ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የአድዋ_ተራሮች ትዝብት
_____

ቲሺ ምናለ ከዚህ ንበር ትንሽ ቀቅ ብዬ በተፈጠርኩ ካድማሱ ባሻገር እንደ ሰንሰለት ከተያያዙት ከአድዋ ተራሮች በመጠኑ ተለቅ የሚለው የአንዱ ተራራ የምሬት ንግግር ነበር

#እንዴ ይህ እኮ እኛ የተፈጠርንበትን የነጻነት ጀንበር የተፈነጠቀበት የኢትዮጱያ መሬት ነው ይህን መሬት ስንቱ ተራራ ሊፈጠርበት እንደሚመኝ እረስተህው ነው ።

ሌላኛው ከግራ ያለው ተራራ ቀበል አርጎ የዓለምና የአፍሪካ ስመ ጥር ተራሮች ኤቨረስትና ኪሊማንጃሮ እራሳቸው ረጃጅሞች ስመ ጥር ተራራሮች ሆነው ከሚታወቁ ይልቅ እዚህ ቦታ ተፈጥረው የጥቁር ሕዝብ ድልን የሰውልጅ እኩልነት የነጻነት ቀንዲል መለኮሰን ዕብሪተኝነት አንገት ሲደፈ ጨዋነት ሲረታ ቢያዮና የጀግኞች የዐይን መስክር ቢሆኑ የበለጠ ደስተኛ ይሆኑ ነበር። አንተ እዚህ በመፈጠረህ ታማርራለህ

#ግዙፉ ተራራ ከመካከላቸው ሆኖ ዐይ የልጅ ነገር እሱ መቼ ጠፋኝ " ለቀባሪው አረዱት አሉ " እናንተ በዚህች ምድር ከመፈጠራችሁ በፊት እኔ ቀድሜ ነበርኩ አድዋ ጦርነት እራሱ ከእናንተ የተሻለ ቁመናና ርዝመት ያለኝ በመሆኔ ከናንተ በተሻለ የጦርነቱን ሙሉ እንቅስቃሴ ለማየት ታድያለው የአባ ነብሶ ድፍረት መድፉን ለብቻ ሲያጓራው ፣የገበየው ደረት ደልብጦ መግባት ፣የጣይቱ ብልሐት፣ የምኒልክ ጽናት የሰማዕቱ እርዳታ ሁለም እንደ ትላንትና ሆኖ በሐይኔ ሕሊናዬ ተሰሎ ተቀምጧል መቼም ልረሳው አልችልም ያቺ የኃላ ደጀን የነበረች አዝማሪ ጻድቄ እራሱ ሳትቀር ከነ ግጥሞቿና ከነ አበረታች መሰንቆዋ የዕለት ለዕለት ትዝታዬ ነች እንዲያውም አንድ ጊዜ ጠላት በአድዋ ሥላሴ በኩል ገፍቶ ሲያይል "የአድዋን ሥላሴ ጠላት አረከሰው ገበየው በሞቴ ግባና ቀድሰው " ብላ ገጥማ ነበር።
ታድያ ይህን ያክል የምታስታውሰው ከሆነ ምን ቢመር ነው ከዚህች የነጻነት ድንበር ውጪ መፈጠርን የፈለክ? ሆ ሰው እንዴት ሰው አልኩ እንዴ ተራራ እንዴት በተመረጠ መሬት በነፃነት ሀገር ተፈጥሮ ሲያበቃ ለምን በዚህ የነፃነት ሀገር ተፈጠርኩ ብሎእንዴት በከንቱ ያማርራል?
#በከንቱ_አይደለም ማማረሬ እውነት ይዤ እንጂ ። በግራና በቀኝ ያሉት በመጠናቸው አነስ የሚሉት ተራሮች በተመሳሳይ ሰዓትና ቃል ማለት አልገባንም? አሉ።

