ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#እንኳን_ለአባታችን_የፍልሰተ_አጽሙ_በዓል_በሰላም_አደረሰን 🙏
#ከደብረ_አስቦ (አሰቦት) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ

#ኢትዮጵያዊው_ኤልሳዕ
በአጽሙ ሙት ያስነሳ
፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ -፳ ፩
ገ/ተ ሃይማኖት ም/፶ ፫
አጥንት በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌነት ሲጠቀስ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል።
፩ የሰው ኃይልን ያመላክታል መዝ ፶ ፫፥፭ ኢሳ፴ ፰፥፲ ፫
፪ የቅርብ ዝምድና መግለጫ ሆኖ ቀርቧል ዘፍ ፳ ፱÷፲ ፬ ሳሙ ፱÷፪
፫ የሞተ ሰውን ክብር ያስረዳል ዘፍ ፶÷፳ ፭ ዕብ ፲ ፩÷፳ ፪
# ይበልጡኑ_የቅዱሳን_ሰዎች ሞት /አጥንት (አጽም)/ እጅግ የከበረ ነው ። መዝ ፻ ፲ ፭ (፻
፲ ፮) ÷፲ ፭ ለአብነትም ተቀብሮ የነበረው የኤልሳዕ አጥንት /አጽም/ ሌላ የሞተ ሰው ከሞት እንዳስነሳ መመልከት በቂ ነው። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። ፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ - ፳ ፩
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው ኤልሳዕ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም የሥጋ ድካም ከትጋቱ እንዳያስታጉለው በስምንት ሰለታም ጦር እራሱን ከቦ ከደብረ አስቦ ዋሻ ከቆመ ሳይቀመጥ
ከዘረጋ ሳያጥፍ ፳ ፪ ዓመት ሲጋደል ሳለ ከመቆም ብዛት አንዲቷ የእግሩ አገዳ ተሰበረችና ከሰውነቱ ተለይታ ወደቀች።

# ደቀ_መዛሙርቱም እንደ ማንም መስሏቸው ስባረ እግሩን ከመቃብር ሥፍራ ወረወሯት የኤልሳዕን አጽም ሲነካው ከሞት ድኖ እንደተነሳው ሰው የአባታችን የእግራቸው አጥንት
የነካው በመቃብሩ ሥፍራ ተቀብሮ የነበረ አንድ ሰው አፈፍ ብሎ ድኖ በእግሩ ቆመ ። ገ/ተ ሃይማኖት ፶ ፫
የአባታችንንም ስባረ አጽም (ስባረ እግር) እያመሰገነ ሰላምታ ሰጠ " ይህን ያዮ ደቀ
መዛሙርቶቻቸውም የጻድቁ ስባረ አጽም ገባሬ ተአምራት መሆኗን አውቀው ከመንበሩ እግር በታች አክብረው በሰበን ጠቅልለው ቀብረዋታል:: " #የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር
አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። " መዝ ፴ ፫{፴ ፬}÷፲ ፱-፳

ይህ የቅዱሳን አጥንት (አጽም) #እግዚአብሔር የማይለየውና ሌት ተቀን የሚጠብቀው ነውና ቅዱሳን ጻድቃን ካረፉበት ሄዶ መሳለም በረከትን ያሰጣል ከሥጋም ከነፍስም ህመም አድኖ በጤና ያቆማልና የአጽማቸውን በዓል ማክበር እጅግ የሚገባ ነው ::

ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ " (ሐዋ፲ ፱÷፲ ፩-፲ ፪) ቅዱስ ጴጥሮስ በሰውነቱ ጥላ ድውያንን ሁሉ ይፈውሳቸው ነበር ። ( ሐዋ ፭÷፲ ፭ ) ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸው ቅድስና ለለበሱት ልብስና ለአካላቸው ጥላ ተርፎ ድንቅ ተአምራትን የሚሰራ ከሆነ እግዚአብሔር የሚጠብቀው አጽማቸውማ እንዴት አብልጦ ድንቆችን አይሰራ?!:: #አጥንት_ለሰዉ ልጅ ተክለ ሰውነት ወሳኝ ድርሻ አለው። ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች
መካከል የተወሰኑት ብንዳስስ፤ ለሰዉነታችን ቅርፅ ለመስጠት፣ የሰዉነት የውስጥ አካላት (Organs) ከአደጋ ለመከላከል #ለምሳሌ ደረት የሚያርፍበት ክፍለ አጥንት ለሳንባና
ለልብ ከለላ(covering) ይሰጣል፤ የራስ ቅል አጥንት አንጎል ምንም አይነት ጉዳት
እንዳይገጥመው ጠንካራ ልባስ ሆኖ ይከላከላል ፣ ሥጋና ጡነቻዎቻችንን አጣብቆ ለመያዝና የካልስየም ንጥረ ነገርን ለማጠራቀም ይረዳል፡፡

