አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
576 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እማማ_ዣ


#ክፍል_ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

#ትንሽ_ወሰድ
ይኼን ሁሉ ውጣ ውረድ አሳልፌ ለእማማ ዣ የገዛሁትን ኦሞ “ይኼው” ስላቸው፣

“ምኑ!?” ይሉኛል ...ኦሞ ግዛ ብለው መላካቸውን ረስተውታል፡፡ አንዳንዴ እንዲ
“ልባቸውን ወሰድ የሚያደርገው ነገር አለ” እያለ የሰፈሩ ሰው ያማቸዋል፡፡ በእርግጥ
የመንደሩ ሰው እንደሚያወራው አይጋነን እንጂ አልፎ አልፎ ነገር ይረሳሉ። ይኼ ደግሞ ማንም ሰው ሊያጋጥመው የሚችል ነገር ነው። እኔ ራሴ ብዙ ነገር እረሳ የለ እንዴ?! ስንት ጊዜ ነው እናቴ የተጣደ ነገር ጠብቅ ብላኝ የረሳሁት? እዚያው እንደ አሻሮ ከስሎ፣ ቤቱ በጭስ ከታፈነ በኋላ አይደል እንዴ፣ ትዝ የሚለኝ?! …ማንም ሰው ይረሳል …ምን ሰው ብቻ …የሰፈራችን ትልልቅ ሰዎች ራሳቸው በሬዲዮ የድርቅና የወረርሽኝ ምናምን ዜና በሰሙ ቁጥር፣ ስንት ጊዜ ነው “ምነው እግዚሐር ኢትዮጵያን ረሰሃት!?” የሚሉት?! እንግዲህ እግዚሐርም ቢረሳ ይሆናላ፤ ያውም ስንት ሚሊየን ሕዝብ በየቀኑ ቤተክርስቲያን እየሄደ አትርሳኝ እያለው፤ ጎረቤቱ እማማ ዣ ላይ ለምን እንደሚያጋንነው
አይገባኝም! እማማ ዣ ሽቅርቅር! ባል ነበራቸው እየተባለ ይወራል፡፡ (ሽቅርቅር ቃሉ ስለሚገርመኝ አልረሳውም!) ታዲያ ያ ባላቸው ይኼን ሆንኩ ሳይል ድንገት ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ቀረ፡፡ መጀመሪያ አንዱ ዘራፊ ገድሎ ጥሎት ይሆናል ብለው ያላመለከቱበት ፖሊስ
ጣቢያ አልነበረም አሉ፡፡ ጎረቤቶቻችን ሲያወሩ ነው እንግዲህ የሰማሁት:: ብዙ ቀን ስለ እማማ ዣ ሲያወሩ ሰምቻቸዋለሁ የኛ ሰፈር ሰው ከሥጋ ቅርጫ ቀጥሎ የሚወደው ነገር፣ እማማ ን ማማት ይመስለኛል።
እናቴ እራሷ ታወራለች! በእርግጥ እናቴ ያወራችው እማማ ዣን ለማማት አልነበረም አልፎ አልፎ እቤታችን የምትመጣውን የአክስቴን ልጅ ስትመክር እንደ ምሳሌ ነው ያነሳቻቸው።የአክስቴ ልጅ ሔለን (ሳይሞቅ ፈላ ነው እናቴ የምትላት) አንድ ቅዳሜ ቀን እኛ ቤት አደርኩ ብላ፣ ሌላ ቦታ ማደሯ ታወቀ:: ከማን ጋር እንዳደረች ባላውቅም፣
ከእናቴ አወራር ግን፣ ከሆነ ወንድ ጋር አድራ መምጣቷን ጠርጥሪያለሁ.……. የዚያን ቀን እናቴ እማማ ዣን ምሳሌ አድርጋ ስትመክራት እንዲህ አለች “ይችን የኛን ጎረቤት ያንዣብን ታውቂያቸው የለም ?…. ይኼውልሽ እሳቸው እንዲህ ነካ አድርጓቸው የቀሩት በወንድ ነው…” ካለች በኋላ፣ እማማ ዣ ለባላቸው ያደረጉለትን ውለታ…ከአመድ አንስተው ሰው እንዳደረጉት፣ በሕልሙ እንኳን አይቶት የማያውቀውን ኑሮ እንዳሳዩት
ብዙ ብዙ ነገር እንዳደረጉለት አውርታ በቁጭት እንዲህ አለች…

