አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_አራት(🔞)


#የራኪን_ማስታወሻ_አነበብኩት

ራኪ እልህ ተጋባችኝ። እኔ ስጽፍ አይታ መጻፍ ጀመረች። ጭራሽ ያልፈጠረባትን። ለምን እንደምትጽፍ ስጠይቃት ያን የምትነግረኝ እኔ ለምን እንደምጽፍ ስነግራት ብቻ እንደሆነ ነገረችኝ፤ ፍርጥም ብላ። ገረመኝ። ለምን የኔ መቸክቸክ ይህን ያህል እንዳሳሰባት አልገባኝም።

አንድ ቀን ማስታወሻ ደብተሯን አልጋዋ ላይ ጥላው ወጥታ ደረስኩ። ከራሴ ጋር ከፍተኛ ዉዝግብ
ዉስጥ ገባሁ። ማንበብ አለብኝ ወይስ የለብኝም በሚል። ግማሽ ሰዓት ከራሴ ጋር ከተጣላሁ በኋላ
ተሸነፍኩ። ለሽንፈቴ የሰጠሁት ሰበብ «ራኪ የምትጽፈውን ማንበቤ ጥሩ ጓደኛዋ እንድሆን ይረዳኛል»
የሚል ነበር። በሩን ከዉስጥ ቆልፌ ቶሎ ቶሎ ማንበብ ጀመርኩ።

ምንም የረባ ነገር አልነበረውም። በየገጹ ትጽፋቸው ከነበሩ ዝብርቅርቅ ያሉ የተበጣጠሱ አረፍተ ነገሮች
የተረዳሁት ወደዚህ ሕይወት እንድትገባ ምክንያት የሆናት ዶ/ር ባይከዳኝ በሕይወቷ ዉስጥ ትልቅ
ቦታ እንደያዘ ብቻ ነው። እሱን ስታስታውስ እናቷን፣ እናቷን ስታስታውስ ሕይወቷን ታየዋለች። ያኔ እናቷ የሞቱ ሰሞን ዶክተር ባይከዳኝን ባታገኘው ራሷን ልታጠፋ ትችል እንደነበረ ጽፋለች። አጻጻፏ
ግን ያስቃል። በየገጹ ትሳደባለች። አንድ ነገር አንስታ ወደሌላው ትዘላለች። የሕጻን ልጅ ደብተር ነው የሚመስለው። ብቻ ከማስታወሻዋ የገባኝ ነገር ባይከዳኝን ትወደዋለች። የመጀመርያዋ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፤ ላለመሞቷ ምከንያት ስለሆነ ሊሆን ይችላል፤ ብቻ ለሱ ልዩ ስሜት እንዳላት በደንብ አድርጌ
ተረዳሁ።
እሱም ደግሞ እንደሚስት ባይሆንም እንደ ሸሌ እንደሚወዳት ጽፋለች። ብዙ ነገር ተባብሯታል
በምናውቀውና የማናውቀው። ለምሳሌ የብርክታዊት ልጅ አቡሻ ልቡን አሞት ዉጭ ሄዶ ካልታከመ
በሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ ይሞታል የተባለ ጊዜ ተሯሩጦ፣ በቦርድ እንዲወሰን አድርጎ፣ከአገሪቱ ሐብታም ሰውዬ ስፖንሰር አፈላልጎ፣ ባንኮክ ያሳከመላት እሱ ነው፡፡ ይሄን ታሪከ እኔም አውቀዋለሁ። ሁላችንም እናውቃለን ለምን በማስታወሻ መፃፍ እንደፈለገች ግን ገርሞኛል።

እኔ እስከማውቀው ድረስ አቡሻ ድኖ መመለሱን ነበር።

በመጨረሻ እቡሻ ድኖ ተመለሰ። ልክ ድኖ የተመለሰ ቀን እናቱ ብርከታዊት የልጁን ስም ከአቡሻ ወደ
"ባይከዳኝ" ለመለወጥ ጊዜ አልወሰደባትም። እኛ ግን አሁንም ልጇን አቡሻ ነው የምንለው። ባይከዳኝ
ካልነው ትልቅ ሰው የሆነብን ይመስለናል። ራኪም ስሙ ወደ ባይከዳኝ መለወጡ እንዳልተመቻት ማስተዋሻዋ ላይ ፅፋለች።እናትየው ብርክታዊት ግን ወይ ፍንክች! ያባ ቢላዋ ልጅ።

