ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል
በሰሙነ ሕማማት ጠቅለል ባለ መልኩ የምናስባቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት አሥራ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡ ለክርስቲያኖች እነዚህን ሕማማተ መስቀል ማወቅና ዘወትር ማሰብ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
1. ተኰርዖተ ርእስ (ራስና በዘንግ መመታት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በዘንግ መመታቱንና መቀጥቀጡን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተኰርዖት›› የሚለው ቃል ኩርዐ -
መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ርእስ ደግሞ ራስ ማለት ነው፡፡ አገረ ገዥው ጲላጦስ ‹‹እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› ብሎ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፎ ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች አሳልፎ ሰጥቶት ነበር፡፡ በአይሁድ ሕግ የተገረፈ አይሰቀልም፤ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም፡፡ እርሱ ጲላጦስ ግን ከገረፈው በኋላ፣ የበደል በደል፣ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው (ማቴ 27¸24፤ ማር 15¸15፤ ሉቃ 23¸25፤ ዮሐ 18¸39)፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ የእሾህ አክሊል ጐንጉነው ራሱ ላይ ደፍተውበታል፡፡ ራሱንም በዘንግ መትተውታል (ማር 15¸19)፡፡ የሰው ዘር ከአዳም ጀምሮ በጠላቱ በዲያብሎስ በተጐነጐነ የኃጢአት እሾህ ራሱ ተይዞ ነበርና ይህንኑ ለማስወገድ ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ የሆነ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ ተንኮል የተጐነጐነ አክሊለ ሦክ እንደ ዘውድ ደፋ፡፡ በሲኦል ወድቆ በዲያብሎስ ተረግጦ ራሱ የሚቀጠቀጠውን የሰውን ልጅ ለማዳን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱን በመቃ ተቀጠቀጠ፡፡ ከራሱ ላይ በሚወርደው ደም ፊቱ ተሸፈነ፡፡
2. ተፀፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጃቸው በደም፣ ጣቶቻቸው በበደል በረከሰ በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተፀፍዖ›› የሚለው ቃል ፀፍዐ በጥፊ መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡
መልታሕት ደግሞ ፊት ጉንጭ ማለት ነው፡፡
ጌታችን ለሊቀ ካህናት ቀያፋ እውነትን መናገር እንደ ስድብ ተቆጥሮበት መላልሰው ፊቱን በጥፊ መትተውታል፡፡ ፊቱንም በጨርቅ ሸፍነው ‹‹ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማነው? ትንቢት ተናገርልን›› እያሉ ዘብተውበታል፡፡ በጠላት ዲያብሎስ እጅ ወድቆ በነፍሱ ይቀለድበትና ይንገላታ የበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ብሎ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ ወድቆ ተጐሰመ፤ ተንገላታ፤ በጥፊም ተመታ (ማቴ 27¸27)፡፡ ጲላጦስ አሳልፎ ከሰጠው በኋላም አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ አኑረው ቀይ ልብስ አልብሰው ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን›› እያሉ እየተሳለቁበት በጥፊ መትተውታል (ዮሐ 19¸2-4)፡፡ አላወቁትም እንጂ እርሱ በመንግሥቱ ሽረት፣ በባሕርዩ ሞት የሌለበት የዘለዓለም አምላክ ነው፡፡
3. ወሪቀ ምራቅ (ምራቅ መተፋት)፤
ርኩሳን አይሁድ በብርሃናዊው የክርስቶስ ፊት ላይ በሚያስጸይፍ ሁኔታ ምራቃቸውን እንደተፉበት የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ወሪቅ›› የሚለው ቃል
