ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
በላይኛው ቀርሳ፣
በታችኛው አውሳ፣
እየተናጠረች፣
በሽንሽን ቀሚሷ፣
ድረስልኝ ብላ፣ ጁምኣ ልካብኝ፣
እረግ ነገ ደግሞ፣
ባቲ አጣሪ ገንዳ፣ ቀጭን ሀጃ አለብኝ፣
አውሳ በር፣
አግኝቸሽ በነበር!!!
አጣሪ ገንዳ፣
ሙቸልሽ ነበረ፣ በሃድራ ስነዳ።
ገንደድዩ፣
መገን እንሶሱላ፣መገን ቀጠናዩ።
ይኸው ደሞ ዛሬ፣
በቀርሳ ብርቱካን፣ ደብዳቤሽ ተጣፈ፣
ጥርስሽ ውልብ አለኝ፣
እንደትርሙብሌ፣እየተሰለፈ።
አለብኝ ፣
አለብኝ፣
ባቲ ያሉ ጊዜ ፣
ሸጋና ደም ግባት፣ ከተፍ እሚልብኝ።
ቅዳሜ በሸጋ፣
ቅዳሜን በሙና፣
ብቅ ያለች እንደሆን፣ በሃድራው መኪና፣
እንደ አፋር ምንሽር፣አምራ ተሽሞንሙና።
መስፈሪያው ባቲ ነው፣ ዛትና ቁመና።
እንደ ብርቱካኑ፣ እንደ ማር ወለላ፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ፣
የጠየመ ከንፈር፣ የመከከ ገላ፣
ቀርሳ ላይ ተጋግሮ፣ ባቲ ላይ ሲበላ።
ዘለቀች ልጅቱ፣
ደሞ ጀማመረች፣
በደመነው ሰማይ፣ ብርድ እያባረረች፣
ሀድራ ተሟሙቃ፣ ቡና እየካደመች፣
እኔን የማይበርደኝ፣ ባቴን ነው እያለች።
ከመንዙማ መሃል፣
መደዱን ጎንጉና፣ ተቀኘችላችሁ፣
" ባቴን ተረከዜን፣ ላኩልኝ ብያችሁ፣
ምነው ባቴን ብቻ፣ታስቀሩታላችሁ። "
ቅዳሜና ናፍቆት፣ ሃድራና ዝየራ፣
እንዴት ይጣፍጣል፣ከባቲዎች ጋራ።
አሳ በራ ጊቴ፣
አውቶብስ የሚቴ፣
ቡርቃ ተረከዜ፣
ሃውሳ መቀነቴ፣
እንደ አጀብ፣ ይቀልጣል ቅዳሜና ባቴ።
ያች የሀድራ ሹፌር፣
ድረስልኝ ብላኝ፣ ልካለች ከባቲ፣
ባቲና ቅዳሜ፣ቅዳሜና አሽኩቲ፣
ሀድራና መቀነት፣ ጀምኣና አርቲ፣
እየጎዘጎዘች፣ ድረሱልኝ ካለች፣
መገን ድረሱላት፣ ሀጃ ታወጣለች፣
ቅዳሜም ይቀልጣል፣ ባቲም ትነዳለች።


((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!!!


ሸጊቷ ቅዳሜ!!!!!

ዘበናይ ቅዳሜ!!!!!!!!!
ሽሙንሙን ፣
ሽሙንሙን፣
ሽቅርቅር፣
ፍንድቅድቅ፣
ፍልቅልቅ በይልኝ፣
ሳቄ ይቀድመኛል፣
ሰማዩ ሲገለጥ፣ አንች ስትመጭልኝ።



ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!

#የኔዋ ቅዳሜ!!💚💛

ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ...ወርቆቼ!!!!!!

@balmbaras
@getem
@getem