ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ባለማወቅ ማወቅ !
" #አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም .... "

ደመና ከማረግ ከማይጋርደው ከእናቶቻችን ጸሎቶች መካከል አልፎ አልፎ የምንሰማው ንግግር ነው። አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም ፣ አንተ የፈጠርከኝ ሚካኤል ....ወ.ዘ.ተ
ታድያ ይህን የየዋሃን ጸሎት የሰማ እንደኔ ያለ በማወቅ ያላወቀ ሰው "እናቴ የፈጠረሽኮ እግዚአብሔር ነው ለምን እንደሱ ትጸልያለሽ ? " ብሎ ለማረም ይቃጣዋል።

በርግጥም ሥነ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ካለመታየት ወደ መታየት አምጥቶ የፈጠረው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሆኖም ግን ይህ የእናቶቻችን የዋህትን ገንዘብ ያደረገች ንግግራቸው በኃያሌው ትክክል ነች ! እንዴት የሚል ካለ ጥቂት ያንብብ ።

#እናቶቻችን የመረዳት እምነት ሲኖራቸው እኛ ደግሞ የማወቅ እምነት አለን ። እውቀት ተኮር እምነት ለሰዋሰው ፣ ለንግግር ጠባይ ፣ ለነጠላና ብዙ ቁጥር እንዲሁም መደብን ጠብቆ አሳክቶ መናገር ወይም መጻፍ ሲሆን ይህን ያላሞላ ንግግርና ጽሁፍም ስሕተት እንደሆነ እናስባለን ስለዚህ የእናቶቻችን ንግግሮችና ጸሎቶች የሚሰምር አይመስለንም። የመረዳት እምነት ያላቸው እናቶቻችንና አባቶቻችን ግን ትክክለኛውን የእምነት መሠረት በልባቸው ይዘው እና አውቀው ማለትም #እግዚአብሔርን ፈጣሪ #እመቤታችንን እመ ፈጣሪ /የፈጣሪ እናት/ እንደሆኑና እንደሚባሉ እያወቁ ለቋንቋ አጠቃቀማቸው ሳይጨነቁ እርሱ የማያውቀው የለም በማለት በየዋህነት ብቻ አንዱን በአንዱ ሊጣሩበት ይችላሉ።
ለምሳሌ እግዚአብሔር ጠባቂያችን ነው ። ቅዱሳን መላእክትም ጠባቂዎቻችን ናቸው። ታድያ አንድ ሰው ተነስቶ ጠባቂዎቼ ቅዱሳን መላእክ ሆይ ብሎ ቢጸልዬ መላእክቱን ፈጣሪ አደረጋቸው አያሰኝም ።ከፈጣሪ ጋር የሚያመሳስላቸውን አንድ ዘርፍ መርጦ ለጸሎት ተጠቀማቸው እንጂ ፈጣሪና ፍጡርን አስተካለ እኩል አደረገም አያሰኝም። በተመሳሳይ እናቶቻችንም የፈጠርሽኝ እመቤቴ ሲሉ እንደ ፈጣሪ የሆንሽ ፈጣሪን የምትመስይ ማለታቸው ነው። የእመቤታችን የማርያም መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል እንደሚል /ተአምረ ማርያም መቅድም / አያይዞም ዓለሙ ሁሉ የተፈጠረው ስለ ድንግል ማርያም እንደሆነ ሲያስረዳ አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነርሱ (ዘር) እንድትወለድ ተፈጠሩ ይላል።
#ሌላው አዳሪ በማኅደሩ ማኅደርም በአዳሪው ይጠራል። ለምሳሌ ሰይፍ በሰገባው ያድራል ይህን የሚያውቅ ሰው ሰይፉ የተለየው ሰገባን ቢያይና ሰይፉ በሰገባው እንደሌለ ባያስተውል ሰገባውን ሰይፍ ብሎ በአዳሪው ሊጠራው ይችላል ።በተመሳሳይ ዳዊት የሌለው ማኅደር ያየ አንድ ሰውም ማኅደሩን አይቶ ብቻ ዳዊቱን አቀብለኝ ብሎ ማኅደሩን ዳዊት ብሎ ሊጠራው ይችላል ትክክል ነው አዳሪ በማኅደሩ ማኅደሩም በአዳሪው መጥራት ልማድ ነውና ሰውየውን ከመግባባት አያግደውም ።
እናቶቻችንም እመቤታችንን አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም ሲሉ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣሽን ፈጥረሽ የምትመግቢን በኃላም እንደ ብራና ጠቅልለሽ ዓለምን የምታሳልፊ ፈጣሪያችን ነሽ ማለታቸው አይደለም 9ወር ከ5ቀን በማኅጸንሽ ያደረብሽ (የተዋሕደሽ ) ሦስት ዓመት በጀርባሽ ያዘልሽው ሁለት ዓመት ከድንግልና የተገኘ አሊበ ወተት ያጠባሽው እመ ፈጣሪ የፈጣሪ እናት ነሽ፤ እንደ ፈጣሪ የሆነሽ ማለታቸው ነው።
#በርሷ ባደረ በፈጣሪ ልጇ እርሷን ፈጣሪተ ዓለም /የመፈጠር ምክንያት/ ብሎ እንደ መጥራት ነው። ልክ ሰገባውን ሰይፍ ማኅደሩንም ዳዊት ብሎ እንደመጥራት ያለ አጠራር። አንድም በቀደመች ሔዋን እናታችን አማካኝነት ሞት ወደ ዓለም መጣ በዳግሚት ሔዋን በእመቤታችን አማካኝነት ደግሞ በዳግም ተፈጥሮ ሕይወት ተሰጠን ።
ስለሆነም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የመዳን ምክንያት ብቻ ሳትሆን አዳምና ሔዋንም (የሰው ልጅ ሁሉ) ድንግል ማርያምን ለማመስገን የተፈጠሩ በመሆናቸው የመፈጠራችን ምክንያት ናትና የተፈጠርንብሽ ብለው መጥራታቸው ለእውነት የቀረበ እንጂ ስሕተት አይደለም። ይህን በመሰለችሁ በመረዳት ላይ በተመሠረተችሁ የዋህትን ገንዘብ ባደረገች የእናቶቻችንና የአባቶቻችን ንጽህት ሃይማኖት እናምናለን እንታመናለን !።