“ያን ሁሉ አርገውለት፣ አፈር አይንካህ ብለውት አፈር ያስበላውና! ..ሌላ ሴት በላያቸው ላይ ወዶ፣ ባዶ ቤት አስታቅፏቸው ሄደ። የጠፋ ሰሞን ...እሳቸው ምን ሆነብኝ ብለው
ፊታቸውን እየነጩ በየፖሊስ ጣቢያው፣ በየሆስፒታሉ ሲዞሩ ከረሙ …ምን መዞር ብቻ፣ በየሜዳው ሞቶ የተገኘውን ዘመድ ያጣ የስንት ቀን ሬሳ እያገላበጡ ሲያዩ ከርመው በኋላ ባልሽ ተገኝቷል' ሲባሉ ከቤታቸው የጀመሩ እልልል… እያሉ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ! የምስራች ሰምተው በደስታ ፖሊስ ጣቢያ የደረሱት ሴትዮ፣ ሌላ መርዶ ጠበቃቸዋ!”

“ምን ሆነ? ሞተ?” አለች የአክስቴ ልጅ፡፡

“በምን ዕድሉ! …ባለጌ ይሞታል እንዴ?! …ፖሊሶቹ አርፈሽ ተቀመጭ! እሱ አንዲት ሴት ወዶ ጠቅልሎ ገብቶልሻል
አሏቸው እንጂ! እንግዲህ ያኔ እዛ ፖሊስ ጣቢያ ሲደነግጡ ያግኛቸው፣ አልያ የማንንም ሬሳ ሲያገላብጡ ሰይጣን ይስፈርባቸው እንጃ .. ይኼው ስንት ዘመን አይምሯቸው ተቃውሶባቸው ቀሩ!”
“ሚስኪን! ታዲያ ምናደረጉ?” አለች የአክስቴ ልጅ ማስቲካ እያላመጠች ስትናገር እንደ መሞላቀቅ ያደርጋታል!
“…ምን ያደርጋሉ ... እየፈነጠዙ የሄዱት ሴትዮ፣ የመንደሩን ዓይን ለማየት ተሸማቀው ጥፍር አክለው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፤ ቤታቸውን ዘግተው ከርመው በስንተኛው የባላቸውን ልብስ ነሽ፣ ፎቶ ነሽ፤ ሁልጊዜ የሚቀመጥበትን ሶፋ ሳይቀር፣ ከሌላው ሶፋ ነጥለው ግቢያቸው ውስጥ ከመሩና እሳት
ለቀቁበት ... ቤታቸውን ታውቂው የለም? …እሳቱ ያንን ረዥም ግንብ አልፎ ሲንቀለቀል ደመራ መሰለ ...

ከዚያ ወዲህ ወንድ የሚባል ነገር አታንሱብኝ አሉ፣ በቃ… ማንም አጠገባቸው ስለሌ ትንፍሽ ብሎ አያውቅም:: ይኼው ስንት ዘመናቸው እንደ ባህታዊ ቤታቸውን ዘግተው
ልብስ ሲለኩና ሲያወልቁ ...በየቀኑ ኦሞ እየገዙ ምኝታ ቤታቸውን ሲያጥቡ ይውላሉ...አንድ ቀን ምኝታ ቤታቸውን በኦሞ ሳያጥቡ ውለው አያውቁም!! እና ምን ልልሽ ነው
….ወንድ አምነሽ እማይሆን ነገር ውስጥ እንዲች ብለሽ እንዳትገቢ… እንኳን ባዶ እጅሽን እየተወዘወሽ ቤታቸው ሂደሽ ቀርቶ፤ ወንዶች ከየትም አንስተው ወርቅ ላይ ቢያስተኟቸው፣ ልባቸው የማያርፍ ሰላቢዎች ናቸው ..” አለች።

የመጨረሻዋ ስድብ አባቴ ላይ ያነጣጠረች መሆኗን ከልምድ አውቃታለሁ..እናቴ “ሰላቢ” የሚል ቃል የምትጠቀመው፣ እኔን በወለደች በሁለት ዓመቷ የፈታትን አባቴን ስታነሳ ነው፡፡ ለፍቻቸው ዋናው መንሥኤ የአባቴ ቤተሰቦች “ልጁ ምኑም ምኑም አንተን
አይመስልም” ብለውት ነው አሉ፤ ታዲያ የአባቴን ፎቶ ባየሁ ቁጥር እንኳንም እሱን
ያልመሰልኩ እላለሁ፡፡ ..ሰው ልጄ እንደኔ መልከ ጥፉ ካልሆነ ብሎ እንዴት ሚስቱን
ይፈታል?!

