አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከ ‹‹ፈሮግራምህ›› #ውልፍት_የለም !

አንሾ ባልታወቀ ምክንያት የምትወደው ባሏ አባተ ጋር ትጣላለች ,,,,,እናም ኮብልላ ወላጆቿ ቤት ታድራለች ! በበነጋታው የአገር ሽማግሌወች ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ሽምግልና ይቀመጣሉ !
‹‹ ችግርሽ ምንድነው ?››
‹‹ምንም››
‹‹እንዴት ያለምንም ችግር ትዳርሽን ታፈርሻለሽ ››
‹‹ በቃ አልፈልግም ››
‹‹እኮ ለምን ?›› አሉ ሽማግሌወች በማግባባት አንሾ ስትፈራ ስትቸር አንዲት ነገር ተናገረች ‹‹ አሱ ሰው አይደለም ዝንጆሮ ነው ›› ሽማግሌወቹ ገባቸው ! ባሏ እንደዝንጆሮ ወሲብ ያበዛል አልቻለችውም ማለት ነበር ትረጉሙ…. እናም ሽማግሌወቹ ጉዳዩን በዝርዝር እንድታስረዳቸው ጠየቁ… እ,ሷም አንዴ ከአፏ ወጥቷልና በዝርዝር ጉዳዩን ታስረዳ ጀመረ !
‹‹ እንደው በኔ የደረሰ አይድረስባችሁ … ባለቤቴ ሳያገባኝ በፊት ጎበዝ ገበሬ …. አገር ያወቀው ጀግና ነበር ታውቃላችሁ መቸስ ….ከተጋባን ጀምሮ መሬቱ ሁሉ ጦም አደረ በሬወቹ እንደተጠመዱ ትቷቸው ይመጣና እኔን ይጠምደኛል …. ሌሊት ወገቤ አያርፍ እግሬ አይገጠም ጧት በግድ ተነስቸ ያዘጋጀሁትን ቁርስ ቀመስ አድርጎ ይተውና ወደመደቡ መጎተት ነው ….ውሃ ቀድቸ ስመለስ እንስራየን አውርዶ ወዲያ ይወረውርና ‹ያዥ እንግዲህ › ነው … አልቻልኩም በዛብኝ ምነው ሸዋ ! ›› አለችና ሽማግሌወቹ ፊት አለቀሰች ! ሽማግሌወቹም ችግሯን ስለተረዱ እዛው ተቀምጦ ጉዱን የሚሰማውን ባሏን ጠሩና መከሩት
‹‹አባተ ››
‹‹አቤት አባቶቸ ›› አለ እየተቅለሰለሰ
‹‹እንግዲህ የተባለውን ሰምተሃል እውነት ነው ሃሰት ? ››
‹‹ኧረ ሃቅ ነው አባቶቸ ….›› ሲል አመነ
‹‹ ጥሩ እንግዲህ ጥፋት አይተንብሃል በል አሁን የምንመክርህን ስማ ›› አሉና ሽማግሌወቹ ተመካክረው በአንድ ወግ አዋቂ ሽማግሌ በኩል እንዲህ አሉት
‹‹ እንግዲህ አባተ <እንትን > እንደሆነ ዝም ብለው ቢውሉበት ቁርስ አይሆን ምሳ ርስት አይሆን ሃብት …. እየናፈቀ ሲገኝ ነው ደጉ …ይሄው አረጀንበት ከልጅነት እስከእውቀት ኖርንበት እሱ እንደሆን እያደር አዲስ ነው ከምን እንደሰራው አንድየ ይወቀው …..እና አሁንም አንተም ሚስትህን አንሻን እንዳታማርራት በ ‹ፈሮግራም › እንዲሆን ወስነንበሃል ›› ሲሉ አስረዱ
‹‹ እሽ አባቶቸ እንዳላችሁ ….ግ…..ን ‹ፈሮግራሙ› እንዴት እንዴት ነው ›› አለ አባተ
