ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የሰሙነ ሕማማት - ሐሙስ - "የምስጢር ሐሙስ፣ የትዕትና ሐሙስ ፣ ጸሎተ ሐሙስ እና ምሴተ ሐሙስ " ትባላለች !

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና መምህር ሲሆን የአገልጋዮቹን የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ ማጠቡ ይታሰብበታል።

#አንድም አዲስ ምስጢር በተግባር ምስጢረ ጥቅምት እና ምስጢረ ቁርባን የተመሰረቱበት ቀን ነው።

#አንድም ጌታ የመጨረሻውን ጸሎት በ ጌቴሴማኔ የጸለየበት ነው ። ለሐዋርያቱ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሎ ያስተማረበት ዕለት ነው።

#አንድም ከስቅለት በፊት የምትገኝ ሐሙስ ናት እና የመጨረሻዋ ሐሙስ ትባላለች። በሲኦል ቁራኝነት ለሚኖሩ ነፍሳት የመጨረሻቸውም ናትና ።

ስለትዕትናው ግን ሊቁ እንዲህ ያመሰግናል !

ተራሮችን በኀይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፤ የባሕርን ውሃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በወንዞች መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውሃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፤ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን እንዲታጠቡ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በኦሪቷ ድንኳን ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውሃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ጀመረ።

መጽሀፈ ምስጢር በቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንንም ተቀብሎ ይህችን ሳምንት በደህና ያስፈጽመን በሰላም ዘንድ የትንሳኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጥያታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ #ጸልዩ

#እግዚኦ_ተሰሃለነ
#በሕማሙ_ይታረቀን
#ጸልዩ_በእንተ_ቤተ_ክርስቲያን_ቅድስት