀዘን ይወርሰኛል፡፡
አንቺን ካላየሁሽ፤
ኑረት ምናባቱ የለም እኔነቴ፤
አንቺን ካላየሁሽ፤
ቀብር እንዳትቀሪ የዛን ለት ነው ሞቴ፡፡
✍ ዐብይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
.
.
አንቺን ያየሁኝ 'ለት፤
ከደርባባ ፊትሽ፣
ቁጥብ ፈገግታሽን በስስት ገበየሁ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
የጥርሴ ሲገርመኝ ፊቴም ሲስቅ አየሁ፡፡
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ተፈጥሮ ቀረበኝ ዝኑፌ ቀጥ አለ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ልቤ ልብ አገባ በደስታ ዘለለ፡፡
አንዳች የማላውቀው፤
የማልገልፀዉ ሰሜት፤
ከልቤ ማማ ላይ ድቤውን ደለቀ፣
አንቺን ያየሁኝ ለት፤
ከልቤ ተስማምቶ አይኔም ሰው ናፈቀ፡፡
አንቺን ያየሁሽ ለት፤
ታጌጣለች ነፍሴ አንቺ ነሽ ውበቷ፣
አንቺን ያየሁሽ ለት፤
ሶሪት አትናፍቀኝ ጣዖስ ምናባቷ።
.
.
አንቺን ሳላይ ብቀር፤
አዘጋገመብኝ ምን ነክቶት ነው ቀኑ፣
ኧረ የምን ጉድ ነው፤
ከቤትሽ ስትገቢ ከዋክብት ያዘኑ ?፡፡
የሰማዩ ድምቀት፤
ወዴት ሸሸች ደሞ የታለች ጨረቃ፣
አንቺን ስላላየች፤
አኮረፈች መሰል አልወጣችም ደምቃ፡፡
አንቺን ካላየሁሽ፤
ምስኪኑ ታዛዬ ቤቴም ያስጠላኛል፣
አንቺን ካላየሁሽ፤
ደስታ እንዴት ሊታሰብ ሀዘን ይወርሰኛል፡፡
አንቺን ካላየሁሽ፤
ኑረት ምናባቱ የለም እኔነቴ፤
አንቺን ካላየሁሽ፤
ቀብር እንዳትቀሪ የዛን ለት ነው ሞቴ፡፡
✍ ዐብይ ( @abiye12 )
@getem
@getem
@getem
👍1
ግጥም ብቻ 📘
ጀመኣው ቅድም ማታ ላይ ምርጥ ቀደዳ አለ ብያቹ ነበር በቃሌ መሰረት ይዤው መጥቻለሁ ያው #ግጥም ባይሆንም ሁላችንንም በቀጥታ የሚመለከት ስለሆነ ነው! #በደንብ ይነበብ!! የሰንበት ረፋድ ምርጥ ቀደዳ!! 💚 . . እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? የዚህ ሳምንት ቀደዳችን ደግሞ ይለያል! የፀዳ ነው! ይጠቅምሃል አንብበው!😀 . . ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ…
#ተሳስተሻል
:
:
ሻማ ስትለኩሺ ኬክም ስትቆርሺ ላየሽ ሰው በሙሉ፤
የምጓጓለት ቀን ልደቴ ነው ዛሬ እያልሽ ነው አሉ።
:
:
እውነት ነው ወይ ውዴ እንደዚያ ብለሻል?
የሰማሁት ነገር ትክክል ከሆነ በጣም ተሳስተሻል።
:
:
ምክንያቱም ውዴ ...