ብርክታዊት በዚያው ከህክምና በተረፈው ገንዘብ ወዲያው ከሽርሙጥና ሕይወት ተሰናበተች። አሁን ለቡ አካባቢ «ካፕል ሀውስ» ያለው ምርጥ ካፌ ከፍታ አሪፍ ብር ትሰራለች። አትላስ የምትመጣው
ራኪ ወይም እኛ ስንናፍቃት ብቻ ነው።

ራኪ ጠርቀም ያለ ገንዘብ የግድ ሲያስፈልጋትም ዶክተር ባይከዳኝን እንደምትበደረው ጽፋለች
“የተበደርኩት ብር ዝርዝር በሚለው ስር ብዙ ዜሮ ያለባቸው ቁጥሮች ተደርድረዋል። ራኪ ነፃ ስለሆነች ነው መሰለኝ ዶ/ር ባይከዳኝ ይወዳታል። በሞቅታ ቢሆንም ብቻ አንድ ልጅ ከሷ እንዲኖረው እንደሚፈልግና ያንንም እንድትፈጽምለት እንደጠየቃት ከዚህ በፊት በምስጢር ነግራኛለች።
ማስታወሻዋ ላይም ይህንኑ ጽፈዋለች። እንዲህ ብላ

“ .እሺ ባንዳፍ አልኩት። እሺ ስለው ግን ያለኮንዶም ከኔ ጋር ሴክስ ለማድረግ ፈራ። እንደዚያ ሰሞን ሸሌነቴን ጠልቼው አላውቅም። በብስጭት ታመምኩ። …በምን እንደታመምኩ ማንም አያውቅም።

ደግነቱ ያው እንደተለመደው እሱ ከሊኒክ ሄዳ አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎች ሲነካካት ወድያው ይሻላታል።

ራኪ ማስታወሻዋ ላይ ባትጽፈውም ከዚህ በፊት እንደነገረችኝ ከሆነ ዶክተር ባይከዳኝ አምስት ትልልቅ
ሴት ልጆች አሉት። የሁሉንም ልጆቹን ፎቶ አሳይቷታል። ትልልቅ ናቸው፤ እንደሱ ረዥም እና ጥቋቁር ናቸው፡፡ የሚገርመው ሁሉም ሐኪም መሆናቸው ነው፡፡ አራቱ አሜሪካ ናቸው። ኢህአዴግ
ስልጣን ካልለቀቀ አገር ቤት መምጣት አይፈልጉም። የመጨረሻዋ ትንሿ ጅማ ሕክምና ትማር ነበር።
ሚስቱም የቆዳ ሐኪም ናት። አሜሪካ ቺካጎ በምትባል ስቴት ነው የምትሰራው። በሦስት ወር አንድ ጊዜ መጥታ ትጎበኛቸዋለች፤ እሱም በተራው አሜሪካ ሄዶ ሚስቱንና ልጆቹን በየተወሰነ ጊዜ ልዩነት ይጎበኛቸዋል። ከሚስቱ ጋር በተኽሊል ስለተጋቡ እስከዛሬም አልተፋቱም። ኾኖም ፈታ ብለው ነው
የሚኖሩት። እሷም በፈረንጅ ትደከላለች፣ እሱም ራኪን ይደከላል።

ዶክተር ባይከዳኝ ከራኪ ዉጭ ግን ሴት ያሻፍዳል እንጂ አይነካም ይባላል፤ ለራኪና ለሚስቱ ታማኝ ነው። ራኪ ሆስፒታል ያሉት ነርሶች እንዴት እሱን ለማጥመድ ቀን ተሌት እንደሚሰሩ ታውቃለች።
እሱ ግን አልተሸነፈላቸውም” ብላኛለች።

ሮዚ ሙች! ምን እንደሚያስፈራኝ ታቂያለሽ? አንድ ቀን ነርሶቹ በር ዘግተው ባይከዳኝን እንዳይደፍሩት ብቻ ነው፤ እመቤቴን የውነቴን ነው፤ እንዴት እኮ እንደሚሻፍዱ ስላላየሻቸው ነው አንቺ!" ብላ ስጋቷን ነግራኝ ታውቃለች።

ራኪ አፍቃሪ ናት። “ሮዚ! አንድ ነገር ልንገርሽ? ባይከዳኝን ቂጤ እስኪንቀጠቀጥ ነው የምወደው!»
ትላለች፤ እንዲህ የምትለው ግን ስትሰክር ወይ ስትጦዝ ብቻ ነው።

ራኪ ነፍሴ!!