‹‹ እንግዲህ ፈሮግራሙ እንዲህ ነው …. ቀን ቀን እቤት ድርሽ ሳትል እርሻላህ ላይ ትውልና ማታ ጀምበር ሲያዘቀዝቅ ከብቶችህን አስገብተህ ስታበቃ አንሾም ናፍቃህ ትውል የለም …..አንደዜ ! ….ደሞ ራት ተተበላ በኋላ ኩራዝ ጠፍቶ ጋደም ስትሉ ….አንደዜ ! ወደንጋጋቱ ላይ ዶሮ ሲጮህ ደሞ አንደዜ ! ሶስት ሃቅህ ነው !›› አሉት
አባተ ቅር እያለው እንዲህ አለ ‹‹ እንደ…..ው ኣባቶቸ ምክራችሁ ጥሩ ነበር ግ…..ን እነደው …. ለጠራራውም ለውሃ ጥሙም ቀን ላይ አንደዜ ብትጨምሩልኝ ›› ሲል ጠየቀ
አንሾ በተራዋ ‹‹ የዶሮ ጩኸቱን ብታነሱልኝ ምናለ …. ሁለቴ ካገኘ ምን አነሰው ›› ስትል ቅሬታዋን አቀረበች ! ሽማግሌወቹ ግራ ቀኙን አድምጠው ‹‹ አንሾ አንችም አትሰስች ….አንተም ከ ‹ፈሮግራምህ› ውልፍት የለም ! ከተሜው ሁሉ እንዲሁ ነው የሚያረግ ›› አሉና በውሳኔያቸው ፀኑ !
አንሾና አባተም እርቅ አውርደው ወደቤታቸው ሄዱ ! ልክ እቤታቸው ሲደርሱ ጀምበር አዘቅዝቆ ስለነበር አባተ እየተጣደፈ አንሾን ወደመደቡ ጎተታት …. አንሾም ተጣልተው ስለቆዩ ናፍቋት ስለነበር አልከፋትም ኧረ እንደውም ደስ አላት !
‹‹ አንድ በል ቁጥር እነዳትስት ›› አለች ቀሚሷን እያጠለቀች ! አፍታ ሳይቆይ አባተ አንሾ አማረችው ! አለፍ ስትል ሳብ አደረገና እነሆ ! ሁለት ! ገና እራት ሳይቀርብ አንሾ ጉድ ጉድ ስትል ጠይም ፊቷ በምድጃው እሳት ወጋገን ወርቅ መስሎ ታየው አባተ አላስችል አለው በቃ ሳብ አደረጋና ሶስተኛውን ሃቁን አነሳ !
እራት ቀርቦ በሉና ጋደም እንዳሉ አባተ የአንሾ አርቲ እና አሽኩቲ ጠረን አቅሉን ነሳው ! ሽማግሌወች የወሰኑለትን ኮታ ደግሞ ጨርሷል እናም በጨለማው ውስጥ ቀስ ብሎ እንዲህ አለ ‹‹አንሾ ››
‹‹ምን ፈለክ…..የዛሬውን ድርሻ ሶስትህን ጨርስሃል ነገር ትፈልገኝና ውርድ ከራሴ ›› አለች አንሾ በቁጣ
‹‹ እንደው አፈር ትሆንልሽ …..ተነገው አንድ አበድሪኝ አንሾዋ ›› አላት ያልሆነ ቦታ እየደባበሳት .....አንሾ አሰብ አደረገች እሽ እንዳትል ኩራቷ ያዛት እምቢ እንዳትል የአባተ እጅ ቀልቧን ወስዶታል እናም እንዲህ አለች ‹‹ ምን የነገውን አበዳደረህ የትላንቱስ ሶስቱ መች ተነካ ›› ትላንት ተጣልተው አብረው አላደሩም !!
ወደቁም ነገራችን ስንመለስ በባልና በሚስት እንዲሁም በፍቅረኞች መሃል ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄው ሶስተኛ ወገን ሳይሆን ፍቅር ራሱ ነው #ፍቅር_ብቻ !!!!
👍3