እንደ ሾላ ጥላ እንዲያ ተንዠርግጎ ሀዘን በኔ አጥልቶ፤
ፍቅርን ተርቦ እኔነቴ ዳምኖ ልቤ በቁም ሞቶ፤
በሁሉም አቅጣጫ ከቦኝ ባለ ጊዜ ዕፀፁ በረሀ፤
ነብስ የዘራሁት ጠጥቼ አይደለም ወይ ከልብሽ ምንጭ ላይ የህይወትን ውሀ።
:
:
መውደድን ተርቦ ባለም ላይ ሲዳክር ለነበረው ልቤ፤
ዕፁብ የሆነውን የልብሽን ፍቅር ለልቤ መግቤ፤
ደመነፍሴን ይዤ ትናንት እንዳላደርኩ ተስፋ ባጣ ግርጌ፤
ታውቂ የለም እንዴ ዳግም ሰው እንደሆንኩ ትንፋሽሽን ምጌ።
:
:
በውሀ ላይ ስሮጥ አንዳች ለማልጨምር ሁሌም ሆኜ እዛው፤
ላላተርፍ ነገር ጉልበቴን ስጨርስ ድካሜን ሳበዛው፤
ያለምንም ስስት ኑሮዬ እንዲሰልጥ ህይወቴ እንዲቀና፤
አንቺ አይደለሽ እንዴ ደርሰሽ ያሳየሺኝ የፍቅርን ጎዳና።
:
:
እውነት ለመናገር ብሶት እየጫረች ዐለም በፍዳዋ ደርሳ እንዳትማግደኝ፤
በዚች ቅድስት ዕለት ያንቺ መወለድ ነው ዳግም እንደገና እኔን የወለደኝ።
:
:
ውሉ ጠፍቶት ልቤን ህይወት በኔ ሲከር፤
አንቺን ባላገኝሽ ማን ይወልደኝ ነበር።
:
:
እናልሽ እንቁዬ ...
ገና ከጅምሩ ልደቴ ነው ዛሬ ማለትሽን ስሰማ፤
ተሳስተሻል ያልኩት ምንም ሳላቅማማ፤
ባንቺ መወለድ ውስጥ ዳግም እንደገና እኔ መወለዴን፤
መዘንጋትሽን ሳውቅ ቢቆርጠኝ ነው ሆዴን።
:
:
እናም ካሁን ወዲ ...
ይህን ቀን ለማክበር ሽር ጉድ ስትዪ፤
ከሁሉ አስቀድመሽ ይህቺን አስተውዪ።
:
:
በፍቅርሽ እስትንፋስ በተቸረሽ ጥበብ በትንሳዬሽ ጉልበት፤
ባንቺ መወለድ ውስጥ ዳግም እንደገና ስለተወለድኩኝ ሞቼ ካለሁበት፤
ዛሬ ቀን ምንድነው ብሎ ለጠየቀሽ እንዲ ብለሽ አስረጂ፤
ልደቴ ነው አትበዪ ያንቺ ብቻ አይደለም ልደታችን እንጂ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb

#ተውበሽ በቀላል !
.
#በተውሶ ፀጉር ... በተውሶ ጥፍር
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው👌
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#እንጂማ.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉ አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. . በወርቅ ልደምቅ ነው።
....
ሚካኤል አስጨናቂ ....
@getem
@getem
@getem
.
#በተውሶ ፀጉር ... በተውሶ ጥፍር
በተውሶ አልቦ ... በተውሶ አንባር
አጊጠው መንገድ ዳር ...
የሚመላለሱ ዘመናይ እንስቶች
በአርቴፊሻል ውበት
ተመስጠው ያሉ ... አላወቂ ወንዶች
ለኔ መልካም ናቸው
ሁሉም ይመቻቸው👌
.
#ካፌ በረንዳ ላይ ተሰብስበው ያሉ
አንድ ላይ ነን ብለው አንድ ላይ ያልዋሉ
ቀጣፊ ጓደኞች
አስመሳይ ዋሾዎች
እንጀራን በሹካ እንቁረስ የሚሉ
ፎጋሪ አራዶች
በፋሽን ውድድር.. . በቅድ አልባሳቶች
ገላን በማራቆት አጌጥን የሚሉ
የሴት ትናንሾች.. .
ቅጥ በሌለው ጩኸት.. .ባልተገራ አንደበት
እንዲሁ እንደዘበት
እኛን እዩ ብለው አቧራ 'ሚያነሱ
ከተቀመጡበት በግድ የሚነሱ
እነሱን ለማጥመድ የሚከተል አዳም
ሁሉንም እያየሁ ሳጣ አንድ ልባም
እኔን ደስ የሚለኝ ለምን ይመስልሻል?
በአንፖል ሲጋረድ ፀሀይ መች ይታያል?
.
#እንጂማ.. .
በላስቲክ ሳይለበጥ ለሚታየው ጥፍር
የውበት ተዓምር
ሁሉ ባረገደ ... ሁሉ በሰገደ
ከተማው ባበደ
.