ይህ የእማማ ዣ ታሪክ እኔን እንባዬ እስኪመጣ አሳዘነኝ እንጂ ላክስቴ ልጅ እንደሆነ ምንም አልጠቀማት፡፤ እንደ ቆንጆ የሬዲዮ ትረካ ማስቲካዋን እያላመጠች ይኼን ሁሉ የክህደት ታሪክ በኮመኮመች ልክ በአስራ አምስተኛው ቀን፣ ከአንድ ጉጉት ከመሰለ ልጅ
ጋር (እናቴ ናት ያለችው) ተያይዛ ጠፋች፡፡ እንዲያውም አብረው መኖር መጀመራቸውን ለእናቴ ደውላ ነገረቻት:: አክስቴ በሷ ምክንያት ታማ ስንት ወር ጠበል ለጠበል ዞራለች፡፡ በዓመቱ የአክስቴ ልጅ ሔለን ፊቷ አባብጦ፣ የግራ ክንዷ ተሰብሮ፣ ወደ ጤና ጣቢያ
የምትመጣ ይመስል እየተንከረፈፈች እቤታችን መጣች፡፡ “በትንሽ ትልቁ መቅናት ነው! መደብደብ! ..ነጋ ጠባ በጥፊ ጆሮ ግንዴን እየጠረቀመኝ፣ ይኼው የቀኝ ጆሮዬን ያዝ ያደርገኝ ጀምሯል ...” ብላ ተነፋረቀች፡፡

እናቴ ታዲያ እሱ እንኳ ድሮም ጆሮሽ ምክር አይሰማ! ዋናው ነገር እንኳን ነፍስሽ ተረፈ" ብላ ተቀበለቻት። ምስኪን የአክስቴ ልጅ! እንደማማ ዣ አቃጥላ እልኋን የምትወጣበት ልብስ እንኳን ሳይሰጣት፣ ተከትላው የሄደችው ወንድ ቀጥቅጦ ቀጥቅጦ መለመላዋን አባረራት፡፡ እናቴም ለወንዶች ባላት ጥላቻ ላይ፣ የአንድ ሰላቢ ወንድ ታሪክ ተጨመረላት። ታዲያ አንዳንዴ፣ ከአክስቴ ጋር እያወሩ እናቴ፣ “ያ! ሰላቢ…” ስትል
“የትኛው?” ትላታለች አክስቴ! አክስቴም ትንሽ ወሰድ ያደርጋታል!

#ከፈረሱ_አፍ
አንዳንዴ፣ “ይኼን የእማማ ዣ ታሪክ፣ እናቴ የአክስቴን ልጅ ለማስፈራራት የፈጠረችው ቢሆንስ!?” እያልኩ መጠራጠሬ አልቀረም! በእርግጥ የኦሞው ታሪክ እውነት ነበር፡፡በየቀኑ ከሱቅ የምገዛው እኔ ራሴ ስለነበርኩ ለዚህ ምስክር ነኝ፡፡ የተጠራጠርኩት
በባላቸው አጠፋፍ ላይ ነበር፤ምክንያቱም ከብዙ ጊዜ በኋላ ራሳቸው እማማ ዣ ፈፅሞ እናቴ ካወራችው የተለየ ታሪክ ሲያወሩ ስለሰማሁ ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ እናቴም ሆነች እማማ ዣ፣ አልያም ጎረቤቱ የሚስማሙበት ነገር ሴትዮዋ ባላቸው ሄደ መጣ፣ ምንም ኤልጎደለባቸውም! እራሳቸውም “እኔ ያንዣቡ ምን ጎደለብኝ… ባቄላ አለቀ ..ምን ቀለለ አሉ!” እያሉ ከፍ ባለ ኩራት ይናገራሉ.ኩራትን መቸም እሳቸው ይኩሯት!

አንድ እሁድ ቀን ታዲያ እማማ ዣ ታጥቦ የተከመረ ልብስ እያዘጋጁ፣ እግረ መንገዳቸውን ብዙ ጊዜ ጀምረው
1