ግጥም ብቻ 📘
67.3K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#ሠማይ_የላሰ_መሬት
.
ዘማሪው "ወደ ላይ!" ...
ዘፋኙም "ወደ ላይ!" ...
መጽሐፉም "ወደ ላይ!" ...
''ወደ ላይ!'' .... "ወደ ላይ!' ... ሰማነው ይበቃል
እስኪ ጎንበስ እንበል፣
''ወደ ታች!" ..... "ወደ ታች!" ......
ከ'ኔ ቢጤዎች ጋር ፣ እግዜር መሬት ወድቋል!!
-----------------------//-------------------------------
---------------( በርናባስ ከበደ )----------------

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የሱፍ አበባ ነሽ
( ናትናኤል ጌቱ )
አልተመለከትሽም ?
ሳቅሽ ዘቢብ ሁኖ ፣ ምድሩን ሲያጣፍጠው
የፈገግታሽ ዘሀ ፣ ሁሉን ሲቀይጠው
ሰሌን የነበረው ፣ ለሐፍ ሁኖ ሲያበራ
የበዛ ውበትሽ ፣ ላንቺም እስኪያስፈራ
አይኖችሽ ሲፈኩ፣ ኮኮበ ዝሑራ
መስለው እንደሚያድሩ አልተገነዘብሽም ?
የሱፍ አበባ ነሽ ፣ የበረሀ ኮሽም
...
ንቦቹ ያልቡሻል ፣ አኮሌ ገድበው
ፀሀያቱ ሁሉ ፣ ይሞቁሻል ከበው
የሽቱ አበባዎች ፣ ይምጉሻል ቀርበው
እንዚራሽን ይዘሽ ፣ ለአንባው ሳትዘይሚ
የገረጀ መንፈስ ሳታለመልሚ
ከወዘናሽ በታች ፣ ድንጉል ስትስሚ
ጀንበር ሁነሽ ሳለ ፣ ኩራዝ ተከትለሽ
እንደ ስናር በቅሎ ፣ በዳገቱ ሰግረሽ
እድሜሽን አባክነሽ ፣ እንባ ለብሰሽ ቀረሽ ?
የሱፍ አበባ ነሽ !
...
አየሩን በእጆችሽ ፣ ስትችይ ልትቀዝፊ
አየሁሽ ስትለፊ
ከእርከንሽ ዝቅ ያለ ፣ ለማበጀት አጋር
አጵሎን ሁነሽ ሳለ ፣ ከደርባባዎች ጋር
አኮፋዳ ከፍተሽ ትለማመኛለሽ
ከጠዋት እስከማታ ፀሀይ ተከትለሽ
ማለዳ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ምሽቱን
አንገት መቀልበሱን
ተለማምደሽዋል
ሊቅ ሁኖ ተፈጥሮ ፣ ዘሊብ ሁኖ መዋል
ለፀፀት ያልዳረሽ ፣ የሱፍ አበባ ነሽ
ሐር ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ !
...
ባንቺ አልተፈወሰም ?
ዝማ ያስጨነቀው ፣ ፈዋሽ ዳማከሴ ?
ዘማዊ ሆንሽና ፣ ልብስሽ የመነኩሴ !
ቢጫ እየለበሱ ፣ ከአንድ ፀሀይ ጋራ
ዝም ብሎ ዳንኪራ … ?
ከቡኒ ክብሽ ላይ ፣ ነጭ ሁኖ ተሰቅሎ
ኮኮብ መሆን ሲችል ፣ ዘርሽ ሆነ ቆሎ !!
የሱፍ አበባ ነሽ ! አንሰሽ አትተከይ
ስለራቀሽ ብቻ ፣ ጀንበር አትከተይ
አይንሽን ብታይ ፣ የብርሀን ምንጭ አለው
ፀሀዮች ይዙሩ ፣ አንቺን ተከትለው
አልተመለከትሽም ? የሱፍ አበባ ነሽ
ሰርፍ ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ
ባንገትሽ ሳትዞሪ ፣ የነጋው አይመሽም
አበባ ነሽ የሱፍ ፣ ከረባት የለሽም !
ከስቃይ ተዋደሽ ፣ መንፈስሽ ዋለለ
ዘባተሎ ተባልሽ ፣ ቬሎ ሁነሽ ሳለ
ማር እየከነበልሽ ተጣባሽ ጡት አስጥል
ጨለማ አታፈቅሪም ስለማያቃጥል !
የሱፍ አበባ ነሽ …የሱፍ አበባ ነሽ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
(#ፋሲል_ስዩም)
(!የምስራብ ስባሄ!)
.........
አሜን ተባረኪ፣
እድሜሽን 'ባውድ አመት፣
በጠሃይ ምስረቃ፣
ያፍካው ያለምልመው፣
ዱልዱሙ ገፅሽን፣
የዘመን ሽክር ሞረድ፣
ይሞርድ ይሳለው!...
(አሜን ተማረኪ!)
ያ ስሉ ዘመንሽ፣
አንገትሽን ይቅላው፣
አንጀትሽን ያውልቀው፣
ጣየ ምስራቅሽን፣
ምዕራብሽ ይነቀው!
(አሜን ተባረኪ!)
(አሜን ተማረኪ)


