ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እሾህ #የሌለባት_ጽጌ_ሬዳ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ጊዜው የአበባና የፍሬ ጊዜ ነው ቤተክርስቲያንም ዘመነ ጽጌ ወርሃ ጽጌ ብላ ስለ ጽጌያት ታስተምራለች:: #ከመስከረም 26 እስከ #ህዳር 6 ቀን ያሉት ተከታታይ 40 ቀናት ናቸው ስለ ጽጌ ወይም ስለ አበባ የምታስተምረው ትምህርት ይህ እኛ የምናውቀውን በአፈር፣ በውኃና በፀሐይ ብርሃን አማካኝነት የሚያድገውን የእጽዋት አይነት ብቻ የሚመለከት አይደለም። ከዛ ይልቅ አማናዊት አበባ ስለምትባል ስለ ድንግል ማርያም በዚህ ወቅት በምልዐት ታስተምራለች ትሰብካለች:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እውነተኛ አበባ ነች።
እንደ ሳይንሱ ገለጻ አንድ እጽዋት እጽዋት ለመሰኘት ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን ሊያሞላ ይገባል ይላል። እነርሱም እውነተኛ ሥር እውነተኛ ግንድ እውነተኛ ቅርንጫፍ ናቸው ። እነዚህ እጽዋት በሥሮቻቸው አማካኝነት ከአፈር ውስጥ ውኃና ሚኒራልን በመውሰድ ከቅርንጫፍቻቸው ካሉ ቅጠሎች ደግሞ የፀሐይ ብርሃን በማምጣት በግንዶቻቸው አጓጓዠነት በመጠቀም ፖቶሰቴንስስ በተባለ ሂደት ምግቦቻቸውን ማዘጋጀት ይችላሉ ።እውነተኛ ሥር ግንድና ቅርንጫፍ የሌላቸውን አረንጓዴ ተክሎች ግን አልጋይ እና ፈንጋይ እየተባሉ ይጠራሉ እውነተኛ ሥር ግንድና ቅርንጫፍ የላቸውምና ምግባቸውን ማዘጋጀት አይችሉም ስለዚህ እጽዋት ተብለው አይጠሩም ::

#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ታዲያ ከእውነተኛም እውነተኛ የሆነች ( እጸ ሕይወት) እውነተኛ የሕይወት አበባ ነች መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች እውነተኛ የወይን ግንድ አብቃይ ቅርንጫፎቿም በሰማያተ የሚገኑ አረገ ወይን ነች:: (ሥር) መዝ 86÷1 (ግንድ)ኢሳ11÷1 (ቅርንጫፍ)ዮሐ 15÷5 ።

የሕይወት መብል መጠጥ የሆነ ክርስቶስን የወለደችልን ድንግል ማርያም እውነተኛ ሥር ግንድና ቅጠል ያላት እውነተኛ አበባ መሆኖን አሰረግጦ መናገር የተገባ ነው። ለምን ቢሉ
አንዳንድ ዲያቢሎስ ያደረባቸው ደፋር ሴቶች በዘመኑ ብኖር እኔም ክርስቶስን እወልደው ነበር ብለው የድንግልን ክብር ከእራሳቸው ክብር ጋር በትቢት ባልተገባ የሚያስተካክሉ ልካቸውን ማሳወቅ ስለሚገባ ነው በእስራኤል ያሉ ሴቶች ደግሞ ዛሬ ድረስ ክርስቶስ አልተወለደም ወደፊት ከአንዳችን ይወለዳል ብለው በድፍረት በከንቱ ይጠባበቃሉ በእውነት ግን እነዚህ ሴቶች እንኳን የሕይወት መብልና መጠጥ የሆነውን ክርስቶስን ሊወልዱ ቀርቶ ሊወልዱት የሚችሉትል ተራ ሰው እንኳ በአግባቡ ስለመመገባቸው እርግጠኞች አይደሉም ስለዚህም ምግባቸውን እንኳን ማዘጋጀት እንደ ማይችሉ አልጋይና ፋንጋይ ናቸው ማለት ይቻላል። እውነተኞች አይደሉምና ።

