ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
መልሱን በቀጥታ ለመመለስ ይህል በአንድ ጥያቄ እንጀምር የእመቤታች ጸሎት ማለትም "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ....የሚለው ጸሎት ማለት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #የለም ያለው ማነው ???በደንብ አለ እንጂ መጻሕፍ ቅዱስን በደንብ ሳንመለከት ይህ አለው ያለ የለውም ማለት ተገቢ አይደለም ስለዚህ አጠያየቁ ይታረም ::ይህ ጸሎት መጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ ተብሎ ይጠየቃል እንጂ የለም ብሎ መጀመር መጻሕፉን አለማወቅ ያስመስልብናልና::


#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶቾን በሙል ሥትሰራ በግለሰብና በማሕበረ ሰብ የሥጋ ሀሳብ ወይም በድምጽ ብልጫ አይደለም:: ንባብን ከትርጓሜ ትርጓሜን ከምስጢር አስማምታና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሁሉን ታሰናዳለች እንጂ: በዚህም ስንዱ እመቤት ለብላ ትጠራለች::

አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ከቁጥር 8ጀምሮ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው :: ሙሉ ያስተማረውን ጸሎት ቃል በቃል ለመመልከት ያክል "፤ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ "፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። " ....የሚል ነው (የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 8-13)

ታድያ ይህ ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ ካለ የእመቤታችንስ በየት ቦታ ነው ያለው ሊባል ይችላል ::ይህ የእመቤታችን ጸሎት ከሁለት የ መጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የተገኘ ነው የመጀመሪያው ከአብሳሪው መላእክ ከቅዱስ ገብኤልና ከቅድስት ኤልሳ ቤጥ የተገኘ የምስጋና ጸሎት ነው እስቲ ሁለቱንም ከግጥም እንመልከታችው

👉 የቅዱስ ገብርኤል ምሥጋና

"፤ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 28)

👉 የቅድስት ኤልሳቤጥ ምሥጋና

"፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 42)

አሁን ደግሞ እስቲ እኛ የምንጸልየውን እንመልከት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል አንቺ ከሴቶች ለተይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ(3)ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመዳኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን ለዘለዓለሙ አሜን
.....የሚል ነው
እስቲ ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ንግግር ውጪ የተጠቀምነው አዲስ የራሳችንን ምስጋና የቱ ጋር አለ?? በፍጽም የለም ሁሉንም ከእነርሱ ያገኘነው በመጻሕፍ ያነበብነው ነው
እመቤታችንም ፀጋን የተመላች ነችና ከተሰጣት ብዙ ፀጋዎች በአንዱ ነቢይት ነችና በአንዱ በቅዱስ ገብርኤልና በአንዱ በቅድስት ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል ስትል ከፈጣሪዋ ከልጇ ከወዳጆ ቀጥላ በአማኝ ትሁልዶች ሁሉ የምትመሰገን መሆኑን ነግራናለች ይህም ሐሰት የለውም የእውነት መንፈስ ሐሰት አያናግርምና እያመሰገናትም ነውና::

ሌላው አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ከፈጣሪ የተሰጠ ነው ቢሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የሚለውም ከፈጣሪ የተሰጠ ነው:: እንዴት ቢሉ ከላይ እንደ ተመለከትነው ጸሎቱን ያገኘነው ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ነው እነርሱን ልኮ ያናገረ ደግሞ እራሱ አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዮ ያለው እራሱ እግዚአብሔር ነውና ::

"፤ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ
(የሉቃስ ወንጌል 1÷ 26-27


"፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም #መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ " በታላቅ ድምፅም ጮኻ #እንዲህ አለች። #አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ #የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው አለቻት"

