ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የማርያም መንገድ
.
.
መንፈሴ ሲዝል ሰላሜ ጠፍቶ፤
ልቤ ሲታወክ ዉስጤ ተረትቶ፤

ቢጨንቀኝ ጊዜ........

አጥብቄ ለመንኩ የማርያም መንገድ፤
ካለሁበት ማጥ ያሻግረኝ ዘንድ።

በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
43🔥5👍2
ኤሊና ጥንቸል ተቀጣጠሩ
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
                
                — አዝማሪው —

በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ

መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ



አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል

አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።

ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።

ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል

አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል

#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።

የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
34👍5🔥3
( ልመለስ ነበር )
============

ከእናቴን ማህጸን ልክ ስወጣ
ያቀፉኝ እጆች ሚሞቀው ፎጣ
ገና ሳለቅስ የጎረስኩት ጡት
እኒያ ደግ አይኖች የማይቆጡት
የእሹሩሩ ድምጽ አባባይ ዜማ
የምቾት ዓለም የህልም ከተማ

ዘልቀው ላይዘልቁ ላይቆዩ ነገር
የውሸት ደልለው በማደናገር
አስቀሩኝ እንጂ .. ከዚህ ሞት መንደር
      አመጣጤ እኮ
ጥቂት ቆይቼ ልመለስ ነበር  !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
74🔥5😱5👍3😢2
አብሮ መጥፋት

በፍቅር ሰንሰለት እኔን ላንቺ ድሮ፣
ያለፈ ታሪክሽን
የኀጢአቴን ግርሻት ሊያጠፋ ቀን ቀጥሮ፤
"ወደ ኋላ መዞር ላ'ፍታ ሳትመኙ፣
ወደ ፊት ተጓዙ ነጋችሁን ቃኙ!
ለፍቅር ታመኑ ለፍቅር ተቀኙ!"
የሚል ትእዛዝ ሰጥቶን
ትናንትናችን ላይ እቶን እሳት ቢለቅ፣
ወላዋይ መንፈስሽ
ልክ እንደ ሎጥ ሚስት ታየ ሲፍረከረክ፡፡

የቀድሞ ፍቅረኛሽ…
ያ ሁሉ ትዝታ
መጥፋት አብከንክኖሽ በድንገት ስትዞሪ፣
የጨው ሐውልት ግግር
አድርጎ ቢያስቀርሽ የፍጥረት ፈጣሪ፤
ሎጥን ልምሰል ብዬ…
የፍቅርሽ እርምጃ
ከኋላዬ ሲቀር ወደ ፊት አልሄድም፣
አይቼሽ ለማልቀስ
አይቼሽ ለመድረቅ
ያ'ምላኬን ቃል ሽሬ መዞሬ አይቀርም፡፡

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
14🔥3🤩1