#እንጂማ
ተሸፍነው ባሉ ዞማ ፁጉሮችሽ
ሳይጮህ በሚዘምር ውቡ አንደበትሽ
እንደ ሀይቅ በረጋ የሰከነ ፀባይ
ሁሉ ቀልቡን ሰጥቶ አንቺን ነበር የሚያይ።
.
#እንጂማ.. .
ሰም ቃል ባይዘራ ... እንዲህ እንደቀላል
ሁሉ አመሳጥሮ .. .ቅኔውን ይፈትላል።
.
#ለምን ደስ አይለኝም?
የአዳም ዘርን ሁሉ...
ጌጥ መሳይ ስስ ብረት ...መዳብ ሲያማልለው
ያለ ተቀናቃኝ.. . በወርቅ ልደምቅ ነው።
....
ሚካኤል አስጨናቂ ....
@getem
@getem
@getem
#ይከብደኛል
:
:
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት
አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም
ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምክንያቱ ደግሞ...
እንኳን ተራርቀን እንኳን ሳንተያይ
ቀኑን አብረን ውለን ማታ ስንለያይ
አንድ ሁለት እርምጃ እንደመሰንዘሬ
ባሳብ እነጉዳለው እያሰላሰልኩኝ ውሎዋችንን ዞሬ።
ያላየውሽ ቀንም ያነጫንጨኛል፤
ሰዎች ሰላም ሲሉኝ አሽሙር ይመስለኛል።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ንፋስ ለምናለው ማደርገው ሲጠፋኝ ልክ አማራጭ ሳጣ፤
ዝባድ ሚያስንቀውን ያንን ጠረንሽን ካለሁበት ድረስ ይዞት እንዲመጣ።
:
:
ይህ እንዳለ ሆኖም ...
እውነት ለመናገር ናፍቀሺኛል ማለት
አንቺን ይከብደኛል፤
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶም
ይመስለኛል።
:
:
ለምን ይመስልሻል ውሸታም እንዳይለኝ
ፈራ ተባ ምለው ልቤ እንዳይኮንነኝ?
:
:
ይሄኔ እኮ አንቺ አሉታ አስበሻል
ምንም ትዝ ያላልሺኝ እንደዚያ መስሎሻል።
:
:
እውነት እውነት ውዴ...
እረስቼሽ ብቻ የመሰለሽ እንደው
እንዲያ በማሰብሽ በጣም ነው ምነደው።
:
:
ምከንያቱ ደግሞ...
ገና ከጅምሩ ስላንቺ ማንነት ሚጨበጥ ሳይኖረኝ ውጥኑን ሳሊዘው ፤
አይተሽ የለም እንዴ ካንጀት ስትስቂ ውስጤን ሀሴት ደስታ እንደወዘወዘው።
መቼስ ታውቂዋለሽ ለማብሰል ስታገል ወጥን በስልቻ፤
ያለምንም ስስት አንቺ እንደሰጠሺኝ ድስትና ጉልቻ።
ይሄም አይጠፋሽም ልክ ዐይንሽን ሳየው የልቤ ትርታ፤
በፊት ከነበረው ፈጥኖ እንደሚመታ።
ከጎኔ ስትገጥሚም ሙሉነት ሲሰማኝ
በርግጥ የት ይገኛል ካንቺው በላይ እማኝ።
:
:
እርግጥ ነው ታውቂያለሽ እኔም ብሆን አውቃለው፤
ይህ በንዲ እንዳለ አንቺን ናፍቀሺኛል ማለት እፈራለው።
ልቤ አፍ አውጥቶ ውሸታም የሚለኝ ደርሶ ይመስለኛል
ናፍቀሺኛል ማለት አንቺን ይከብደኛል።
:
:
ምክንያቱም ውዴ
ላንቺ ያለኝን ናፍቆት «ናፍቆት» የሚለው ቃል፤
ችሎ እንደማይገልፀው ልቤ በደንብ ያውቃል።
ከመናፈቅ በላይ ሲናፍቅ የዋለ፤
እንደው እንደ ቀላል ናፍቀሺኛል ቢልሽ ውሸትስ አይደለ።
:
:
ትክክል ውሸት ነው ...
