አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ሁለት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#አዲስ_መንገድ


#የነጻነት_ሕመም

የምሽቱ ድባብ የማልቆጣጠረው ስሜት አሳደረብኝ፡፡ የአየሩ ቅዝቃዜ ቆዳዬን ሲነካው፣ ለሳንባዎቼ አየሩ ሲቀላቸው፣ በዓይኔ ላይ የሚጨፍሩት እልፍ አዕላፍ ክዋክብት በውበታቸው ሲያፈዙኝ ነፍሴን ‹‹ተመስገን አምላኬ!›› ብላ እንድትዘምር አደረጓት፡፡
‹‹ምን ላይ ነው ያፈጠጥሺው? እንሂድ እንጂ - በአስቸኳይ መሄድ
አለብን!›› ሲሉ የመጀመሪያዋን የነጻነት መጠጥ እንደተጎነጨሁ ቄስ ሙሪንዚ ትዕግሥት አጥተው ሾር ብዬ እንድሄድ ተናገሩ፡፡ ቄሱ ከሌሎቹ ሴቶችና ወደ ፈረንሳዮች ምሽግ አብሮን ሊሄድ ከተነሣው ከዮሃንስ ጋር በሩ ጋ ይጠብቁናል፡፡ ዮሃንስ በጣም አረፈደ እንጂ መባነኑና እፊት እፊት ማለቱ ባልከፋ፡፡ በዚህ ጊዜ ከዘር ጭፍጨፋው መትረፌንም ሆነ ንጋትን እንደገና ለማየት መቻሌን አላወቅሁም - የግንኙነታችንም መሞት አልታወቀኝ፡፡ ቄሱ በራቸውን ሲከፍቱት ከቤት ወንድ ልጆቻቸው (ከሴምቤባ በስተቀር) ጦሮች፣ ቢላዎችና ቀስቶች ይዘው ወጡ፡፡ ዙሪያችንን በሚገባ ከበው በሩን አስወጡን፡፡ ከጠርጣራ ወንድ የቤት ሠራተኞቻቸውና ክፉ ጎረቤቶቻቸው አደገኛ ዓይኖች ከለሉን፡፡ ከዚያም ወደ ውጪ ወጣንና ወደ መታጠቢያ ቤቱ ከሦስት ወራት በፊት ባመጣኝ በአቧራማው የእግር መንገድ በፍጥነት ተራመድን፡፡ ዓይኖቼ ጨለማውን እየተላመዱት ሲሄዱም ቄስ ሙሪንዚም ሆኑ ዮሃንስ እንደታጠቁ አየሁ፤ ዮሃንስ ረጅም ጦር የያዘ ሲሆን ቄሱ በበኩላቸው ጠመንጃቸውን በትከሻቸው አንግተዋል፡፡ የገዳዮች ቡድን መንገዳችን ላይ ቢያጋጥመን ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሰብኩ፡፡ ሰዎች በመንገዱ ሌላኛው አቅጣጫ ከጨለማው ውስጥ ብቅ ሲሉ በድንገት አየናቸው፡፡ ምን አልባትም 60 የሚሆኑ ኢንተርሃምዌዎች በሁለት መስመሮች በሰልፍ ይመጣሉ፡፡ አስፈሪ የደንብ ልብሶቻቸውን ያልለበሱ ቢሆንም ቅሉ ትዕይንቱ ያስበረግጋል፡- እስካፍንጫቸው ታጥቀው በፍጥነት ይጓዛሉ፤ ገጀራዎችን፣ ጠመንጃዎችን፣ ቦንቦችን፣ ጦሮችንና ረጃጅም ማረጃ ቢላዎቻቸውን ይዘው ወደ እኛ በመጠጋት ላይ ናቸው - አንደኛው እንዲያውም ቀስት ይዟል፡፡በአጠገባቸው በጣም ተጠግተን ስለሄድን እንዲያውም የሰውነታቸውን ጠረንና ከትንፋሻቸው የሚመጣውን የሚተናፈግ አልኮል ሳይቀር ማሽተት ችያለሁ፡፡ በሚገርም ሁኔታ በመታጠቢያ ቤቱ ከእነርሱ ተደብቄ ከነበርኩበት ጊዜ ይልቅ በአጠገባቸው ሳልፍ በአንጻራዊነት ፍርሃቴ ቀንሷል፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን በደኅና እንዲያቆየንና ፍራቻዬን እንዲያረግብልኝ ለመንኩት፡፡
