▶️ በ18ኛው ክፍለ ዘመን 2ኛ #የጎንደር #ሥዕል #አሳሳል ከቀዳማዩ በጣም ይለያል። #በቀዳማዊ #ኢያሱ ዘመነ መንግስት {1682-1706 እ.ኤ.አ} የተጀመረው #ሽግግር #በ18ኛው ክፍለ ዘመን #መጀመሪያ 20 #ዓመታት ውስጥ ተገድቦ #በዳግማዊ #ኢያሱ ዘመነ መንግስት {1730-1755 እ.ኤ.አ} #ሙሉ #በሙሉ ዳበረ። ይህ #ስልት በሚያብብበት ወቅት #የውጭ ሃገር #ሞዴሎች የጨመሩበት #ጊዜ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም የውጭ ሃገር #ሰዓሊዎችና #የስነ ጥበብ #ሰዎች በተለይም #ግሪኮች እና #አርመኖች #በቤተመንግስት አብያተ #ሙያዎች የሚሰሩበትን ጊዜ ጭምር ነበር። በተለይ #ዳግማዊ ኢያሱ እና #እቴጌ {እፃቱ} ምንትዋብ {ንግሥተ ወለተ ጊዎርጊስ} #ቤተ መንግስታቸውንና #አብያተ ክርስቲያናትን #እንዲያንጹና #እንዲያስውቡ እነዚህን #ጠበብት ቀጥረው ያሰሩም ነበር። #እቴጌ #ምንትዋብ ባቋቋሙት አውራጃ በሚገኘው #ቤተ ሙያ ውስጥ የተሳሉት #ስዕሎች አንድ #ተመሳሳይ የሆኑ #ስልት ስለሚያንፀባርቁ <<የቋረኛው ቤተ ስልት>> የሚል #ስያሜ ሲሰጣቸው ስያሜውንም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጣቸው #ኮንቲሮሲኒ የተባለው የኢትዮጵያ #ጥናትና #ምርምር #ሊቅ ነው። . . . #የአውሮፖና #የመካከለኛው ምስራቅ #የባሮክ #ብልጭልጭ #ሞዴልም በዚህ ባለንበት ዘመን ተጨማምሮበት ዳበረ። @gedlatnadersanat