አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
482 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በራ_የመስቀል_ደመራ


በራ የመስቀል ደመራ
የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ
ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ
#የመስቀል_ደመራ_በራ
በራ የአዲስ ዘመን ችቦ
በመስከረም ሰብል አብቦ
ከዋክብቱን ፈነጠቀ
ርችቱን አንፀባረቀ
ተኳለ አዲስ ደመቀ
መልኩን በቀለም አዝርእት፤ በጥበብ
አጥለቀለቀ።
ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፡ ተራራው አሸበረቀ
ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ፡ ምድር ሕይወት አፈለቀ፡፡
ነጋ፡ የአዲስ ዘመን ችቦ
ፈካ፡ ፀደይ አረብቦ
ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፤ ጨለማው እንደቀን
ጠራ
እንደውቅያኖስ ዕፅዋት፤ እንደጠፈር ኮከብ
ደራ
ምድር ሥጋጃ ለበሰ፤ የጌጥ አልባሳት ተቀባ
ሰማይ በእልልታ አስተጋባ
ኢዮሃ መስከረም ጠባ፡፡
ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፤ ምድር ሕይወት
አፈለቀች
የምሥራች አዝርእቷን፤ አዲስ ቡቃያ ወሰደች
የአደይ አበባን ለገሠች
ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን፤ አዲስ
መስከረም ገበየች
#ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ
#ፈካ ፀደይ አረብቦ
#በራ
የመስቀል ደመራ፡፡

🔘ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን🔘

💚💛❤️