#ሁቱትሲ
፡
፡
#ምዕራፍ_ዘጠኝ
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
፡
#የማዋየው_ወዳጅ_ሳጣ
፡
በመታጠቢያ ቤቱ ውስጥ የራሴ የምለው ስፍራ እግኝቻለሁ - የልቤን ትንሽ ጥጋት፡፡ ስነቃ ወዲያውኑ ወደዚያ አፈገፍጋለሁ፤ እስክተኛ ድረስም በዚያው እቆያለሁ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የምነጋገርበት፣ ቃሉን የማሰላስልበትና መንፈሳዊ ማንነቴን የምንከባከብበት የተቀደሰ ስፍራዬ ነው፡፡
በምመሰጥበት ወቅት ከእምነቴ ምንጭ ደርሼ ነፍሴን አጠናክራለሁ፡፡ ሽብር ሲከበኝ በጎበኘሁት ቁጥር በሚያስደተኝና ነይ ነይ በሚለኝ ዓለም ከለላ አገኛለሁ፡፡ ሰውነቴ ሲንኮታኮት እንኳን ነፍሴ ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ የጠለቀ ግንኙነት ትፋፋለች::
ወደ ልዩ ስፍራዬ በጸሎት እገባለሁ፤ አንዴም ከገባሁ በኋላም ያለ ማቋረጥ እጸልያለሁ፣ መቁጠሪያዬን ሃሳቤንና ሃይሌን ወደ እግዚአብሔር እንዳተኩር እንደመልህቅ እጠቀመዋለሁ፡፡ የመቁጠሪያው ዶቃዎች በወንጌል ላይ እንዳተኩርና የእግዚአብሔርን ቃል በአእምሮዬ ህያው አድርጌ እንዳቆይ ረድተውኛል፡፡ በጸጥታ እጸልያለሁ፤ ግን ራሴን በእውነት እያልኳቸው እንደሆነ ለማሳመን ሁልጊዜ ቃላቱን በአፌ ድምፅ ሳላሰማ እላቸዋለሁ… ያ ባይሆን ኖሮ ጥርጣሬ ይገባኝና አሉታዊው ኃይል እየተጣራ ይመጣብኛል፡፡
የአንድን ነጠላ ቃል ትርጉም ሳሰላስል ሰዓታትን እወስዳለሁ፣ እንደ ምኅረት፣ እምነት ወይም ተስፋ ያሉትን፡፡ እጅ መስጠት የሚለውን ቃል ሳሰላስል ቀናትን አሳልፌያለሁ፡፡ በዚህም ምክንያት የራስን ስብዕና ለአንድ ከፍ ላለ ኃይል መስጠት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተረዳሁ፡፡ ራሴን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፌ ሰጠሁ፡፡ በማልጸልይበት ጊዜ በእርሱ ብርሃን ውስጥ እንዳልሆንኩ ይሰማኛል፤ የመታጠቢያ ክፍሉ ዓለምም በበኩሉ ለመቋቋም የሚከብድ ነው፡፡ በተደበቅንበት የመጀመሪያው ወር መጨረሻ አካባቢ ቄስ ሙሪንዚ አንድ ሌሊት ላይ በጣም አምሽተው ትርፍራፊ ምግብ ይዘውልን መጡ፡፡ ወደዚህ ሲያስገቡን በሃዘኔታ ስሜት ቢሆንም አሁን ግን ያ እየጠፋ የሄደ መሰለ፡፡ በዚህ ምሽት ፊታቸው ከወትሮው የአሳቢነትና የሃዘኔታ ገጽታ ወደ መኮሳተር መጣ፡፡ ‹‹አባትሽ በጣም መጥፎ ቱትሲ ነበር!›› ሲሉ አያገጣብሩኝም!