#እርሷ_እመቤታችን እንኳን ስለራሷ በትንቢት የተጻፈውን ባነበበች ጊዜ ከዚህች ቅድስት ሴት ከዘመኗ ደርሼ ውኃ ቀድቼ እንጨት ፈልጬ ገረዷ ሆኜ ባገለገልኳት ብላ በትህትና ገረድነትን ተመኘች እንጂ እኔ በሆኩ አላለችም ጊዜው ደርሶም መላእኩ ገብርኤል መጥቶ አምላክን ለመውለድ በተገባ ተገኝተሻል ብሎ የመውለዷን ዜና ሲያበሥራት እንኳ ይህ እንዴት ይሆንልኛል እኔ #የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለችሁ እንጂ ከወነማ ከመጣህማ ብላ በኩራት ሆና አልተናገረችሁም .....ይህ እንዴት ያለህ ትህትና ነው? የአምላክ እናቱ ነሽ እየተባሉ እራስን ገረድ ማለት! ሊቁም ይህ ትህትና ቢገርመው ልዕልናዋን ከትህትናዋ አስማምቶ " #በትህትና_የተናገርሽ ተራራ ሆይ " ብሎ ጠራት::
እውነተኛይቱ አበባ ግን አስቀድማ ዓለም ሳይፈጠር በተዘክሮተ ፈጣሪ ዋላም ዓለም ከተፈጠረ በኃላ በነቢያት ትንቢት በሐዋርያት ስብከት በደቂቀ አዳም ልብ የነበረች፣ ያለችና ፣የምትኖር የማደርቅና የማጠወልግ እንቡጥ አበባ ነች።
#አበባ የዓይን ማረፊያ የልብ ተስፋ የአፍንጫ መዐዛ ነው እመቤታችንም አስቀድማ ለእናት ለአባትዋ በኃላም ለደቂቀ አዳም ሁሉ የዓይን ማረፊያ የልብ ተስፋ የነፍስ መዐዛ ነች " #ከዕሴይ_ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ " እንዳለ ሊቁ #ውዳሴ_ማርያም ዘእሁድ ኢሳ11÷1
#አበባ መድኃኒትን ያስገኛል እውነተኛይቱ አበባ እመቤታችንም መዳኒ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን አስገኝታለች እስለዚህ " እሙ ለመዳኒት" የመዳኒት እናት ትባላለችና አባባ ነች ሉቃ 2÷10-11
አበባ ንብቦችን ይስባል ማርን ያሰራል እውነተኛይቱ አበባ እመቤታችንም ወልድ ክርስቶስን ስባለች ማር የሆነች የወንጌል ሕግን አሰርታለች። ማር ጥዑም ነው ክርስቶስና ወንጌልም ጥዑማን ናቸው አንድም ማር መድኃኒት ነው ክርስቶስ እና ወንጌልም መድኃኒት ናቸው::"ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል" መዝ 86(87)÷2
"ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና" መዝ 44(45)÷10-11
አበባ ምግበ ሥጋን ያስገኛል (ለምሳሌ አበባ ጎመን የመሰሉ ተክሎች ወዘተ...) እውነተኛይቱ አባ እመቤታችንም ምግበ ሥጋወነፍስ የሆነ ክርቶስን አስገኝታለች ዮሐ 6÷56 ማቴ 26÷26
"በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ " እንዳሉ ሊቃውንት ድንግል ሆይ በምንና በማን እንመስልሻለን ክብርሽን የሚገልጥ ነገር አጣን ብለን በተደሞ ዝም እንበል እንጂ እመቤታችንንስ አበባ ብቻ የሚገልጣት ሆኖ አይደለም።
እንዴት? ቢሉ አበባ ከምድር ተገኝቶ በምድር ይቀራል አበባይቱ እመቤታች ግን ከምድር ብትገኝም ቅሉ የማትደርቅ የማትጠወልግ ምድራዊት ወ ሰማያዊት የሆነች ለምለም አበባ ነች።
አበባ ይልቁኑ ጽጌ ሬዳ በእህሾ የተከበበ ነው ። አበባይቱ እመቤታችን ግን የጥንተ አብሶ እሾህ ያልከበባት ንፁህ ጽጌ ሬዳ ናት። ወርቅ ከመሬት ከጭቃ ይገኛል ነገር ግን ጭቃ አይደለም እመቤታችንም ከምድር የተገኘች ሆና ሳለ ግን ምድራዊ በደል ያላቆሸሻት እሾህ አልባ የወርቅ አበባ ነች ለይቶ ቀድሷታልና “ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።” መዝ45(46)፥4
አበባ መድኃኒት ቢያስገኝ ከጊዜያዊ ሕመም የሚያድን ጊዜያዊ መድኃኒት ነው የሚያስገኘው አበባይቱ እመቤታችን ግን አንዴ ከተበላ አንዴ ከተጠጣ ዳግመኛ የማያስፈልገውን ዘላለማዊ ፍቱን መድኃኒትን ያስገኘች ሕያው አበባ ነች።
አንድ ንጥል አበባ ዘሩን የሚተካው ወንዴና ሴቴ የተባሉ ክፍሎቹን በመጠቀም ነው የወንዴው ብናኝ ጊዜውን ጠብቆ እራሱን ሲያበን ማጣበቅ የሚችለው የሴቴ ክፍል ብናኙን ይቀበልና ሌሎች አበቦችን ማፍራት ይጀምራል ። ይህ ሂደት ኢ ተሻጋሪ(እዛው በዛው) የማፍራት ሂደት ይባላል ። በሌላ በኩል ደግሞ የአንዱ ንጥል አበባ የወንዴ ብናኝ በንቦች ፣በወፎች፣ እንዲሁም በሰዎች ንኪኪ ወይም በንፋስ ሽውታ አማካኝነት በኖ ከራሱ የሴቴ ብናኝ ተቀባይ ውጪ ተሻግሮ በሌላ አበባ የሴቴ ክፍል ላይ በመጣበቅ የሚያፈራበትም መንገድ አለ ይህም ተሻጋሪ የአረባብ ዘዴ በመባል ይታወቃል ።

አበባ እንዲ ባለ መልክ ሲያብብ አማናዊቷ አበባ እመቤታችን ግን ያለ ዘርዐ ብዕሲ ያለ ወንድ ዘር ) በ ግብረ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጸንሳ መውለድ ችላለች ስለዚህ በእጅጉ ከአበባዎች ሁሉ ትበልጣለች አልን።

"ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች #አንቺ_እንደ_እርሷ_ነሽ #ውዳሴ_ማርያም_ዘእሁድ
.......ይቆየን ............
ምልጃ ቃልኪዳኗ ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያኖች ጋር ለዘላለሙ ጸንቶ ይኑር ...አሜን!
ኃ/ ማርያም
ጥቅምት 1/2013 ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጲያ
👇👇👇👇👇👇👇
#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ስለ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉ ተአማኚነት ያላቸው ይትባህሎች

፩. #አስታራቂነት ፡-ነብርና አንበሳ አይስማሙም፤ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥዕል ሥር ግን ነብርና አንበሳ ተስማምተው ይታያሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ለመታረቅ አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለማስታረቅ የሚሄዱ ሽማግሌዎች ‹አቦን ሆነን መጥተናል› ይላሉ፡፡

፪. #የአቦ_ጠበል ፡- አንድ ሰው እየተመገበ ቢያንቀው ‹የአቦ ጠበል› እያልክ ውኃን ሦስት ጊዜ ጠጣው ይባላል፡፡
፫. #የአቦ_ብቅል ፡- አንድ ሰው ከማያውቀው ቦታ ስሙ ቢጠራና በአካባቢው የሚያውቀውን ሰው ቢያጣ የጠራው ሰይጣን ሊሆን ስለሚችል ‹‹የአቦን ብቅል እፈጫለሁ› በል ይባላል፡፡

፬. #የአቦ_መገበሪያ ፡- አንድ ሰው አንድን ነገር አጥፍቶ ተሠውሮ እንደማይቀመጥ ለመግለጥ ‹‹የአቦን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይውላል›› ይባላል፡፡

፭. #አቦ_ሰጥ ፡- አንድ ሰው የማያውቀውን ነገር በግምት ሲናገር ‹አቦ ሰጥ› ይባላል፡፡

፮. # በአቦ_ይዤሃለሁ ፡- አራዊት የቤት እንስሳትን እንዳይበሉባቸው ገበሬዎች ‹በአቦ ይዤሃለሁ› ብለው ይገዝቷቸዋል፡፡

፯. #የአቦ_መንገድ ፡- በሰሜን ሸዋ መራኛ አካባቢ ባሉ ሕዝቦች ዘንድ ‹የአቦ መንገድ› የሚባል ብሂል አለ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሚዳ ከሚገኘው የአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዳም ጥቂት ጊዜ ቆይተዋል ይባላል፡፡ በኋላ ከዚያ ገዳም ሲወጡ አቡነ መልከ ጼዴቅ ‹‹የት ሊሄዱ ነው›› ብለው ቢጠይቋቸው ‹እርሱ ወደ መራኝ›› ብለው መለሱላቸው፡፡
ከተማው ‹‹መራኛ›. የተባለው በዚህ ምክንያት ነው ይባላል፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት አንድ ሰው መድረሻውን በውል ሳያውቀው መንገድ ሲጀምር መንገዱ ‹የአቦ መንገድ› ይባላል፡፡

፰. #የአቦ_ቁራ ፡- ሰይጣን በቁራ ተመስሎ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዓይናቸውን ሊያወጣ ስለመጣ በጎ ነገር የያዘ መስሎ የሚመጣ ክፉ ሰው ‹የአቦ ቁራ› ይባላል፡፡

፱. #በአቦ_በሥላሴ ፡- በሕዝቡ ብሂል ውስጥ ከሥላሴ ጋር ተያይዘው ብዙ ጊዜ የሚጠሩት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ‹በአቦ በሥላሴ› ሲባል አጥብቆ መለመን ነው፡፡ በሕዝባዊ መዝሙሮችም ውስጥ ‹በአምስት አቦ ናቸው በሰባት ሥላሴ› የሚል ሐረግ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡
ስለ አቡዬ  ሌሎች የሚያውቋቸው ይት ባህሎች ካሉ ይጨምሩበት!

#የጻድቁ እረድኤት አይለየን...አሜን!

#ምንጭ :- ከሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጽሁፍ የተቀነጨበ
ከሞተ ሰው አፍ ውስጥ ጽጌ ሬዳ አበባ በቅሎ ተገኘ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ከኢየሩሳሌም በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው በኢያሪኮ ደሰት የሚኖር እመቤታችንን እጅግ አብዝቶ የሚወድ ስመ " አስቴራስ " የሚባል አንድ ዲያቆን ነበር ከሴቶች ሁለ ተለይተሽ #የተባረክሽ_ድንግል_ማርያም_ሆይ_አምላክን_በድንግና_ጸንሰሽ_በድንግልና_ትወልጃለሽና_ደስ_ይበልሽ እያለ #ቅዱስ_ገብርኤል_ያበሰራትንና ያቀረበላትን ሠላምታ ሳያቆርጥ ዘወትር ይጸልይ ነበር :: ሉቃ 1÷26 -29
ከዕለትም በአንዲቱ ቀን ለሥራው ወደ እሩቅ ሀገር ሲሄድ እርህራኄ የሌላቸው ሰዎች በመንገድ አገኙትና ገድለው ሳይቀብሩት ሄዱ። ነገር ግን ሊሎች ሰዎች በመንገደድ ሲያልፉሁ አስክሬኑን አይተው ከመንገዱ ጥግ መቃብር ቆፍረው ቀብረውት ሄዱ።
ከተቀበረም ከሦስት ቀይ በኃላም ክፉ ሰዎች ባሉባት በዚያች ሀገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅንነት ለሚያገለግል አንድ ዲያቆን እመቤታችን በእራይ ተገልጻ ወዳጄ ሆይ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለገለና ጸሎቱ በእኔና በልጄ ዘንድ እጅግ የተወደደችለት አንድ ዲያቆንን ስለገደሉት ሰዎች አዝኛለሁ ጓደኞችህ ዲያቆናትን ይዘህ በመንገድ ጥግ ወደ ተቀበረው ዲያቆን ሂዱና መቃብሩን ቆፍራችሁ አስክሬኑን አውንታችሁ በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ቅበሩት አለችው ። ዲያቆኑም እመቤታችን እንደ ነገረችው አጓደኞቹ ጋር ሄዶ መቃብሩን ቆፍረው አስክሬኑን ባወጡ ጊዜ " #ርሔ " እንደሚባል ሽቶ መዐዛው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ከአፉሁ የበቀለ አንድ የጽጌ ሬዳን አበባ አገኙ " #መንክር_እግዚአብሔር በላይለ ቅዱሳኒሁ " # እግዚአብሔር_በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው " ተብሎ በነቢይ የተነገረውንም አስበው ፈጽመው አደነቁ መዝ 67÷ 65 ክዎች ሰዎች ከገደሉት ከዲያቆን "አስቴራስ " አስክሬን አፍ የጽጌ ጌዳ አበባ በቅሎ መገኘቱን ያዮና የሰሙ ሰዎችም ሁሉ ይህስ ከዚህ በፊት በዐይናችን ያላየነውና በታሪክም ያልሰማነው አዲስና አስደናቂ ነገር ነው እያሉ በማድነቅ ለዲያቆን እንደሚገባ አድርገው እንደ ሥርዓቱ አክብረው በቤተክርስቲያን ቅጥር ቀበሩት ::
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ልመና ክብሯ አማላጅነቷም እስከ ዘላለሙ ድረስ ከና አይራቅብን አሜን!
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ምንጭ:-
በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ደብረ ገነተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያለ የብራና ተአምረ ማርያም ገጽ 223 ጠቅሶ የጻፈው ማህሌተ ጽጌ የተሰኘው ትንሽዬ መጻሕፍ ነው
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
     +++🙏  የጉጠቱ ፍም 🙏+++
 🙏 እግዚአብሔርን በመለኮቱ ልዕልና ያየው ማንም የለም ነገር ግን እርሱን መስለው ለኖሩ ቅዱሳን በአቅማቸው ልክ ይገለጥላቸዋልያናግራቸውማል።
ለአብርሃም በሽማግሌ ፣ ለሙሴ በሃመልማል እንዲሁም ለእነ ዳንኤል ዕዝራ ኢሳይያስ አይቶ በቃላት ድርድር ማስረዳት በማይቻልበት ክብር ተገልጦላቸዋል።
    🙏የጉጠቱን ፍም ስናስብ ከክርስቶስ ልደት በፊት ንጉስ ዖዝያን የሞተበትን ዓመት እናስታውሳለን መጽሐፍ እንደሚነግረን የይሁዳ ሕዝብ እስራኤልን እንዲመራ ዖዝያንን ገና የ16 ዓመት ጎልማሣ እያለ ነበር የቀቡት የንግስናን ዘውድ ደፍተው የወርቅ ካባን የደረቡለት።በንግስናውም ዘመን መልካሙንም ክፋውንም አሳልፏል።ከፍልስጥኤማውያን ጋር በነበረው ጦርነት እግዚአብሔር ረድቶት እነርሱን ድል አድርጎል በኋላ ዝናው እና ስሙ በዓለም ሁሉ ተሰማለት በደስታውም ተነሳስቶ ሦስት መቶ ሰባ ሺ አምስት መቶ ለሚሆኑ ጭፍሮቹ ልዩ ልዩ የሆኑ ጋሻና ጦር ቀስቶችን ሰርቶ አስረከባቸው ነገር ግን ይህን ሁሉ የስኬት ጫማ ሲጫመት የረዳውን አምላክ በመዘንጋቱ ልቡ ታበየ አምላኩንም በደለ በዙፋኑ በቀኝ አብሮት የሚቀመጠውን ካህኑን አዛርያስን ለምን በቀኜ ትቀመጣለህ በማለት ሠማያዊ ወምድራዊ ሥልጣን ካለው ጋር ይፎካከር ጀመረ እርሱም መልሶ "ካህን ይነብር በየማንከ(ካህናት በቀኝ ይቀመጣሉ)" ይልብሀል ህጉ ይለውና ደንቡን ነግሮ ዝም የስብለዋል ቀኝ የክብር መገለጫ ነውና።ኋላ ግን ዖዝያን በድፍረት ቤተመቅደስ ገብቶ ያለ ሥልጣኑ በዕጣን መሰዊያ ላይ አጠነ ያኔ እግዚአብሔር አምላክ በለምጽ መታው ከሰው ተለይቶ  በተለየ ቤት ለምጻም ሆኗልና ተቀመጠ ጊዜውም ደረሰና የንግስናውን ዘውድ ለልጁ አስረክቦ ከዚች አለም በሞተ ተለየ።
     🙏ንጉስ ዖዝያን በሞተበት አመት ልጁ ኢዮአታም በምትኩ በነገሰበት ዘመን ነበር ነብዮ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ በሚያስፈራ ዙፋን የልብሱ ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት የተመለከተው። ቅዱሳን የቅድስናቸው ደረጃ ጥግ ሲደረስ እግዚአብሔርን የማያት ክብር ላይ ይደርሳሉ። እንዴት መታደል ነው! እግዚአብሔርን ማየት! ማነው ይህንን ክብር'ስ የማይፈልግ? ነቢዩ በዙፋኑ ላይ ለማመን የሚከብዱ ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የመጠቁ ዕጹብ የሚያስብሉ ድንቆችንም ተመልክቷል፤ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማያ ስድት ክንፍ ያላቸው በመቅደሱ ዙሪያ ረበው አንተን ማየት አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ በአንተ ፊት መቆም አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን ሸፍነው በቀሪው ሁለት ክንፋቸው እየበረሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሠግናሉ። ምግባቸው መጠጣቸው ህይወታቸው ምስጋና! የእኛስ ህይወት? በምስጋና የተሞላ ወይስ በማማረር? መልሱን ለእራሳችን ። የሚደንቀው ነገር ሱራፌልም እኛም እርሱን ብናመሰግን ለእግዚአብሔር የምንጨምረው የምንቀንሰው ባለመኖሩ ነው ይልቁንስ አመስግነን መንግስቱን እንወርሳለን እንጂ።
🙏በመላእክቱ የምስጋና ቃል ጩኸት የመድረኩ መሠረት ተናወጠ ቤቱም በጢስ ተሞላ ነብዪም ተጨነቀ እጅግም ፈራ “እንዲህም ሲል ተናገረ፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! "
ትሁት አነጋገር! እግዚአብሔርን አይቻለሁ በቅቻለሁ ብሎ አልታበየም ነብዩ ኢሳይያስ ዖዚያን ከብርያለው ገንኛለሁ ብሎ እንደታበየ ይልቁን እራሱን ከነፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሰዎች ጉባኤ መሀል ወረወረ ራሱን ዝቅ አደረገ የሠራዊት ጌታ ዝቅታውን ፀፀቱን ተመልክቶ አንዱን ሱራፌል ላከለት ያም መልአክ በእጁ ከመሠዊያው በጉጠት ፍም ወስዶ አፋንም ዳሰሰለት ቀጠለና ታላቅ የድኅነት ቃል አሰማው " እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ።” በነብዩ ኤርሚያስ የተነገረው “እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ” የሚለው ትንቢት ተፈጸመ።
     🙏+ ጌታ ሆይ እንደ ነብዩ የተተረኮሰ አንደበት ስጠን ለእርሱም የላከውን ፍም እሳት ላክና ከአርያም የሚያቃጥለንን በደል ኃጢአት የሚያሰራንን በውስጣችን ያለውን እንክርዳድ አቃጥልልን። +
    15/02/2014
     ድሬዳዋ ኢትዮጵያ
       ተጻፈ በባሮክ ዘ አሚን
ዐውደ ምሕረት
Photo
እንግዲህ ምን እንላለን!
#ከጸሎተኛው_አፍ_በሚወጣ_አበባ ያመኑ ሽፍቶች
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ከሮም ነገሥታት ወገን የሆነ ስሙ ዘካሪያስ የሚባል ጎልማሳ ሰው ነበር ከዕለታት አንድ ቀን #ቤተ_ክርስቲያን ገብቶ #ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ሲጸልይ ከሥዕሏ ማማር የተነሳ እጅግ ደስ አለውና ለዚህች ሥዕል ምን ዐይነት እጅ መንሻ ላቅርብላት እያለ ሲያወጣና ሲያወርድ ወራቱ የጽጌ ጌዳ ወራት ነበርና ፶ (50) የጽጌ ጌዳ አበባ ወስዶ ዘውድ አስመስሎና አክሊል ሰርቶ ከሥዕሏ እራስ ላይ ወስዶ በክብር አቀዳጃት ይህ ሰው እንዲ እያደሰገ ሲጸልይ ከቆየ በኃላ የጽጌ ወራት ባለፈ ጊዜ ግን ለሥዕሏ ክብር የሚያቀርብላት የጽጌ ሬዳ አበባ በማጣቱ እጅግ አዝኖ ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ሄደና #እመቤቴ ሆይ የጽጌ ሬዳ፣ የአበባ ወራት እንዳለፈ አንቺ ታውቂያለሽ በ፶ (50)ው የጽጌ ሬዳ አበባ ፈንታ (ምትክ) ፶ (50)ጊዜ #በሠላመ_ቅዱስ_ገብርኤልን የሚለውን ጸሎትሽን ወይም ሠላምታሽን እጸልያለው በማለት እንዲ አለ " #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ_በመላእኩ_በቅዱስ_ገብርኤል_ሠላምታ_ሠላም_እልሻለሁ_እግዚአብሔር_ካንቺ_ጋር_ነውና_ደስ_ይበልሽ " እያለ በየቀኑ ፶ (50) ጊዜ ሲጸልይ ኖረ ።
ከዕለታት አንድ ቀን ግን እረስቶ ይህችን ጸሎት ሳያደርስ መንገድ ጀመረ በመንገድም እያለ ይህችን ጸሎት አለማድረሱ ታወሰውና ጉዞውን ገታ አድርጎ ከመንገድም ወጣ ብሎ እንደ ቀድሞው እየሰገደ ሠላምታዋን ፶ (50) ጊዜ በጸሎት ማድረስ ቀጠለ ሲጸልይም ከአፉሁ በእያንዳንዱ ሠላምታ አንድ አንድ ጽጌ ሬዳ አበባ ይወጣ ነበር። #እመቤታችንም አበባው ፶ (50) እስኪሞላ ድረስ ከአፉሁ እየተቀበለች በክንዷ ሰብስባ ትታቀፈው ነበር :: በአካባቢው የነበረ የሽፍቶች አለቃ የሆነ አንድ ሰው ይህንን አይቶ ዘካሪያስ ጸሎቱን እስኪ ጨርስ ድረስ ከአፉሁ የሚወጡትን የጽጌ ሬዳ አበቦች ይቆጥር ጀመር። ዘካሪያስም ጸሎቱን ሲጨርስና አበባዎቹም ፶ ሲሞሉ #እመቤታችን ባርካው አበባዎቹን ይዛ ወደላይ ስታርግ ይህ የሽፍቶች አለቃ አይቶ እጅግ አደነቀና ጓደኛቱይ ጠርቶ " የጌታን ተአምራት ታዮ ዘንድ ኑ " ተብሎ እንደ ተጻፈ "የእመቤታችንን ተአምራት ያዮ ዘንድ ኑ " ብሎ ወደ ዘካሪያስ ወሰዳቸው መዝ 45÷8 ሽፍቶቹም ዘካሪያስን ይህ ድንቅ ተአምራት ምንድ ነው? ብለው ጠየቁት እርሱም እኔ ኃጢያተኛ ከመሆኔ በቀር ሌላ በጎ ሥራ የለኝም ነገር ግን የሠማይና የምድር ንግሥት የሆነች አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች የእመቤታችንን በሠላመ #ቅዱስ_ገብርኤል_መላእክ ሠላም እልሻለሁ እያልኩ #በቅዱስ_ገብርኤል ሙሉ ሰላምታ በየ ቀኑ ፶ ( 50)ጊዜ ሠላም እላታለሁኝ አላቸው በዚህ ጊዜ ደስ ብሏቸው ዘካሪያስን ሸኙት እነርሱም ከዛች ቀን ጀምሮ ከክፉሁ ሥራቸው ተመልሰው ወደ ገዳም ሄደው በምንኩስና ሕይወት ተወስነው መኖር ጀመሩ::
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ምንጭ:-
በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ደብረ ገነተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያለ የብራና ተአምረ ማርያም ገጽ 223 ጠቅሶ የጻፈው ማህሌተ ጽጌ የተሰኘው ትንሽዬ መጻሕፍ ነው
ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሺ..።”
#መኃልየ. 7፥1

አዎን ገጸ ምሕረትሽን ወደ አስራት ሀገርሽ ወደ ኢትዮጵያ መልሺ🙏 ተመለሽ እንደ በደላችንም አትሽሺ🙏