...///...
ዲላ

@getem
@getem
መፍትሄ
(በረከት በላይነህ)

በር መስኮት ዘግተህ ፣
ቀዳዳውን ደፍነህ
የለኮስከው ሻማ "በራ"! ፣"ጠፋ"! ካለ፤

ጠርጥር!
ቤት ያፈራወ ንፋስ ከጎጆው እነዳለ።

@getem
@getem
@gebriel_19
TESFA ., [16.05.19 16:17]
[ Photo ]

TESFA ., [16.05.19 16:17]
[ Photo ]
#ሮሐ_ሙዚቃል
32ተኛ ምሽት
ደግነት
:
#ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን

ግጥሞች
ዲስኩር
ከመፅሀፍ ገፅ
ሙዚቃ

እሁድ ግንቦት 11/2011 ዓ/ም በ10 ሰዓት
#በፈለገ_አረጋዊያን_መርጃ_ማዕከል
(አድራሻ;–አለም ሆቴል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ)

#መግቢያ
①የንፅህና መጠበቂያ ቁሶች(ሳሙና፣ዲቶል፣ላርጎ…)
ወይም
② የምግብ ውጤች (ስኳር፣ዘይት፣ፓስታ…)
ወይም
③ ፍርኖ ዱቄት

@tebeb_mereja
@teneb_mereja
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከቃል በላይ

ቢሆንልኝ ኖሮ ፀሐይን አውርጄ በእጄ በያዝኳት

ፈካ ያለ ፊቷን ብርሃንዋን እያየው እስከ ለተሞቴ ከጎኔ ባኖርኳት

ብችልማ ጨለማን ደምስሼ እለውጠው ነበር ምሽትን በንጋት

ተፈቅዶልኝ ቢሆን ሙታንን አንስቼ
አፅምን በስጋ ገንብቼ

ተነስተው ሊኤዱ በሙሉ አካላቸው ነፍስንም ዘርቼ
ያዳም የሄዋንን ጥፋትንም ትቼ

በፍቅር ባኖኩዋት ይችን ምድር በጄ (*2)

ውዴ--ዴ---ዴ---(*2)

ብችልማ ኖሮ ከቃል በላይ ሆኜ ሁልጊዜ በኖርኩኝ

ፍቅርዬ አንቺኑ እያልኩኝ
ደግሜ እንዳላጣሽ ከጎኔ ባኖርኩኝ

ከቃል በላይ በሆንኩኝ።


(ሀብታሙ ወርቁ)

@getem
@getem
@gebreil_19
*ምን አለበት**** (ሳሙኤል አዳነ)
     አሁን ምን አለበት ...
 ሰው እንዳሻው ቢኖር
    በራሱ ዳር ድንበር ፣
በልበ ጥፉዎች
       ልብ ባይሰበር ።