ሌሎቹ ሴቶችና እኔ ኢንተርሃምዌዎቹ ሴቶች መሆናችንን እንዳይለዩ በማለት በቡድን አጀባችን መካከል ራሳችንን ዝቅ አደረግን፡፡ ያለ ምንም ችግርም አለፍን፡፡ እንዲያውም የተወሰኑት ገዳዮች ሰላምታ አቀረቡልን፤ ሲያልፉም ለዮሃንስና ለቄሱ መልካም ዕድል ተመኙላቸው፡፡ አንድም እኛን ሌሊት ድረስ ቆይተን እያደንን ያለን ገዳዮች አድርገው አስበውናል አለያም አምላክ ዓይናቸውን አሳውሯቸዋል … ሁለቱም ምክንያት እንደሆነ አሰብኩ፡፡ በተጨማሪም አሁን ባለው የዘር ፍጅቱ ደረጃ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ቱትሲዎች በአንድ ቦታ በሕይወት ይኖራሉ ብለው አልጠበቁም፤ ወይንም አላመኑም፡፡ በየመንገዱ አስከሬኖች ስለወደቁ እንደዚያ ብለው ለማመን ጥሩ ምክንያት ነበራቸው፡፡
አምላክ ለጸሎቴ ምላሽ ሰጠኝ፡፡ ለገዳዮቹ ያለኝንም ፍራቻ አሽቀንጥሮ ጣለልኝ፡፡ ግን ከሁኔታው ሳየው ጌታ ለቄስ ሙሪንዚና ለዮሃንስ ተመሳሳይ በረከት ያጋራቸው አይመስልም፡፡ ኢንተርሃምዌዎችን በማግኘታችን ሁለቱም ተደናግጠዋል፡፡ ዮሃንስና ቄስ ሙሪንዚ ገዳዮቹ ከእይታችን እንደተሰወሩ የገቡበትን ጣጣ እንደገና አጤኑት፡፡ ቄሱ ‹‹እናንተ ሴቶች ከዚህ በኋላ ብቻችሁን ሂዱ›› አሉን፡፡ ‹‹ፈረንሳውያኑ ከዚህ ቅርብ ናቸው… ሂዱ ቀጥሉ፤ ከእይታችን እስክትሰወሩ እናያችኋለን፡፡›› ቄሱና እኔ በፍጥነት ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ እርሳቸው፣ ወንዶች ልጆቻቸውና ዮሃንስ ከመንገዱ ወደ ጥሻ ውስጥ ለመደበቅ በችኮላ ሄዱ፡፡ ያኔ ሌሎቹ ሴቶችና እኔ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ቦታ ላይ ስለሆንን የምናባክነው ምንም ዓይነት ጊዜ አልነበረንም፡፡ የፈረንሳውያኑ ምሽግ 500 እርምጃዎች ገደማ ይርቃል፤ ስለሆነም እግሮቻችን በቻሉት መጠን በፍጥነት ተጓዝን፡፡
የተተወ የወንጌላውያን ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በተቋቋመው ምሽግ ጋ ስንደርስ ልቤ ድው ድው ይል ጀመር፡፡ የተቀረው ቡድን ከዋናው በር ፊት ለፊት በጣም ፈርቶ ተመስጎ ሳለ እኔ በቻልኩት መጠን በሩን እደበድብና በጣም ጮኬ