ክቡር የሆነ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ለቀናች ሃይማኖቱ አጥንት ነው። አጥንት የሌለው አካል ጤፍ እንደሌለው ማዳበሪያ መቆም አይቻለሁም:: ሀገሪቱና ቤተክርስቲያኒቱ ዶግማ ቀኖናና ትውፊቷን ይዛ ቅርጻን ሳትለቅ ቀጥ ብላ እንድትቆም አድርጓታልና።

#ምዕመኗ ልዮ ልዮ በሆነ በእግዳ ትምህርት ከበረትቷ እንዳይኮበልሉ ኖላዊ ትጉሁ ሆኖ በጾም በጸሎቱ የሀገር ዋልታ በመሆንም አካል ለምትባል ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ አጥንት ጋሻ፣ መከታ፣ ጥላ ፣ከለላ ሆነላት። የሃይማኖት ማነስ የምግባር ጉድለት እንዳያጋጥማትም በቃሉ ትምህር በእጁ ተአምራት በበረከቱ ሞላት፤ በረድኤቱ ጋረዳት እንደ አጥንት የሃይማኖት መፍሰሻ ነቅ የወንጌል መፍለቂያ ምንጭም አደረጋት።

ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር ፳ ፬\፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም # ለስባረ አጽሙ ከጻፍኩት በከፊል የተወሰደ::
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ክፍል :- #ስምንት (8)
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #22ደቂቃ ከ09 ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #5.2 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
°°°°°°°°°°°
Audio
ዐውደ ምሕረት
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ምዕራፍ :- #ዘጠኝ (9)
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #14:ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #3.4 mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
°°°°°°°°°°°
ዐውደ ምሕረት
Photo
#አንተ ዐለት ነህ !
_____
በተዋህዶ ከበረ የሚል አዲስ ሀሳብ ያመጡት ዶ/ር እጓለ ገ/ ዮሐንስ አይደሉም !። #ከበህሪ_አባቱ_ከአብ_ከብህሪ_ሕይወቱ_ከመንፈስ_ቅዱስ ጋር ትክክል የሆነው #እጓለ_እምሕያው_ወልድ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው።

አንዳንዴ በአግባቡ በዕውቀት የልተወቀረ ልቡናና የተዋቀረ ሕሊና ግንዛቤ የሌላቸው ዐለት ሰዎች እንውቀራችሁ ሲሉ ያበግነኛል።

በፊሊጲስዮስ ቄሳርያ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ መልስ ለሰጠው ጴጥሮስ በአውንታዊ መንገድ አንተ አለት ነህ የሚል ጽኑ መጠሪያ ተሰጥቶት እናያለን።

#ዛሬ ግን እኔ ይህን በአሉታዊ መንገድ እጠቀመው ዘንድ ግድ ሆነብኝ ስለዚህ አንተ ያልተወቀርክ አለት ነህ አልኸሁ ።
#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፤ ...”

#መዝሙር 4፥3
| በድጋሚ የተለጠፈ
" #ከምድር_ወደ_ሰማይ_ለማረግ_መሰላል_ሆንሽ "
________
#ውዳሴ_ማርያም ዘ አርብ

የውዳሴ ማርያም ጸሐፊ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ቢሆንም ቅሉ ደራሲው ግን መንፈስ ቅዱስ ነው። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ በገለጠለት መሠረት ሊቁ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ " ሲል አራቆ ጽፏል ።

አዎን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መሰላል ነች ። በመሠላል እታች ያለው ወደላይ ይወጣል እላይ ያለውም ወደታች ይወርድበታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የምድራዊ ሰዎችን ጸሎትና ልመና ወደ ሰማይ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ታደርሳለች ታሳርጋለች የእግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረትን ደግሞ ወደ ሰው ልጆች ታወርዳለት ፣ታመጣለችና አማናዊት መሰላል ነች። #ሊቁ_አባ_ጽጌ_ድንግል በማህሌተ ጽጌው "አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌከ ማርያም የዓአርግ ሉዓሌ" #ድንግል_ማርያም_ሆይ ያላንቺ አማላጅነት ወደ ሰማይ የሚያርግ ጸሎትና ልመና የለም" እንዳለ

ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ስለ ጌታችን ዕርገት ሲናገር እንዲ ይላል "እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። " #ሉቃ 24÷50