እውነት ምን አለበት ...
    ሜዳውን ፈልጎ ዳገቱን ለወጣ፣
ሌላ መሰናክል
      ሌላ እክል ባልመጣ ።
ምን አለበት
      ሰው ከገንዘብ በላይ
ለፍቅር ቢታደል፣
   በምንዝር አለቃ ፍትህ ባይጓደል ።
ቢቻል ለፈጣሪ ባይሆን ለህሊና፣
     ምናል  ይሄ ትውልድ  ለክፋት ባይቀና።

እውነት ምን አለበት ...
        በውዥንብር አለም
ግራ ባይገባ፣
ቁማር ባይጫወት
       ሰው ከግዜሩ ጀርባ ።

ምን አለበት...
       ላዳም የተሰጠው
የማፍቀር  ልቦና ።
        ዛሬም በዚህ ጊዜ ቀጥሎ ቢፀና።

 እውነት ምናለበት ...
   ሰውን በ ሰውነት
              ሁሉ ባከበረ ፣
    ግን በሚል አንድምታ
               ተቃርኖ ባልኖረ  ።
.....
ይገርመኛል ....
    ሰው በትምህርት አለም
              ጎልቶ እየዘመነ ፣
     በጭላንጭል እውቀት
                በራሱ መስተዋል
                  እየተማመነ ፣
     ከጥቁር ሀሳብ ጋር
                አብሮ እየዳመነ ፣
    ትናንትን ተወና
               የባቶችን ፀጋ
                የበረከቷን ቀን ፣
      በጦር አውድማ ላይ
        ተጨንቆ  እየዋለ
         ያድራል በሰቀቀን ..

እና ምን አለበት
      ሰው መነሻውን ቢያቅ
                  ትናንትን በይረሳ ፣
       በአምላክ ፍጡር ላይ
                   እጁን ባያነሳ ፣
    አውነት ምን አለበት
             በአባቶች ልቦና ፤
             በአባቶች እግር ፤
             መራመድ ቢበጀው ፣
ይሄን ጭንቅ ጊዜ
             በጥበብ ቸሻግሮ
              በፍቅር ቢዋጀው።

ምን አለበት ??????????......
 
