ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ይህ ፍጽም ስህተት ነው በሥርዋጽ (በቃል ስሕተት) የገባ ነው::
ትክክለኛ ቃል #ኢንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲት ነው የሚለው #ኢ በግእዙ አፍራሽ ነች ለምሳሌ

👉ይመውት ብንል #የሚሞት ማለት ሲሆን
#ኢይመውት ስንል ደግሞ ኢ #አፍራሽ በመሆኗ የማይሞት ማለት ይሆናል ማለት ነው:: በዚህ መሠረት

ለ ንብሎ ፍጡም እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብሲ ከተባለ ከሴት በሥጋ ስለ ተወለደ ፍጡር ነው ወደሚል ፍጽም ስህተትና ኑፋቄ ውስጥ ይከተናል በትክክለኛው ግን

#ኢንብሎ ፍጡረ እስመ ውእቱ ተወልደ በሥጋ እምብእሲ የሚል ነው ይህም "ከሴት በሥጋ ስለተወለደ ፍጡር አንለውም የሚል ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጋር የማይጋጭ ትርጓሜን ይሰጠናል "


እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርና እኛ ተራ ሰዎች እራሱ ከሴት ስለተወለድን ተፈጠርን አያሰኝም ምክንያቱም #እናቶቻችን #ፈጥረው አይወልዱምና ወይም የወለዱትን #አይፈጥሩትምና ጥንተ ተፈጥሯችን ያኜ በገነት ከአፈር የተገነው መገኘት ካለ መኖር ወደ መኖር የመጣነው መምጣት ብቻ ነው ተፈጠርን የሚያሰኘው ከዛ ወዲ ተዋለድን እንጂ አልተፈጣጠርንም ልንፈጥርም ልንፈጥረም እንችልም::

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ፈጣሪ ፍጥረታት ነውና ለና ከእናታችን ስለተወለድን ተፈጠርን የሚለው ቃል ያልተስማማን እርሱ እንዴት ከሴት ስለተወለደ ፍጡር መባል ይስማዋል ?በፍጽም #አይስማማውም በፍጹም

ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም ድንግልም ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱ ፈጠረ የፈጠረውን ሥጋ መልሶ ተዋሐደ " ይላል

ሰልስቱ ምዕትም ቢሆኑ የቅዱስ ኤፍሬምም ንግግርን አጠንክረውታል ዘወትር በጸሎታችንም የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ብለን እንንጸልይ ትዕዛዝን አስተላልፈውልናል


"፤ በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። "
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3: 16) ተብሏልና ከቤተ ክርስቲያን #የውስጥ ጠላቶች አዋቂ መሳይ ጠምጣሚዎች ልንጠነቀቅ ይገባናል መልእክታች ነው........ ይቆየን.......


#ሎቱ ስብሐት ክብር ምስጋና ይግባውና ከሴት ስለ ተወለደ በሥጋው ፍጡር ነው አይባልም ከሴት የተወለደው መለኮት ጭምር እንጂ ሥጋ ብቻ አይደለምና መወለድን ለሥጋ ብቻ የምንሰጥ ከሆነ ከነገረ ተዋሕዶ አፈንግጠናልና በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ስለሚሆንብን መጨረሻችን #የሞት ገደል ነው

"፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል #ሊያጣምሙ የሚወዱ #አንዳንዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል #የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ #የተረገመ ይሁን። "፤ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን #ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት #የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን። " (ወደ ገላትያ ሰዎች 1÷7- 9)


#ከአባቶቻችን ከቅዱሳን ሐዋርያት የተቀበልነው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ ልጅ የድንግል ልጅ ወልድ ዋሕድ #የምትለው የቅዱስ ጴጥሮስ እምነት #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ ነች!!! ማቴ 6÷13
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
ወለ ወላዲተ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር🙏