ዕርገቱም እንደ ኤልያስ በሠረገላ እንደ ሄኖክም በመሰወር እንደ ሕዝራም ሱቱኤል በመላእክት እገዛ የሆነ አይደለም ። ደመና ከዐይናቸው ሰውራ እስክትቀበለው ድረስ ከፍ ከፍ አለ እንጂ አልጠፋባቸውም። ሰማይን አተኩረው እስኪመለከቱ ድረስ የሰማይ መላእክትም እንኪገስጾቸው ድረስ በተመስጦ ሆነው ሲያርግ አዮት እንጂ አረቀቀባቸውም በሰው አምሮ በሚረዳና በሚገባ መልኩ በርዕቀት ከነርሱ ተለይቶ ከፍ ከፍ እያለ ዐረገ ። "እናትት የገሊላ ሰዎች እንዲህ አትኩራችሁ ወደ ሰማይ የምትመለከቱ ስለምንድነው እንዲሁ ሲሄድ እንዳያችሁ እንዲሁ ደግሞ ይመጣልና" #ሐዋ1÷11

መሰላል ሁለት ትይይዮ የሆኑ ቋሚ ዘንጎች ያሉት ሲሆን በመካከላቸውም በየተወሰነ ርቀቱ በተደረደሩ አግዳሚ ዘንጎች ሁለቱ ትይዮ ዘንጎች የተጋጠሙ ናቸው ::

ሁለቱ ትይዮ የሆኑ ረጃችም ዘንጎች በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን (ድንግል በክሌ) ያመሰጥራሉ። አንድም ብሉይና ሐዲስን ሲወክሉ በመካከላቸው ያሉ ርብራብ ዘንጎች ደግሞ የብሉይና የሐዲስ መገናኛው ድልድይ እመቤታችን መሆኟን ያስረዳሉ በቡሉይ መጨረሻ በሐዲስ መጀመሪያ ተገኝታለችን አንድም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ፈራጅ የሆነ ንጉሥ ሰው ሲሆን አምላክ አምላክ ሲሆን ደግሞ ሰው የሆነውን መካከለኛ ትወልደዋለችና። አንድም የጠቡ ግድግዳ የፈረሰባት ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ የታረቁባት የተቀራረቡባት የዕርቅ ሰነድ እመቤታችን ነችና መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ነው።
በመጻሕፍ ቅዱስ ላይም ይህ ነገር የጎላ የተረዳ ነው::..." ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ #እነሆም_መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም_የእግዚአብሔር_መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥# እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ #ዘፍ 28÷10-13

ታድያ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ አንቺ ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ሲል ግን እንደ መሰላል ተረግጧት ወጣ ማለት አይደለም የወጣው ወደ ሰማይ ነው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቁመትም እንደ ሰው ሁሉ ሦስት ክንድ ከስንዝር ብቻ ነው ።

በምሥጢር ሊናገር የፈለገው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ባይነሳ ኖሮ ለመለኮት ወደ ሰማይ ዐረገ የሚልል ነገር ባልተነገረለት ነበር የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ውጣ ፣ከፍ ፣ከፍ አለ ዐረገ የሚሉት ነገሮች ተነገረለት ። ቅዱስ ኤፍሬም ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብቻ ይበል እንጂ ቅሉ እመቤታችንስ ለቃል ከሰማይ ወደ ምድር ለመውረድም መሰላል ሆናዋለች። ድንግል ማርያም ባትኖር ኖሮ ከማን ሰው ይሆን ነበር? መንክር ኦ ዝ ምሥጢር!

እንዲያውም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዕርገቱንና ሰው የመሆኑን ምሥጢር ሲያወዳጁ እንዲ ይላሉ"የቃል ርደት በማኅጸን የሥጋ ዕርገት በአርባ ቀን"

ምን ማለታቸው ነው ቢሉ ለቃል ርደትም ለሥጋ ዕርገትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ መሰላል ሆና ለች ያለ እመቤታችን የቃል ርደት (መውረድ) ሆነ የሥጋ ዕርገት አይታሰብምና ነው።

ክቡር ዳዊትም ይህን የሊቁን ሀሳብ የቅዱስ ኤፍሬምን ሀሳብ ሲደግፍ እንዲ ይላል። “ #በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ #ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።” #መዝ (68) 68፥33 በምሥራቅ በኩል ማለቱ አቅጣጫን ብቻ የሚጠቁም ሳይሆን ከምሥራቅ ፀሐይ እንደሚወጣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም ፀሐየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ይወጣልና እመቤታችን ምሥራቀ ምሥራቃት ሞጻ ፀሐይ ትባላለችና ፀሐይ ክርስቶስ የወጣባት ምሥራቃዊ መሠላል እርሷ ነች ። መለኮት በሁሉ የመላ ፣ በሁሉ ያለ ነው የሌለበት ቦታ የለም በዚህ አለ በዚያ የለም አይባልለትም #መዝ 138(139)÷7-10 ነገር ግን የምሥራቅ የእመቤታችንን ሥጋና ነፍስ በመዋሕዱ ግን ከምድር ወደ ሰማይ ሄደ ከፍ ከፍ አለ ዐረገ ተባለለት ። መለኮት ዐረገ እንዲባል ምክንያትቱ ምሥራቁ ሆነችው ።