ወረቀ ካለው ግእዛዊ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም እንትፍ አለ፣ (ተፋ) ማለት ነው፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ (ምዕራፍ 5ዐ¸6) ‹‹ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኩም›› ተብሎ እንደተነገረ እየዘበቱበት ምራቃቸውን ተፉበት (ማቴ 27¸29-3ዐ፤ ማር 15¸19)፡፡ በኃጢአት የቆሸሸውን የሰውን ሕይወት ለማጥራት የመጣው ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፋበት፡፡ በሥራው ከገነት ተተፍቶ፤ ተንቆ፤ ተዋርዶ የነበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ ጌታችን ያለ ኃጢአቱ ተተፋበት፤ ተናቀ፤ ተዋረደ፡፡ እንኳን በአምላክ ፊት በሰው ፊት እንኳን መትፋት እጅግ ያስነውራል፡፡ እርሱ ግን የኃጢአታችንን ነውር ከእኛ ሊያጠፋ ነውር የሆነውን ምራቅ ተቀበለ፡፡
4. ሰትየ ሐሞት ( መራራ ሐሞት መጠጣት)፤
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሳለ ተጠማሁ ባለ ጊዜ መራራ ሐሞት መጠጣቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ሰተየ›› ማለት ጠጣ ማለት ነው፡፡ ሐሞት የሚለውም አሞት ተብሎ በቁሙ ይተረጐማል፡፡ በመዝሙር 68 ቁጥር 21 ላይ ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ ነቢዩ ዳዊትን ትንቢት ያናገረ የነቢያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ‹‹ተጠማሁ›› ባለ ጊዜ ሆምጣጤ ተሞልቶበት ተቀምጦ ከነበረው ዕቃ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡ ውኃ አጠጡኝ ቢላቸው በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፡፡ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም (ማቴ 27¸34)፡፡ ጌታችንም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ (ማቴ 27¸48፤ ማር 15¸36፤ ሉቃ 23¸36፤ ዮሐ 19¸29)፡፡
ቢጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ ውኃ የሚሰጥ አምላክ፤ የተጠማችውን ነፍስ የሚያረካ ጌታ፤ ለዘለዓለም የሚፈልቅ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሚያድል ፈጣሪ በተጠማ ጊዜ የፈጠረውን ውኃ እንኳን የሚያጠጣው የሚያቀምሰውም አላገኘም (ኢሳ 55¸1)፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ በቃዴስ በረሃ ኳትነው ለነበሩ አባቶቻቸው ከሰማይ መና አውርዶ የመገባቸው፤ ከአለት ላይ ውኃ አመንጭቶ ያጠጣቸው ክርስቶስ በተጠማ ጊዜ ቀዝቃዛ ውኃ ነፈጉት (ዘዳ 16¸1-2ዐ፤ 1ቆሮ 1ዐ¸3)፡፡ የዝናማት፤ የባሕርና የውቅያኖስ ጌታ በውኃ ጥም ተቃጠለ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሲኦል በረሃ ወድቀው በሕይወት ውሃ ጥም የተቃጠሉትን ነፍሳት ለማርካት ሲል እርሱ ተጠማ፡፡ በኃጢአት ወድቀው፣ በበደል ረክሰው፣ በነፍሳቸው ተጐሳቁለው፣ መራራ መከራን የሚቀበሉትንና ምረረ ገሃነም አፉን ከፍቶ ሆዱን አስፍቶ የሚጠብቃቸውን ሁሉ ለማዳን መራራ ሐሞትን ቀመሰ፤ ሆምጣጣውንም ጠጣ፡፡ የመረረውን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማጣፈጥ የመረረውን መጠጥ ተቀበለ፡፡
5. ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀርባው እስኪላጥ ያለ ርኅራኄ የመገረፉን ነገር የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተቀሥፎ›› የሚለው ቃል ቀሠፈ- ገረፈ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ ዘባን›› ደግሞ ጫንቃ፣ ትከሻ፣ ጀርባ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጠው የተገረፈ አይሰቀልም፡፡ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም ነበር፡፡ ጲላጣስ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን አስገረፈው፡፡ ከደሙ ንጹሕ ነኝ ብሎ ከታጠበ በኋላ ክርስቶስን ያለ ኃጢአቱ በመግረፍ ለአይሁድም አሳልፎ በመስጠት ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› እንዲሉ የታጠበ እጁን መልሶ አቆሸሸው (ማቴ 27¸28፤ ማር 15¸15፤ ዮሐ19¸1)፡፡