07/09/2011
 ከምሽቱ 2:45
አ.አ


@getem
@getem
@gebriel_19
እኔ ያለሁት ማርስ፣ አንቺ ቬነስ ማዶ
የውስጤን ነበልባል፣ ለመላክ ተስኖት፣ ልቤ አለቀ ነዶ።
፨ ፨ ፨
በእግሬ አልመጣ ነገር ፣ ያለሁት ማርስ ላይ
መልእክቴን የሚያደርስ ፣ ቢጠፋም አገልጋይ
ምንም ቢወላገድ ፣ ቋንቋዬም ባይጠራ
ቀንቶኝ እንደ ሰለሞን ፣ ንፋሱ ሲግራራ
ልጣፍ ቢያደርስልኝ ፣ ካለሺበት ሥፍራ።
፨ ፨ ፨
ብታዪኝ ሆድዬ
ሌጣዬን ቁጭ ብዬ፤
፤የማርሱ ኖሕ ሆኜ
ላለመስጠም ብዬ ፣ በናፍቆትሽ እንባ
ልሰራ ስል ጀልባ
ቁሳቁስ አጣሁኝ ፣ ለኔ የሚረባ።
፨ ፨ ፨
እኔ ያለሁት ማርስ፣ አንቺ ቬነስ ማዶ
የውስጤን ነበልባል፣ ለመላክ ተስኖት፣ ልቤ አለቀ ነዶ
መራራቁም ሰፋ ፣ በምንም ተጋርዶ።
፨ ፨ ፨
መንታ ጭንቅ ጥሎ ፣ የኮቴሽ መጥፋቱ
መራራ ሆነብኝ ፣ የማርስ ላይ ስደቱ
ቀኝ ቀኙን ሳስበው ፣ ያንቺ መበርታቱ
ስሜትሺን ሚረዳ ፣ ጓደኛ ማጣቱ።
፨ ፨ ፨
መንኮራኩር ባጣ ፣ መንገዱ ባይቀና
ሞገድ ልላክልሽ ፣ በሙዚቃ ቃና
"ሰላም ነሽ ወይ ጤና ፣ ድምፅሽ ጠፋ ምነው
ተስማማሽ ወይ ኑሮ?አገሩስ እንዴት ነው?"
፨ ፨ ፨
ዝምታሽ ሲበዛ ፣ ባሰብኝ ከመርዶ
እኔ ያለሁት ማርስ፣ አንቺ ቬነስ ማዶ
የውስጤን ነበልባል፣ ለመላክ ተስኖት፣ ልቤ አለቀ ነዶ
መራራቁም ሰፋ ፣ በምንም ተጋርዶ።
፨ ፨ ፨
ውዴ ከ(ካል)ተረዳሽየኔን የማርስ ቋንቋ
እንዳልኩት ንፋሱ አድርሶልኝ ካንቺ
በቃ ሁሉን እርሺው ስጪው ባዶ ፍቺ
ቁስልሺን ሊወጋሽ ፣ ላይሆንሽ መዳኛ
ቢገባሺም ተዪው
ከቁብ አትቁጠሪው
ይህን ፣ የማርስ ስደተኛ
~~~~~~ነውና ወረኛ።


ረያን አብዱ(@Rethepac)
ቀን 4:24~28-07-2011~
ደብረሲና

@getem
@getem
@getem
👍1
ክፉ እድሌ ነሽ


አዎ ያኔ ነበርሽ....ሰማይ ተከድኖብኝ
ምድር ስትዞርብኝ
ህያዋን ግዑዛን ሁሉ ሲከፉብኝ
አንቺ ግን ከጎኔ ላፍታ ሳትለዪኝ
ሁሉም ቀናቶች ላይ አሻራ አኖርሽልኝ፡፡
በድካም ዝለቴ
በጭንቀት ጥበቴ
ተከፍቼ ሳዝን
አዝኜ ስባዝን
በሁሉም ዉድቀቴ
በሁሉም ጉድለቴ
አንቺ አብረሺኝ ነበርሽ ውዷ እመቤቴ፡፡

መቼም ማረሳቸዉ ከዉስጤ ማይጠፉ
በልቤ ፅላት ላይ ደምቀው የተፃፉ
እነኛ አብሮነትሽ እንዳሸን የፈሉ
ነፍሴን ብሰዋትስ መች ይከፈላሉ ፤

አንቺ ኮ ልዩ ነሽሁሌ ትገኛለሽ
በክፉ በመጥፎ ቀናቶቼ አለሽ፡፡

ስሚኝማ ውዴ ያ ቀን ትዝ ይልሻል
ያኔ ተመርቄ እንዲያ ስፈነጥዝ
በደስታ ሰክሬ ጢንቢራዬ ሲጦዝ
አያትሽ ሞቱና ሄደሽ ወደ ገጠር
በደስታዬ ቀን ላይ አንቺ አዝነሽ ነበር፡፡
ደሞ ሚያዚያ ወር በአስራምስተኛው ቀን
