ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
<<ድንግል ሆይ የልጅሽን በረከት በእኔ ላይ #አዝንቢ፥ የሚጻረረኝን የሚቃወመኝን ሰው አፉን #ለጉሚው አንደበቱን #ዲዳ አድርጊ፥ ጉሮሮውን #ዝጊ፣ ጆሮውን #አደንቁሪ ኃይሉንም #አዳክሚ፣ በልጅሽ መለኮታዊ ሰይፍ አንገቱን #ቆርጠሽ #ጣይ፣ ባላየ የሚያንዣብበውን የጠላት ዲያብሎስን ክንፍ #ስበሪ አሜን።>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት፥ አርኬ 3]

▶️ ይህ <<እስመ ክብርት>> የሚባለው #መጽሀፍ በሙሉ #እርግማን የሚያወርድ የ"ጸሎት" አይነት ነው። አንዳንድ #ምእመናን ሁልጊዜ #ጠዋት #ጠዋት ሲነጋ ይደግሙታል። አንዳንዶችም #ለጠላት ዋነኛ #መፍትሄ አድርገው ቆጥረውት #ይመኩበታልም

▶️ በዚህ በተጠቀሰው #አርኬ ላይ #ድንግል #ማርያም #የበረከት #አዝናቢ ሆናለች። መጽሀፍ ቅዱስ ግን <<በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።>> ይላል {ያዕ 1፥17}። ስለሆነም #በጎ #ስጦታ ፍጹምም የሆነ #በረከት #ከእግዚአብሄር ዘንድ እንጂ #ከማርያም ዘንድ ወይም #በማርያም በኩል አይደለምና ይሄ ግልጽ #ስህተት ነው።

▶️ ሌላው <<የሚጻረረኝን የሚቃወመኝን ሰው>> ተብሎ አፉ #እንዲሎጎም፣ አንደበቱ #ዲዳ እንዲሆን፣ ጉሮሮው #እንዲዘጋ፣ ጆሮው #እንዲደነቁር፣ ኃይሉም #እንዲዳከም፣ አንገቱ #እንዲቆረጥ መጸለዩ የትኛው መንፈስ ሆኖልን ይሆን? የእግዚአብሄር ሰው ግን ቃሉ እንደሚል <<ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግማችሁን መርቁ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉ>> በማለት #በብሉይ ሳይሆን #በአዲስ ኪዳን #ፍቅር ይመራል [ማቲ 5፤ 44-45]። ደግሞም <<ጠላትህን ግን ቢራብ አብላው ቢጠማ አጠጣው ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና ፤ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ>> ይላል [ሮሜ 12፤ 20-21]።

ይሄው ረጋሚው <እስመ ክብርት> #መጽሀፍ ይቀጥልና <<ድንግል ሆይ ተአምራዊ ኃይልን ማድረግ የሚቻልሽ የዓለም ንግስት አንቺ ነሽና ሊያጠፋኝ የሚያሴረውን ጠላት አጣድፈሽ #ከጥፋት #ገደል #ጣይው። ተከታትሎ አድኖ ሊያጠፋኝ የሚፈልገውን ጠላት ፈጥነሽ ደርሰሽ አይኑን #አሳውሪው እጁን #ሽባ አድርጊው እግሩንም #አሳጥሪው>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት አርኬ 5] ይላል። ደግሞም <<በዚህ አለም የሚጠላኝን የሚቃወመኝን ሰው #ከምድር ላይ #ነቅለሽ #ጣይልኝ>> [እስመ ክብርት፥ የኅሊና ጸሎት፥ አርኬ 9] ይላል።
▶️ እንግዲህ ከላይ እንዳየነው #በጥንት #ስነ ፅሁፎች ውስጥ #ሥዕሎች ወይም #ሃውልቶች #ይናገራሉ ብሎ መቁጠር ወይም #እንደተናገሩ አድርጎ መናገርና ሌሎች #ምትሃታዊ ነገሮችንም ያደረጋሉ በሚል ሰፊ #እምነትና #ማስፈራራት ነበር። #መጽሀፍቅዱስ ግን ይህን #ሁኔታ በማያሻማ መልኩ #የአውሬው {የዳቢሎስ} #ተግባር እንደሆነ ይገልጻል {ራዕ 13፥15}።

▶️ ከላይ #ከተጠቀሱት ጥቂት #ማስፈራሪያዎች ሌላ #ስዕሎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው #ስዕሎቹ ፊት #መጸለይና #መስገድ የተለየ #በረከት ያስገኛል ብሎ #በማጓጓትና #ለአማናዊቷ #ማርያም #የመስገድ ያክል ይቆጠራል የሚል #አብይ #ምክንያትም አለ።