ምናለ ፈጣሪ ህልምሸን ቢያሳካው የስንቱን ቀጣፊ ሰባኪ ሕልም ያሳካ የለ? በየቀኑ የስንቱን ሸርሙጣ ወንድ ፀሎት ይሰማ የለ? አንቺ እኮ ገላሽ በአጋጣሚ አጓጉል ስራ ዉስጥ ገብቶ ነው እንጂ ልብሽ ቅዱስ ናት። ራኪ ሙች! ይሄንን እንኳን እኔ እግዚአብሔርም መመስከር የሚችለው ነው። እወድሻለሁ!
#ስሙን_የማይነግረኝ_ዶከተር

ዶከተር የሚለውን ቃል እንደ ዲክሽነሪ ተርጉሚው ብባል "A person full of himself” ብዬ የማስል ይመስለኛል። ሁሉንም ዶክተሮች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ይኸው ነው። ስለ ራሳቸው አውርተው አይጠግቡም።እኛ ዘንድ የሚመጡት በዋናነት ለሴክስ አይመስለኝም። ለጀሮ ነው። ጆሯችን
በልጥጠን ስለምንሰጣቸው ይወዱናል።

አዳዲስ ደንበኞቼ ዶ/ር መሆናቸውን ካወቅኩ የጆሮ ሰርቪስ እያልኩ extra ባስከፍል ስግብግብ ልባል አይገባም። እነሱስ “የካርድ" እያሉ በየሆስፒታሉ መቶ መቶ ብር ይነጩን የለ? ማን ይሞታል!
በዚያ ላይ ጢባራቸው። ዶክተር ሲባሉ ደሞ አንድ አይነት፤ ሁሉም። እጅ በኪስ አድርገን ሴክስ እናርግሽ ማለት ነው የሚቀራቸው። ሲያስጠሉ!

ለነገሩ እኛም ሰፍ እንልላቸዋለን መሰለኝ። እንደምንደነግጥላቸው ስለሚያውቁ ነው የሚንጠባረሩት ማዕረጋቸው የትኛዋንም ሴት እንደሚያስበረግግ አሳምረው ያውቁታልየሚንጠባረሩት። ለዚያ ይመስለኛል ትንሽ ኢጓቸው ሲነካባቸው የሚንጰረጰሩት። ስሙን የማይነግረኝ የነበረ ደምበኛዬን አልረሳውም።

አንድ ከእግሩ ሸፈፍ፣ ከቁመቱ አጠር፣ ከኩራቱ ረዘም ያለ ደምበኛ ነበረኝ። ስሙን እንኳ ለመናገር
የሚጠየፈኝ። Just call me “The Doctor! » ይለኛል ስሙን ተሳስቼ ከጠየቅኩት። ደሞ የኔን ስም
ስንቴ እንደነገርኩትና ስንቴ እንደሚረሳው። ይህ ባህሪው እርር ነበር የሚያደርገኝ። እልህ ስለሚይጠዘኝ
ደሞ እጥፍ አስከፍለዋለሁ፤ አይከራከርም፡፡ ይህም ያናድደኛል። ከወጣሁለት በኋላ ደግሞ በራሴ
እናደዳለሁ። ምናለ እምቢ ባልኩት ብዬ እርር ደብን ትካን እላለሁ።

ዶክተሩ ከፍተኛ የሸሌና የሕዝብ ንቀት አለበት። የሚገርመኝ እንዲህ ሁሉንም ህዝብ ከናቀ ለምን በጊዜ ታንቆ እንደማይሞት ነው። እንዲህ ከሚንቀው ህዝብ ጋር ዘላለም ተናንቆ ከመኖር መታነቅ የሚቀል መሰለኝ፤ ሆ! ስንት አይነት ወንድ አለ!
👍31