ለልደቴ ድምቀት አንቺን ስተማመን
ሲበዛ በፅኑ ታመምሺብኝና
ሳስታምምሽ ዋልኩኝ ልደቱም ቀረና፡፡

እና እቴሜቴ አንቺ የኔመቤት
ሳስብ ሳሰላስል ዘልቄ በጥልቀት
እውነቱን ተረዳው እንዲ የሆንሽበት
በሰቆቃዬ ቀን ከጎኔ እየሆንሽ
ፍስሀ ሲሆንልኝ ከቶ ካልተገኘሽ
እንቅጩን ልንገርሽ
..............አንቺ ማለት ለኔ ክፉ እድሌ ነሽ

@selamfikadu

@getEm
@getem
👍1
ላይሰጥ አያስችልም
(ቡሩክ ካሳሁን)
ከእንጨቶች ይልቅ አንገት ይበረታል
አንገት ይደነቃል
ከዝሆን የሚከብድ ሃሳብ ተሸክሞ መች ተሰብሮ ያውቃል
እፁብ ድንቅ እላለሁ ይህን ተመልክቼ
ዳግም አስባለሁ ባ'ንገቴ ፅኑነት ይበልጥ ተመክቼ
እሱ አያልቅበት እንበል እንጂ መገን
ፅኑ አንገት ሲሰጠን መች ሃሳብ ነፈገን?!
ቀድሞም አስቦ ነው ብርቱ አንገት የሰጠን
በሀሳብ አፍላቂነት ከአሸን ሊያወዳጀን
ስለዚህ አንተ ሰው ሰፊ ጫንቃ ካለህ
ሰፋፊ ችግሮች ትሸከማታለህ፡፡

ቡሩክ ካሳሁን ቴሌግራም ቻናል
@burukassahunC


@getem
@getem
የሰው ሀገር የት ነው
የግጥም ስብስብ እና አጫጭር ታሪኮች
በቅርብ ቀን
#እሱባለው_ኢትዮጵያዊ

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
(Ati TaAdi)
❤️❤️እናቴ❤️❤️
"እናቴ" የኔ አመል ክፉ ነው😡
ማንም የማይችለው😔😔
ተነጫናጭ እና ብስጩ ፀባይ ነው
"እናቴ"ሁሉም አቅቶታል
ፀባዬን መሸከም😒😒😒
ሁሉም ይርቀኛል ክፉ ያደርገኛል😥
ሲያምረኝ ይቅር እንጂ "እማ"
ልክ እንዳንቺ ማን ያባብለኛል😕
እማ❤️ አንቺ ብትሆኚማ
ያ ብስጩ ፀባዬን ያ እሳት ፀባዬን
በፍቅርሽ አብርደሽ ያመናጨኩሽን
ያየጮውኩብሽን
ሁሉንም እረስተሽ ❤️❤️❤️
ናልኝ ልጄ እያልሽ ታባብይኛለሽ
እናቴ አንቺ ነሽ እረፍቴ
አንቺ ነሽ ሰላሜ
የመኖሬ ትርጉም ነሽ የዘላለሜ
እማ ናፍቀሽኛል😔😔😔
ለኔ ካንቺ ውጪ ሰው አስጠልቶኛል
ያመሌ ወዝ አደር የኔ ተሸካሚ😒
የፍቅር ዋሻዬ አይዞህ ልጄ ባዬ
ጥበብ አስተማሪ አንቺ የኔታዬ
አጥንቴ ይድቀቅልሽ
ስጋዬ ይፈጭልሽ
እኔ ባንቺ ቦታ ባዶ ልሁንልሽ🌓🌓
ያንቺን ቅጣት ለኔ ያርገው ፈጣሪዬ
አንቺ እናት አለሜ
ሰላምሽ ይብዛልኝ💋💋
የሚወድሽ አምላክ
በእድሜ ላይ እድሜ
በጤና ላይ ጤና
ጨምሮ ይስጥልኝ
ሌላምለው የለም
የምልሽ እሄው ነው
ብቻ አንድ ቃል አለኝ
ላንቺ የምሰጠው
ውቧ እናት አለሜ
የኔ ልዩ ፍጥረት
ሁሌም ወድሻለው 💋💋❤️❤️
ያምላኬ በረከት😔😔😔😔



Ati TaAdi
19-04-2011
4:50 PM


@getem
@getem
👍4
አንቺ ና ስትዪኝ ፣ መንገዶች ቢያርጉ