‹‹እባካችሁ እርዱን! እባካችሁ እገዛችሁን እንፈልጋለን!›› እል ጀመር፡፡ ከሹክሹክታ በላይ ከተናገርኩ በጣም ረጅም ጊዜ ስለሆነኝ ለመጮህ ካደረግሁት ጥረት የተነሣ ጉሮሮዬን አመመኝ፡፡ ድምጼ የታፈነና በጣም ዝግ ያለ ስለሆነ አይሰማም ለማለት ይቻላል፡፡ ሊያድነን የሚጠብቀን ማንም ሰው ሳናገኝ ስንቀር ሴቶቹ በፍርሃት ራዱ፤ ለቅሶና እዬዬም ጀመሩ፡፡ ከአፍታ በኋላ ስድስት ወይም ሰባት ወታደሮች መትረየሶቻቸውን ወደ እኛ ደግነው በአጥሩ በአንደኛው አቅጣጫ ብቅ አሉ፡፡ ፈረንሳይኛ የምናገረው እኔ ብቻ ስለሆንኩ ባልንጀሮቼን ዝም አስባልኩና ለወታደሮቹ ስለማንነታችንና ስለአመጣጣችን ነገርኳቸው፡፡
ወታደሮቹም በጥርጣሬ ተመለከቱን፣ ጠመንጃዎቻቸውንም እንዳቀባበሉ ናቸው፡፡ ‹‹እውነት ነው! የነገርኳችሁ ሁሉ እውነት ነው… ታድኑን ዘንድ እናንተን ስንጠብቅ ቆይተናል›› አልኳቸው በተስፋ መቁረጥ፡፡
በቡድኑ ውስጥ ካሉት ወታደሮች ትንሹ፣ ኮስታራው፣ መልኩ ፈገግ ያለውና ጸጉሩን የተላጨው ሰውዬ ወደ ዋናው በር መጥቶ በፊታችን ላይ ባትሪ አበራብን፡፡ የአፍንጮቻችንን ቅርጽ እየተመለከተ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ነባሩ አስተሳሰብ ሁቱዎች ደፍጣጣ ቱትሲዎች ደግሞ ሰልካካ አፍንጫ አላቸው የሚል ነው፡፡ ስለሆነም ፈተናውን አልፈን ሳይሆን አይቀርም በሩን ከፍቶ አስገባን፡፡ ይሁን እንጂ መታወቂያ ደብተሮቻችንን ለማየት ሲጠይቀንም መሣሪያውን እንደደገነ ነው፡፡ሴቶቹ በኃይል ሲተነፍሱ ይሰማኛል - ማናቸውም ቢሆኑ መታወቂያዎቻቸውን አልያዙም፡፡ በዚህም ምክንያት ፈረንሳውያኑ እዚያው የሚረሽኗቸው መስሏቸዋል፡፡ ደግነቱ በኔ በኩል መታወቂያዬን ከሦስት ወር በፊት ቤቴን ለቅቄ ስወጣ በኋላ ኪሴ ይዤዋለሁ፡፡ ወታደሩ ቱትሲ የሚል ቃል ከዳር እስከዳር የታተመበትን የኔን መታወቂያ አይቶ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ፡፡ ወዲያውኑ ለሌሎቹ ሴቶች በእርግጠኝነት
‹‹ምንም የምንሆን አይመስለኝም›› ስል አረጋገጥኩላቸው፡፡
ለወራት የታመቀ ፍራቻ፣ ብስጭትና ሥጋት ከነፍሳችን ወንዝ ፈሰሰ፤ በውስጣችን ያለው የስሜት ግድብ ፈረሰ፤ የተወሰኑት ሴቶች ሊቆጣጠሩት በማይችሉት መልኩ አለቀሱ፡፡ የወታደሮቹም አቀራረብ ከዚያ በኋላ ተቀየረ - ድምጻቸው በደግነትና በያገባኛል ስሜት ተሞልቶ ጠመንጃዎቻቸውን ዝቅ አድርገው በሐዘኔታ ያነጋገሩን ጀመር፡፡ በወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየነው የታሸገ ውሃና አይብ ተሰጠን፡፡ ቄሱ እንደገመቱት ፈረንሳውያኑ እንደማይገድሉን አውቀን በጣም ሰፍ ብለን መጉረስ ጀመርን፡፡
‹‹አይዟችሁ ምንም ችግር የለም›› አለ ትንሹ ወታደር፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ቅንጣት ታክል ልትጨነቁ አይገባችሁም … ቅዠታችሁ አክትሟል፡፡ ማንም ሰው እንዲጎዳችሁ አንፈቅድም፡፡ ገባችሁ? ምንም ሥጋት አይግባችሁ፤
👍2