‹‹ምን? ምን ማለትዎ ነው?›› ሙሉ በሙሉ የማደርገውን አሳጣኝ፤ ቢሆንም ግን በአባቴ ላይ የሰነዘሩት ጥቃት አባቴን ባለፈ ጊዜ የመግለጻቸውን ያህል አላናደደኝም፡፡ ከቤተሰቤ አባላት ማናቸውም ሊሞት የሚችልበትን እሳቤ አልቀበልም ብያለሁ፡፡ ‹‹አባቴ ጥሩ ሰው ነው ቄሱ - ምን አልባትም ካገኘኋቸው ሰዎች ሁሉ መልካሙ ሰው!››
‹‹አይ ኢማኪዩሌ አባትሽማ መጥፎ ቱትሲ ነበር - መጥፎ ሰው … የሩአግ አማጽያን የእርስ በርስ ጦርነት ያቅዱ ዘንድ ይረዳ ነበር፡፡›› ሌሎቹን ሴቶች አይተው እኔ ላይ ጠቆሙና እንዲህ አሉ፤ ‹‹ይዘው ቢገድሏችሁ በኢማኪዩሌ ምክንያት ነው፡፡ ገዳዮቹ እሷን የሚያድኗት እኮ በአባቷ ድርጊቶች ሰበብ ነው፡፡›› ቄሱ አፍጠውብኛል፤ በዚያም ላይ የሌሎቹን ሴቶች ዓይኖችም በኔ ላይ እንደ ጦር መሰካታቸው ይታወቀኛል፡፡
‹‹እናንተ ቤት ውስጥ 600 ጠመንጃዎችን አግኝተዋል›› ሲሉ ቀጠሉ ወደኔ ተመልሰው፡፡ ‹‹ቦምቦችንና የሚገደሉ ሁቱዎችን ስም ዝርዝርም አግኝተዋል፡፡ ለዚያ ነው እናንተ ቱትሲዎች እየታደናችሁና እየተገደላችሁ ያላችሁት፡፡ ሁቱዎች ቀድመው ወደ ተግባር ባይገቡ ኖሮ ይሄኔ እኛ ነበርን በቱትሲዎች የምንገደለው!›› የሚናገሩትን ለማመን አልቻልኩም፡፡ ጽንፈኛ ሁቱዎቹ የሚያሠራጯቸው መርዘኛ ውሸቶች ቄስ ሙሪንዚን ምክንያታዊነት አሳጥተዋቸዋል፡፡ ከአባቴ ጋር ለዓመታት ወዳጅ ነበሩ፡፡ አባቴ የድሆችንና ኑሮ የማይሞላላቸውን ሰዎች ሕይወት ለማሻሻል ሕይወቱን የሰጠ ሰው ነው፡፡ አባቴ ትምህርት ቤቶችንና ለቱትሲዎች፣ ለሁቱዎችና ለትዋዎች ሁሉ አነስተኛ የጸሎት ቤቶችን ሰርቷል፡፡ ታዲያ ቄሱ መሣሪያ በመደበቅም ሆነ ግድያን በማቀነባበር እንዴት ሊወነጅሉት ቻሉ? አባቴ ከደጃችን ሆነው ተስፋ የቆረጡትን ቱትሲ ስደተኞች ሁቱዎቹን ሊገድሏቸው ቢመጡ እንኳን እንዳይገድሉ አላሳሰበም ነበር?