መድኃኒታችን መንፀፈ ደይን ወድቆ በእግረ አጋንንት ተጠቅጥቆ በእሳት አለንጋ የሚገረፈውን የሰው ልጅ ለማዳን ሲል ጀርባውን ለግርፋት ሰጠ፡፡ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገረፈ፡፡ አይሁድ አገረ ገዥያቸው ጲላጣስ ላቀረበላቸው ምርጫ ይፈታላቸው ዘንድ ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣውን ክርስቶስን ሳይሆን ራሱን እንኳን ከምድራዊ ወህኒ ማውጣት ያልቻለውን ወንበዴውን በርባንን መረጡ፡፡ መገረፍ ይገባው የነበረ በርባን ተለቀቀ፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ ‹‹ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ›› (በኢሳ 5ዐ¸6) ተብሎ እንደተነገረ ጀርባውን ለገራፊዎች አሳልፎ ሰጠ፤ ጽሕሙንም ተነጨ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የሰው ልጅ ከሚያድነው አምላክ ይልቅ የሚገርፈውንና የሚዘርፈውን ወንበዴ መርጦ ስለተገኘ ነው፡፡
6. ተዐርቆተ ልብስ (ከልብስ መራቆት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስስቶስ ልብሱን መራቆቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተዐርቆተ›› ማለት ታረዘ፤ ተራቆተ ማለት ነው፡፡ ፀሐይና ከዋክብትን ብርሃን አልብ
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
ሶ የፈጠረ አምላክ ተራቆተ፡፡ ጸጋውን ለዕሩቃን የሚያለብስ አምላክ ልብሱን ተገፍፎ ዕራቁቱን ቆመ፡፡ ጨለማን ለብሶ ጨለማን ተንተርሶ ይኖር የነበረውን ሰው መልሶ ብርሃን ያለብሰው ዘንድ የብርሃናት ጌታ፣ የጸጋ ሁሉ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገፈፈ፤ ተራቆተ፡፡
የሲኦል ወታደሮች የሆኑት አጋንንት የሰውን ልጅ ጸጋ ገፍፈውት ነበርና ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ በሰጣቸው ሰዓት ወታደሮች ልብሱን ገፍፈውታል (ማቴ 27¸27)፡፡ የሰው ልጅ ለቀረበለት ምርጫ የሰው ምላሽ ዘራፊው፤ ገራፊው ወንበዴ በርባን እንዲፈታለት ነበር፡፡ ‹‹አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኅበ ዘፈቀድከ! እነሆ እሳትና ውኃን አቅርቤልሃለሁ፣ እጅህን ወደ ፈቀድከው ስደድ›› ሲባል የሰው ልጅ እጁን ወደ እሳት ሰደደ፡፡
7. ርግዘተ ገቦ (ጎንን መወጋት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ጎኑን በስለታም ጦር መወጋቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ርግዘት›› የሚለው ቃል ረገዘ- ወጋ ከተሰኘ የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ገቦ ማለት ደግሞ ጎን ማለት ነው፡፡ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ፣ በግራና በቀኙ ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ነበር፡፡ ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር ጭናቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ አይሁድ ጲላጦስን በለመኑት መሠረት ጭፍሮቹ የሁለቱን ወንበዴዎች ጭን ጭናቸውን ከሰበሩ በኋላ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ሲመጡ ፈጽሞ እንደሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፡፡ ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ስለወጋው ወዲያው ከጎኑ ደምና ውኃ ፈሰሰ (ዮሐ 19¸33)፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ያደርገው ዘንድ ሞተ፤ የሰው ልጅ በዘለዓለማዊ ሞት ተይዞ ነበርና፡፡ ትልቁ ሞት በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ በጌታችን ሞት ግን ሞት ራሱ ድል ተነሣ፡፡ የሞት መውጊያ በሆነ ኃጢአት የሞተውን ሰው ለማዳን ጎኑን በጦር ተወጋ፡፡ በሰው ልቡና ተተክሎ የነበረውን ኃጢአት ከነሥሩ ነቅሎ ስለጣለው ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?›› ተባለ፡፡ የሞት መውጊያው ኃጢአት ነበርና (1ቆሮ 15¸54-55፤ ኢሳ 25¸8፤ ሆሴ 13¸14)፡፡
ከተወጋው የጌታችን ጎን ደምና ውኃ መፍሰሱም የእግዚአብሔርን ልጅነትና የዘለዓለምን ሕይወት አጥቶ የነበረው ሰው ልጅነቱና ሕይወቱ እንደተመለሰለት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ምክንያቱም ከጎኑ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቆ ልጅነትን፣ ደሙንም ጠጥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛልና (ዮሐ 3¸5፤ ዮሐ 6¸54)፡፡
