አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶሮን_ቢያማት_በሬ_ተሳሉላት

አንድ ቀን ፣ በአንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ለሚካሄድ ፕሮጀክት የበጅት ኤክስፐርት ሆኖ የሚሰራ ወዳጄን ፤ ሳገኘዉ ፣ያለወትሮው ተደብሮ
ነበር።

“ምን ሆነኸል? አልኩት ።

“አንጀቴ አርሮ ነው ባክሽ...”

“አጂጀትህ ማረሩ ፊትህ ላይ ተጽፏል ። ግን ምን ሆነህ ነው?”

“እንግhዝ ያለው ዋና መስርያ ቤታችን የሠራው ሥራ እርር ድብን አድርጎኛል ።"

“ምን አደረጉህ?”

“ባለፈው ኢትዮጵያ የሚገኘው ቢሮ በየወሩ አላስፈላጊ በሆኑ ነገሮች አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር እያባከነ ስለሆነ መፍትሔ ማበጀት ፈልገናል” ብለው ኢሜይል ጻፉልኝ ።

“እ... ሺ

“የሚሉትን፣ ለመስማት ሰፍ ብዬ ስጠብቅ ፣ ከትናንት ወዲያ መፍትሔ ያሉትን ሊነግሩኝ ከለንደን ድረስ ደወሉ።''

“እህስ ... ምን አሉህ?”

ባለፈው እንዳልንህ በወር የሚባክነው፣ አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ለማዳን የሚያስችል ሲስተም የሚዘረጋ ሰው ከዚህ እንልካለን ሰውየው
በዘርፉ በዓለም የገነነ አማካሪ ነውና በደንብ ይረዳችኋል አሉኝ።እኔም በዛውም ከሰውየው ብዙ እማራለሁ ብዬ ደስ አለኝ እና እሺ አልኩ ...”

“ደስ ካለህ ታዲያ ምን አናደደህ? ” አልኩ፥ ነገሩን፣ ፈታ ለማድርግ ።

“አታሹፊ : : የምሬን ነው : : ”

“እሺ... ምን አናደደህ? ”

“በነጋታው ሰውየው ሥራውን፤ ለመሥራት የሚከፈለውንና ተያያዥ ወጪዎቹን... አለ አይደል የአውሮፕላን ቲኬት ፣የቤት ኪራይ፣ ጥበቃ ፣ ኢንሹራንስ ምናምን በጀት ሠርተው ላኩልኝ ።

"እ....?"

ይሄ ሁኑ ሲደማመር የኢትዮጵያው ቢሮ ለሰውየው አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር በየወሩ መክፈል ይጠበቅበታል ።

አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ለማዳን አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ማውጣት! ሃ ሃ ሃ ሃ አልኩ እየሳቅኩ ።

“እኮ...አይገርሙሽም?” ሲለኝ አሰብ አደረግኩና ፣

“ቆይ ግን... አማካሪው ለምን ያህል ጊዜ ነው የሚመጣው? ምናልባት በረጅም ጊዜ ሲሰላ ለሱ የሚወጣው ወጪ ከሚያድነው ገንዘብ ያንስ
እንደሆነ?” አልኩት ።

“የበጅት ኤክስፐርት ሆኜ ይህን አላስብም ብhሽ ነው ...? ባሀ አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ደሞዙ ሰውዬ የሚመጣው ለአራት ወር አገልግኬት ነው
በወር አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር አባከነ የተባለው ፖሮጀክታችን ሊያልቅ የቀረው ግን ስድስት ወር ብቻ ነው" : : ብሎ መለሰልኝ።

ወይ የእኛ ነገር ፣ ትንሽ ሽንቁር ለመድፈን ሰፋ አድርጎ መሸንቆር፡ ፡
የሀገሬ ሰው ፣ #ዶሮ_ቢያማት_በሬ_ተሳሉላት ያለው ነገር ገጥሞት መሆን አለብት!

🔘ሕይወት እምሻው🔘

#MUTE ያደረጋቹ #UNMUTE እያደረጋቹ በተቻለ መጠን Post የማደርግበት ሰአት ተመሳሳይ ለማድረግ እሞክራለሁ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