(የሉቃስ ወንጌል 1÷41-42


ስለዚህ ሁለቱም ሊነጣጠሉ የማይገቡ በአንድነት እንደየ ክብራቸው የተሰደሩ ሥርዓታዊ መጻሕፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ጸሎቶች ናቸው ...ይቆየን...
ስንክሳር ነሐሴ 7
=>+”+ እንኩዋን ለእመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +”+
+”+ ቁጽረታ (#ጽንሰታ) ለማርያም +”+
=>ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት “ጥንተ መድኃኒት_የድኅነት መነሻ ቀን” ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::
“ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ::”
#ድንግል_ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው::” (#መጽሐፈ_ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)
+ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል:: የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ከነገደ #ይሁዳ የሚወለድ #ቅዱስ_ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ #ሌዊ (#አሮን) የተወለደች #ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች “ልጅ የላችሁም” በሚል ይናቁ ነበር::
+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን “ኅጡአ በረከት-ከጸጋ #እግዚአብሔር የራቀ” ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት #የአብርሃምና_ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች #ቅድስት_ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: “እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?” ብላ አዘነች::
+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- #ነጭ_ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::
+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) #መልአከ_ብሥራት_ቅዱስ_ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: “ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ” ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::
+እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው #እመ_ብርሃን ተጸነሰች::
#ኦ_ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ
¤ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም” እንዳለ ሊቁ:: (#ቅዳሴ_ማርያም)
+”+ #ቅዱስ_ዼጥሮስ_ሊቀ_ሐዋርያት +”+
=>ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ዼጥሮስ መታሰቢያ ናት:: #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ #ቂሣርያ_ፊልዾስ ይዟቸው ሔደ:: በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በርስ ይከራከሩ ገቡ::
+የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር:: የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ “ኤልያስ ነው”: ሌላኛው “ሙሴ”: 3ኛው “ኤርምያስ ነው” በሚል ተከራከሩ:: #ቅዱስ_ዼጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው “ሃሳባችንን አስታርቅልን:: ላንተስ ማን ይመስልሃል?” አሉት::
+አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው:: “እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን “እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው” አላቸው:: ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ::
+ቸር አምላክ “ለምን ተጠራጠራችሁኝ” ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ:: “የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?” አላቸው:: እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ::
+ጌታችን “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ቢላቸው ጸጥ አሉ:: ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና:: በዚያን ጊዜ ቅዱስ ዼጥሮስ ተነስቶ “#አንተ_ውእቱ_ክርስቶስ_ወልደ_እግዚአብሔር_ሕያው-
አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ” አለው:: (ማቴ. 16:16)
+ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን “አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ” ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ:: ለቅዱስ ዼጥሮስም “#መራሑተ_መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)” ተሰጠው::
+ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስን “#አምላክ_ወልደ_አምላክ:_ወልደ_ማርያም:_አካላዊ_ቃል:_ሥግው_ቃል:_ገባሬ_ኩሉ:_የሁሉ_ፈጣሪ” ብለው ካላመኑ እንኩዋን ጽድቅ ክርስትናም የለም::
+”+ #አፄ_ናዖድ_ጻድቅ +”+
=>ሃገራችን #ኢትዮዽያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት:: ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው:: ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ:: ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል::
+ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .)
የደረሷት እርሳቸው ናቸው:: ትልቁን #መልክዐ_ማርያምም ደርሰዋል:: ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው::
+የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (#ማርያም_ክብራ): ልጆቻቸው (#አፄ_ልብነ_ድንግልና #ቡርክት_ሮማነ_ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ:: ንጉሡ #አፄ_ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ #ድንግል_ማርያምን “እመቤቴ 8ኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?” አሏት::
+እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው:: ንጉሡም አዝነው “#እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ” አሏት:: በዚህ ምክንያት የ8ኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል::
=>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ዼጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን::

7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+”+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
#ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ #እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው #እናታችን_ጽዮን ይላል:: +”+ (መዝ. 86:1-6) ስንክሳር ነሐሴ 7
=>+”+ እንኩዋን ለእመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +”+
+”+ ቁጽረታ (#ጽንሰታ) ለማርያም +”+
=>ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት “ጥንተ መድኃኒት_የድኅነት መነሻ ቀን” ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::
“ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ::”
#ድንግል_ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው::” (#መጽሐፈ_ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)
+ይሕች ዕለት