የነዚህ የዳዊትና የኤፍሬም የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ምን ይረቅ?
__#ለምን_ዐረገ ? ___
#ትንቢቱን_ለመፈጸም :-"አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። #መዝ46(47)÷5-6 ነቢዮ ዳዊት ይህን የተናገረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ነው።
#ሥፍራን_ለማዘጋጀት :- መግሥተ ሠማያት ቀድማ ያልተዘጋጀች አሁን ሄዶ የሚያዘጋጃት ሆና ሳይሆን ለእናንተ ለአባቴ ብሩካኖች የተገባች ሆና በመጨረሻው ቀን ተገልጣ እንድትሰጣችሁ የማደርግ እኔ ነኝ አሁን ሄጄ በአባቴ ዕሪና (ትክክል ) በአብ ቀኝ በክብሩ ዙፋን ልቀመጥ ይገባኛል ሲል ነው “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” #ዮሐንስ 14፥2
#መንፈስ_ቅዱስን_ለመላክ :- “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።” #ዮሐንስ 16፥7

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ ማርያም
ሰኔ ፫/፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
ዜና እረፍት!
#የእግዚአብሔር_ቤት_ጠራጊ ናታኔም !
________________°°°°°°°_____________
😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢
የደብራችን ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ትጉ እና ቅን አገልጋይ፣ በእምነት የፀና እጅግ ሲበዛ ሃይማኖተኛ ከእምነቱ እና ከየዋህነቱ የተነሳ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ተገልጠው ያነጋገሩት፣ በደብሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ሁሉ በአግባቡ በፍቅር የተወጣ ታላቅ ወንድማችን አቶ ሄኖክ ታምሩ በ፳፭/፱/፳፻፲፬ ዓ•ም ከዚህ ዓለም በሥጋ ሞት ተለይቷል።
አምላከ ተክለሃይማኖት የወንድማችንን ነፍስ በቅድሳኑ እቅፍ ያኑርልን! አሜን
#cradit መ/ም@ ሚኪያስ ዳንኤል እና
ቴዎድሮስ ክፍሎም
26/09/2014 ዓ/ም
Audio
#የፍቅር_ሕብረት
እንኳን ሊፋቀሩ በእህልና ውኃ
የሚገለማመጡ ሲልፉ በጉዳና
ጠላቶች ነበሩ ሳምርና ይሁዳ

#ዛሬ ግን በአንድነት ይህው ተባበሩ
በአንድ አካል በአንድ አምሳል በፍቅር ከበሩ

ዲያቆኑ በጥበብ በአራራይ ዜማ
አራርቶ ቢነግራት ውኃ እንደተጠማ
ሳምር ተሸነፈች በድምጹ ተደማ
ትቀዳለት ጀመር ገንቦዋን አዝማ

ከክርስቶስ ቀድሞ ውኃ ካሰጠማ
በል ንገረኝማ
ማነው ያስተማረ እንዲህ ያለ ዜማ?

#ደሞ ወንድም ጋሼ
የአይሁድ መምህራቸው አንተ ሆነ ሳለህ
እንዴት ከሳምር ሴት ውኃ ትጠጣለህ ? ብለው ቢጠይቁህ

ክርስቶ ተጠመቶ ውኃ አጠጪኝ ያለው
ሄኖክ ሰብኮ ደክሞ እንዲጎነጭ ነው
ብለህ መልሳቸው
ፍቅር ድንበር አልባ ነው እኮ በላቸው

#ተክለ ኤል ኃ /ማርያም
ሰኔ 04/2014 ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ
ዐውደ ምሕረት
Photo
#መንፈስ_ቅዱስ ወረደ ላይለ ሐዋርያት
ተመሲሎ(5) በነደ እሳት

#መንፈስ_ቅዱስ ወረደ በሐዋርያት ላይ
ተመስሎ (5) በሚነድ እሳት
"ይህ ቀን #የቤተ_ክርስቲያን_የልደት ቀን ነው"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ቤተ ክርስቲያ ሆይ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅጸነ ሐዋርያት እንኳን በዛሬዋ ዕለት ተወለድሽልን👏

ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሰኔ05/2014 ዓ.ምአ
አ.አ ኢትዮጵያ
ገቢው ሙሉ በሙሉ ለአ.አ ደብረ አሚን #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማሳደሻነት የሚውል!