ደግሞስ ያንቺ ናፍቆት ስንለያይ ብቻ ደርሶ የሚሰማኝ መናፈቅ አይደለም፤
እውን ፍቅር እንጂ ጊዜ ቦታ ማይመርጥ በልቤ ታትሞ የሚኖር ዘላለም።
:
:
ስለዚም የኔ ሴት ...
እንደው እንደዘበት ናፍቀሺኛል ፍቅሬ ብሎ ለመናገር አንቺን የከበደኝ፤
ስጋት ያደረብኝ የራሴው ልብ ዞሮ እራሴን መልሶ እንዳያዋርደኝ፤
ለዚህ ነው ንግስቴ ለዚ ነው እንቁዬ፤
በልቤ ተክዬሽ እንዲያው ስለማድር ከመናፈቅ በላይ ስናፍቅሽ ውዬ።

👍4
እቱ
ኧረ ባዛኝቱ፡
ይብቃሽ ካባነቱ
አንቺን የደረበ የማንም ትከሻ፡
በተጋፋኝ ቁጥር
እንኳን መመከቻ፡ አጣለሁ መድረሻ።
አንቺዋ
እንደው በግሸኗ ፡ በማር ወለላዋ
ነፍስያሽ ጳዚዮን፡ ገላሽ የሉል ፅዋ
ምነው ባትግቺኝ፡
የጨመቁብሽን፡ ሬትና ግራዋ?
ናተይ
በማርያም አደይ
እግር ላለው ሁሉ፥ ጫማነትሽን ተይ
ትቁምብህ ተብሎ፡ ገላ- አፈር ቢሰ'ጠኝ
ባንቺ እየመጣ ነው፡
ስንቱ ተረከዛም፡ ጥፍራም የረገጠኝ።
የደረቡሽ ሁሉ፡ የተጫሙሽ ሁሉ
በካባሽ በጫማሽ- ፅዋሽን ታቅፈው
ጣዕሟ ነን እያሉ-"ታደልን" እያሉ
በደጄ ያልፋሉ።
እውነትም ታደሉ!
ላንድ አንቺ ቆፍረው
እኔንም ለመቀብር -ከተደላደሉ
አንቺ ላይ ተኩሰው እኔን ከገደሉ
ትርፍ ነፍስ አገኙ፡ እውነትም ታደሉ።
ምርቃት ፈቃዴ የፍቃድሽ ቅጣይ
ይች ጭማሪ ነፍሴ የነፍስሽ ተከታይ
ስንቱ ሬት አጠጣት
ስንቱስ ደፈጠጣት፡
ፅዋና ካባሽን ፡ውብ ጫማሽን ስታይ።
ከእንግዲህስ ይብቃኝ
አይግፉኝ
አይድፉኝ
የሷ ነው እያሉ- ግራዋ አያል´ፉኝ
አያታልለኝም
ካባሽም ፅዋሽም- ጫማም ካሁን ወዲህ
ራቁትሽን ነይ- እንዳምንሽ ከእንግዲህ።
# እንቅልፍ_አያ_ጥጋብ_አትመጣም ?
@getem
@getem
@paappii
#Rediet Aseffa
ኧረ ባዛኝቱ፡
ይብቃሽ ካባነቱ
አንቺን የደረበ የማንም ትከሻ፡
በተጋፋኝ ቁጥር
እንኳን መመከቻ፡ አጣለሁ መድረሻ።
አንቺዋ
እንደው በግሸኗ ፡ በማር ወለላዋ
ነፍስያሽ ጳዚዮን፡ ገላሽ የሉል ፅዋ
ምነው ባትግቺኝ፡
የጨመቁብሽን፡ ሬትና ግራዋ?
ናተይ
በማርያም አደይ
እግር ላለው ሁሉ፥ ጫማነትሽን ተይ
ትቁምብህ ተብሎ፡ ገላ- አፈር ቢሰ'ጠኝ
ባንቺ እየመጣ ነው፡
ስንቱ ተረከዛም፡ ጥፍራም የረገጠኝ።
የደረቡሽ ሁሉ፡ የተጫሙሽ ሁሉ
በካባሽ በጫማሽ- ፅዋሽን ታቅፈው
ጣዕሟ ነን እያሉ-"ታደልን" እያሉ
በደጄ ያልፋሉ።
እውነትም ታደሉ!