ከመካከላቸው መሆኑ እንደፈለጉ ጥያቄ እየጠየቁ እንደ ገና ዳቦ በጥያቄ ሊጠብሱት የተዘጋጁ አስመስሏቸዋል። ከዛ አንደኛው ተራራ ከአድመኝነት መንፈስ ወጣ ለማለት ብሎ ሀሳቡን ለመረዳት ትንሽ ፋታ ከወሰደ በኋላ እስቲ በል ንገረን ምንድነው ይህን ያክል ቁጭት አሳድሮ የተፈጠርክበትን የነፃነት ምድር ለመጸየፍ ያበቃህ? ሲል በእርጋታ ጠየቀው
እሳት አመድ ወልዶ ሳይ እንዴት የቁጭት ቆፈን አይውረሰኝ? በዕድሜ አንጋፈ አዛውንት የሚመስለው ተራራ ሳግ እየተናነቀው እንዳይታወቅበት ጉረሮውን እያጸዳ ቀስ ብሎ ቁጭቱን ሊያስረዳቸው ጀመር።
#በዚህ ቦታ በኖርኩበት በእስኳሁኑ ዕድሜ እንዲህ ዐይነት ውርደትና መሸማቀቅ ደርሶብኝ አያውቅም ። ጥንት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጠላትን በዚህ ሥፈራ ድል ሲነሱ ለ ሀገር ለድንበር ለሃይማኖት ለአንድነት ለአንድ ሕዝብ ብለው ዋጋ ፍለው ደም አፍስሰው ሥጋ ቆርሰው አጥንት ገብረው ባለፉበት በዚሁ ሥፍራ በገደሉበት ሥፍራ ሲገዳደሉ ነጻ በወጡበት ሰፈር ምርኮ ሲገቡ ድል በነሱበት ሀገር ድል ሲነሳሱ ከማየት ሌላ ምን ውርደት አለ? የዘንድሮስ አድዋ ፋሽሽት ኢጣሊያንን ወይስ የእናት ልጅ ወንድምን ድን የነሳንበት በዓል ነው ብለው ሊያከብሩት ነው ?

የጀግኖች ደም ዋጋ ቢስ ሲሆን ከማየት ሌላ ምን አስቆጪ ነገርስ ይኖራል ? እነሱስ አንዴ ለሀገር ለድንበር ለነፃነትና ለሃይማኖት የሚገባቸውን ዋጋ ከፍለው በክብር አርፈዋል ይብላኝ እንጂ ለኔ ሞት ወስዶ ለማይገላግለኝ ግዑዝ ነው ይሉኛል ምንም የማይሰማኝ ንግግሬን ማድመጥ ያልቻሉ እነሱ መሆናቸው ማን በነሱ ቋንቋ በነገረልኝ

#ያኔ ቋንቋ ብሔር ዘር ሳይለያቸው እንደ አንድ ልብ መካሪ አንደ አንድ ቃል ተናጋረ ሆነው ጠላትን ያስጨነቁ ዛሬ ብሔሬ ቋንቋዬ ተባብለው ሲተላለቁ በዚሁ ሥፍራ ሳይ ለምን አልበግን

ደሞኮ ቋንቋውም ቢሆን በቅጡ የአባቶቻቸውን ቋንቋ አቀላጥፈው አያውቁትም ሁሉም ባለ ቋንቋ ነኝ ባይ ከእንግሊዘኛ ሳያዳቅል ማን በቅጡ የሚናገራቸው አለ እስቲ ቆንጆ ኦሮምኛ ተናጋሪ አምጡልኝ እስቲ ንጹሑ አማርኛ አንደበት ያለው ፈልጉልኝ እስቲ ትግርኛን አቀላጥፎ የሚያወራ የሰሜን ሰው ፈልጉልን የለም አታገኙም ። ለመጠፋፋትና ለመገዳደል ሲሆን ግን ብሔሬ ቋንቋዬ ይባልልኛል አስቀድመህ በቅጡ ውረስወ እስቲ ።