ቄስ ሙሪንዚ ይህን መረጃቸውን ከባለሥልጣናት እንደሰሙት ነገሩኝ፡፡ ጥሎባቸው እንደ ብዙው ሩዋንዳዊ ሁሉ በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የሚነግሯቸውን በጭፍን ያምናሉ፡፡
መንፈሴ ተንኮታኮተ፡፡ እንደዚህ ዓይን ያወጣ ውሸትን በአባቴ ላይ ማንም እንደዋዛ ሊያሠራጭ እንደማይችል እርግጠኛ ሆንኩ… አስቀድመው ገድለውት ካልሆነ በስተቀር፡፡ እርሱን አደገኛ ሰው አስመስሎ ማቅረብ በግልጽ የእርሱን መገደል ትክክለኛነት ለማሳየት የተጠቀሙበት እቅዳቸው መሆን አለበት፡፡ እኔ ግን ስለዚያ ላስብ አልችልም፡፡ ከቤተሰቤ ማንም ሰው ሞቷል የሚለውን ሐሳብ ለማስተናገድ አልፈለግሁም - ለዚህ ጊዜው አሁን አይደለም፡፡ ገና ያንን ለመቀበል አልጠነከርኩም፡፡ በቄሱ በጣም ስለተናደድኩባቸው ለመጮህ ፈለግሁ፤ አንዳች ነገር ማድረግ ግን እንዴት ይቻለኛል? እርሳቸው በኛና በሞት መካከል የቆሙ ብቸኛው ሰው ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በወቅቱ ልግስናቸውን በጣም ባያሳዩንም በእርሳቸው በጎ አድራጎትና መልካም ፈቃድ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኞች ነን፡፡ እኛን አደጋ ላይ እንዳለንና እገዛ እንደሚያስፈልጋቸው ጎረቤቶቻቸው ማየታቸውን እንዳቆሙ አውቀነዋል፡፡ አሁን እያዩን ያለው ልክ ገዳዮቹ አንደሚያዩን ነው - ሰው እንዳልሆንን፣ ጦርነቱ ሳያልቅ መጥፋት ዕጣ ፈንታችን እንደሆነ በረሮዎች፡፡
ቄስ ሙሪንዚ የአባቴን መልካም ስም ሲያጠፉ ንዴቴ በውስጤ ተንተገተገ፡፡ ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም - አባቴ የሚበቃውን ያህል ተዋርዷል! በመታጠቢያ ቤቱ ከቆለፉብን ወዲህ ድምጼን ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍ አደረግሁ - ‹‹አባቴ ያን ያህል መሣሪያ ቢኖረው ለምን እኛ ጋ ከለላ ፈልገው ለመጡት በሺዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች አልሰጣቸውም? ያን ያህል መሣሪያ ቢኖረው ገዳዮቹ ቤታችንን ሲያቃጥሉት ለምን አላስቆማቸውም? ሁቱዎችን ለመግደል ቢያስብ ቤተሰቡን ወደ መደበቅ ሳይገፋፉትና ኑሮውን ሳያበላሹት በገደላቸው ነበር! ይንገሩኝ ቄሱ፣ መሣሪያዎቹን ለምንድነው ሚስቱንና ሴት ልጁን ከገዳዮችና ከደፋሪዎች ለመከላከል ያልተጠቀመባቸው?››
ቄስ ሙሪንዚ ድንገት መገንፈሌ ደነገጡ (ሴቶቹም እንደዚያው - ሕይወቶቻቸውን በእጁ ከያዘው ሰው ጋር ስገዳደር ሲያዩኝ ባለማመን ዓይኖቻቸው ፈጠጡ)፡፡ ዝም እንድል በእጃቸው ተዪ የሚል ምልክት አሳዩኝ - ከዚያም መሣሪያዎች በልጅነቴ መነኩሲት እንዲያደርጉኝ ጠይቄያቸው በነበሩት በደጉ ሽማግሌ አባ ክሌሜንት ቤተክርስቲያንም እንደተገኙ ነገሩኝ፡፡ እኝህ አባት እንስሶች ሲጎዱ ማየት ስለማይፈልጉ ዕድሜ-ልካቸውን አትክልት ብቻ የሚመገቡ፣ አመፅ የሚያንገፈግፋቸውና ጠመንጃ የሚጠሉ ነበሩ፡፡ የቄሱ ሐሳብ እንዲህ ያለ ነጭ ውሸት ስለሆነ ነው መገዳደር ያለብኝ፡፡
‹‹እርስዎ ከነዚህ ከሚሏቸው መሣሪያዎች አንዱን እንኳን አይተዋል ቄሱ?›› ‹‹አይ… ግን ከትልልቅ ሰዎች ነው የሰማሁት - ከሚታመኑና ከማይዋሹ፡፡›› ከዚያን ጊዜ በፊት በተለይ በሀገሪቱ እየተከሰተ ከነበረው ነገር አንጻር የተማረ ሰው እንደዚህ እንጭጭ መሆን ይችላል ብዬ ላስብ አልችልም፡፡ ‹‹ስለዚህ አባቴን ለሚወነጅሉባቸው ነገሮች ምንም ማረጋገጫ የለዎትም፣ እስኪ ካለዎት ያምጡት፡፡›› ባዶ ነጭ ወረቀት ከኪሳቸው አውጥተው

👍2