መንገድ ጠራጊዎች ፣ መንገድ ቢፈልጉ
መንገድ በሚሰሩ ፣ መንገዶች ቢዘጉ
መንገድ የጀመሩ
ከመንገድ ቢቀሩ
መሔጃ ባይኖርም
ክንፍ አውጥቼ ባልበር ፣ እግሬ ቢሰበርም
መስዋእት ሆኜ ፣ ከፍዬልሽ ዋጋ
አልቀርም አንቺጋ
በህልምሽ መጣለሁ ፣ ህልሜ ካልተዘጋ

(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የጨለማው ጊዜ ሌሊቱ ሲያበቃ፣
ደስ ይለኛኛል እኔ
ፀሀይ በልጅ አፏ ጧት ስማኝ ስነቃ።
:
አምባዬ ጌታነህ

@getem
@getem
@amba88
*ላ'ንዲት ሴት የተፃፉ ሶስት የፍቅር*😍😜 ደብዳቤዎች
ለራስ ያለ እውነት
ልክ እንደ 'ፋውንቴን' ከውስጥ ገንፍሎ ለውጩ ይተርፋል
አፍቃሪ ሆዳም ሰው
ከሆዱ ላለች ሴት ከሆዱ ባለው ልክ የሆዱን ይፅፋል
"ዳሌሽ አገልግል ነው - ቅቅል ነው ደረትሽ
ባ'ስራ ሁለት ቅመም
ጣፍጦ የተሰራ ያ'በሻ ዶሮ ወጥ ይመስለኛል ፊትሽ
ክትፎ ነው ከንፈርሽ - ሽፍታ ጥብስ አንገትሽ
ኮተት ያልበዛበት ወገብሽ ሠላጣ
ጡቶችሽ ክሬም ኬክ - ጭኖችሽ ሚጥሚጣ
ተርቤአለሁ ባንቺ እሺ በይኝ ልምጣ"
ለሆዳም አፍቃሪ - የሚያፈቅራት እንስት - ቡፌ ነው ውበቷ
ለመብል የታጨ በ'ያይነት ነው ፊቷ
ለራስ ያለ እውነት
ልክ እንደ 'ፋውንቴን' ከውስጥ ገንፍሎ ለውጩ ይተርፋል
አፍቃሪ ሰካራም
ከሆዱ ላለች ሴት ከሆዱ ባለው ልክ የሆዱን ይፅፋል
"ዳሌሽ ብላክ ሌብል - ሻምፓኝ ነው ደረትሽ
የፈረንሳይን ወይን ያስታውሰኛል ፊትሽ
ከንፈርሽ ጊዮርጊስ - ዳሽን ነው አንገትሽ
ጡቶችሽ ቄንጠኛ የወይን መጠጫ
የጠጅ ብርሌ ክብ መቀመጫ
አረቂ ፈገግታሽ ነፍስ ያንቀጠቅጣል
ደረቅ ጅን ነው ጭንሽ
ባንድ እይታ ብቻ አናት ላይ ይወጣል
እባክሽ ፍቅሬ ሆይ
እሺ በይኝና ዓለምን እንቅጫት
ነፍሴን ከፍቅርሽ ወይን ቀድተሽ አጠጫት"
ለጠጪ አፍቃሪ - የሚያፈቅራት እንስት - ኪወስክ ነው ፊቷ
ቢራ ነው ቁመቷ - አረቂ ነው መልኳ - ወይን ነው ውበቷ
ለራስ ያለ እውነት
ልክ እንደ 'ፋውንቴን' ከውስጥ ገንፍሎ ለውጩ ይተርፋል
አፍቃሪ ደራሲ
ከልቡ ላለች ሴት ከልቡ ባለው ልክ የልቡን ይፅፋል
"ጭኖችሽ ትኩሳት - ፈገግታሽ ዙቤይዳ
ልብ የሚያንጠለጥል ወሬሽ ዴርቶጋዳ
የልም ዣት ነው ዳሌሽ - ደረትሽ አደፍርስ
ዓይኖችሽ የንስር ኑ ግድግዳ እናፍርስ
ውበትሽ ረቂቅ እሳት ወይ አበባ
የልብ ማኅተም አንገትሽ ወለባ
አንብቢኝ ላንብብሽ ተረጃት እውነቴን
ዡልየቴ ሁኝልኝ ሮሜዎሽ ልሁን ውሰጃት ህይዎቴን"
ላፍቃሪ ደራሲ - የሚያፈቅራት እንስት - ድርሰት ነው ውበቷ
ቅኔ ነው ቀለሟ - ቴአትር ነው መልኳ - ልብ ወለድ ነው ፊቷ