#ሁለቱ ተራሮች ምንም ሊመልሱለት አልቻሉም ከልብ ያልኖረ እውነት ከየት ይገለጣል።

እሱማ እውነትህን ነው በሚል በተጸጸተ አስተያየት ከግራም ከቀኝም ተመለከቱት

የላሊበላ መቅደስ ሰሪዎች እናንተ አይደላችሁም ቢሆንማ ኖሮ ሌላም አስደማሚ የኪነ ሕንጻ አብዝታችሁ ሰርታችሁ ከድኅነት አረንቋ በወጣችሁ ነበር የሚሉን የቀደመ ሥልጣኔያችንን ሊያስክዱን የሚዳዱ የነጭ እባቦች ከንፈር አደዋም የናንተ የኢትዮጵያዊያዊያን ድል አይደለም ቢሆንማ ዛሬ አንድነታችሁን ምን ፈታው መተባበራችሁን ማን ወሰደው ቢሉን ምን እንመልስ ይሆን?
በዚህ የመበላላት መንፈስ ውስጥ ሆነን የአፍሪካዊያን የነፃነት ቀንዲል የተለኮሰው ከዚህ ሀገር በነዚህ ተራሮች ሥር ነው ቢባል ማን ያምናል?

#አንዱ ወጣት እግር የሆነ ተራራ ይህማ አይሆንም እኔ አንደበት አውጥቼ እንደ ቢታንያ ድንጋይ አድዋ የኢትዮጵያዊያን ድል ነው ስል ጮክ ብዬ እመሰክራለዋ ሲል ሌላላው ቀበል አርጎ አዎ እኔም ዝም አልልም አድዋ ከኢትዮጵያ ምድር የተገኘ የጥቁር ሕዝበ ሁሉ ድል ነው ሲል አሳቡን ተጋራው
አንጋፈው ተራራ ግን ከሰማይ ደመናትን ሰብስቦ እንደ ጋቢ ተከናንቦ ጆሮ ዳባ ልበስ በሚል በሽሙጥ ተከናነበ ቀጠል አርጎም አንድነቱና ህብረቱ እንዲመጣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ካልጣረ እመሆኝ ወደፊት እኔ እንዳልኳችሁ ሳይሆን አይቀርም በርግጥ ሁሉም ነገር ከትምህት ቤት መማር አይቻልም የዕድሜ ባለ ፀጋ ሲነግራችሁ ግን እህ ብላችሁ ብሰሙ መልካም ነው ዕድሜ እዚህች ዮኒቨርስ ላይ ያልተገነባና የማይገነባ ትልቅ ዮኒቨርስቲ ነው ።

እናንተ ይህ ትላላችሁ አክሱም፣ ጀጎል፣ አባይ ፣ጣና ሁሉ ሳይቀር ከሀገር ሊወጡ ሲሉ አገኘዋቸውና ስለምን ይህችን ምድር ለቃችሁ ትወጣላችሁ ስል ሞገትኳቸው ሲሉ የነበሩ ኢትዮጵያ አብጠርጥረው ያውቋታል የሚባሉ ለምድ የከበዱ ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ዛሬ መሀመድ ግራኝ ወራሪአይደለም ሲሉ እየተደመጡ ነው ተደምጠዋል ምን ያርጉ ሥልጣን ወደ ሐሰት ዘወረቻቸው ። ታድያ ግራኝ ወራሪ ካልሆነ አርበኛ ነውንን? አምባ ሳደር ነውን? ወይ ብሔራዊ ጀግናችን ነው? በዚህ ዓይነትኮ ወደፊት ዐውልት ይቁምለት መንገድ ይሰየምለት መባሉ አይቀሬ ነው ። በዕድሜ የምታንሱኝ ልጆቼና ወንድሞቼ ይህ አበክራችሁ ስሙኝ በልባችሁም ጽላት ጽፋችሁ አኑሩት እውነት ሁል ጊዜም እውነት ነች ለማቻቻልና ሚዛን ለመጠበቅ አልያም ዲሞክራት ለመሆን ብለህ ልትሸፉፍናት መልኳን አጥፍተህ ልታጠይማት አትችልም ። መሀመድ ግራኝ ሀገር ያፈረሰ ሃይማኖት ያጠፈ ወራሪ ነው። ግራኝ ወራሪ አይደለም ካልን 11 ሚሊየን አይሁዳዊያንን በዘራቸው ምክንያት የጨፈጨፋቸው ኢትለር ቅዱስ ነው ሀገሩም ከደጋጎቹ ሀገር ከመንግሥተ ሠማይ ነው ማለት ነው