ዋቢ :- #ተአምረ ማርያም መቅድም ዘዘወትር
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም
#24ቱ_ካህናተ_ሰማይ_25 ሆኑ !
_______

አስቀድመው ቅዱሳን ሐዋርያት 12 ብቻ ነበሩ ከመካከላቸውም ይሁዳ ገንዘብ ወዶ ዘመድ ለምዶ አገልግሎቱን ትቶ ሄደ ሐዋርያትም ወንጌል በዓለም ሳይሰበክ ቢቀር አገልግሎታችን ተስተጎግሎ መቅረቱ አይደለ ብለው እግዚአብሔር ባወቀ ይሁዳ በተዋት አገልግሎት ፈንታ ሌላ ሰው እንዲሿምላቸው በርናባስንና ማትያስን አቀረቡ መንፈስ ቅዱስም ማቲያስን መርጦ ሰጣቸው:: የሚገርመው ነገር የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ ነው በአንዱ ይሁዳ ፈንታ ሁለት ምትኮችን ሰጣቸው አንዱ ማቲያስ ሲሆን ሌላው እራሱ በቃሉ ሐዲስ ሐዋርያ ብሎ የሾመው ተክለ ሃይማኖት ነው ቅዱስ ጳውሎስን ከአሳዳጅነት ቅዱስ ጴጥሮስን ከዓሳ አጥማጅነት እደጠራቸው ሐዋርያትን በጠራበት አጠራሩ አባታችን ተክለ ሃይማኖትን እንሰሳ ከሚያድኑበት ("ድ")ጠብቆ ይነበብ) ጫካ ጠርቶ በወንጌል መረብነት ሰው የሚድኑ ("ድ")ላልቶ ይነበብ አዳኝ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጉ ሾማቸው የሐዋርያት ቁጥረም 12 ቢሆንም በሐዲሱ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አማካኝነት ያለ ወትሮ 13 ሆነ ምነው መጻሕፍት 12ቱ ሐዋርያት አይደል የሚለው ቢሉ መጻሕፍት በቀረበው የመጥራትም ፀባይ አላቸው 12ቱን ሐዋርያት አስሩም አያለ እንደጠራቸው ማለት ነው ስለዚህ 12ሐዋርያት ስላለ 13ተኛ አይጨመርም አያሰኝም