8. ተአሮተ ድኅሪት (ወደ ኋላ መታሠር)፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እጆቹን ወደኋላ የፊጥኝ መታሠሩን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተአሥሮት›› የሚለው ቃል አሠረ (ሲነበብ ይላላል) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አሠረ ማለት ነው፡፡ ‹‹ ድኅሪት ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተድኅረ- ወደኋላ አለ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ በሰጠባት በዚያች ዕለትና ሰዓት ሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች እጁን የኋሊት አሥረው መሬት ለመሬት ጎትተውታል፡፡ አፍገምግመውታል (ዮሐ 18¸12)፡፡
በኃጢአት ሰንሰለት የኋሊት ታሥሮ ጠላት ዲያብሎስ የሚያፍገመግመውን የሰው ልጅ ለማዳን፣ ሰውንም ከኃጢአት እሥራት ይፈታ ዘንድ ሲል መድኃኔዓለም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ የኋሊት ታሠረ፡፡
9. አምሥቱ ቅንዋተ መስቀል፤
መድኃኒታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረባቸውን ጠንካራ የብረት ችንካሮች (ምስማሮች) የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ቅንዋት›› የሚለው ቃል
ቀነወ- ቸነከረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ መስቀል ማለት ደግሞ ዝም ብሎ የቆመ ግንድ ሳይሆን አሁን በየሥፍራው እንደምናየው ምልክት የተመሳቀለ እንጨት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች ሳዶር፣ አላዶር፣ዳናት፣ አዴራ፤ ሮዳስ ይባላሉ፡፡ እነዚህም የአምሥቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌዎች መሆናቸውን አበው ያስተምራሉ፡፡
ሐዋርያው ቶማስ ከትንሣኤ በኋላ ወንድሞቹ ሐዋርያት ስለ ትንሣኤው በነገሩት ጊዜ ‹‹የችንካሩን ምልክት በዓይኖቼ ካላየሁ፣ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላስገሁ፣ በእጄም የተወጋውን ጎኑን ካልዳሰስኩ አላምንም›› ማለቱ በብረት ቀኖት በመቸንከሩ ነበር (ዮሐ 2ዐ¸25)፡፡ መድኃኒታችን በኃጢአት ቀኖት (ምስማር) ተይዞ የነበረውን ሰው ለማዳን በብረት ቀኖት ተቸነከረ፡፡
እንግዲህ አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ድሀ ያይደለ ጌታ፤ ፍጡር ያይደለ የፈጠረውን ሥጋ ገንዘብ ያደረገ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ብሎ ተናቀ፡፡ የሕማም ሰው፤ ደዌንም የሚያውቅ ሆነ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፡፡ ሕማማችንንም ተሸከመ፡፡ ይህም የሰውን ልጅ ለማዳን ማለትም እኛን ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰንና ከሕማመ ሥጋ ከሕማመ ነፍስ ሥቃይ ያሳርፈን ዘንድ ነው፡፡ ቁስለ ኃጢአታችንን ያደርቅልን ዘንድ ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፡፡ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ስለ በደላችን ደቀቀ፡፡ ሊያረጋጋን ተጨነቀ፡፡ ሊያሣርፈን ተሠቃየ፡፡ አፉንም አልከፈተም፡፡
የእግዚአብሔር የመሥዋዕቱ በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ መልካምን እንጂ ግፍን አላደረገም ነበር፡፡ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ወሰብእ ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ በተመረመረ ጊዜ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም፡፡ በፈቃዱ ነፍሱን ስለ እኛ መሥዋእት አደረገ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሥጋውን ቆረሰልን፣ ደሙንም አፈሰሰልን (ኢሳ. 53¸1-13፤ ዮሐ. 10¸18፤ ዮሐ. 19¸30፤ 1ኛቆሮ. 5¸7)፡፡ በዚህ የተቀደሰው ሳምንት ይህንን የጌታን ውለታና የድኅነት ሥራ እናስተውል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