ላንድ አንቺ ቆፍረው
እኔንም ለመቀብር -ከተደላደሉ
አንቺ ላይ ተኩሰው እኔን ከገደሉ
ትርፍ ነፍስ አገኙ፡ እውነትም ታደሉ።
ምርቃት ፈቃዴ የፍቃድሽ ቅጣይ
ይች ጭማሪ ነፍሴ የነፍስሽ ተከታይ
ስንቱ ሬት አጠጣት
ስንቱስ ደፈጠጣት፡
ፅዋና ካባሽን ፡ውብ ጫማሽን ስታይ።
ከእንግዲህስ ይብቃኝ
አይግፉኝ
አይድፉኝ
የሷ ነው እያሉ- ግራዋ አያል´ፉኝ
አያታልለኝም
ካባሽም ፅዋሽም- ጫማም ካሁን ወዲህ
ራቁትሽን ነይ- እንዳምንሽ ከእንግዲህ።
# እንቅልፍ_አያ_ጥጋብ_አትመጣም ?
@getem
@getem
@paappii
#Rediet Aseffa
👍1
#አይ_ገጣሚ_ሞኙ
:
:
የገጣሚው ግጥም ሀረጉ ስንኙ
ዘንድሮስ ያስብላል አይ ገጣሚ ሞኙ።
:
:
የዋህን እና ሞኝን ባንድ ላይ ሚያዋዛ
የዋህ የዋህ ሚሸት
ሞኝ ሞኝ የሚሸት
ዛሬስ ግጥም በዛ።
:
:
ተቀጥራ ምትቀር ሴት
ባትመጪም ቅጠሪኝ
ደግሞም የኔ ፍቅር
አትመጪም አውቃለው
ቢሆንም ሳልታክት እጠብቅሻለው።
እያለ ገጠመ እያለ ተቃኘ
አይ ገጣሚ ምስኪን እጅጉን ተሞኘ።
:
:
ማይመጣ ሰው መቅጠር
የሚቀር ሰው መቅጠር
እንደው ምን ይባላል ከሞኝነት በቀር።
:
:
ኮከብ ነው እንትንሽ
ፀሀይ ነው እንትንሽ
ያ እንትንሽ ደግሞ ጨረቃን ያስንቃል
ዘንድሮው ገጣሚው
መሬት እየኖረ
መሬትን እረስቶ ሰማይን ያደንቃል።
:
:
ለተሸከመችው እትብቱ ላለበት ግጥም ካልነቀሰ
ያጠገቡን ትቶ ውበትን ፍለጋ ሰማይ ከጠቀሰ
ሰማይ ካንዣበበ ሰማይ ካንጋጠጠ
ብልሀት ኮስሶ ሞኝነት በለጠ።
:
:
በየግጥሞቹ ቃል እያረቀቀ
በየስንኞቹ ሴት እያደነቀ
ውይ እንትኗ ሲያምር ውይ እንትኗ እያለ
ባንባቢ ምናብ ውስጥ ቁንጅና እየሳለ
ውይ እንትኗስ ይባስ ውይ እንትኗ ደግሞ
ሰውነቷን ሙሉ ባድናቆት ቃል ስሞ
ወረቀት ብዕሩን ብዙ ጊዜ አናድፏል
እራሱን የሚያደንቅ አንድ ግጥም እንኳን ለራሱ ሳይገጥም እየው ዛሬም አልፏል።
:
:
ገጣሚው በሞላ ከራስ በላይ ንፋስ መሆኑን ከረሳ
በስንኝ ቋጠሮ በየግጥሞቹ ሌላ ሰው ካወሳ
ከሞኝነት ውጪ ምን ይባላል እሳ።
:
:
ያለማንም ግፊያ ያለማንም ሽሚያ ሊያፈቅራት አስቦ
ዘንድሮ ገጣሚው ያለ የሌለውን ክፉ ቃል ሰብስቦ
የሚያፈቅራትን ልጅ በርግማን አጥቧትል
ቁንጅናዋን ነስቶ አስቀያሚ እንድትሆን ስለት አስገብቷል።
:
:
የሚያፈቅሯትን ሴት የሚወዷትን ሴት ክፉዋን መመኘት
ከዚህ የተሻለ አይገኝም ሞኝነት።
:
:
ዘንድሮ ...
እንዲ ነው ገጣሚው
እንዲ ነው ስንኙ
አይ ገጣሚ ምስኪን
አይ ገጣሚ ሞኙ።