#አባታችን ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወገን ብቻ ሳይሁን ከስማዕታትም ጋር ጭምር ነው ምነው ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሥጋቸውን የቆረሱ ደማቸውን ለምስክርነት ያፈሰሱ እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉ ሰዎች አይደሉም እንዴ ቢሉ አባታችን ተክለ ሃይማኖት መከራን አብዝቶ በመቀሎል ከሰማዕቱ በምን ተለዮ?በዳሞቱ ንጉስ እጃቸው በሰይፍ ተቆረጠች እግዚአብሔር እንደ ቀድሞ ጤነኛ አደረገላቸውጉልያድን በሚያካክሉ በሞተሎሚ በወታደሮች በሽምግልና አቅማቸው ደም በአፍና በአፍንጫቸው እስኪተፉ ተደብድበዋል በንብ ቀፎ ተደርገው ወደ ገደል ተጥለዋል ከዚህ ሁሉ ስቃይና ደም መፍሰስ በኃላ እራሱ አልበቃ ብሏቸው ወደ አደባባይ ወጥቼ ስለ ስምህ መስክሬ እንደሰማዕታት ደሜን አፍስሼ ልሞት እፈልጋለው አሉ:: እግዚአብሔር ግን ከዚህ በላይ ሰማዕትነት አንደሌለ ሲነግረን እኔ ከአንተ ሰውነት በእመምህ ምክንያት የሚወጣውን ፈሳሽ እኔ እንደ ሰማዕታት ደም አቆጥርልሃለው ብሎ ዕረፍታቸውን በሰማዕታት ዕረፍት ቆጠረው ::
#አንዳንድ ሞኝ ሰዎች ይህን በማንበብ እንዴት የተክለ ሃይማኖት በእመም ከሰውነታቸው የወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ)እንዴት ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል ይሆናል? ሲሉ ይሰማሉ ጌታችን መዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ" ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል"ሲል ተደምጧል #ማቴ 25 ÷40 ታዲያ ለሰው ማድረግ ለእርሱ እንደማድረግ ተደርጎ ከተቆጠረ ወይም የአባታችን የሰውነት ( ፈሳሽ ተቅማጥ) እንዴት አንደ ሰማዕታት ደም መቆጠሩ ስህተት አይደለም እንደውም ይህ ነገር ስህተት ነው ከማለት ይልቅ የጌታችን ምሳሌ ስህተት ይመስላል ሰው ሲራብ ማብላት ሰው ሲጠማ ማጠጣት ሰው ሲታሰር ሄዶ መጠነቅ የማይራበው እግዚአብሔር ተርቦ እንደ ማብላት የማይጠማውን እግዚአብሔርን ተጠምቶ እንደ ማጠጣት የመይታሰረው እግዚአብሔርን ታስሮ እንደተጠየቀ አድርጉ መቁጠር አንዴት ይቻላል? ሌላውና ወሳኙ ነጥብ በህመም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ) እና ደም ከሚያስከትሉት ችግር አንጻር ምንም ልዮነት የላቸውም በሳይንሱም ዓለም አገልግሎቱን ያልጨረሰ ፈሳሽ ከሰውነት ከወጣ በቶላ በሌላ ፈሳሽ ምግቦች እንዲተካ ይደረጋል ለምሳሌ" ሀተት "የተሰኘውን የጠቅማጥ በሽታ ብንወስድ ለሁለት ሳምንት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ቀኞች ተተኪ ፈሳሽ ምግብ ሳንወስድ ዝም ብንለው ወደ ሞት ያደርሰናል ይህ ማለት ደም ሥር ተቆርጦ ብዙ ደም ከፈሰሰ በኃላ ምንም ተተኪ ፈሳሽ ሳይወስዱ እንደመቀመጥ እና እነደሚያስከትለው ችግር ሊቆጠር ይችላል:: ስለዚህ ሰማዕታት ደማቸውን አፈሰሱ ሲባል ለመኖር የሚያስችላቸውን ወሳኝ ነገር(ደም)ከሰውነታቸው ወጣ ማለት ነው አባታችን ተክለ ሃይማኖትም ልክ እንደ ደም ጥቅምነቱን ሳይሰጥ ከሰውነታቸው በመውጣቱ ደሙ ሳይፈስ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ሰማዕታት የክብርን አክሊል ወደ ሚቀዳጅባት ሞት እንደማይቀርቡ ሁሉ አባታችንም ለሞት ባልቀረቡ ነበር::

አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወይም ከሰማዕታት ወገን ናቸው ተብሎ ብቻ አይታለፍም ከካህናተ ሰማይ ከሡራፌል ጋርም ይመደባሉ ለወትሮ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል ቁጥራቸው 24ብቻ ነበሩ ኢትዮጵያዊው አባት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ሲሳይ ሐዲስ ሐዋርያ ሰማእት ወነብይ ወካህን በተወለዱ እና ባደጉ ጊዜ ግን 25ለመሆን ተገደዋል ::ኃዳር 24ቀን 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል እንደለመዱት ሥሉስ ቅዱስ ብለው መንበሩን አያጠኑ ሳለ ድንገት ቅዱስ ሚካኤል ከሰዎች ወገን የሆነ ሰው ሲሆን እንደ መላእክት ስድስት የፀጋ ክንፎች የተሰጡት ብርሃን ዘኢትዮጵያ የሆነውን አባታችን ተክለ ሃይማኖትን ይዞ አመጣው የወርቅ ማዕጥንትም ተሰጠው ከዙፋኑም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ቁጥርህ ከንግዲህ ወዲህ ከ24ቱ ሰማያተ ካህናት ጋር ይሁን አለው:: 25ተኛ ካህንም ሆኖ የሥላሴን መንበር ሥሉስ ቅዱስ እያለ በወርቅ ማዕጥንት አጠነ: : ራዕ ዮሐ 4÷4 ገድለተክለ ሃይማኖት
*ይቆየን*****
#የአባታችን እረድኤትና ምልጃው አይለየን ለዘላለሙ አሜን!!!
#በድጋሚ የተለጠፈ
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ኅዳር 23ቀን 2012 ዓ,ም