እሷ ግን እሷ ነች
ምግብም መጠጥም መፅሐፍም አይደለች
(ደሱ ፍቅረኤል)😍😂
@getem👈
@getem👈
@kaleab_1888
1👍1
አይንጋ አልፈልግም ጨረቃም ታጊጣ
ይቅር ጨላልሞልኝ ጠሀይቱም አትውጣ
ዱሩ ከቶ አይከብደኝ የለብኝ ምቀኛ
መሮኛል ያዳም ልጅ ይቅር እንደተኛ።
09-10-2011ዓ.ም ቀን 3:09
ረየን አብዱ(@Rethepac)
ወሎ - ደሴ
@getem
@getem
ናማ ! እንዋቀስ
--------------
ስልቻህን ጭነህ ፥ በግልገሏ ጥጃ
በዝግማኔ ጉዞ ፣ በኤሊ እርምጃ
ላትጠጋ ዝንዝር ፥ ላትሔድ እርቀህ
በመዳሰስ እምነት ፣ በቀልን ሸምቀህ
በጎሣ ስካሪ ፣ እሽክርክሪት ናውዘህ
አያትህ ባኘኩ...
ያንተ ጥርስ ይቦርቦር ፣ ለምን ትለኛለህ ?
.
በ' ጠል ከመረስረስ ፣ አንተን ከከለለህ
ከሞላው ሳር ክዳን፥አንዲት ሙጃ መዘህ
ስለ ሙሉ ጎጆ ፣ ለምን ታውራለህ?
እንኳንስ በሐገር ፥ በትልቋ መድረክ
ከቤተሰብህ ስር ፣ አንተም ነጠላ ነክ
አባትህ በበላው ፣ የማይሞላ ሆድክ
.
አይታመም ጥርስህ ፣ ባያትህ እኝካት
ጭንቅላትህ አይዙር
በከረመች ድፍድፍ ፣ አባትህ በጠጣት
በልሐ ልበልህ ፥ ናማ ! እንዋቀስ
በስልጡን እይታ በቃላት እንገስግስ
እንደ ላሜ ቦራ...
ከታች እየታለብክ ፥ አሞሌን አትላስ
በስሜት ብዕርህ ፣ ታሪክን አትውቀስ
እንደ ጠላ አሻሮ
ለቆላህ ሰው ሁሉ ፥ በገፍ አትታመስ
በላ መልስልኝ…
እነሱን ባባላች ፣ በድፍርስ አተላ
አባትህ አባቴ ፣ ባነገቧት ዱላ
እንደምን አድርጌ ፣ ካንተ ጋር ልጣላ?
.
ከእርሻው መስክ ላይ፥ከውድማው ራስ
ከወጣህ በኋላ ፥ እርፍ ይዘህ አትመለስ
እንደ ደጀን በሬ ፣ እፊት…ፊቱን እረስ
ኋሊትን ላትይዘው...
ጠርበህ ላትሞርደው…
ታሪክ እንደ መንገድ ፥ ላይታደስ ጅናው
ተሰርቶ ያለፈን ፣ አትውቀስ ከኋላው
እግርህ የዛለ ቀን ፥ ከምታርፍባት ጥድ
ከዛሬዋ ጥላ ፣ ቅጠልን አትመድምድ
እንደ ውሃ ድፋት...
በቁልቁለት ፈፋ፥ተስገምግመህ አትንጎድ
ላንዲት መናኛ ቃል…
አተን የገነቡ ፥ .....'ሺ' ገፆች አትቅደድ
ቅን አውጣ ከክፋት
ከስድብ ምርቃት
ትምርትን ግለጣት፥ከታሪክህ እልፈት
ከተልወሰወሱት፥ከቦኩት እንደ ሸጥ*
ተከትለሃቸው ፣ አትነከር ከድጥ
አጥር ተቀብለህ ፣ ሃገርህን አትስጥ
ያንተን ግዙፍ ዳቦ፥በጢቢኛ አትለውጥ
ለበይ እንዲቀለው
አንተም እንዳትቦካ፥ሙዝ ልጠህ አትሽጥ
.
«ሚኪ እንዳለ»
@MMiku

ማንፀሪያ፦ * ሸጥ ማለት ውሃ የሚወርድበት ፈረፈር ፤ ሁሌም ከጭቃነት እና ከርጥበት የማይለይ መሬት መለት ነው፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM