ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
📢ዓውደ ምህረት🎤

ውድ የዓውደ ምህረት ታዳሚዎቻችን ነገም በወንድማችን #በሙሖዘ ጥበባት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት "#መንፈሳዊ አገልግሎት" በሚል ርዕስ እንማማራለን::



የነገ ሰው ይበለን ሰለ ሁሉም የልዑል እግዚአብሔር ስም ከእናቱ #ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር እና ከወዳጆቹ #ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር የከበረ የተመሰገነ ይሆን ለዘለዓለሙ አሜን❤️


ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ ካለ በ @YeawedMeherte ላይ ያድርሱን::
📢ዓውደ ምህረት 🎤

መምህር:-#ልዑለ ባህሪ ቅዱስ እግዚአብሔር
ተናጋሪ:-#በሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የት/ም ርዕስ :- #መንፈሳዊ አገልግሎት
የት/ም:- #ይዘት

#የመንፈሳዊ አገልግሎት አራት መሠረታዊ ጠባዮች

#1 ሰማያዊ ዋጋን ታሳቢ የሚደረግድ ከሆነ
#2 በመንፈስ የሚመራ ከሆነ
#3 በትህትና የሚሰራ ከሆነ
#4 ዋትነት ካለው

#ሦስቱ የመንፈሳዊ አገልግሎት ጠላቶች (ጠንቆች)

#1 ከንቱ ውዳሴ (የማይጠቅም ምስጋና)
#2ወሬ
#3የእራሱ የፈተና አለመኖር

በእውነት ለወንድማችን #ለሙሐዘ ጥበባት ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት እግዚአብሔር አምላክ የሕይወትን #ቃል ያሰማልንየአገልግሎት ዘመኑንም ይባርክልን:: አሜን!!!


ሀሳብ ጥቆማ አስተያየትና ጥያቄ ካሎት በ @YeawedMeherte ያድርሱን ::በቀጣይ መጋቢ አዲስ እሸቱ አለማየሁ ያስተምሩናል ስለነበረን ጊዜ የአምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን አሜን!!🙏
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
__መንፈሳዊ__አገልግሎት__.mp4
55.5 MB
መምህር:-#ቅዱስ እግዚአብሔር
ተናጋሪ:-#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ርዕስ :- #መንፈሳዊ አገልግሎት
#የመንፈሳዊ አገልግሎት አራት መሠረታዊ ጠባዮች
#1 ሰማያዊ ዋጋን ታሳቢ የሚደረግድ ከሆነ
#2 በመንፈስ የሚመራ ከሆነ
#3 በትህትና የሚሰራ ከሆነ
#4 መሰዋትነት
#3ቱ የአገልግሎት ጠላቶች
#1ከንቱው#2ወሬ #3የፈተና
#መንፈሳዊ_ተጋድሎ_ዓላማው_ምንድነው?

ሀ. የድል አክሊል (የዘለዓለም ሕይወት) ለመቀበል
እግዚአብሔር አምላካችን ሰዎች ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው
ከአምላካቸው ጋር መኖር ከመረጡ ሊሰጣቸው ያዘጋጀው
ከመነገርና ከመታሰብ በላይ የሆነ የዘለዓለም ሕይወት አለ፡፡ የሰው
ልጅ ሕሊናዊ ነፃ ፈቃዱ ደግሞ ከአዳምና ከሔዋን ውድቀት በኋላ
በየጊዜው እየደከመና ወደ ኃጢአት እያዘነበለ መጥቷል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ዘንድ ከብሮ ባየ ጊዜ
ከአባቶቻችን ጀምሮ ዘወትር የሚቀና ክፉ ጠላትም (ዲያብሎስ)
አለን፤ ባገኘው አጋጣሚ ስንፍናችንንና ድካማችንን እየተከተለ
እነዚህንም በመጠቀም ዘወትር ከአምላካችን ሊለየን እንደሚተጋም
ከላይ ተመልክተናል፡፡
ሽልማት፣ አክሊል የሚሰጠው ደግሞ ማሸነፍ ለሚችል ጎበዝ ሰው
ነው፡፡ ሰነፍና ቸልተኛ ሰው ግን ሊሸለም አይገባውም አንድ ሰው
ጎበዝ ወይም ሰነፍ መሆኑ የሚታወቀው ደግሞ በፊቱ ያጋጠመውን
ውድድር ወይም ፈተናና መከራ ማሸነፍና ማለፍ ሲችል ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ የመንፈሳዊ ተጋድሎ ዓላማ በገዛ ባሕርያችን ያለን መጥፎ
የኃጢአት ዝንባሌና ጠላታችን ዲያብሎስ የሚያመጣብንን ፈተናና
ሽንገላ ከእግዚአብሔር ርዳታና ቸርነት ጋር ሕሊናን በማንቃት፣
ራስን በመግዛትና ጠንክሮ በመጋደል አምላካችን ያዘጋጀልንን
የድል አክሊል የዘላለም ሕይወትን መቀበል ነው፡፡ ‹‹
የተጠራህለትን የዘለዓለም ሕይወት ትቀበል ዘንድ መልካሙን
የሃይማኖት ገድል ተጋደል›› አንዲል (1ኛ ጢሞ 6፥12) ሐዋርያቅ
ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ መከራዎችን አልፎ ገድሉን በድል አድራጊነት
ሲፈጽም ‹‹ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፤
ሃይማኖቴንም ጠብቄያለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል
ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ
ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ
አይደለም፡፡›› ብሏል ( 2ኛ ጢሞ 4፥7-8)
ለ. ለመንፈሳዊ እድገት
ክርስቲያናዊ ሕይወታችን ለፍሬ የሚበቃው የድል አክሊልን
መቀዳጀት የምንችለው የማያቋርጥ (የማይቆም) መንፈሳዊ
ዕድገት ሲኖረን ነው፡፡ በጥምቀት ያገኘነው አዲሱ ሕይወታችን
ዘወትር ማደግ ይኖርበታል፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወታችን በዛፍ ተክል
ይመሰላል፡፡ ከችግኝ ማፍላት ጀምሮ ፍሬ እስከሚያፈራለት ጊዜ
ድረስ ያለው ድካም ቀላል አይደለም፡፡ የዛፉ ችግኝ እንዲያበቅል፣
እንዲለመልም፣ አንዲያብብና እንዲያፈራ አትክልተኛው ያልተቆጠበ
ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፤ በየጊዜው ውሃ ማጠጣት፣ ማረምና
መኰትኰት፣ ፀረ ዕፅዋትና ፀረ ሕይወት የሆኑ በሽታዎችን
መከላከል ያስፈልጋል፡፡ እንደዚሁ ክርስቲያናዊ ሕይወታችን አድጎ
ለፍሬ እስኪበቃ ድረስ ዕለተ ዕለት ጠንክረን በትዕግሥት መሥራት
በመንፈሳዊ ተጋድሎ መጽናት ይገባል፡፡ የመንፈሳዊ ተጋድሎም
ዓላማው መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያቀጭጩ ከጸጋ
እግዚአብሔርም የሚያራቁቱ ኃጢአትና የዲያብሎስ ፈተናን
በመቃወም መንፈሳዊ ምግቦችንም በመመገብ አዲሱ
ሕይወታችንን ማሳደግ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

(በዲያቆን እስጢፋኖስ ደሳለኝ)

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#መንፈሳዊ_ተጋድሎ_ዓላማው_ምንድነው?

ሀ. የድል አክሊል (የዘለዓለም ሕይወት) ለመቀበል
እግዚአብሔር አምላካችን ሰዎች ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው
ከአምላካቸው ጋር መኖር ከመረጡ ሊሰጣቸው ያዘጋጀው
ከመነገርና ከመታሰብ በላይ የሆነ የዘለዓለም ሕይወት አለ፡፡ የሰው
ልጅ ሕሊናዊ ነፃ ፈቃዱ ደግሞ ከአዳምና ከሔዋን ውድቀት በኋላ
በየጊዜው እየደከመና ወደ ኃጢአት እያዘነበለ መጥቷል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ዘንድ ከብሮ ባየ ጊዜ
ከአባቶቻችን ጀምሮ ዘወትር የሚቀና ክፉ ጠላትም (ዲያብሎስ)
አለን፤ ባገኘው አጋጣሚ ስንፍናችንንና ድካማችንን እየተከተለ
እነዚህንም በመጠቀም ዘወትር ከአምላካችን ሊለየን እንደሚተጋም
ከላይ ተመልክተናል፡፡
ሽልማት፣ አክሊል የሚሰጠው ደግሞ ማሸነፍ ለሚችል ጎበዝ ሰው
ነው፡፡ ሰነፍና ቸልተኛ ሰው ግን ሊሸለም አይገባውም አንድ ሰው
ጎበዝ ወይም ሰነፍ መሆኑ የሚታወቀው ደግሞ በፊቱ ያጋጠመውን
ውድድር ወይም ፈተናና መከራ ማሸነፍና ማለፍ ሲችል ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ የመንፈሳዊ ተጋድሎ ዓላማ በገዛ ባሕርያችን ያለን መጥፎ
የኃጢአት ዝንባሌና ጠላታችን ዲያብሎስ የሚያመጣብንን ፈተናና
ሽንገላ ከእግዚአብሔር ርዳታና ቸርነት ጋር ሕሊናን በማንቃት፣
ራስን በመግዛትና ጠንክሮ በመጋደል አምላካችን ያዘጋጀልንን
የድል አክሊል የዘላለም ሕይወትን መቀበል ነው፡፡ ‹‹
የተጠራህለትን የዘለዓለም ሕይወት ትቀበል ዘንድ መልካሙን
የሃይማኖት ገድል ተጋደል›› አንዲል (1ኛ ጢሞ 6፥12) ሐዋርያቅ
ቅዱስ ጳውሎስ ብዙ መከራዎችን አልፎ ገድሉን በድል አድራጊነት
ሲፈጽም ‹‹ መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፤
ሃይማኖቴንም ጠብቄያለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል
ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ
ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ
አይደለም፡፡›› ብሏል ( 2ኛ ጢሞ 4፥7-8)
ለ. ለመንፈሳዊ እድገት
ክርስቲያናዊ ሕይወታችን ለፍሬ የሚበቃው የድል አክሊልን
መቀዳጀት የምንችለው የማያቋርጥ (የማይቆም) መንፈሳዊ
ዕድገት ሲኖረን ነው፡፡ በጥምቀት ያገኘነው አዲሱ ሕይወታችን
ዘወትር ማደግ ይኖርበታል፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወታችን በዛፍ ተክል
ይመሰላል፡፡ ከችግኝ ማፍላት ጀምሮ ፍሬ እስከሚያፈራለት ጊዜ
ድረስ ያለው ድካም ቀላል አይደለም፡፡ የዛፉ ችግኝ እንዲያበቅል፣
እንዲለመልም፣ አንዲያብብና እንዲያፈራ አትክልተኛው ያልተቆጠበ
ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፤ በየጊዜው ውሃ ማጠጣት፣ ማረምና
መኰትኰት፣ ፀረ ዕፅዋትና ፀረ ሕይወት የሆኑ በሽታዎችን
መከላከል ያስፈልጋል፡፡ እንደዚሁ ክርስቲያናዊ ሕይወታችን አድጎ
ለፍሬ እስኪበቃ ድረስ ዕለተ ዕለት ጠንክረን በትዕግሥት መሥራት
በመንፈሳዊ ተጋድሎ መጽናት ይገባል፡፡ የመንፈሳዊ ተጋድሎም
ዓላማው መንፈሳዊ ሕይወታችንን የሚያቀጭጩ ከጸጋ
እግዚአብሔርም የሚያራቁቱ ኃጢአትና የዲያብሎስ ፈተናን
በመቃወም መንፈሳዊ ምግቦችንም በመመገብ አዲሱ
ሕይወታችንን ማሳደግ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

(በዲያቆን እስጢፋኖስ ደሳለኝ)

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#መንፈሳዊ ውይይት

#በወንድማችን ብሩክ መልሳቸው እና
#በወንድማችን ተርቢኖስ ሰብስቤ
ይዘት :- #ደብረ ታቦር
👉የት ይገኛል?
👉በእርሱ ምን ምን ነገር ተገለጠ?
👉ለነማ ተገለጠ?
👉የቡሄ ታሪካዊ ድኃራ ምንድነው?
👉እንዴት እናክብረው?
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ 13/2012