ምንጭ :-ማህበረ ቅዱሳን ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት

ዓውደ ምህረት የእናንተ
የሰሙነ ሕማማት - ሐሙስ - "የምስጢር ሐሙስ፣ የትዕትና ሐሙስ ፣ ጸሎተ ሐሙስ እና ምሴተ ሐሙስ " ትባላለች !

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና መምህር ሲሆን የአገልጋዮቹን የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ ማጠቡ ይታሰብበታል።

#አንድም አዲስ ምስጢር በተግባር ምስጢረ ጥቅምት እና ምስጢረ ቁርባን የተመሰረቱበት ቀን ነው።

#አንድም ጌታ የመጨረሻውን ጸሎት በ ጌቴሴማኔ የጸለየበት ነው ። ለሐዋርያቱ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሎ ያስተማረበት ዕለት ነው።

#አንድም ከስቅለት በፊት የምትገኝ ሐሙስ ናት እና የመጨረሻዋ ሐሙስ ትባላለች። በሲኦል ቁራኝነት ለሚኖሩ ነፍሳት የመጨረሻቸውም ናትና ።

ስለትዕትናው ግን ሊቁ እንዲህ ያመሰግናል !

ተራሮችን በኀይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፤ የባሕርን ውሃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በወንዞች መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውሃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን እንዲታጠቡ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በኦሪቷ ድንኳን ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውሃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ።

መጽሀፈ ምስጢር በቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንንም ተቀብሎ ይህችን ሳምንት በደህና ያስፈጽመን በሰላም ዘንድ የትንሳኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጥያታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ #ጸልዩ

#እግዚኦ_ተሰሃለነ
#በሕማሙ_ይታረቀን
#ጸልዩ_በእንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅድስት
<< በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን >>
#ኢሳ 53÷5
እልልልልል👏👏👏👏👏እልልልልል

እንኳን መዋዕለ ጾሙን አስፈጽሞ ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በፍቅር አደረሰን አደረሳችሁ !!!!

🛑አዲስ ዝማሬ🛑

  👂  እያደመጣችሁ!!! 👂

https://youtu.be/wwl49jul0qI
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

#ውድ_የዐውደ_ምሕረቱ ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (😷ተርቢኖስ ሰብስቤ😷)
Audio
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (😷ተርቢኖስ ሰብስቤ😷)
ዐውደ ምሕረት
Audio
#የሁለት_ጥንዶች_ወግ
_______
ጸሐፊና ተራኪ : -ተርቢኖስ ሰብስቤ
#ፍጆታ
5 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ
1.2 mb ብቻ
#ሐናና ቀያፋ !
____________

የሚባሉ አንቱ
ሊቀ ካህናቱ
የከበሩ ቡንቱ

ጠንቅቀናል ያሉት
ሕግና ነቢያት
የብሉይ ጠምጣሚ
ሊቃውንተ ኦሪት
ዳዊት የደገሙ
የወንጌል እንግዶች
የዲቢሎስ መረብ
የሲዖል መንገዶች

እውነትን ተምረው
እውነት የገደፉ
ሐናና ቀያፋ
የተማሩት ከፉ
የዕውቀትን ሰሌዳ
ሰቅለውት አረፉ.......... + + +
~ ~ ~

#መታሰቢያነቱ :- ለተማሩ ማሕይሞች ይሁን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሚያዝያ 08/2015 ዓ.ም
|የማይለመድ እንግዳ ሞት !
" ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ
በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ
ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና። "
|ሮሜ 6÷ 7-9
# አቶ ሰብስቤ መታፈሪያ ወልደ አረጋይ ወስመ ጥምቀቱ /ወልደ
ኪሮስ /
የ40ቀን መታሰቢያ
1933-2015 ዓ.ም
ግንቦት 13' ን በተራራማው ስፍራ !!!!!

በደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ካቴድራል የቅዳሴ ቤት ክብረ በዓል!!!

#አድራሻ
#በታክሲ 👉 ከመሐል ፒያሳ (ጊዮርጊስ) 👉 አዲሱ ገበያ ፣ ድልበር
#በታክሲ 👉 ከጎጃም በረንዳ(መርካቶ) - አዲሱ ገበያ ፤ ድል በር
#በታክሲ 👉 ከሽሮሜዳ - አዲሱ ገበያ
#በታክሲ 👉 ከአስኮ - ቀለበት መንገድ መጨረሻ
#በታክሲ_በአውቶቡስ 👉 ከመገናኛ - አዲሱ ገበያ
#በታክሲ_በአውቶቡስ 👉 ከሜክሲኮ - አዲሱ ገበያ
#በአውቶብስ 👉 ከቄራ ፮/6/ቁጥር - አዲሱ ገበያ
#በአውቶቡስ 👉 ከለገሃር ፵፭/45/ ቁጥር
#በአውቶቡስ 👉 ከቀለበት መንገድ ዙሪያ ፻፩፪/112/ ቁጥር - አዲሱ ገበያ
#በአውቶቡስ 👉 ከቦሌ - አዲሱ ገበያ

https://www.facebook.com/Etsepatoss
@Etsepatossundayschool